Telegram Web
'የሙታን መንፈስ ሳቢዎች'

ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን በዐለመ ነፍስ ያሉ ቅዱሳንን ስታከብር፥ አንዳንዶች
ኦርቶዶክሳውያንኮ የሞቱ ቅዱሳንን ስለሚያከብሩ" የሙታን መንፈስ ሳቢዎች ናቸው" ይላሉ።

ያረፉ ቅዱሳንን ማክበር የሙት መንፈስ መጥራት ከሆነማ በሐዲሱ ኪዳን የመጀመርያው 'ሙታን ጠሪ 'ራሱ ጌታችን ክርስቶስ ነው።

ከሞተ ሺ ስድስት መቶ ዐመት የሆነውን ሙሴን ጠርቶ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠለት እሱ ነውና። ከሙሴም በፊት 'የአብርሃም የይሥሐቅ የያዕቆብ አምላክ እኔ ነኝ' እያለ የሙታንን ስም ይጠራ ነበርና።

ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ደብረ ታቦር ናት። ከጌታዋና ከአምላኳ እንደተማረችው ሕያዋንና ሙታን የሆኑ ቅዱሳን ስማቸው በክብር ስለ ሚጠራባት።

©ሊቀ ሊቃውንት ስሙር አላምረው
10🥰1
🔴ብታምኑም ባታምኑም ይሄ ፈረንሳይ ነው🔴
የግብፅ ኦርቶዶክስ እጅግ የተሳካ ኦርትዶክሳዊ የወንጌል አገልግሎት በፈረንሳይ እያካሄደች ነው ። #ወደ_17_ሺህ የሚጠጉ ፈረንሳዊያን ባለፈው ዓመት በጥምቀት ወደ አማናዊቱ ቤተክርስቲያን መጨመራቸው ይታወቃል ።
➨ድንግል ማርያም በፈረንሳይ በተዋህዶ ልጇች ከበረች♥️
➨የፓሪስ እና የሰሜን ፈረንሳይ ሀገረ ስብከት የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በቅድስት ድንግል ማርያም ካቴድራል እና በሊቀ መላእክት ሩፋኤል (የሀገረ ስብከቱ መንበር) ድራቪ። የእየሩሳሌም እና የቅርቡ ምስራቅ መንበር ሜትሮፖሊታን ብፁዕ አቡነ አንቶኒዮስ ከጸጋው ጳጳስ ማ ጋር ተሳትፈዋል።

©ayu prince fb
3
2025/08/27 20:55:10
Back to Top
HTML Embed Code: