ቤተክርስቲያንን በሁለት መንገድ ማወቅህን አረጋግጥ
እንደ አሕዛብ ጠላቷ እንዳትሆን በትምህርትዕወቃት እንደ ፈሪሳውያን እንዳትሆን በኑሮ ዕወቃት!
ለሥርዓቷ ታማኝ ሁን፥ አንተ ወደ ሥርዓቷ እደግ እንጅ ሥርዓቷ ወደ አንተ ፈቃድ እንዲወርድልህ አትውደድ፤ ሰማያውይቷን ቤተክርሰቲያን ምድራዊት እንድትሆንልህ አትፍቀድ!
በቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አንድነቶች ካልተሳተፍክ ከቤተክርስቲያን አንድነት እየተለየህ እንደሆነ እወቅ፤ እሊህም ኪዳን ማስደረስ፥ ማስቀደስና ንስሐ ገብቶ መቁረብ፥ በምህላ ጸሎቶቿ በአዋጅ አጽዋማቷ መተባበር ናቸው!
ከቤት ከሚጸለይ አሥር ጸሎት ይልቅ በቤተክርስታያን የሚደረግ አንድ ጸሎት እንደሚበልጥ አውቀህ በየቀኑ ወደ እርስዋ ገሥግሥ፤ በሕይወትህ ሁሉ ቤተክርስቲያናዊ ሁን!
#አባ_ገብረኪዳን

❤21👍5🙏4
👉ዮናስ ጎርፌ የተባለው የፕሮቴስታንት ግለሰብ የጻፈው ነው። ተጠንቅቃችሁ በጥንቃቈ አንብቡት
የኦርቶዶክሱ ጳጳስ ቅድስት ድንግል ማርያምን ”ቤዛ” አይደለችም የሚለውን ጉዳይ ማንሳታቸው ሞቅ ያለ ሞቅታ በእኛው ቤት ሰሞኑን ገጥሞት ሳይ፣ “ለመሆኑ ይህ ጉዳይ የእኛ ስነ መለኮት ጥያቄ ጉዳይ ነው? ካልሆነስ እንደው እኛን የዚህን ያህል ከንክኖን የጨዋታው ማእከላዊ ኮከብ ለመሆን ለምን ፈለግን?” የሚለው እንደው ሲያሳስበኝ ከርሟል። በተሀድሶ ስም (ተሀድሶ የተም ሀገር ሰርቶ አያውቅም፣ እነ ሉተርም ካቶሊክን አላደሱም ጥለው ወጡ እንጂ) የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን መንኮታኮት ማየት የሚፈልግ አለ ማለት ነው? ብዬ እንድታዘብም አድርጎኛል።
እንደገባኝ መነኩሴው "ማርያም ቤዛ ልትሆን አትችልም" የሚል ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቀኖና ወጪ የሆነ ትምህርት አስተምረው ነበር የሚል ክስ ነው ዋናው ጉዳይ። በኃላም እንደሰማንው ጳጳሱ ለዚህ ጉዳይ መልስ ሲሰጡ ነገሩ እሳቸው ካሉት ሀሳብ ውጪ (out of context) ተመንዝሮብኛል እንጂ እኔ እንደዛ አላምንም የሚል ማስተባበያ ሰጥተዋል። ይህ ማስተባበያቸው የኛን ቤት ሰዎች ብዙም ያስደስተ አይመስልም።
የእኔ ሀሳብ ያለው እሳቸው ያሉትና በኃላም እንደሱ ማለቴ አይደለም በሚለው ውዝግብ ላይ አይደለም። የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጉዳዩን ጠበቅ አድርጋ ይዛ ማስተካከያ እንዲደረግበት ማድረጓ ቀነኖዋ ነውና ልክ አድርጋለች። የእኛዎቹም ቤት ሰወች በተለያዩ አስተምህሮቶች ላይ የሚያምኑትንና የቆሙበትን ቀነኖ በትክክል ቢያውቁ ከእነ እዩ ጩፋ ጋር መድረክና ድርጅት ባልተጋሩ ነበር። ይህ ቤተ ፕሮቲስታንቱ (ጰንጠቆስጤው) ትምህርት ሊወስድበት የሚገባ ነገር ነው።
የፕሮቲስታንት/ጰነጠቆስጤው ማሕበረሰብ ማርያም “ቤዛ ናት አይደለችም” የሚለው አስተምህሮት የሚመለከተው ካልሆነ ይህን ያህል በሌላ ቤተ እምነት ውስጥ ገብቶ ለመፈት ፈት ምን ግድ አለው? የሚለው ጥያቄ ለእኔ ሚዛን ይደፋል። የክርስቶስ ልብ አለን እንደሚል አማኝ (ጰንጠቆስጤው) በዛኛው በኩል ክርስቲያን ወንድሞቹ (ኦርቶዶክሳውያኑ) የተካረረ ጠብ ውስጥ ሲገቡ (ጉዳዩ ስነ መለኮታዊ ብቻ ሳይሆን ጳጳሱ ፖለቲከኛ ሹመኛም ናቸው የሚል አስቀያሚ አዝማሚያም ይዞ ስለነበር) አባቶቹዋ ወደተሻል መግባባት እንዲመጡ መጸለይና ቤተ ክርስቲያኒቱ ከመናጋት እንድትጠበቅ በቅን ልብ ሊመኝ በተገባው ነበር።
ይህ ትውልድ ለዚች ቤተ ክርስቲያን የታሪክ ባለእዳ እንደሆነ ሊያውቅ ይገባዋል፣ እስከነ ችግሯ። ጠንካራ መሰረት ላይ የተመሰረተች ቤተ ክርስቲያን ባትሆን ዛሬ ኢትዮጵያ ፍጹም በእስልምና አስተምህሮት ውስጥ በወደቅች ነበር። ለዚህ ብዙ ርቆ መሄድ አያስፈልግም፣ ግብጽ፣ ቱኒሲያ፣ አልጄሪያ፣ ሞሮኮ፣ ቱርክ ሌሎችም የሰሜን አፍሪካ ሀገራት ሙሉ በሙሉ የክርስቲያን ሀገራት (መዲናዎች) የነበሩ አሁን ግን ከግብጽ 10 ፐርስንት በቀር ፍጹም ክርስትና ጠፍቷል። ኢትዮጵያ ግን በዚህች ቤተ ክርስቲያን ብዙ ስደትና እንግልት (የነገስታቱም ጣልቃ ገብነት ሳይዘነጋ) ክርስትናን በተጠናከረ መልኩ እዚህ አድርሰዋለች። በዚህም የተነሳ የፕሮቲስታንቱ፣ ማናልባት ከሰማንያ በመቶ በላይ አበል የተገኘው ከዚችው ቤተ እምነት ከፈለሰ ሕዝብ ነው። ሀገሪቷ ከላይ እንደዘረዝርኳቸው ሀገራት በእስልምና ተውጣ ቢሆን ኖሮ ይህ እድል በጭራሽ ባለተገኘ ነበር። ፕሮቲስታንቱ ለኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የታሪክ ባለእዳ ነው። RESPECT THAT!!!!
