Telegram Web
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኙ ሁሉም ጤና ጣቢያዎች ለሥነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎት ክፍያ እየጠየቁ መሆኑ ቅሬታ ቀረበበት

የአዲስ አበባ ከተማ ወጣት ተወካዮች ለስነተዋልዶ ጤና አገልግሎት ከካርድ ክፍል ጀምሮ ክፍያ እንደሚጠይቁ እና በክፍያ ፍራቻ አገልግሎቱን እንደማያገኙ ተናግረዋል።

ይህንን የተናገሩት ቪኤስኦ ኢትዮጵያ (VSO) እና የስነ ተዋልዶ ጤና ማኅበራት ጥምረት (CORHA) ባዘጋጁት Advocacy Dialogue on health care financing የውይይት መድረክ ላይ ነው።

ወጣቶቹ በሌሎች ክልሎች እና ከተሞች ለወጣቶች የስነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት ክፍያ ሳይጠየቅ ለምን አዲስ አበባ ላይ  እንጠየቃለን የሚል ጥያቄም በውይይቱ ላይ አቅርበዋል።

ምን ምላሽ ተሰጠ?

በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ተወካይ ሲስተር አስቴር፥ ጥራቱን የጠበቀ የሥነ-ተዋልዶ ጤና አገልግሎት በሁሉም ጤና ጣቢያዎች ለመስጠት የበጀት እጥረት መኖሩን ጠቁመዋል።

በስነተዋልዶ ጤና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደረብን ያለው ወጣቶች ክፍያ መፈፀማቸው ነው የሚሉት ሲስተር አስቴር ይህ ደግሞ አገልግሎቱን እንዳያገኙ እንቅፋት መሆኑን አንስተዋል።

በዚህም ለቀጣይ ዓመት የስነተዋልዶ ጤና አገልግሎት ከክፍያ ነፃ ለማድረግ እየተነጋገርን ነው ሲሉ አመላክተዋል።

#ገጣሚአበበተሾመ@tztbt
@abepoet
መረጃ ‼️

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን ሲርካ ወረዳ ሰሞኑን በመንግሥት ኃይሎችና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል ከፍተኛ ግጭት እየተካሄደ መኾኑን ዋዜማ ሠምታለች።

በተለይ በሶጂ ሳዴ ቀበሌ ትናንት ንጋት ላይ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ እንደነበር ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በመርቲ ወረዳ ደምበቃ ቀበሌም ትላንት ሌሊት ቡድኑ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች በሠፈሩበት ቦታ ላይ ድንገተኛ ጥቃት እንደፈጸመና ይህንኑ ተከትሎ ውጥረት እንደሠፈነ የአካባቢው ነዋሪዎች ገል
#ገጣሚአበበተሾመ@tztbt
መረጃ ‼️

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን ሲርካ ወረዳ ሰሞኑን በመንግሥት ኃይሎችና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል ከፍተኛ ግጭት እየተካሄደ መኾኑን ዋዜማ ሠምታለች።

በተለይ በሶጂ ሳዴ ቀበሌ ትናንት ንጋት ላይ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ እንደነበር ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በመርቲ ወረዳ ደምበቃ ቀበሌም ትላንት ሌሊት ቡድኑ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች በሠፈሩበት ቦታ ላይ ድንገተኛ ጥቃት እንደፈጸመና ይህንኑ ተከትሎ ውጥረት እንደሠፈነ የአካባቢው ነዋሪዎች ገል
#ገጣሚአበበተሾመ@tztbt
የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል መቼ ነው ?

