አኬ የሚባለው ልጅ ጥሩ መረዳት ያለው አንባቢና ምክር ቢሰማ ብዙ ሊያገለግል የሚችል ልጅ መሆኑን አልፎ አልፎ ሲናገር በሰማሁት ለመገንዘብ ችያለሁ፡፡ ዳሩ ግን ትዕቢት የተባለ ጾር ለዲያብሎስ አሳልፎ እየሰጠው ይመስላል፡፡
በጋሻውና ደጋፊዎችም 'ሕዝቡን ይዘን ስለምንወጣ ማንም አይነካንም፣ ስለዚህ እናቡካው ወይም ጨርሰን ይዘነው እንሂድ' ብለው ነበር፡፡ አሁን በጋሻው የት እንዳለ እንኳን የሚያስብ ኦርቶዶክሳዊ ያለ አይመስለኝም፡፡
ቤተ ክርስቲያንን ከሥሯ ለመነቃቀል አስበው የተነሡ አርዮሳውያንን የመሳሰሉ ፈተናዎችን ተቋቁማ እዚህ የደረሰች ቤተ ክርስቲያን አኬ የሚባልን ወጣት አሽሩሩ ትላለች ተብሎ አይታሰብም፡፡
አሁን መስመር እያለፈ ስለሆነ ያለው አማራጭ ወይ ንሥሐ ግብቶ መመለስና አቅልን መሰብሰብና እህ ማለት ካለሆነ ግን እስከ መጨረሻው አብረውት በጥፋታቸው የሚጸኑ መንጋዎቹን ይዞ መቆረጥ ነው፡፡
ነውር፣ ትክክል ያልሆነን እና መሠረታዊ ጥፋት የሚያሰድርስን ነገር ባለመወያየትና በማለባበስ ሳይሆን በግልጽ ተነጋግሮ አቋም በመያዝ መቋቋም የሚገባውም የሚቻለውም፡፡
ስለልጁ አስቡበት!!!
ዶ/ር አረጋ አባተ

👍7⚡3🤔2
በታቦተ ህግ ላይ የተሳለቀው ግለሰብ
የጥምቀትን በዓልን ምክንያት በማድረግ በታቦተ ህግ ላይ የተሳለቀው ግለሰብ 1 ዓመት ከ4 ወር እንዲቀጣ መወሰኑን የወላይታ ዞን አረካ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት አስታወቀ።
አረካ: መጋቢት 26/2017 ዓ.ም የጥምቀትን በዓልን ምክንያት በማድረግ በታቦተ ህግ ላይ የተሳለቀው ግለሰብ 1 ዓመት ከ4 ወር እንዲቀጣ መወሰኑን የወላይታ ዞን የአረካ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት ገልጿል::
ወንጀሉን ከፈፀሙት መካከል በቀን 25/05/2017 ዓ.ም በቁጥጥር ስር በማዋል የቆየው ወጣት አቤል አዳፍሬ ሲሆን ነዋርነቱ የአረካ ከተማ አረዳ ቀበሌ አስተዳደር ውስጥ ነው
ግለሰቡ በማህበራዊ ትስስር ገፅ ለተከታዮቹ ባጋራው የቲክቶክ ቪዲዮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ክብር የሚነካ እና የእምነቱ ተከታዮችን ያስቆጣ ተግባር መፈጸሙን ተከትሎ፤ በርካቶች "በሕግ መጠየቅ አለበት" የሚል ሀሳባቸውን ሲያንፀባርቁ እንደነበር ይታወሳል።
የተከሳሹም ክስ ሂደቱን መርማሪው ፖሊስ የምርመራ ሂደቱን ጨርሶ ወደ አቃቤ ህግ በማስተላለፍ ተከሳሹ በተከሰሰበት የወንጀል ህግ ጥፋተኛ በመሆኑ ፍርድቤቱ 1 አመት ከ 4 ወር ቀላል እሥራት እንድቀጣ ወስኖበታል።
የአረካ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ስምኦን ጋዲሳ የቅጣቱ ዋና ዓላማ አንድን አጥፊ ከንጹህ ህብረተሰብ በመለየት ላጠፋው ጥፋት በቂና ተመጣጣኝ ቅጣት በመወሰን አጥፊውን ማረም ማስተማር ማነጽ እና ሌላው ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈጽም ማስጠንቀቅና የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
አሁንም ፖሊስ አዛዡ አክለው ወንጀለኛው በቁጥጥር ስር እንዲውል ህብረተሰቡ ላደረገዉ ጥቆማና ፀጥታ አካላት ላደረጉት ብርቱ ክትትል በራሱና በተቋሙ ስም ምስጋና አቅርበዋል።
ወላይታ ዞን አረካ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት ህዝብ ግኑኝነት

👍7
ዘንድሮ ፕሮቴስታንቶች ከእውቀት ጋር የተጋፈጡበት ዘመን ነው!
…………………………………
በማህበራዊ ሚዲያ(ቲክቶክ) እቅበተ እምነት ላይ የሚሰሩ ኦርቶዶክሳዊ ወጣቶች ተመልክተን ተገርመን ሳንጨርስ ከወደ አሜሪካ የተገኘው ኦርቶዶክሳዊ ወጣት ዲን ምህረት ልዩ አገልግሎት ፈጽሟል፡ በየ ዩንቨርስቲ እየዞሮ ጠይቁን እንጠይቃችሁ በሚል ስራቸው ብዙ የማያውቁት፡ ወደ ራሳቸው እምነት በመጨመር የሚሰሩ አባትና ልጅ ፓስተር ትላንት የገጠማቸው ዲን ምህረት እንደሌሎቹ ቀላል አልሆነላቸውም እምነታችንን እናስጨብጠዋለን ብለው ክርክር የገጠሙት አባትና ልጅ ፓስተሮች ለሚጠይቁት ጥያቄ ባላሰቡት መንገድ እየመለሰ በሚጠይቃቸው ጥያቄ እያስቸገራቸው መውጫ ሲያሳጣቸው አባት ፓስተር ነገሩ ይረዝማል ብለው ሊያቋርጡት ተገደዋል።
ሁኔታው የዓለም መነጋገሪያ ሆኗል ሁለቱ ፓስተሮች በዚህ ስራቸውና በሚሰጡት እርዳታ በጣም ተቀባይነት ያላቸው ሰዎች ነበሩ በዚህ ውይይት የገጠማቸው ነገር ግን መወያያ ሆኗል።
እንግዲህ እግዚአብሔር እንዲህ አድርጎ የትኩረት ቀን ከሰጠን ይህን አቅም ሰብሰብ አድርገን ወንጌልን ለዓለም ለመግለጥ እንድንጠቀምበት ብዝዎቹን እውነት መስሏቸው ከሚኖሩበት የስህተት ጎዳና ማስመለጥ ሊሰራበት የሚገባ፡ የግል፡ የማህበራትና የቤ/ክ የወደፊት ትኩረት ስራ መሆን ይጠበቅበታል።
የተወሰነውን ውይይት በጽሁፍ በግርድፉ እንመልከተው
#ዲያቆን፣- በጥምቀት እና በቅዱስ ቁርባን ላይ ስላሎት አቋም ተናግረዋል እና እነሱ በመሠረቱ ምሳሌያዊ ናቸው ብለው እንዴት ያምናሉ? በእውነቱ ለመዳን ውጤታማ አይደሉም? በመሠረቱ የእኔ ትችት ወይም የእኔ ጥያቄ የአንደኛ፣ የሁለተኛው እና የሶስተኛው ክፍለ ዘመን ክርስቲያኖችን መዛግብት ስንመለከት እነዚህ ሁሉ ተምሳሌታዊ እንዳልሆኑ ለመዳን የሚረዱ ናቸው ይላሉ:በተቀበላቸው ሰው ላይ ትክክለኛ የመለኮት ውጤት እንዳላቸው ይታመናል። ጥያቄዬ ይመስለኛል የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜህ መጽሐፍ ቅዱስን በቀጥታ ከተቀበሉት ሰዎች ጋር ካልመጣ እንዴት መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን እየተከተልኩ ነው ትላለህ?የአዲሱን ኪዳን ቀኖናን እንኳን አሟልቷል?
#ፓስተር፦ የቀድሞ አባቶች ጉዳይ ነው ብለው የማያስቡም አሉ&በሁለቱም በኩል የምትጠቅሰው ማንን ነው?
#ዲያቆን፥- ሁለቱም ወገኖች የሉም ምክንያቱም በአንተ በኩል የሚያምን የተቀመጠ ማስረጃ የለንም።
#ፓስተር፥- ስለዚህ በኋላ ከሉተር ጋር ነው የመጣው የምትለው?
#ዲያቆን፥- ሉተር እንኳን አይደለም።ምክንያቱም ሉተር በታወቀ መንገድ ከፖፕ ጋር ደም መጠጣት እመርጣለሁ ብሏል።
#ፓስተር፥- ታዲያ እንዴት መጣ?
#ዲያቆን፥- የመጣው ዙዊንጊሊ እና ከአንዳንድ አክራሪ ተሃድሶ አራማጆች ነው 500 ዓመት ገደማ ማለት ነው።
#ፓስተር፦ ከቀኑ ጋር ያለው ችግር ምንድም፡ነው?
#ዲያቆን፥- ችግሩ በክርስትና የምናምን ከሆነ ክርስቶስ ለሐዋርያው የሰጠው እምነት በታሪክ ውስጥ በሐዋርያቱ ዘመን ይኖሩ ከነበሩት የአንደኛው መቶ ዘመን ክርስቲያኖች ማስረጃ ትጠብቃለህ ያ ካልሆነ በእነሱ እምነት ላይ እምነት እንዳይኖርህ ያደርጋል።
#ፓስተር፥- በዚያን ጊዜ ሁሉም ቁርባንን በወሰዱ ጊዜ ኢየሱስ የገዛ ሥጋውን እየበላ ደሙንም ይጠጣ ነበር ብለው በጥሬው ይህን አላሰቡም።ሁሉም ክርስቲያን አላደረገም። በታሪክ ቃል ልገባህ እችላለሁ፡ የታሪክ ማስረጃዎችህን አረጋግጥ:: አብዛኞቹ የቤተክርስቲያን አባቶች ባሳለፉት ነገር ልክ ነህ ብዙዎቹ ኢየሱስ በህብስቱ እንዳለ ደሙም በወይኑ ውስጥ እንደነበረ ይናገራሉ ነገር ግን እንዲህ ዓይነቱ ሃሳብ በጣም የተለጠጠ ነው
#ዲያቆን፦ አልተለጠጠም፡ ምክንያቱም ከቀደምት የቤተክርስቲያን አባቶች መካከል እያንዳንዱ ሰው በእርግጥ ሥጋውና ደሙ ነው ይላሉ።ወደ መጀመሪያው ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ 11 ስትሄድ የጌታን እራት ከመብላቱ በፊት ራሳቸውን በትክክል ያልመረመሩ ሰዎች ሊሞቱ ይችላሉ ይላል። ተራ እንጀራና ወይን ብቻ ከሆነ ቅዱስ ጳውሎስ ይህን ለምን አለ?
#ፓስተር ተገቢ ጥያቄ፡ ምክንያቱም ሰዎች በግልጽ የሚገባውን ያህል ለእግዚአብሔር አምልኮ፡መንገድ እያደረጉት አልነበረምና ነው። ያንተን ሃሳብ አከብራለሁ፡ እውነተኛ ሥጋና ደም ነው የሚለውን አከብራለሁ በዚህ ላይ ትልቅ ክርክር አላደርግም።ነገር ግን ይህም ሆኖ ጠንካራ ክርስቲያ ለመሆን ወይም አንድ ክርስቲያን በፍፁም ድኗል አትሉም። በtransubstantiation/መለወጥ/ ስለምታምኑ
#ዲያቆን፦ [አቋርጦ] በመለወጥ አላምንም በእውነተኛ መገኘት ነው የማምነው። መለወጥ የሚለው ፊዚካል ለውጥ ማለትም ህብስቱ ባህሪያዊ ልውጥ አድርጎ ሥጋ ይሆናል የሚል የካቶሊክ ትምህርት ነው በኦርቶዶክስ ግን እንዲህ አይደለም ባህሪያዊ ለውጥ ሳይሆን "እንደ ነው" እንደ ሥጋው ይሆናል ነው።ዋናው ነገር በሐዋርያት እምነት መያዝ አለብን እነሱ እውነተኛ ሥጋና ደም ነው ያሉት ያንን መቀበል አለብን
#ፓስተር፥- በሐዋርያት ካመንክና ሥጋውና ደሙ እውነትኛ ከሆነ ከዛስ አልዳንክም?
#ዲያቆን፦ ሳስበው መዳንን እንደ አንድ ጊዜ ነገር ነው የምትመለከተው ይሄ የፕሮቴስታንት አለም እይታ ነው።የጥንት ክርስቲያኖች መረዳት መዳን ከእግዚአብሔር ጋር አንድነት ነው, ስለዚህ ሂደታዊ ነው።
#ፓስተር፡- ሂደታዊ ነው ላልከው የምታቀርበው ቃል አለ?
#ዲያቆን፡- የቅዱስ ጳውሎስን መልዕክት ካነበብክ እንዴት እንደዳንን፡ እንዴት እየዳንን እንደሆነና እንደምንድን ያስቀምጣል,ያላፊ የአሁንና የመጪውን ነው ግን ጥቅም ላይ የዋለው ቃል በሁሉም ውስጥ መዳን ነው፡
#ፓስተር፥- ሂደታዊ ነው የሚለው ትንሽ ስሜታዊ ያደርጋል መጽሃፍ ቅዱስ በጸጋው ድናችኋል ይላል
#ዲያቆን፦ እናምናለን በጸጋው ድነናል፡ የእግዚአብሔር ኃይል አለ እርሱም ጸጋ ነው። ነገር ግን እኛ ደግሞ ከእግዚአብሔር ጸጋ ጋር መተባበርና ለእሱ ታማኝ መሆን አለብን ለዛ ነው ቅዱስ ጳውሎስ በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ መዳናችሁን ፈጽሙ ያለው።

👍10
#መጽሐፉ_ታግዷል!
ብፁዕ አባታችን አቡነ ዘካርያስን እናመሰግናለን!
ብፁዕነታቸው በእርግና እንዲህ ያለ ፈጣን መልስ መስጠታቸው ለመንጋው የሚጨነቁ ምን ያህል ታላቅ አባት እንደሆኑ ግልፅ ማሳያ ነው።
ጉዳዩን በፍጥነት በማዛመት መፍትሔ እንዲመጣ ያደረጋችሁ ሊቃውንት ሁሉ እግዚአብሔር አስበ ፃማችሁን አያጉድልባችሁ ።
መጽሐፉ በቀጣይ በዐይናማ ሊቃውንት ተመርምሮ እንደገና እንደሚታተም ተስፋ እናደርጋለን።
ይህን አይነት ስህተት እንዳይፈፀም ትምህርት ሊወሰድበት ይገባል።

👍9❤1
+ ምሕረት የለሹ ምሕረት +
የወንድሜ የዲያቆን ምሕረት መላኩንና የሁለቱን ፓስተሮች ውይይት ዘግይቼም ቢሆን አየሁት:: ውይይቱ በጣም በሰከነው የዲያቆኑ ኦርቶዶክሳዊ ጨዋነት የተነሣ ሁለቱን የፕሮቴስታንት ዋርካዎች በትሕትና ብቻ የገነደሰ ነበረ:: ቅመሙ ዲያቆን ምሕረት ውይይቱ እንደሚቀረጽ በደንብ ስላስተዋለ ጠይቆአቸው ሳይመልሱ ያለፉትን ወይም ያልተጠየቁትን ጉዳይ ያነሡበትን ቦታ ሁሉ ልክ ነጥብ "ተመልካች ይፍረድ" በሚመስል ብልጠት እየተወ ወደ ቀጣዩ ነጥብ የሚሸጋገርበት ፍጥነት ድንገት የገባበት ውይይት ሳይሆን የተጠና (scripted) ውይይት እንዲመስል አድርጎታል:: በጣም በትሕትና ሆኖ እየጠየቀ ዕርቃናቸውን ያሳየበት መንገድ ምን ያህል ሊያናድዳቸው እንደሚችል ሳስብ ውይይቱ በሰላም አለቀ እንጂ "ከአሁን አሁን ይመቱት ይሆን?" ብዬም ተሳቅቄያለሁ::
በውይይቱ ላይ ካየኋቸው ያስገረሙኝን ጥቂት እውነታዎች ውይይቱን እየተረክሁ ላስቀምጥ:-
ዲያቆን ምሕረት ውይይቱን የጀመረው የፓስተሮቹን አስተምህሮ ከቤተ ክርስቲያን ቅድምና አንጻር በማንሳት ነበር:: በዚህም ለፕሮቴስታንቱ ዓለም ደካማ ጎን የሆነውን ስስ ብልት በመምታት ጀመረ::
ነገሩ እንዲህ ነው:: መጽሐፍ ቅዱስን አሁን ባለው ቅርጽ እንዲህ አድርጋ የሠራችው ቤተክርስቲያን ናት:: ይህ እውነታ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስን በቀጥታ ከሐዋርያት እጅ የተቀበሉትንና ሐዲስ ኪዳን በቀኖና ወስነው ለእኛ ያስተላለፉትን የመጀመሪያዎቹን ክርስቲያኖች ትርጉምና አረዳድ እንድንቀበል ያስገድደናል:: ልክ እስራኤል ሕግን ተቀብሎ የመጣውን ሙሴን እንደ ባለ ሥልጣን እንደተቀበሉትና ስለ ሕጉ የእርሱን አሳብ ያለማወላወል እንደተቀበሉ ሁሉ ሐዲስ ኪዳንን ከሐዋርያት እጅ የተቀበሉትን የመጀመሪያው ክፍለ ዘመን አባቶችም በሐዲስ ኪዳን ትርጉም ላይ ያላቸውን ሃሳብ መቀበል ግድ ይለናል:: ይህን ጠንቅቆ የተረዳው ዲያቆን ምሕረት:-
ጥምቀትና ቁርባን ተምሳሌቶች እንጂ ለድኅነት ፍቱን አይደሉም ስትሉን ነበር:: ከአንደኛ እስከ ሦስተኛው ክፍለ ዘመን ያሉ ክርስቲያኖችን ሃሳብ ስናይ ደግሞ እነዚህ ነገሮች ለመዳን የግድ እስፈላጊ መሆናቸውን ጽፈው እናገኛለን:: የእኔ ጥያቄ መጽሐፍ ቅዱስን በቀጥታ ከተቀበሉትና ሐዲስ ኪዳንን በቀኖና ከደነገጉ ክርስቲያኖች ጋር ትርጓሜያችሁ ካልገጠመ ምኑን በመጽሐፍ ቅዱስ አመናችሁ ይባላል? አላቸው::
በአጭሩ መጽሐፍ ቅዱስን ያዋለዱትን አዋላጆች ካልሰማችሁ ምኑን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሆናችሁት "ድምፅህ የያዕቆብን ይመስላል ጸጉርህ ግን የኤሳው ነው" ያለው ለእናንተ አይደል ወይ? እንደማለት ያለ ነው::
ዲያቆን ምሕረት በዚህ ጥያቄው ሰዎቹን ጨርሶ ወደማውቁት ጨለማ ክፍል ወስዶ ቆለፈባቸው:: የአንደኛው ክፍለ ዘመን አባቶች ሥነ ጽሑፍና ታሪክ ለእነርሱ የማያውቁት የውጊያ ዐውድ ነው:: ወደ በኋላም በምሥጢረ ቁርባን ዙሪያ ባለው ግልፅ አቋምና ከሐዋርያት ጋር በነበረው ቅርበት የተነሣ የፕሮቴስታንት ሊቃውንት "ምነው ባልተፈጠረ" የሚሉትንና አንዳንዶቹም "እሱ አልጻፈውም" ብለው መጽሐፉን ለመካድ የሚገደዱበትን ቅዱስ አግናጥዮስን በመጥቀስ አስጨንቆአቸዋል::
የሚገርመው የሠጡት መልስ :-
የምትለው እውነት ከሆነ ለምን ሚልዮኖች ሳይቀበሉት ቀሩ? የሚል ልፍስፍስ ጥያቄ ነው::
ምሕረት መለሰ :- ይህማ እጅግ ብዙ ሰዎች ወንጌልን ላለመቀበላቸውም የሚቀርብ ምክንያት ነው::
ብሎ የራሳቸውን አመክንዮ በራሳቸው ላይ መለሰው:: በሳልሽው ተመተሪ!
ፓስተሩ :- እስቲ በሁለቱም ወገን (ጥምቀትና ቁርባን ለድኅነት ያስፈልጋል አያስፈልግም) ከሚሉ ወገን አባቶችን በስም ጥቀስልኝ አለው::
"መረጃ ተጠናክሮ በሁለቱም ወገን ይቅረብልን" እንደሚል ዳኛ ውይይቱን ትቶ ዳኛ ሊሆን ተማጸነው::
"በሁለት ወገን ብሎ ነገር የለም:: ከዚህ ውጪ ሃሳብ ያለው ሰው ስለመኖሩምንም የተቀመጠ ታሪካዊ ማስረጃ የለም" አለ ምሕረት የለሹ ምሕረት::
እዚህ ላይ እንኳን ደንግጠው ነው እንጂ እርሱ የጠቀሳቸው እነ ቅዱስ ሄሬኔዎስና ቅዱስ አግናጥዮስ መልስ የሰጡት ታዲያ ለማን ነበር? ብለው መጠየቅ ይችሉ ነበር:: ዶሲቲስቶችና ግኖስቲኮች ሙሉ በሙሉ የፓስተሮቹን ሃሳብም ባይሆን ቁርባን ላይ ተቃዋሚዎች ነበሩ:: የምሕረት መልአክ ቀሳፊ መልአክ ሆኖባቸው ግን ትንሽ እንኳን አልታገሉም:: ግን ዶሲቲስቶችና ግኖስቲኮች ተጠቃሽ ክርስቲያኖች ስላልሆኑ ሁለት ወገን አልነበረም ቢል ዲያቆን ምሕረት ልክ ነው::
"So you are saying” አለ ፓስተሩ:: የJordan Peterson እና የCathy Newmanን አስቂኝ ቃለ መጠይቅ ከሰማሁ ወዲህ ክርክር ላይ "So you are saying” ብሎ ተከራካሪው አፍ ውስጥ ቃላት ለመክተት የሚሞክር ሰው የራሱን ቀብር ጡሩምባ እየነፋ ይመስለኛል::
ፓስተሩ "እሺ ሉተርስ?" አለ:: (ኸረ ባልወልድህም አደርስሃለሁ ተው በሰው ፊት አታዋርደኝ:: ሉተር እንኳን ቁርባንን ተቃውሞአል በልልኝ [በሆዱ ያለ ይመስለኛል])
ምሕረት ወይ ፍንክች የሉተርን መፍቀሬ ቁርባን የሆነ "I would rather drink pure blood with the pope than mere wine with the radicals” የሚል ንግግር ሊጠቅስበት ጀመረ:: (በዚህ ጉዳይ ሉተርና ሚካኤል የሚል ያልታተመ መጽሐፍና ያልተለቀቀ የYoutube video ስላለ ሁለቱንም በቅርብ እዚሁ ላይ Link አደርጋለሁ) "ነገሩ የመጣው ገና 500 ዓመት ከሆናቸው ከራዲካል ሪፎርመሮች ነው" ብሎ የሉተርን ባላንጦች ጠቀሰበት::
ፓስተሩ "ጊዜው ምን ያደርጋል" አለ:: ስለ ታሪክ እየተወራ ጊዜው ምን ያደርጋል ከሚል ሰው ይሰውራችሁ::
"ከታሪክ አንጻር ክርስትና ጌታ ለሐዋርያት የሠጠው እምነት ነው ብለህ ካመንህ በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች የምታምነውን እንደሚያምኑ የሚያሳይ ነገር ልታገኝ ይገባሃል" አለው::
ፓስተሩ "ወዳጄ እመነኝ በዚያን ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች ሁሉ ክርስቶስ 'የራሱን ሥጋ' በልቶአል ብለው አላመኑም" ብሎ ነገሩን ridiculous ሊያደርገው ሞከረ:: ይህን ስሰማ ትዝ ያለኝ “ይህ ሰው ሥጋውን ልንበላ ይሰጠን ዘንድ እንዴት ይችላል?” ብለው አይሁድ የተከራከሩት ክርክር ነው:: ዮሐንስ 6:52
ጌታ ሥጋዬ እነሆ እያለ የለም ሥጋህ አይደለም ብሎ ክርክር እንዴት ያለ ነው::
ዲያቆኑ ሐዋርያውን ጠቅሰ "ሳይገባው ይህን እንጀራ የበላ ወይም የጌታን ጽዋ የጠጣ ሁሉ የጌታ ሥጋና ደም ዕዳ አለበት። ስለዚህ በእናንተ ዘንድ የደከሙና የታመሙ ብዙዎች አሉ አያሌዎችም አንቀላፍተዋል" 1 ቆሮ. 11:30 ከዚያም : "ሥጋና ደሙ ተራ እንጀራና ወይን ብቻ ከሆነ እንዴት ሳይገባቸው ተቀብለው የሞቱ ሰዎች ሊኖሩ ቻሉ?" ብሎ ጠየቀ::
አዝናኙ ውይይት እንደቀጠለ ነው:: ሰውዬው ጥያቄውን መመለስ ትቶ Unworthy ማለት worthy ያልሆነ ነው ብሎ ቃሉን አብራራ:: ቀጠለና ጉዳዩን ከማይገናኘው የሴት ጠጉር አለመሸፈን ጋር አገናኘው:: (ሲጀመር ጠጉር ስላልሸፈነች የሞተች የለችም እየተወራ ያለው ቆርበው ስለሞቱ ሰዎች ነው) አልበቃው ብሎ ስለ sex godess ስለ me too movement ዘባረቀ:: መልስ ስታጣ የምታውቀውን ሁሉ ልትዘባርቅ እንደምትችል ያሳያል::

👍2
ዲያቆኑን ማባበልም ጀመረ "የአንተን ሃሳብ የሚያራምዱ ሰዎችን ከልቤ አከብራለሁ:: እውነት እውነት እላችሁዋለሁ የሚለውን ይዘው ይህ እውነተኛ ሥጋው ነው የሚሉት ከልብ አከብራለሁ" አለ:: አክባሪ ይሥጥልን ግን እኛ ይሄን ጥቅስ እንደማስረጃ አላነሣንም:: ዲያቆኑ እዚያው ቆሞ "ለተራ እንጀራ ሰው እንዴት ይሞታል?" ብሎ የጠየቀውን ፍጥጥ ያለ ጥያቄ ትቶ ከዚህ በፊት ሌሎች ሰዎች ያነሡትን weak argument እየጠቀሰ እንዲህ በለኝና ልርታህ ብሎ ተለማመጠ:: (ተው ባልወልድህም አባትህ እሆናለሁ is in my head)
ከዚያ ደግሞ በmystical change የሚያምነውን ኦርቶዶክሳዊ በግድ transubstantiationን ካላመንክልኝና እርሱን ለመቃወም ያጠራቀምኩትን መከራከሪያ አንተ ላይ ልጠቀመው ይል ጀመር::
ቀጥሎ የተነሣው ድኅነት ሒደት ነው የሚለው ሃሳብ ነው:: ይሄን ጊዜ ፓስተሩ ከቁርባን ርእስ እርፍ ያለ መስሎት ፈነደቀ::
"It is now becoming a salvation issue” እያለ ሲቅበጠበጥ አሁን ገና ተመቻቸህልኝ ብሎ ደስ እንዳለው ያስታውቅ ነበር:: ምሕረቱ "ድናችኋል ብቻ ሳይሆን ትድናላችሁም ይላል" ብሎ የድህነትን ሒደታዊነት አብራራ::
ይህን ጊዜ ሌላው ፓስተር ጸጋ አላስቻለውምና ገባ
ፓስተር ጸጋ " በጸጋው ድናችኋል” ይላል አለና ዘሎ ገባ::
ድኅነት synergetic ስለሆነ የጸጋው energy የእኛን ትብብር ይሻ የለም ወይ? አለና ምሕረቱ "መዳናችሁን ፈጽሙ"ን ጠቀሰ:: አብርሃምም ልጁን የመሠዋቱን ሥራ አነሣ:: እነርሱ ግን "work out your salvation” የሚለው ቃል ውስጥ “work” የሚል ቃል ሲሰሙ ደስታቸውን መሸከም አልቻሉም:: ቃሉን ጳውሎስየተናገረው መሆኑም አላሳሰባቸውም::
ሥራን ለማጣጣል የቀኙን ወንበዴ ጠቀሱ:: ተቸንክሮ ምን ሊሠራ ይችላል አለ:: (Though the thief on the cross was nailed, he still worked on his salvation. He confessed his sin, saying that he was worthy of the cross. He taught his companion to fear God, and he professed the purity of Christ and the coming of His kingdom)
እግዚአብሔር ባልሠጠው መክሊት አይጠይቅምና circumstantial ነው አለ:: ሊሞት አልጋ ላይ ስላለ ሰው አለመጠመቅ አላወራሁም ብሎ ሞገተ::
ከዚህ በኋላ ያለው ውይይት ዲያቆን ምሕረትን በግድ ካቶሊክ ካልሆንክ የሚል ንትርክ ነው:: inflability of the councils, vatican 1 2 3 etc
"የቅዱስ ቁርባን ደምን የሰጠው ከእጁ እየፈሰሰ ነበር" የሚል ያላልነውን በሉ የሚል ቃልም በጌታ እንደመዘበት እያለው ተናገረ:: It is not right to ridicule Christ for the sake of argument.
አራት መቶ ዓመት አልፎ ሃሳቡን የAugstine ሊያደርግበት ሲጥር ምሕረት ውይይቱን ወደ አግናጥዮስ ዘመን መለሰው:: የመጨረሻው ጥያቄያቸው
Who is the ultimate authority? የሚል ነበር::
ሲመስለኝ ከዲያቆን ምሕረት የጠበቁት መልስ "The Bible” የሚል ነበር:: እርሱን ካለ "If the Bible is the ultimate authority, where does it say that the first Christians believed it is the actual body and blood?” ብለው ሊዘጉትና መጽሐፍ ቅዱስን ከጻፈው እውነት በላይ ያንን እውነት ሰዎች እንዲህ ተረድተውት ነበር እንዲል ጠይቀው ውይይቱን ሊዘጉ ነበር::
ምሕረት የለሹ ዲያቆን ግን Bible በማለት ፈንታ Bibleን በቀኖና የወሰነችውን The Body of Christ ይዞ የሙጥኝ አለ:: የእናቱን የቤተ ክርስቲያንን ቀሚስ ይዞ ድርቅ ሲል
Good to meet you brother አሉና ጨበጡት በአማርኛ ሲተረጎም
"አንተን ብሎ ምሕረት መዓት ሆንክብን እንጂ" እንደማለት ነው::
My beloved brother, Deacon Mihret, may God bless you. We saw ‘Berekete Estifanos’ in you. May God guide your path
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ሚያዝያ 3 2017 ዓ.ም.

👍4❤1