ይህ ትውልድ ልብ ሊለው የሚገባ ነገር ቢኖር፣ እኳን ሁለት ሺህ አመተ የዘለቀች ቤተ ክርስቲያን ይቅርና (በተለያየ የአስተምህሮት ውጥንቅጥ ውስጥ ማለፏ ማለቴ ነው) የዛሬ 500 አመት የመጣው የተሀድሶ እንቅስቃሴ በሺዎችና በሺዎች ቦታ ተሰነጣጥቆ የክርስትና መዳከም ዋና ምክንያት ሆኗል። አውሮፓና ሰሜን አሜሪካ ለዚህ ሕያው ምስክር ነው። የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ሲነሳ በፕሮቴስታንት (በሉተራዊ) ቤተ እምነት ውስጥ እንዳለ ሰው በታሪካችን ይህን ያህል ደረታችንን ነፍተን የሚያስኮፍሰንና ሌላውን (ኦርቶዶክሱን/ካቶሊኩን) በንቀት አይን እንድናይ የሚያረገን የሞራል ብቃት ያለው ማሕበረ ሰብ አይደለንም። የሰሞኑንን የሟቹን የካቶሊኩን ጳጳስ የሀብት ታሪክ ለሰማ (በባንካቸው ውስጥ 100 ዶላር ብቻ ነው የተገኘው) የኛዎቹ የእግዜር ሰዎች የሀብት ማማና የፎቅ ብዛት ወይም የሚለዋውጡትን መኪናና ሱፍ ብዛት ላየ እንደው በየትኛው የሞራል ሆነ የመንፈሳዊ ብቃቱ ነው ይህ ህዝብ (ፕሮቴስታንቱ/ጰንጠቆስጤው) በነዚህ ሰወች ላይ አፉን ማላቀቅ የሚችለው?! (የኛን ሀገር ጳጳሳትም የሀብት ማማ አልዘነጋሁትም። እርሱም ሌላ ማፈርያ ነው)
ነጥቤ ሲሰበሰብ፣ በወንድሞቻችንና በአባቶቻችን መካከል የተፈጠረውን የስነ መለኮት አስተምህሮ ልዩነት ጉዳይ ሲነሳ፣ ብንችል በዝምታ እየጸለይንላቸው (የክርስቶስ ልብ ያለው ይህን ነው የሚያደርግ) ጉዳዩን ማየት፣ ካልሆነም ደግሞ በጉዳዩ ላይ የስነ መለኮት interest ካለን (ለምን እንደሚኖረን ግን አይገባኝ፣ ምክንያቱም ይህ ጉዳይ በፕሮቴስታንቱ መካከል ጥያቄ ሆኖ ሲነሳ ሰምቼ አላውቅም) ጉዳዩን ለራሳችን ሰወች በሚመጥን መልኩ ከመጽሐፍ ቅዱሱም ከቤተ ክርስቲያን ታሪክም እያቀረቡ ማስረዳት ነው እንጂ የሌላውን ቤተ እምነት በሚያዋርድና በሚያንቋሽሽ ሁኒታ ማቅረቡ ልክ አይመስለኝም። ንጽጽር ውስጥም መግባቱ በጭራሽ ልክ አይደለም። ምክንያቱም ሁለት የተለያየ ቀኖና ነውና።
በዚህ ላይ ይህ የማርያም ቤዛነት ጉዳይ (ከማማለድ ጋር የተያያዘ መሆኑ ልብ ይሏል) አዲስ የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮት አይደለም። Athanasius of Alexandria (c. 296–373 CE)፣ ወላዲት አምላክ/ Theotokos ("God-bearer" or "Mother of God" የሚለውን አስተምህሮት ሽንጡን ገትሮ የተሟገተ ነው። Ambrose of Milan (c. 340–397 CE) ማርያም ያለሀጢያት (sinless) ነበረች ብሎም አስተምሯል። Gregory of Nyssa (c. 335–395 CE) ደግሞ ስለ አማላጅነቷና በድንግልነቷ ወልዳ በድንግልነቷ እንደኖረች (ከዚያ በኋላ አልወለደችም ማላት ነው) ጽፏል። ከዚያም ቤተ ክርስቲያን (“ቤተ ክርስቲያን” ነው ያልኩት “ካቶሊክ ወይም ኦርቶዶክስ” አላልኩም። በዚያን ጊዜ እንዲህ የሚባል ነገር አልነበረምና። አንዲት ሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን-One Apostolic Church ብቻ ነበረችና) በ Council of Ephesus (431 CE): Declared officially that Mary is Theotokos — Mother of God, not just mother of Christ’s human nature. (የፈጣሪ እናት እንጂ የክርስቶስ የስጋው እናት ብቻ አይደለቸም) ብላ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ቀንናለች። (ልብ በል ቤተ ክርስቲያን ነች ይህን የቀነነችው፣ ግለሰብ ጳጳሳት አይደሉም) እንግዲህ ይህቺ ቤተ ክርስቲያን የነዚህ ጥንት አባቶች አስተምህሮት ተከትዬ ነው የመጣሁት ነው የምትለው። አንዳንዶች፣ በተለይ ከተሀድሶ መጣን ከሚሉት እንደምንሰማው ዘረ ያቆብ ነው ይህቺን ቤተ ክርስቲያን እንዲህ ያበላሻት እንድሚሉን አይደለም ታሪክ የሚነግረን።

👍8❤1
በስነ መልኮት አፈታቷ ላይ አለመስማማት ይቻላል። የእኔም አቋም እንደ አንድ ሉተራዊ አማኝ በዚህ አስተምህሮቷ ላይ አልስማማም። ግን ይህ ባለመስማማት መስማማት ላይ ነው እንጂ ቤተ ክርስቲያኒቱ በራሷ አስተምህሮት ላይ ውዝግብ ውስጥ ስትገባ የእብድ ገላጋይ ሆኜ ድንጋይ አቀባይ መሆኑ አግባብነት ያለው አይመስለኝም፣ በተለይ በፍጹም የእኔ ስነ መለኮት ጥያቄ ባልሆነ ጉዳይ ውስጥ።
“የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ” ነው የሰሞኑ የፕሮቴስታንት/ጰንጠቆስጣውያን ጉዳይ!!