1446ኛው የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል ዓርብ ግንቦት 29 ቀን 2017 ይከበራል።

ዛሬ በሳኡዲ አረቢያ የዙልሂጃህ ወር ጨረቃ ታይታለች። ነገ ረቡዕ የተቀደሰው የዙልሂጃህ ወር የመጀመሪያ ቀን ነው።

የዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል ግንቦት 29 ቀን 2017 በጁምዓ ዕለት ተከብሮ ይውላል።

#ገጣሚአበበተሾመ@tztbt
በዋህምራ ብሄረሰብ ዞን አስተዳደር በምግብ እጥረት ምክንያት አርሶአደሮች እየተፈናቀሉ ነው ተባለ

በ አማራ ክልል በዋግህምራ ብሄረሰብ ዞን አስተዳደር በድርቅና የተፈጥሮ አደጋ ምክንያት በተፈጠረ የምግብ እጥረት ምክንያት አርሶአደሮች አካባቢያቸዉን እየለቀቁ መሆኑ ተነግሯል።

ተደጋጋሚ የሆነ የተፈጥሮ አደጋ የሚከሰትበት አከባቢው በ2016ዓ.ም በሳህላ ወረዳ በዚህ አመት ደግሞ በዳህና ዛጊብላ ጻግምጅ ፣ ሰቆጣ፣ አበርገሌ ፣ እና ዝቋላ አካባቢ በተከሰተ ድርቅ እና ተፈጥሮአዊ አደጋ ምክንያት 118,000 ሰዎች የእለት ምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ዶቼ ቬለ ዘግቧል።

የጻግምጅ ወረዳ ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ ኪሮስ ወልዴ፤ ባለቤታቸውን ጨምሮ 7 የቤተሰቡ አባላት በአካባቢው በተከሰተው የተፈጥሮ አደጋ ጋር ተያይዞ ህጻናት ልጆቻቸውን ይዘው በደሴ ከተማ ምጽዋት በመጠየቅ ህይወታቸውን እየመሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

#ገጣሚአበበተሾመ@tztbt
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለጉብኝት ቬትናም ዋና ከተማ ሃኖይ አውሮፕላን ማረፊ ደርሰው ከአውሮፕላን ሊወርዱ ሲሉ የሆነው በዓለም ዙሪያ መነጋገሪያ ሆኗል። የአውሮፕላኑ በር ተከፍቶ ፕሬዝዳንቱ ፊት ለፊት በሚታዩበት ጊዜ አንድ እጅ ጸብ በሚመስል ሁኔታ ፊታቸውን በኃይል ሲገፋ ታይቷል።

#ገጣሚአበበተሾመ@tztbt
ጉድ እኮነው
እንዳው ምን ይሻላል እያንዳንዱ
ኢትዮጵያዊያን 👉71 ሺብር እዳ አለባችሁ አለ ምንግስት
571 dollar
#ገጣሚአበበተሾመ@tztbt
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ " አልተዘረፍኩም ግን የዝርፊያ ሙከራ ተደርጎብኝ አከሽፊያለሁ " አለ።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ የነበረ 7.7 ቢሊዮን ብር መዘረፉን ወይም ከባንኩ ወደ ግለሰቦች አካውንት መዞሩን ፤ ዘራፊዎቹ እንዳልተያዙ ፤ በዚህ ላይ የተሳተፉ አካላት እያንዳንዳቸው 50 ሚሊዮን ብር እንደደረሳቸው እና ባንኩም ጉዳዩን አድበስብሶ እንዳለፈው የሚገልጽ መረጃ እየተሰራጨ ነው።

ባንኩ ግን ይህ " ፍጹም ውሸት ነው ፤ ምንም የተዘረፈ ገንዘብ " የለም ብሏል።

" ከባንካችን ምንም የተዘረፈ ገንዘብ የለም " ያለው ንግድ ባንክ " ይልቁንም ከፍተኛ ገንዘብ ለመዝረፍ የተደረገ ሙከራ ነው " ሲል ገልጿል።

ባንኩ ፤ የመዝረፍ ሙከራው በተደረገ በጥቂት ደቂቃዎች በውስጥ ቁጥጥር ስርአቱ አጠራጣሪ ግብይት መፈፀሙን ደርሶበት ምንም ዓይነት ገንዘብ ወጪ ሳይደረግ ሙከራውን ወዲያውኑ እንዳከሸፈው አሳውቋል።

" ሙከራው በጥቂት ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ባሰቡ ተጠርጣሪዎች የተፈፀመ እንጂ የባንካችንን ሲስተም ተላልፎ የተፈፀመ ጥቃት አይደለም " ብሏል።

ባንኩ፥ " የገንዘብ ዝርፊያ ሙከራው ከከሸፈ በኃላ ጉዳዩን ለሚመለከተው የሕግ አካል በማሳወቅ ተጠርጣሪዎቹ በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተደርጎ የምርመራ ስራ እየተከናወነ ይገኛል " ሲል ገልጿል።

#ገጣሚአበበተሾመ@tztbt
" ከነገ ግንቦት 21 ጀምሮ ወደ ስራ ገበታ ይመለሳሉ " - ፅ/ቤቱ

ላለፉት 12 ቀናት በስራ ማቆም አድማ የቆዩት የመቐለ ዳኞች ስራ ለመጀመር መግባባት ላይ መደረሳቸው ተነግሯል።

ዳኞቹ ያቀረቡት የደህንነት ስጋት ጥያቄ ጊዚያዊ አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚከታተለው በተደረሰው ስምምነት ምክንያት ነው ወደ ስራ ገበታቸው ለመመለስ የወሰኑት።  

የትግራይ ጊዚያዊ  አስተዳደር የፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት " ዳኞቹ ያለባቸው የድህንነት ስጋት በማስመልከት ከፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) እና ከፍትህ አካላት አመራሮች ጋር ተወያይተዋል " ብሏል።

" በውይይቱ በዳኞቹ ላይ ያንዣበበው የደህንነት ስጋት በጥልቀት ተዳሷል ፤ ችግሩን ከስሩ በመረዳት ለመፍትሄው ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል " ሲል ገልጿል።  

" የደህንነት ስጋቱ በዘላቂነት ለመፍታት የአጭርና የረጅም ጊዜ  የመፍትሄ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል። በተደረሰው መግባባት መሰረት የመቐለ ሰባቱ ክፍለ ከተማ ፍርድ ቤቶች ከነገ ግንቦት 21/2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ስራ ገበታ ይመለሳሉ " ብሏል።

#ገጣሚአበበተሾመ@tztbt
ሁለት ሚስት አግብቶ የሚኖር አንድ ሰው ነበር።ሰውዬው አንዷ ሚስቱ አሮጊት አንዷ ደግሞ ወጣት ነበረች ።ታድያ ለሁለቱም ሚስቱ ጥልቅ ፍቅር ስለነበረው ሁለቱን ለማስደሰት ሁሌ ደፋ ቀና እንዳለ ነው......

....በዚ መሀል ሰውዬው ሽበት ማብቀል ጀመረ።ይህንን ያየችው አሮጊቷ ሚስቱ በደስታ ፈንድቃ.......ከእሷጋር በሆነ ጊዜ ጥቋቁር ፀጉሮች ትነቃቅል ያዘች ሙሉ በሙሉ ሽበት ሆኖ ባሏን እኩያዋ ለማድረግ።

ወጣት ሚስቱ ደግሞ የባሏን ሽበት ስታይ በመበሳጨት እና እንዳያስረጀው በመስጋት ሽበቶችን ቀን በቀን ትነቅል ያዘች።

...በሁለቱም ሚስቶቹ ተግባር ባልየው ቅር ቢሰኝም እነሱ ደስ ለማሰኘት ዝምታን መረጠ። ....በመጨረሻም ፀጉሩም ተመለጠ!!!

አንዳንድ ጊዜ ሁሉንም ሰው ለማስደሰት መሞከር ትርፉ እንደሰውዬ ያለንን ነገር አተን ለሰዎችም ሳንደርስ ባዶ እጃችንን ያስቀረናል!!!!

በአለም ላይ ትልቁ ፍሬ አልባ ድካም ሁሉንም ሰው አንድ ላይ ለማስደሰት መጣር ነው!!!!
ካነበብኩት ነው መልዕክቱ ስለተመቸኝ


#ገጣሚአበበተሾመ@tztbt
#ኤልሻዳይ
👍1
ምን ብላው ይሆን በአደጋ መሀል እንደዚህ የሚስቀው?

ይህ የእሳት አደጋ ሰራተኛ በ2013 ብዙ ነብስ ባጠፋው እና ንብረት ባወደመው ጎርፍ መሀል አንዲት ከሞት አፋፍ ስር ፈልቅቆ ያወጣትን የ84 አመት አዛውንት ይዞ ምን እንደሚያስቀው ሲጠየቅ?

ከእቅፌ ውስጥ ሁና ቀና ብላ እያየች" ለመጨረሻ ጊዜ እንደዚክ የታቀፍቁት የሰርጌ ቀን ነበር። ያንን ቀን አስታወስከኝ" ብላኝ ነው አለ።

ንብረቷ ሙሉ በሙሉ በጎርፉ ወድሞ እያለ ከረጅም አመት በፊት ያሳለፈቸውን ደስ የሚለውን ትውስታ ማሰቧ ምን ያክል ለአንድ ሰው የሰጠነው ፍቅር በችግር ጊዜ እንኳ ስንቅ እንደሚሆን የሚያሳይ ነው።

የአሳት አደጋ ሰራተኛውም በዛ አድካሚ ሁኔታ ውስጥ ሁኖ ስሜቷን በመጋራቱ The photogenic Firefighter! የሚል ቅፅል ስም ተሰጦታል

#ገጣሚአበበተሾመ@tztbt
#ኤልሻዳይ
እርግጠኛ ነሽ ግን አርግዘሻል?
ዝሆን እና ውሻ በተመሳሳይ ጊዜ ፀነሱ፡፡ ከሶስት ወራቶች በኋላ ውሻዋ ስድስት ቡችላዎችን ወለደች፡፡ ዝሆኗ
እንዳረገዘች ከስድስት ወር በኋላ ውሻዋ እንደገና ፀነሰች ፣ ዘጠኝ ወር ደግሞ ሌሎች ብዙ ቡችሎች ወለደች፡፡

የእርግዝና ስርዓቱ ቀጠለ ፡፡ ውሻዋ በየሦስት ወሩ መውለዷን ቀጠለች። በአሥራ ስምንተኛው ወር ውሻዋ ወደ ዝሆኗ ጥያቄ ይዛ ቀረበች ፣

“እርግጠኛ ነሽ ነፍሰ ጡር ነሽ? አሁን በሆድሽ ጽንስ አለ? ምክንያቱም በተመሳሳይ ቀን ነፍሰ ጡር ሆነናል ብለን ነበር፣ ከ16 በላይ ቡችሎች ወለድኩኝ እና አሁን ግማሾቹ በዚህ ሰዓት አድገው ትልቅ ውሾች ሆነዋል ፣ ግን አንቺ አሁንም ነፍሰ ጡር ነኝ ትያለሽ፡፡ ምን እየሆነ ነው?

ዝሆኗም “እኔ እንድትረጂ የምፈልገው አንድ ነገር አለ፣ በማህጸኔ የተሸከምኩት ቡችላ ሳይሆን ዝሆን ነው ፡፡ እኔ
በሁለት ዓመት ውስጥ አንዱን ብቻ እወልዳለሁ፡፡
የምወልደው ግን ተራ እንስሳ ስላልሆነ ልጄ መሬቱን ሲመታ ምድር ይሰማታል፡፡ ልጄ መንገዱን አቋርጦ ሲሻገር የሰው ልጅ ቆሞ እያደንቀው ይመለከታል ፣ እርሱ ሲንቀሳቀስ ሁሉም ይንቀጠቀጣል፣ የኔ ልጅ የፍጥረትን ትኩረትን
ይስባል ፡፡

ሌሎች እንደ መቅስፈት በሚመስል ጊዜ ነገራቸው ሲቀየርና የተሳካላቸው ሲመስልህ በነሱ አትቅና፣ እምነትህም
አይጥፋ በፍጹምም ተስፋ አትቁረጥ፣ ምክንያቱም የአንተም ጽንስ የሚወለድበት ጊዜ ይመጣል፣ ምንም ጊዜ ወስዶ
የማይመጣ ቢመስልም የተሻለው መምጣቱ የማይቀር ነው፣ እናም ሲመጣ ሰዎችን ሁሉ የሚያነጋግርና የሚያስደንቅ ይሆናል! የዘገየው የተሻለ ስለሆነ ነውና የእርስዎን ጉዞ ከሌላ ከማንኛውም ሰው ጋር አያነፃፅሩ!

#ገጣሚአበበተሾመ@tztbt
#ኤልሻዳይ@tztbt
#ኡቡንቱ!

አንድ የስነ-ሰብ (Anthropology) ተመራማሪ ወደ ደቡብ አፍሪካ ገጠራማ መንደር ለስራ ያቀናል። በቆይታውም ከህጻናት ጋር መግባባትን ይፈጥራል። እናም ሕጻናቱን ለማስደሰት አንድ ሽልማት ያለው ጨዋታ ያዘጋጃል። 

ጨዋታውም፣  በማንጎ የተሞላ አንድ ቅርጫት ከዛፍ ስር ያስቀምጣል፣ ህጻናቱን ከዛፉ አንድ መቶ ሜትር እንዲርቁ አደረገ፣ ከዛም እንዲህ አላቸው:-

"እኔ ጀምሩ ስል ቀድሞ ቅርጫቱ ጋ  የደረሰ የፈለገውንና የሚችለውን ያህል ማንጎ ይበላል:: "

ጨዋታው ተጀመረ።

ህጻናቱ ግን ከጨዋታው ህግ ውጪ ያልተጠበቀ ነገር አደረጉ።

ይህም ሁሉም እጅ ለእጅ ተያይዘው እኩል ወደ ቅርጫቱ ሮጡ። ከዚያም አንድ ላይ በቅርጫቱ ውስጥ ያለውን ማንጎ በአሸናፊነት መንፈስ ተካፍለው መብላት ጀመሩ::

የስነ-ሰብ ተመራማሪውም በመገረም "ለምን እንዲህ አደረጋቹ?"ሲል ጠየቃቸው።

ሁሉም በአንድነት "ኡቡንቱ! " በማለት መለሱለት።

በመቀጠል አንዱ ህፃን  እንዲህ አለው:-

"እንዴት ሌሎች ጓደኞቻችን ተከፍተው አንድ ልጅ ብቻውን ይደሰታል? ይሄ ባህላችን አይደለም::"

"ኡቡንቱ" የቃሉ መሠረት የደቡብ አፍሪቃው የዙሉ ማሕበረሰብ ሲሆን፤ ትርጓሜውም:-

“ለመኖሬ ምክንያት አንተ ነህ፤ ላንተም መኖር እኔ!” የሚል ሰብዓዊነትን ያዘለ ፍልስፍና ነው።

#ገጣሚአበበተሾመ@tztbt
#ኤልሻዳይ@tztbt
"ዊሊያም ሼክስፒር"

☞ "ሲዖል ባዶ ነው፡፡ ምክንያቱም ሁሉም ዲያብሎሶች ያሉት እዚህ ምድር ላይ ነው፡፡"
.
☞ "ከክፋት ስትርቅ ሰላምህን ታበዛለህ፤ ቅንና መልካም ስትሆን ደግሞ ከጭንቀትና ከጸጸት ትድናለህ።"
.
☞ "ለማንኛውም ሠው ጆሮህን ስጥ፤ ድምፅህን ግን ቀንስ፤ ሁሉንም ውደድ፤ ጥቂቶቹን እመን፤ ማንንም ግን አትበድል፡፡"
.
☞ "የውሸት ጓደኛና ጥላ ሁለቱም አንድ ናቸዉ። ሁለቱም የሚቆዩት ፀሐይ እስካለች ድረስ ነው።"
.
☞ "ጨውን ሺ ጊዜ ስኳር ብትለው ስሙን እንጂ ጣዕሙን መቀየር አይችልም።"
.
☞ "የቀንን ውበት አይቶ ለማድነቅ የግድ ጨለማን መጠበቅ ያስፈልጋል።"
.
☞ "መልካም ስም ለሰው ልጅ የመንፈስ ቀንዲል ናት።"
.
☞ "ማንም ሰው ህይወት ስህተት ወይም ትክክል መሆኑን የሚያውቀው ሲፈተን ነው።

