+ ማርያማዊ ደስታ +
ድንግል ማርያም ‘መንፈሴም በመድኃኒቴ በእግዚአብሔር ደስ ይላታል’ አለች፡፡ የድንግሊቱን ጥበብ ተመልከቱ፡፡ ‘በመልአክ በመመስገኔ ደስ ይለኛል ፣ ከሴቶች ሁሉ የተባረከች በመባሌ ደስ ይለኛል ፣ አምላክን ለመውለድ በመመረጤ ደስ ይለኛል’ አላለችም፡፡ የእርስዋ የደስታ ምንጭ ከእግዚአብሔር የተሠጣት ነገር ሳይሆን ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡
እግዚአብሔር የደስታህ ምንጭ ከሆነ በሕይወትህ ምንም ነገር ቢከሰት ደስታህን አይነካብህም፡፡ ድንግሊቱ ከሴቶች ሁሉ የተባረከች በመሆንዋ ደስ ያላት ብትሆን ኖሮ ከዚያ በኋላ ከሴቶች ሁሉ የተንከራተተች ፣ ከሴቶች ሁሉ ያዘነች ፣ ከሴቶች ሁሉ በዲያብሎስና ጭፍሮቹ የተጠላች ፣ በሔሮድስ በአይሁድ የተነቀፈች መሆንዋን ስታይ ደስታዋ በጠፋ ነበር፡፡
እርስዋ ግን ደስታዋ የመነጨው ከአምላክዋ ብቻ ነበር፡፡ ፍጹም የሆነ ውስጣዊ ደስታን ማግኘት የሰው ልጅ ትልቅ ምኞቱ ነው፡፡ ሰዎች ደስታን ፍለጋ ብዙ ይደክማሉ፡፡ ድንግሊቱ ግን የደስታ ሁሉ ምንጭ የሆነው አምላክ ከእርስዋ ጋር ነውና በፍጹም ደስታ ደስ ይላታል፡፡ የድንግል ማርያም ደስታ ልጅዋ ‘ደስታችሁን የሚወስድባችሁ የለም’ ያለው ዓይነት ደስታ ነበር፡፡ ዮሐ. ፲፮፥፳፪
‘ተፈሥሒ ፍስሕት’ (ደስተኛይቱ ሆይ ደስ ይበልሽ) ፤ ሙኃዘ
ፍሥሓ (የደስታ መፍሰሻ ሆይ) ብለን የምናመሰግናት እመቤታችን ከማንም የሚበልጥ ደስታ በእርስዋ ዘንድ ነበረ፡፡ ደስተኛ የነበረችው በምድር በነበራት ቆይታ የሚያስደስት ኑሮ ስለነበራት አይደለም፡፡ እንደ እርስዋ የተሰደደ ፣ ያለቀሰ ፣ የተጨነቀ ፍጡር የለም፡፡ እንደ ክርስቶስ መከራ የተቀበለ እንደሌለ እንደ ድንግል ማርያምም ያዘነ የለም፡፡ እርስዋ ግን ለሌሎች የሚተርፍ ወደ ኤልሳቤጥ የሚሸጋገር ፣ ሆድ ውስጥ ወዳለ
ፅንስ የሚጋባ ጥልቅ ደስታ ነበራት፡፡ ቅዱስ ያሬድ ‘ተፈሢሓ በነፍሳ ፆረቶ በከርሣ’ ‘በነፍስዋ ደስ ተሰኝታ በሆድዋ ተሸከመችው’ እንዳለ እርስዋ የተደሰተችው ሥጋዊ ደስታን አልነበረም፡፡ (ድጓ ዘቅዱስ ገብርኤል )ከመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎች አንዱ ደስታ ነውና ቅድስቲቱ ማንም ጋር ያልነበረ ደስታ ነበራት፡፡ ገላ. ፭፥፳፪
በእርግጥም ደስታን ወልዳ ደስ ባይላት ይደንቅ ነበር፡፡ እርስዋ የወለደችው ‘የመላእክት ተድላ ደስታቸው’ ነው ፤ እርስዋ የወለደችው መወለዱ ‘ለሰው ሁሉ ደስታ የሚሆን ታላቅ የምሥራች’ የሚሆን ልጅን አይደለምን?
እግዚአብሔር አብ ‘በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወድደው ልጄ ይህ ነው’ ያለውን አንድያ ልጁን ልጅዋ እንዲሆን ሠጥቶአታልና እርስዋም በምትወደው በልጅዋ ደስ ይላታል፡፡ ንጉሥ ዳዊት ‘ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሒድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ’ ካለ እግዚአብሔር የዘጠኝ ወር ቤቱ አድርጎ ያደረባት ድንግል ምንኛ ደስ ይላት ይሆን? መወለዱ ሰውና መላእክትን በደስታ እንዲዘምሩ ካደረገ የወለደችው ድንግል ምንኛ ደስ ይላት ይሆን?
ጌታ ለሐዋርያቱ ‘ስማችሁ በሰማይ ስለተጻፈ ደስ ይበላችሁ’ ካላቸው እግዚአብሔር ሁለተኛ ሰማዩ አድርጎ ዙፋን ያደረጋት በምድር ያለች የጠፈር ባልንጀራ ፣ የአርያም እኅት ማርያም ምንኛ ደስ ይላት ይሆን?
እመቤታችን ሆይ እባክሽን በአንቺ ላይ ከፈሰሰው ደስታ ቀድተሽ ወደ እኛ ወደ ኀዘንተኞቹ አፍስሺ፡፡ ኖኅ እንደ ላካት ርግብ የመከራችን ውኃ ጎደለ ብለሽ ታበሥሪን ዘንድ ወደ እኛ ነይ ‘ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ ኀዘነ ልብየ’ ‘ርግቤ ሆይ ከኀዘኔ ታረጋጊኝ ዘንድ ነይ’ እንዳለ ሊቁ፡፡
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ለበዓለ ዕርገታ ዝክር
ከብርሃን እናት ገጾች የተቆረሰ
ፎቶ :- የ2017 ደብረ ታቦር ከሞገስነ ክቡር የኔታ ሊቀ ጠበብት ሐረገ ወይን አገዘ ጋር

ለብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ሊቀ ጳጳስ የምስጋና መርሐ ግብር ተካሄደ።
ነሐሴ 17 ቀን 2017 ዓ.ም(ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
በሰሜን ወሎ መንበረ ጵጵስና ሀገረ ስብከት የወልድያ ከተማ አስተዳደር ቤተክህነት መንበረ ንግሥት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ከደብሩ ሰንበት ትምህርት ቤት ጋር በመተባበር ለብፁዕ አቡነ ቄርሎስ የምስጋና መርሐ ግብር አካሂዷል።
በሰንበት ትምህርት ቤቱ ሀሳብ አመንጭነት ትናንት ነሐሴ 16 ቀን 2017 ዓ.ም በተደረገው በዚሁ የምስጋናና የእውቅና መርሐ ግብር ብፁዕ አቡነ ኤርምያስን ጨምሮ ተጋባዥ እንግዶች፣ የሀገረ ስብከት፣ የወረዳ አብያተክህነት የሥራ ኅላፊች፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንና በርካታ ምእመናን/ት ተገኝተዋል።
በእውቅና መርሐ ግብሩ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ሊቀ ጳጳስ ባስተላለፉት ቃለ ምእዳን ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ከልጅነታቸው ጀምሮ ለቤተክርስቲያን አገልግሎት ዋጋ መክፈላቸውን ገልጸዋል።
ከመቅደላ እስከ ብልባላ፣ ከወሎ እስከ ጎንደር፣ ከሸዋ እስከ ወላይታና ሲዳሞ ክፍላተ ሀገር በእግር እየተጓዙ ያሳለፉትን ውጣ ውረድ፣ የቀሰሙትን የቤተክርስቲያን እውቀት፣ በተለያየ የአገልግሎት ደረጃ ያደረጉትን ሃይማኖታዊ ተጋድሎም አስታውሰዋል።
ብፁዕነታቸው ኹሉን ተምረው የተሾሙ በመሆናቸው በቤተክርስቲያኗ አገልግሎት ያስቀመጡት ታሪካዊ አሻራ ሳይደበዝዝ ሕያው ሁኖ እንደሚኖርም ተናግረዋል።
የመሠረ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት የብፁዕነታቸውን የማይረሳ አገልግሎት ኹልጊዜ ለማውሳትና ለሕፃናትና ማእከላውያን የነበራቸው፤ አሁንም ድረስ ያልነጠፈው ፍቅራቸውና ጸሎታቸው እንዲበዛላቸው የሰንበት ትምህርት ቤቱን ባለ ሁለት ወለል ኹለገብ ሕንጻ "ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ኹለገብ ሕንጻ" ተብሎ እንዲጠራ የስም ስጦታ አበርከቷል፡፡
የብፁዕነታቸውን ዐለም አቀፍ ሐዋርያዊ አገልግሎት የሚያወሱ ቅኔ፣ ያሬዳዊ ዝማሬና ሌሎች ዝግጅቶች የቀረቡ ሲሆን ሰንበት ትምህርት ቤቱና ሰበካ ጉባኤው ምእመናንን በማስተባብር ለብፁዕነታቸው ያዘጋጀውን ልዩ ስጦታ በብፁዕ አቡነ ኤርምያስ በኩል አበርክቷል።
ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ሊቀ ጳጳስ ሰንበት ትምህርት ቤቱ ሀሳቡን በማመንጨት መርሐ ግብሩን በማዘጋጀታቸው አመስግነው ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ከምሥረታ ጀምሮ ሕጻናቱን በመንፈሳዊ ሕይወት ኮትኩተው ለማሳደግ ብዙ የደከሙ በመሆኑና ውለታቸውን ለማስታወስ ሰንበት ትምህርት ቤቱ ተክለ ቄርሎስ ተብሎ እንዲጠራ ሰይመውታል።
©የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት

❤2