የኔታ ሊቀ ብርሃናት ይባቤ በላይ በዛሬው ዕለት ተፈትተዋል። እርሳቸውን ለማስፈታት የተባበራችሁ ብፁዓን አበው ጳጳሳት (ሁለት ጳጳሳት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ እንደደከሙ መረጃው ስላለኝ ነው)፣ ሊቃውንት፣ ካህናት፣ ምእመናን እግዚአብሔር ረጅም ዕድሜን ይስጥልን።
ሊቃውንት የሀገር ሀብቶች ናቸው። በተለይ እንደየኔታ ይባቤ ዓይነት ሁለገብ ሊቃውንት ደግሞ እንደ ዓይን ብሌን የሚጠበቁ ናቸው። አንዳንዶች ወደላይ አያዳልጣችሁ። ትልቅን ሰው መሳደብ ውርደቱ ለራሳችሁ ነው። ትልቅን ሰው ማክበር ይልመድብን።

❤14
መልካም ዜና!
የኔታ ይባቤ ከእስር ተፈተዋል እግዚአብሔር ይመስገን
የባህር ዳር ህዝብ ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል ለአባታችን
የኔታ ይባቤ ከእስር ተፈተዋል እግዚአብሔር ይመስገን
የባህር ዳር ህዝብ ደማቅ አቀባበል አድርጎላቸዋል ለአባታችን
❤12
✨ #ሕንጸተ_ቤተ ክርስቲያን ዘእግዝእትነ ማርያም።
🍂የቤተ ክርስቲያን መታነጽ በእመቤታችን ስም #ሰኔ_21
🍂 #ጌታችን በዐረገ በስምንተኛው ዓመት ቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ በርናባስ ወደ ፊልጵስዩስ ገብተው በክርስቶስ ስም አሳምነው ብዙ አሕዛብን ካጠመቁ በኋላ ቤተ ክርስቲያን ሊሠሩላቸው ወደዱ፡፡
✨ በዚህ ጊዜ ርእሰ ሐዋርያት እያለ እኛ መሥራት አይገባንም ብለው በሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ መልእክት ላኩበት፡፡ እርሱም ከቅዱስ ዮሐንስ ጋር መጥቶ ከቅዱስ ጳውሎስ እና ቅዱስ በርናባስ ጋር በኢየሩሳሌም ተገናኙ፡፡
🍂 በዚያም በአንድነት ሱባዔ ይዘው ከቆዩ በኋላ ጌታችን የሞቱትን አስነሥቶ፣ ያሉትንም ጠርቶ ቅዱሳን ሐዋርያትን #በፊልጵስዩስ አገር ሰብስቦ ‹‹በእናቴ በድንግል ማርያም ስም ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚሠራዉን የአብያተ ክርስቲያናት ሥራ ላሳያችሁ፤ ሥርዓቱንም ላስተምራችሁ ሰብስቤአችኋለሁ›› ብሎ ወደ ምሥራቅ ይዟቸው ወጣ፡፡
✨ #በዚያም_ሥፍራ የነበሩትን ሦስት ድንጋዮችንም የተራራቁትን አቀራርቦ፣ ጥቃቅኑን ታላላቅ አድርጎ ቁመቱን በ፳፬፤ ወርዱን በ፲፪ ክንድ ለክቶ ለቅዱሳን ሐዋርያት ሰጣቸው፡፡
🍂 ከዚህ በኋላ ቅዱሳን ሐዋርያት ሰም እሳት ሲያገኘው እንዲለመልም፣ ድንጋዩ በእጃቸው ላይ እየተሳበላቸው ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑን ሠርተው ፈጽመዉታል፡፡
✨ #ሕንጻ_ቤተ_ክርስቲያኑ የተሠራዉም ጌታችን በዐረገ በ፲፱ኛው ፤ እመቤታችን በዐረገች በ፬ኛው ዓመት ሰኔ ፳ ቀን ሲኾን፣ በ፳፩ኛው ቀን (በማግሥቱ) ኅብስት ሰማያዊ፣ ጽዋዕ ሰማያዊ ወደ ቤተ ክርስቲያኑ ወረደ፡፡ ጌታችንም ከእመቤታችን ጋር ከሰማየ ሰማያት መጥቶ እመቤታችንን ታቦት፤ ሐዋርያትን ልዑካን አድርጎ፣ እርሱ ሠራዒ ካህን ኾኖ ቀድሶ ካቈረባቸው በኋላ “ከዛሬ ጀምሮ እናንተም እንደዚህ አድርጉ “ ብሎ አዝዟቸው በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡
( መጽሐፈ ስንክስራ የሰኔ 20 ፣ መጽሐፈ ግስ ወሰዋሰው)
✨ ንጽሕት በድንግልና ፣
ሥርጉት በቅድስና
እመቤታችን ወላዲተ አምላክ
ከመከራ ስጋ
ከመከራ ነፍስ
ትሰውረን