አንዳንድ ወዳጆቼ በቂ ማስረጃ በተለይ በጥንቷ ቤተ ክርስቲያንና በማርያም አማላጅነት ዶክትሪን በኩል አላቀረብክም ስላሉኝ (እኔ ጽሁፉ ይረዝማል በሚል ስጋት ነው የተውኩት እንጂ የማስረጃ እጦት አይደለም)፣ ምንም እንኳን በጣም በርካታ መረጃዎች ቢኖሩም የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ድንግል ማርያምን በተመለከት እንዲህ ነበር የምታስተምረው:-
When did the Church start teaching about Mary as Intercessor (አማላጅነት)?
• Very early — The idea that Mary could pray for Christians and help intercede before God started in the 2nd–3rd centuries.
• It wasn’t yet a full "official dogma," but the faithful and some early Fathers were already showing honor and trust in Mary's special role.
(እዚህ ጋር ልብ ሊባል የሚገባው ከሐዋርያት እግር ስር ቁጭ ብለው በተማሩት አባቶች በኩል (ከ30-100 CE)ይህ አስተምህሮት እንደማይታወቅ ነው)
• The teaching grows slowly — first as love and honor ➔ then trust in her intercession ➔ and much later formal dogma.
• 3rd century Some prayers asking Mary's help start appearing
• 4th century Church Fathers begin to explicitly call Mary intercessor
• 5th century Strong defense of Mary’s intercession at Council of Ephesus (431 CE).
• Origen 250 CE Said Mary continues to help spiritually by her role as Mother
• Ephrem the Syrian 306–373 CE Called Mary "the mediatrix" (helper between God and men) — very strong advocate!
• Ambrose of Milan 306–373 CE Taught that Mary prays for all Christians and is honored as the Mother of the Church.
• Augustine 354–430 CE Spoke of Mary as helping bring Jesus to us, and Christians trusting in her prayers.
Ephrem the Syrian 306–373 CE Called Mary "the mediatrix" (helper between God and men. even calling her things like "Mediatrix of all the world. very strong advocate!
• Ambrose of Milan 340–397 CE Taught that Mary prays for all Christians and is honored as the Mother of the Church
በተለይ ይሄ ከዚህ ቀታች ያለው ጸሎት የማርያም አማላጅነት አስተምህሮት የከረመ እንደሆነ ያሳያል
One of the oldest surviving Christian prayers asking for Mary's help is called the Sub Tuum Praesidium, dating from about 250 CE:
"We fly to your protection, O Holy Mother of God; do not despise our petitions in our necessities,but deliver us from all dangers,
O glorious and blessed Virgin."
ባጭሩ ነጥቤ ያለው የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ጉዳይ ላይ ማስተማር ከጀመረች 2000 አመት ሊጠጋው ምንም አይቀረውም። አጼ ዘረያቆብ ወይም ጊዮርጊስ ዘግስጫ የዛሬ 500 የጀመሩት ጉዳይ አይደለም።

👍8
አስደሳች ዜና
የኦሬንታል ኦርቶዶክስና የምስራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት አንድነት ለማድረግ የሚደረግ ውይይቶች ፍሬ ሊያፈሩ ይመስላል።
በዘመናችን፣ በእኛ እድሜ ይህ ታሪካዊ ምዕራፍ ላይ መድረሳችን በእውነትም የእግዚአብሔር ቸርነትና ምህረት ነው::
በኒውዮርክ የተደረገው የሊቃነ ጳጳሳት ስብሰባ እጅግ ፍሬያማ እንደነበርና ለታላቁ የኒቂያ ጉባኤ 1700ኛ ዓመት በዓል ዝግጅት ላይ ያተኮረ መሆኑ እጅግ የሚያበረታታ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በመወከል ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) በውይይቱ መሳተፋቸው ለዚህ አንድነት ያለንን ጽኑ አቋም ያሳያል።
የኦሬንታል ኦርቶዶክስና የምስራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በታሪካዊ ስብሰባ አንድነትን አሳዩ
በኒውዮርክ ከተማ የኦሬንታል ኦርቶዶክስ እና የምስራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ሊቃነ ጳጳሳት ተገናኝተው በአብያተ ክርስቲያናቱ መካከል ስላለው አንድነት እና በዚህ አመት ስለሚከበረው የ325 ዓ.ም. የኒቂያ ጉባኤ 1700ኛ ዓመት መታሰቢያ በዓል ላይ በሰፊው ተወያይተዋል።
በዚህ ታሪካዊ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በመወከል ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) የተሳተፉ ሲሆን፣ የሁለቱን ቤተ ክርስቲያናት አንድነት ለማጠናከርና የጋራ ትብብርን ለማሳደግ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ገንቢ ውይይት ተደርጓል። በተለይም የኒቂያ ጉባኤ ያስተላለፋቸው የሃይማኖት ትምህርቶች የሁለቱም አብያተ ክርስቲያናት የጋራ መሠረት እንደሆኑ በመገንዘብ፣ ይህንንም ታሪካዊ ክስተት በጋራ ለማክበር ዝግጅቶች እየተደረጉ ናቸው።
እነሆ፥ ወንድሞች በአንድነት ቢቀመጡ መልካም ነው የሚያስደስትም!