🙏4❤3
ዘ-ጋርዲያን በትግራይ ጦርነት ወቅት የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ሴቶች ላይ ዘግናኝ ወሲባዊ ጥቃት መፈፀማቸውን የሚገልጽ ሰፊ የምርመራ ሪፖርት አቀረበ‼️
በጦርነቱ ወቅት በትግራይ ከሚገኙ ጠቅላላ ሴቶች 10% የሚጠጉት ሴቶች ለጾታዊ ጥቃት መጋለጣቸውን ጥናቶችን ጠቅሶ ዘጋርዲያን አስነብቧል። ከነዚህ ውስጥ 70% በቡድን የመደፈር የደረሰባቸው ናቸው ብሏል።
እንደ ዘ ጋርዲያን ጥናት ሪፖርት የኤርትራ ወታደሮች አለም አቀፍ የጦርነት ህግ ከሚፈቅደው ውጭ የትግራይ ሴቶችን ዳግም መውለድ እንዳይችሉ በማሰብ በማህጸናቸው ውስጥ ባዕድ ቁሶችን መቅበራቸውን ከተጠቂዎች ማረጋገጥ ተችሏል።
ዘጋርዲያን አንዲት የፅናት ነው የምትባል ተጠቂ አናግሮ ነበር። በትግራይ ጦርነት ወቅት በኤርትራ ስድስት ወታደሮች ተደፍራ እራሷን ስታ ነበር። ፅናት ከመደፈሯም በላይ ኢ-ተፈጥሮአዊ ግፍ እንደተፈፀመባት በገለልተኛ ሀኪሞች መረጃ ተረጋግጧል።
ይህም በኤርትራ ወታደሮች በማህፀኗ የብረት ቁርጥራጭ፣ የማስታወሻ ወረቀት፣ ብሎኖች ብቻ የትግራይ ሴቶች ማህፀን ፍሬ እንዳያፈራ የሚያደርጉ ቁሳቁሶች በሴትነት ገላዋ በኩል ወደ ማህፀኗ እንዲገባ ተደርጓል።
ይህ በፅናት ላይ ብቻ ሳይሆን በሺዎች በሚቆጠሩ የትግራይ ሴቶች ላይ የተፈፀመ አረመኔያዊ የወሲብ ጥቃት መሆኑን ሪፖርቱ ይገልፃል።
ሙሉውን ዘገባ ከስር ባለው ሊንክ ገብተው ያንብቡ👇👇
https://www.theguardian.com/global-development/2025/jun/30/sexual-violence-tigray-women-abuse-gang-rape-ethiopia-eritrea?fbclid=IwZXh0bgNhZW0CMTEAAR7b4oO0CVacVI1Hbh9iOu9QeHvFp_HTwzNtyNu6qUh4N_sMfSM7tpDuQdD-aA_aem_D8a0JLsPn6xgr8lOej5LLA
===============
አዩ ዘሀበሻ