መዝሙር 133:1
የወንድማማችነትን አንድነት ምን ያህል መልካምና ደስ የሚያሰኝ እሙን ነው ።
ሁሉ አንድ ይሆኑ ዘንድ፤ አንተ እንደ ላክኸኝ ዓለም ያምን ዘንድ፥ እነርሱም ደግሞ በእኛ አንድ ይሁኑ፤ አባት ሆይ፥ አንተ በእኔ እኔም በአንተ እንዳለን። እኔም በእነርሱ አንተም በእኔ እንሆን ዘንድ፥ በአንድነት ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ ክብሬን የሰጠኋቸውን እኔ በእነርሱ አንተም በእኔ እንሆን ዘንድ፥ በአንድነት ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ ክብሬን የሰጠኋቸውን አሳውቄአቸዋለሁ።
ዮሐንስ 17:21-23
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ደቀ መዛሙርቱና አማኞች ሁሉ አንድ እንዲሆኑ አጥብቆ አስተምሮል።
ሊቃውንቱም እነ ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ እንዳስተማረው፡-
"አንድነት የፍቅርና የሰላም መሠረት ነው፤ በክርስቶስ ያመኑ ሁሉ በአንድ ልብና በአንድ ሐሳብ ሊኖሩ ይገባል።"
አንድነት የክርስትና እምነት ዋና መሠረት ሲሆን፣ አማኞች በፍቅርና በሰላም በአንድነት መኖር አለባቸው።
ይህ በእውነትም እጅግ ደስ የሚል ዜና ነው! የኦሬንታልና የምስራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት ወደ አንድነት መምጣት የዓለምን ክርስቲያኖች ሁሉ የሚያበረታታና የእግዚአብሔርን ክብር የሚያሳይ ታላቅ ክስተት ነው። ለዚህም ቀን እንድንደርስ ላደረገን ልዑል እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን!
©Tewahido - ተዋህዶ

❤1
አስደሳች ዜና
እጅግ የምንወዳቸው የቦሩ ሜዳ ጉባኤ ቤት ፍሬ የሆኑት፤ በቦሩ ሜዳ ቅድስት ሥላሴ ጉባኤ ቤት የመጻሕፍተ ሐዲሳት መምህር የነበሩት፤ በወሎ ዩኒቨርሲቲ በግዕዝ ቋንቋ መምህርነት እያገለገሉ የሚገኙት ሰይፍ ዘክልኤ አፉሁ መምህራችን የንታ Hailemariam Zewdu ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ Masters of Geez and Literature የሁለተኛ ዲግሪያቸውን በከፍተኛ ውጤት አጠናቀዋል።
የንታ ሃይለማርያም ዘውዱ የመምህር ገብረ መድኅን እንየው የመምህር መዝገበ ቃል የቀለም አባት ናቸው።
የንታዬ እንኳን በሰላም አስፈጸመዎት።
እግዚአብሔር ይመስገን
እንኳን ደስ አለን
"ወትምህርትከ ውእቱ ያጸንዓኒ ለዝሉፉ።"
ትምህርትህ ለዘላለም ታበረታኛለች መዝ 17:35
©mercy abebaw

❤15👍5
+ + ብዙ ዐየን + + +
በዚህ ሂደት ብዙ ዐየን። የብዙ ብዙ ተዛዘብን። በተለይ ባለሁለት መልኮችን። ቀን ቀን እዚህ ፤ ማታ ማታ እዚያ የሚረግጡ ብዙ ነበሩ። አጋጣሚውን ተጠቅመው ሊያጠቁንም የሞከሩ ነበር። አይተን እንደአላየን፤ ሰምተን እንደአልሰማን አልፈናል። ሁኔታው የሚጠይቀው ይህንን ነበረና።
ይህን መዋቅራዊ ሂደት ለማደናቀፍ አንዳንዶች ድግስ ደግሰው አበሉ። አንዳንዶች እኛ ዕግድ እንዳይተለለፍብህ ስንታገልልህ፤ እገሌ ዕግደ እንዲተላለፍ አደረገ አሉ። አንዳንዶች አንተ ብቻ ታግስ፥ ለአንተ የሚስማማ ውሳኔ እንዲወሰን እናደርጋለን አሉ። አንዳንዶች እኛን ከያዝክ ዕዳው ገብሰነው ማለታቸውን ሰማን። አንዳንዶች ለጊዜው የማኅበራዊ ሚዲያውን ጫጫታ ለማብረድ ዕግድ ተጣለብህ እንጂ፥ አጥፍተህ አይደለም እያሉም እንደሆነ ሰማን። እውነታዎቹ ግን እነዚህ አይደሉም። እዚህ ደብዳቤ ላይ የሰፈረው ነው።
ደጋግሜ በግሌም፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና መምህራን ባሉበት ለአቶ ጸጋዬም ሆነ ለፍኖተ ጽድቅ ሰዎች ያልኳቸውን እዚህ ላስታውስ እወዳለሁ። “ፍኖተ ጽድቅ ኦርቶዶክሳዊ የሚያደርገው ወይም የሚያሰኘው ኦርቶዶክሳዊ መሠረት እምነትን፣ ሥርዐተ አምልኮንና ትውፊትን ጠብቆ ማገልገሉ እንጂ፥ የቅዱስነታቸው መሔድ፤ የጳጳሳቱ መመላለስ፤ የኦርቶዶክሳውያን መምህራን መገኘትና የቴክቶክ ወንድሞች ዘገባ አይደለም። ኦርቶዶክሳዊ አሰተምህሮን ካልጠበቀ ለውግዘት ያቀርበው ይሆናል እንጂ፥ አይረባውም።”
አሁንም በይፋ የምለው ይህንኑ ነው። መዳኛህ ኦርቶዶክሳዊ መሆንህ እንጂ፥ ሰዎችን ለመያዝ በመሞከር አይደለም። ሂደቱ ያሰተማረን ይህንኑ ነው። ይቆየን። ለሂደቱ በዝርዝር እመልሳለሁ ።
👉መምህር ታደሰ ወርቁ

👍6
በዋሽንግተን ዲሲ ቅዱስ ጳውሎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 11 ንዑሰ ክርስቲያን ተጠምቀው የሥላሴን ልጅነት አገኙ !
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን !
አሜን !
👉ተሚም እንደዘገበው
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን !
አሜን !
👉ተሚም እንደዘገበው
❤26👍1
አባ ገብርኤል ቋሚ ሲኖዱሱ የወሰነባቸውን ''በጊዜያዊነት በመንበረ ፓትርያርክ በተዐቅቦ ይቆዩ'' የሚለውን ውሳኔ ጥሰው ዛሬ አምቦ ከተማ ውስጥ ሰልፍ አደራጅተው መንገድ ለመንገድ በቲፎዞዎቻቸው (በጴንጤና በንኡስ ብሄርተኛ) መፈክር ሲያሰሙ ታይተዋል።
አቡኑ ከተሾሙ ገና ጥቂት ጊዜያትን ያስቆጠሩ ፊርማቸው ያልደረቀ ቢሆንም ቤተክርስቲያንን በመገዳደር አረጋዊያኑ እንኳን ያልፈጸሙትን መደፋፈር እየፈጸሙ ይገኛሉ።
አባ ገብርኤል ዘረኛና ጴንጤ ከምንም አያስጥሎትም። ለቤተክርስቲያን ትምህርትና ስርአት ይገዙ! ከቤተክርስቲያን ተላትሞ የተረፈ የለምና።
Abune Gabri'eel mee tasgabbaa. Seeraa fi dambii mana kiristaanaatiif bitamaa.
👉maryamawit henok እንደጻፈችው

👍7
"✍️ባለፈው አባ ገብርኤል ከውጭ ወደ ውስጥ በጮኹት ጩኸት ስለፍያታዊ ዘየማን አንሥተው ትውፊትን፣ ትርጓሜን ነቅፈው ሶላ ስክሪፕቱራ (Sola scriptura) አስተምህሮ እየተከተሉ መሆናቸውን ጠቁመን ነበር፡፡ ያ የተቃወሰና እንግዳ ትምህርት፣ ምንፍ*ቅና ብቻ ሳይሆን ስሙ ድንቁ*ርና ይባላል ብለናል፡፡
ታዲያ ያንን ይዞ ትዝታው ሣሚኤል የሚባል ጸጋው የተገፈፈ ልሙጥ፣ በአደባባይ ሲሳለቅ የሚያሳይ ቪዲዮ ማታ ቲክቶክ ላይ ተመለከትኩ፡፡ የሚሳለቀው መምህር ዘበነ ለማ ‘ፍያታዊ ዘየማን እመቤታችንን ወደ ግብጽ በተሰደደች ጊዜ በበረሃ ካገኟት ሽፍቶች አንዱ መሆኑንና፣ የልጇን የወርቅ ጫማና ሰብአ ሰገል የሰጧቸውን ስጦታ ሽፍቶች ሲቀሟቸው ታድጓቸዋል፣ ከዚያም የተነሣ ጌታ ቃል ገብቶለታል’ የሚለውን የዘበነን ንግግር እያሰማ በሳቅ ሲንፈራፈር ነበር፡፡ እንዲህ ዐይነቱ ደፋር ባለማወቁና በድንቁርናው ባያፍር እንኳን ዝም ማለት ሲገባው ሊሳለቅ ሲፈሞክር መታለፍ የለበትም፡፡
መሠረታዊው ነገር፣ ባሕታዊ ዘየማን ሰው፣ በምድር ላይ የኖረ፣ በሞት አፋፍ ላይ እንኳን ሆኖ ለመመስከር ወደኋላ ያላለ አስደናቂ ሰው የነበረ መሆኑ ነው፡፡ የዚህ ሰው ታሪክ በሁሉም ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት አግልግሎት ሥርዓት ዘወትር የሚታወሰው ዝም ብሎ አይደለም፡፡ ባለፈው እንዳልኩት ታሪኩም ይሁን ሐተታው ዘሮኞችና ጥራዝ ነጠቆች እንደሚመስላቸው የሆነ ዛፍ ሥር የተፈበረከ ልብወለድ አይደለም፡፡ በትርጓሜ ወይም በትውፊት የሚወሳው ቤተ ክርስቲያን ታሪካዊት በመሆኗ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ከሕይወቱ ሰዎች የሚማሩበት ጥቅም ስላለ፣ በተጨማሪም የራሱ የሆነ ታሪክ ያለው ሰው የነበረ መሆኑን ለማመልከት ነው፡፡ ይኸ ትምህርቱን ሙሉ ያደርገዋል እንጂ ከወንጌል እውነት ላይ የሚቀንሰው አንዳች ቅንጣት ነገር የለም፡፡
ለመሆኑ ፍያታዊ ዘየማን ማን እንደሆነ ታሪክ ምን ይላል?
***
እንግሊዘኛ ማንበብ ለምትችሉ The Good Thief (Saint Dismas) ብላችሁ ብትፈልጉ በሐተታችን ያለውን ትውፊት ታገኙታላችሁ፡፡ ከወንጌላቱ የሉቃስ ወንጌል ብቻ ነው ‘በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ’ ሲለው ‘እውነት እልሃለሁ፣ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ አለው’ የሚለውን የጻፈልን ሉቃ 23፡ 39፡፡ ሌሎቹ ወንጌላውያን በሁለት ሽፍቶች መሀል መሰቀሉ ጠቅሰው ሌላ ሳይጠቅሱ ነው ያለፉት፡፡
The Gospel of Nicodemus (Acts of Pilate) የተባለ የ4ኛው ክ/ዘመን ሥራ በቀኝ ያለውን ሽፍታ ስሙን Dismas ሲለው የግራውን ደግሞ Gestas ብሎታል፡፡ በሌላ በኩል The apocryphal Arabic Infancy Gospel calls the two thieves Titus and Dumachus, and adds a tale about how Titus (the good one) prevented the other thieves in his company from robbing Mary and Joseph during their Flight into Egypt. ይኸ በጎነቱና መልካም ሥራው ስንቅ እንደሆነውም በዚህ ክፍል ይተረካል፡፡ ስማቸው የሚለያየው ምንጩን ከሚጠቅሱበት ምንጭ የተነሣ ነው፡፡ አንዳንዶች ከአረብኛ ምንጭ ሌሎች ከግሪክ ምንጭ፣ ሌሎች ደግሞ ከላቲን ምንጭ ይወስዳሉ፡፡
የግብጽ ቤተ ክርስቲያንም ከ Dismas የሚቀራረብ ስም ያላት ሲሆን ስሙን Demas ይሉታል፡፡ የሶርያው ምንጭ ደግሞ ስሙን Titus (the good one) and “Dumachus” (the impenitent one) ይሉታል፡፡ የሶርያው ምንጭ የሚከተለውን ይጨምራል ‘during the Holy Family’s flight into Egypt, the infant Jesus and his parents supposedly fell into the hands of a band of robbers. Titus prevented his comrade Dumachus from harming or robbing Mary, Joseph, and the Baby Jesus, and in gratitude the infant Christ (or a heavenly voice through Mary) foretold that Titus would one day be rewarded – this is taken to foreshadow his salvation on the cross years later.’ በአእኛ ትርጓሜ ላይ ካለው ሐተታ ጋር የሚቀራረብ ነው፡፡ ይኸ የፍያታዊ ዘየማን በጎ ታሪኩ በመካከለኛው ዘመን ሥዕላትና ታሪክ ውስጥ ሁሌም ይወሳ የነበረ ትውፊት ነው፡፡ በሁሉም ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት ታሪኩ ትልቅ ስፍራ ያለው ሲሆን፣ በራሺያ ኦርቶዶክስ ዘንድ ስሙ Rakh ይሉታል፡፡
ከጥንት አባቶች ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ታላቁ ባስልዮስ፣ ኦግስቲኖስ፣ አምብሮስ ዘሚላን፣ ሲፕሪያን፣ ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም እና ሌሎችም በልዩ ልዩ ምክንያት ስሙን ደጋግመው ጠቅሰውታል፡፡ አንዳንዶቹ ሽፍታው ከሐዋርያት ቀድሞ ገነት የመግባቱን አስደናቂነት፣ አንዳንዶች፣ የንሥሐን ጥቅም ለማሳየት፣ አንዳንዶች፣ በደም የተጠመቀ መሆኑን ለማሳየት አንሥተውታል፡፡ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ቅድስና ያለው ሲሆን መታሰቢያውም March 25 ነው፡፡
በአጭሩ ልብ ወለድ ያወራውና መሳቂያ መሆን ያለበት ‘ፍያታዊ ዘየማን ክርስቶስን ያየው የዚያን ቀን ብቻ ነው፣ መቼም አይቶት አያውቅም’ ብሎ የተናገረና ሳያውቅ በሌላው የሚያግጥ እንደ ትዝታው ያለ ኮምፒዩተር ፊት ተዘርፍጦ ማንበብ የማይችል ማይም ነው፡፡ ጸጋው ያልተገፈፈና ማስተዋሉ ያለው ሰው ግን የሆነ ነገር ሲያጠራጥረው፣ ምንጭ ይፈልጋል፣ ከሌሎችም ያለውን ምንጭ ያጣራል፣ የማያገኘው ከሆነም ሌሎችን ‘ከየት አመጣችሁት?’ ብሎ ይጠይቃል፡፡ ያ ሁሉ ካልሆነም ከተጻፈውና ካነበበው ውጭ አያነብም አይናገርም፡፡ ምክንያቱም ባላወቀውና ባልተማረው ነገር ላይ አስተያየት ሲሰጥ ይስታልና፡፡ በተለይ ደግሞ እንዲህ በድፍረትና በድንቁርና ሲሆን ያስንቃልና ነው፡፡
ይኸው ነው፡፡
© Dr Arega Abate

🙏8❤3
የፍጥረት ሁሉ ደስታ - ልደታ ለማርያም
ግንቦት አንድ ቀን የእመቤታችን የንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ልደት ስለሆነ የደስታችን ቀን ነው፡፡ የቀደሙ አባቶቻችን ሁሉ በፍጹም ደስታ ያሳለፉት ቀን ነው፡፡
የልደቷ ቀን የሐና የደስታ ዕለት ነበር፤ "አንች ያልወለድሽ መካን ሆይ ደስ ይበልሸ የሚለውን ቃል ሰምታበታለችና" /ኢሳ 54፤1/፡፡ የልደቷ ቀን የኢያቄም የደስታ ዕለት ነበር፡፡ ከዕሴይ ግንደ በትር ይወጣል /ኢሳ 11፤1/ የሚለው ቃለ ነቢይ በውድ ልጁ ሲፈጸምና በበትሩ ሠራዊተ አጋንንትን ሲርቁ አይቷልና፡፡
በእርሷ ልደት ነቢያት ሁሉ ተደስተዋል፡፡ ትንቢታቸው ፍጻሜ ሲደርስ ፤ የንባባቸው መንፈሰ ሲገለጥ፣ ሕግ ለጸጋ፣ ኦሪት ለወንጌል ሊያስረክቡ፣ ነገደ ሌዊ ሊቀ ካህንነቱን ለነገደ ይሁዳ ሊያስረክብ ሲሰላለፉ አይተዋልና፡፡ የእርሷ ልደት የያዕቆብ ፍጹም ደስታ ነበረ፡፡ በሕልሙ ከመሬት እስከ ሰማይ ተዘርግታ ያያት መሰላል በእውን ከምድር ወደ ላይ በቅድስና ስትደርስ ለማየት በቅቷልና፡፡ ራስዋ ላይ እግዚአብሔር የተቀመጠባት እውነተኛዋ መሰላላችን በርግጥም ድንግል ማርያም ናት፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ የሴት ሁሉ ራስ ወንድ ነው/1ኛ ቆሮ 11፤1/ አለ፡፡ የእርሷ ራስ ግን ያዕቆብ እንዳየው እግዚአብሔር ነው፡፡ ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆንልኛል ያለችው ቅዱስ ጳውሎስ የሴት ሁሉ ራሰ ያለው ወንድ በእርሷ ዘንድ ስላልነበረ ነውና፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም ይህን ልዩ መሆኗን ስለሚያውቅ አንቺ ከሴቶች ሁሉ ተለይተሸ የተባረክሽ ነሺ፤ ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ፤ ጽንስሽም እንደ ሌሎቹ ሴቶች አይደለም እያለ ሲሰግድላትና ሲያመሰግናት እርሱን አልፋ ለእግዚአብሔር መቀመጫ ዙፋን ማደሪያ መቅደስ መሆኗን ያየው አባታችን ያዕቆብ በእውነት ደስ አለው፡፡
አብርሃም ልጁን ይስሐቅን የተቤዠለትን አማናዊ በግ ይዛለት የምትወርደውን ዕፀ ሳቤቅ ተወልዳ አይቶ ደስ አለው፡፡ እርሷ ስትወለድ ያች ያያት ቀን መድረሷን አውቆ ፍጹም ደስ አለው፡፡ ይስሐቅም ከታሰረበት ያስፈታችውን ስለእርሱ ፋንታ ቤዛውን ይዛለት ከች ያለችውን ስትወለድ አይቶ በደስታ ቃል ዘለለ፡፡ ከሲኦል እስራት የሚፈታበት ቀንም እንደ ደረሰ በእርሷ ልደት ደወሉን ሰምቷልና ፈነደቀ፡፡
ሙሴ በእርሷ ልደት በደስታ ብዛት ቦረቀ፡፡ ከሩቅ ያያት የማትቃጠል ቁጥቋጦ በሐና ጭን ቁጭ ብላ ሲያይ እንደገነና ወደ እርሷ ሊገሰግስ ወደደ፤ ያኔ ጫማህን አውልቅ ያለውን ድምጽ አቃጨለበትና ባለበት ቆሞ ያያት ጀመር፡፡ ሲያያት ሕብረ ብዙ ሆና አስደነቀችው፡፡ ኦሪትን በሥነ ፍጥረት ሲጀምር በሁለተኛው ቀን ሰኞ እግዚአብሔር ከውኃ ጠፈር ያለውን ሰማይ እንዳሳየው ዛሬ ደግሞ ከመሬት አዳም የተወለደችውን ድንግል አዲስ ሰማይ ሁለተኛ ሰማይ አድርጎ ሲያሳየው ተገረመ፡፡ ያኛው ሰማይ ለዚህ ዐለም ፀሐይ ሲዘጋጅ ወደ ኋላ እንዳየ አሁን ደግሞ የአማናዊው የጽድቅ ፀሐይ መውጫ ስትወለድ ፀሐዩን ሊሞቅ ጊዜው መድረሱን አይቶ ተደሰተ፡፡ እንደገና ሲያያት ደግሞ አሁንም ሕብሯን ለውጣ ታየችው፡፡ ምደር ከመረገሟ በፊት ያለ ዘር ዕፀዋት አዝርእትን ስታበቅል አይቶ የነገረን ሙሴ ከእናቱ ከሔዋን ልጆች ሆና መርገም ያላረፈባት ያለወንድ ዘር የሕይወት እንጀራ ሆኖ የሚሰጠውን ፍሬ የምታስገኘውን አማናዊት ገራኅተ ሠሉስ አይቶ እንደገና አደነቀ፡፡
ሙሴ ከተመስጦ አልተመለሰም፡፡ መንፈስ ቅዱስን እንደ ጣት አድርጎ በጽላት ላይ ቃሉን ጽፎ የሰጠው እርሱ አካላዊ ቃል ሰው ሆኖ የሚታይባትን ጽሌ ተወልዳ ሲያይ ተገረመ፡፡ ፊትህን አሳየኝ ሲለው ፊቴን ልታይ አትችልም ነገር ግን ጀርባዬን ታያለህ ያለው አምላክ የሚወልደባትን ተወልዳ ሲያይ የጌታን ጀርባ በደብረታቦር የሚያይበት ቀን መድረሱን አውቆ በደስታ ዘለለ፡፡ የመገናኛውን ድንኳን የተከለው ሙሴ ከድምፁ በቀር ያላገኘውን አምላክ የሚያገኝባት እውነተኛዋ የመገናኛው ድንኳን ተተክላ ባያት ጊዜ ደስ አለው፡፡ መቅረዝ ፣ ሙዳየ መና፣ ታቦትና የሥረየት መክደኛ ላይ ደም እየረጨ ሲያመልክ የነበረው ሙሴ አማናዊው ብርሃን የሚበራባት መቅረዝ፣ እውነተኛው መና የሚገኝባት ሙዳይ፣ እውነተኛው የሥረየት ደም የሚረጭባት ምሥዋዕ፤ አካላዊ ቃል የተቀረጸባት በሁለተናዋ ጽሩይ ወርቅ በተባለ ፍጹም ንጽሕና ተጊጣ ድንግሊቱን ባያት ጊዜ መደነቁን አበዛ፡፡ ድንኳኑን ሲያስብ እርሷ፣ ታቦቱንም ሲያስብ እርሷ፣ ጽላቱን ሲያስብ እርሷ፣ ሙዳየ መናውንም ሲያስብ እርሷ፣ መቅረዙንም ሲያስብ እርሷ፣ ማዕጠንተ ወርቁንም ሲያስብ እርሷ ስትሆንበት እንዴት አይደነቅ በእውነት፡፡ ሙሴ በዚህ አላበቃም፡፡ ሕግ የተቀበለበትን የጨሰውን ተራራ አስታወሰና ልጁን ዳዊትን ጠራው፡፡
ዳዊትም የአባቱን ሙሴን ጥሪ ሰምቶ ሲነሣ የረጋችው ተራራ ተወልዳ አያትና እርሱም በደስታ ዘለለ፡፡ አዎ "የእግዚአብሔር ተራራ የለመለመ ተራራ ነው፤ የጸኑ ተራራዎች ለምን ይነሣሉ፤ እግዚአብሔር ይህን ተራራ ያድርበት ዘንድ ወደደው " /መዝ 68 ፤ 16/ ብሎ የተናገረላት ተራራ ስትወለድ አይቶ ደስ አለዉ፡፡ ሐላፊውን ብሉይ ኪዳን አባቱ ሙሲ ሲቀበል በነጓድጓድ ድምጽ በረዓድና በፍርሃት ነበረ፡፡ የማያልፈው ሐዲሱ ኪዳን ግን በጸና ተራራ እንደሚሰጥ የተናገረላት ያድርባት ዘንድ የወደደዳት አማናዊት የንጽሕና የቅድስና ተራራ ተወልዳ አይቶ ደስ እያለው መዝሙሮችን በአናት በአናት አከታተለ፡፡ ልጁ ሰሎሞንም "ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ፥ ውብ ነሽ እነሆ፥ አንቺ ውብ ነሽ በዓይነ ርግብ መሸፈኛሽ ውስጥ ዓይኖችሽ እንደ ርግቦች ናቸው፤ ጠጕርሽ በገለዓድ ተራራ እንደሚወርድ እንደ ፍየል መንጋ ነው" /መኃ 4 ፤ 1/ እያለ በምስጋና ተከተለው። ኢሳይያስም ንጹሕ ወረቀቱን አይቶ ደስ አለው፡፡ እንደ ታሸገች የተጻፈባት ሀዝብም አህዛብም ይህን ደብዳቤ ልናንብበው አንችልም ያሏት አካላዊ ቃል በድንግልና የሚጻፍባትን ንጹሕ ወረቀት /ኢሳ 29;11/ አይቶ ተደነቀ፡፡ ሕዝቅኤልም ሁለንተናዋ ዝግ ሆኖ እግዚአብሔር ብቻ ገብቶ የወጣባት መቅደሱን ተሠርታ አይቶ ደስ አለው፡፡
ተራ በተራ ሁሉም ነቢያት ትንቢቶቻቸውን ይዘው ስለእርሷ ያዩትን ራእይ፣ ምሳሌና ትንቢት ፍጻሜውን እያዩ ተደነቁ፡፡ መሐንዲስ የሕንጻውን ንድፍና የሚሠራውን ሕንጻ እንደሚያስተያይ እነርሱም በልደቷ ትንቢታቸውን ከፍጻሜው መጀመሪያ መሠረት ጋር እያስተያዩ ተደሰቱ፡፡
በመጨረሻም የፍትረት ሁሉ አባት አዳም ከልጆቹ ጋር ደስ አለው፡፡ አዳም ሆይ መሬት ነህና ወደ መሬት ትመለሳለህ ያለው ጌታው ከጨለማ ሲኦል ሊያውጣው ልጁን ከመሬት ባሕርዩ አንሥቶ እርሷን ሰማይ አድርጎ ሲያያት በእርሷም ላይ እርሱ ፀሐይ ሆኖ ሊወጣ ወገግታውን ሲያሳየው በደስታ አነባ፡፡ የሰጠኸኝ ሴት አሳተችኝ ብሎ የከሰሳት ሔዋንን ተክታ የሚያመሰግናት ሌላ ሔዋን ተወልዳ ሲያይ ደስስስ አለው፡፡ ምሳሌና የሚተካከላት እንደሌለም ሲያይ ልጁን ሰሎሞንን ጠርቶ "ለእኗቷ አንዲት ናት፣ ለወለደቻትም የተመረጠች ናት" የሚለውን ዘምር አለው፡፡
ልጆቹ ሁሉ ከመረገሙ በፊት ያለ ክብሩን ስላላዩ በተገቢው መጠን የማያደንቁለትን ከስሕተት በፊት የነበረ ክብሩንና ጸጋውን ይዛ ስትወለድ በደስታ ተንሰቀሰቀ፡፡ የአዳምን ለቅሶ ሰምታ ሔዋን እናቷ የመርገም ጨርቋን ጥላ ብድግ አለች፡፡ አንድ ልጇን እያየች በደስታ አለቀሰች፡፡ በልጆቿ ሳይቀር ምነው እባብን ሰማሽው የሚል ወቀሳ እየሰማች ስታዝን የኖረች ምስኪን እናት መርገሟን ወርውራ በቅድስና ከብራ መላአክትን በልጣ እንደ ጨረቃ ስታበራ ስታያት መካሷን አይታ ፈነደቀች፡፡ ያሳታትን ዲያብሎስ በቅድስና መንገዷን ሰውራ የምታስተውን (ግራ

👍1
የምታጋባውን) መድኃኒት ልጇን ተወልዳ አይታ በደስታ አነባች፡፡ የፍጥረት እናትና አባት የሆኑ አዳምና ሔዋን ልጃቸውን እናታችን፣ ካሳችን፣ መድኃኒታችን፣ ሰማያችን ተወለደች እያሉ ሲደሰቱነ ሲያመሰግኑ ልጆቻቸውም ከእነርሱ ጋር የባሕርያችን መመኪያ የድኅነታችን ቀርን ዛሬ ተወለደች እያሉ ተደሰቱ፡፡ ከአንድ ከዲያብሎስ በቀር ሁሉም ደስ አላቸው፡፡
እርሷም በኋላ እንኳን የቀደመው የኋላው ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል አለች፡፡ እንግዲያስ በእርሷ መወለድ እንደ ዲያብሎስ አይክፋን፤ ይልቁንም የፍጥረት ሁሉ አባትና እናት እንደሆኑት እንደ አባታችን አዳምና እንደ እናታችን ሔዋን፣ እንደ ነቢያትና አበው ሁሉ አብረን ደስ ይበለን፡፡ እንኳን ደስ አለን፤ ዛሬ የባሕርያችን መመኪያ፣ ሰማይ የደረሰችው መሰላል፣ እግዚአብሔር ከእርሷ ጋር ሆኖ አማኑኤል ተብሎ ከእኛም ጋር እንዲሆን ምክንያት የሆነችልን የእመቤታችን ልደት የእኛም የሁላችን ልደት ነውና፡፡
ሰማይ የደረስሽው መሰላል፣ ከምድር ባሕርያችን የተሠራሽ ሰማይ ሆነሽ የጽድቅ ፀሐይን ያወጣሽልን ሰማይ ሆይ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነውና ዛሬም የዲያብሎስ ግሣት የሆነውን ኮረና ዘረኝነትን፤ ኮረና መለያየትን እና ኮረና ርኩሰትን ለተግሣጽ ከተላከለን ለጊዜውም ቢሆን ካስደነገጠን ኮረና ቫይረስ ጋራ አንድ ላይ አስወግጅልን፡፡ የባሕርያችን መመኪያ ሆይ ለአጋንንትና ለመናፍቃን መሳለቂያ አታድረጊን፡፡ በእኛ ጉድለት ምክንያት ታመነውባት አፈሩ፣ ተማጽነውባት መልስ አጡ እያለ ዝንጉዎችን እንዳያጠራጥር ቸሪቱ አማላጂቱ ሆይ በልደትሽ ስላስደሰትሻቸው ከሐፍረትና ከውረደትም ስላዳንሻቸው እናትና አባትሽ ስለኢያቄምና ስለሐና ፣ ስለአዳምና ሔዋን ብለሽ ድረሽልን፡፡ በእሥራኤል ትውፊት እሥራኤል በተጨነቁ ቁጥር ራሔል ስትጮህ ይሰማቸው እንደነበረ ዛሬም አንቺ ከጮሕሽ ልጅሽ ይምራልና በእውነት ይቅር ይለን ዘንደ ለምኝልን፤ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡ በክርስትናው ለሚያምን ሁሉ እንኳን ደስ አለን፤ እንኳንም ለእናታችን ልደት ለሁላችንም የጋራ የልደት በዓል አደረሰን፡፡
©ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