😢9❤2
Forwarded from ፍኖተ አበው ዘኦርቶዶክስ (መ/ር ንዋይ ካሳሁን)
የሰላማ አባባሎች
+እኛ ኢትዮጵያውያን የጀግንነታችን ምልክት ሃይማኖታችን ነው፡፡
+ አሁን እናንተ ይህ የነገረ መለኮት ትምህርት እንዴት ይዋጥላችኋል ገና እኮ የምትበሉትንና የምትጠጡትን፣ የሚጠቅማችሁንና የሚጎዳችሁን ለይታችሁ የማታውቁ ሕፃናት ናችሁ፡፡ ምክንያቱም ማርና ወተት ከቤታችሁ አውጥታችሁ ሸጣችሁ አረቄ ገዝታችሁ የምትጠጡ ሰዎች ይህ የነገረ መለኮት ምግብነት ጠቀሜታማ እንዴት ይረዳችኋል፡፡
+ የሰው ልጅ ጽድቅ አስፓልት ሆኖለት ከሚመላለስበት ይልቅ እርሱ የኃጢአት አስፓልት ሆኖ አጋንንት እንዲመላለስበት ይመረጣል፡፡
+ ሰማይ የሚያክል እንጀራ ቢሰጥህ ቀና ብለህ የሰማዩን ከዋክብት ተመልከት፡፡
+ የሰው መውደቅ አምላክን እስከሞት አደረሰው
+ ገዳም መንፈሳዊ ሐኪም ቤትና መንፈሳዊ የጤና መኮንኖች መፍለቂያና ማሠልጠኛ ነው፡፡
+ የምናስተምረው ለአዋቂዎች ነው፡፡ አላዋቂና ሲሚንቶ የጠጣ መሬት አንድ ነው፣ ውኃ አይቋጥርም፣ ሁልጊዜ ደረቅ ነው፤ ለዚህ ምን ይሁን ተብሎ ያጠጡታል፡፡
+ አላስፈላጊ ኢትዮጵያዊነት በልብ መሸጥ ነው፡፡ ራስንም መለወጥ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ሕግ ውጭ የሆነ አሠራር ደግሞ _መጨረሻው የኋሊት መውደቅ ነው፡፡
+ ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ የሚመጣ ሥልጣን ሁሉ የውርደት ሥልጣን ነው፡፡

❤7⚡2
Forwarded from Kesis Getnet Aytenew
ዐዲስ ፍልፈል አጥማቂ
ሰውየው ያልተማረ ጨዋ ነው። ክህነትም የለውም። የተማመነባት ጥንቆላውን ነው። አይዞህ የሚሉት የደብር ዐለቆችም አይጠፉም። መሣሪያው ገንዘብ ነዋ።
ይህ ሰው ጥንቆላውን የጀመረው በቸሪቱ ከተማ በሕገወጥ አጥማቂያን መፍለቂያ በዐዲስ አበባ ነው። የጀመረበት አጥቢያም በአያት ጣፎ ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ነው። ቆሻሻ እንዳገኘ ዝንብ ግርርር የሚለው ወገናችን ይኸው ገና ከአሁኑ መከተል ጀምሯል። በተለይም እነ ወለተ ቡሩኮች ናቸው። ዝም ብሎ ሳያመዛዝኑ መከተልን ያውቁበታል።
እንዲህ ያሉ አጭበርባሪዎች የበዙት ሕዝቡ ተአምር ፈላጊ ዐመጸኛ ትውልድ ስለሆነ ነው። አትራፊ ቢዝነስ ስለሆነ ክህነት አልባው ጨዋ ሁሉ ጀመረው። ደግሞ ለማጭበርበር እንዲመቻቸው። "የንስሐና የቄደር ጥምቀት፣ የፈውስ አገልግሎት ጥሪ" ይሉልሃል። ሕዝቤም በቀጠሮ ሊፈወስ ጀርደድ ይላል።
ሰው እንዴት ክህነት በሌለው ጨዋ ምእመን ይጠመቃል? ቤተ ክህነቱም ሞቶ ቃብር ላይ ስለሆነ እንደዚህ ባለ ጉዳይ አይተነፍስም። አንዳንዶችም የጥቅም ተጋሪዎች ናቸውና አፋቸውም አዕምሯቸውም እስረኛ ነው። ሌቦች ናቸው።

❤2