#ገጣሚአበበተሾመ@tztbt
#ኤልሻዳይ@tztbt
የደግነት ግድግዳ

"አንድ በግምት 60 ዓመት የሚሆናቸው  ሽማግሌ ወደ "የደግነት ግድግዳ" መጡ። በከተማው ብርዳማው የክረምት ወቅት ገብቶ ነበርና በጣም ይበርዳል። የሙቀቱ መጠን ከ 0 በታች እስከ ስምንት ዲግሪ ሴንቲግሬድ (-8°c) ይደርሳል፤ "የጥጥ በረዶም" (snow) እየተግተለተለ ይወርዳል። እኚህ ምስኪን ሽማግሌ "የደግነትግድግዳ" ላይ ከተሰቀሉት ሹራቦች አንዱን በማንሣት አጥንት ድረስ ዘልቆ የሚቆፈድደው ብርድ እያንዘፈዘፋቸው "ልጄ! ይህ ሹራብ ስንት ነው?" ሲሉ በቆፈን ከሚንገጫገጭ ጥርሳቸው ባመለጡ ቃላት ከግድግዳው ጎን የቆመውን ወጣት ጠየቁት።

እርሱም በአካባቢው የክብር አጠራር "አጎቴ" ሲል በመጥራት መልሱን አስከተለ:- "አጎቴ! እነዚህ ልብሶች የሚሸጡ አይደሉም። ነገር ግን ለሚያስፈልገው ኹሉ በነፃ የሚመጸወቱ ናቸው" "በእውነት ከእኔ በላይ የሚያስፈልገው ማን አለ?" አሉ ሽማግሌው። ከአፋቸው ቃላቱ እየተንከባለሉ ሲዉጡ ከዐይናቸውም ትኩስ ዕንባቸው እንደ በረዶ በቀዘቀዘ ጉንጫቸው ላይ ይንከባለሉ ነበር። የዐይናቸው ዕንባ መውረዱን ሳያቆም "ልጄ! ሦስት ሴት ልጆች አሉኝ። ምንም ዓይነት ገቢ የማገኝበት ሥራ ግን የለኝም። የደኻ ደኻ ነኝ" አሉ። ከዚያም ጃኬት፣ ሌሎች ሹራቦችና ጫማዎችን ይዘው፣ ዕንባቸውም በፈገግታ ተለውጦ "ይህን ልግሥና ያደረጉልን እጆች የተባረኩ ይሁኑ" እያሉ ሔዱ።

ይህን ያደረጉት በሕንድ ሥር በምትተዳደረው የካሽሚር ግዛት በቅን ልባቸው የተነሣሡ ወጣቶች ናቸው። "የደግነት ግድግዳ /Wall of Kindness/" ብለው በሰየሙት ግንብ ላይ ያላቸው እንዲሰጡ የሌላቸውም እንዲወስዱ ሁኔታዎችን አመቻቹ። ያላቸው ሰጡ፤ የሌላቸውም ወሰዱ።
"የደግነት ግድግዳው" ላይ ኹለት ጽሑፎች አሉ። አንዱ "ካለህ አንጠልጥል /Hang if you have/" ይላል፤ ኹለተኛው ደግሞ "ካስፈለገህ ውሰድ /Take if you need/"።


#ገጣሚአበበተሾመ@tztbt
#ኤልሻዳይ@tztbt
ቶማስ ሳንካራ የቡርኪናፋሶ ፕሬዚዳንት ነበር―ለአራት አመት ብቻ። በዚህ አራት አመት ውስጥ ግን ተአምር ሰርቷል። ስልጣን የያዘው ገና በ33 አመቱ በመፈንቅለ መንግስት ነበር። በ1983 መሪነቱን ሲቆናጠጥ ሃገሩ በፈረንሳይ የምትበዘበዝ፣ ሙስና እና ንቅዘት የተንሰራፋባት ምስኪን ሃገር ነበረች። ሳንካራ ይህቺን ሃገር ተረክቦ በአይን የሚታይ በእጅ የሚዳሰስ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ ለውጥ አመጣ። ቅኝ ገዢ ፈረንሳዮች ያወጡላትን Upper Volta(የላይኛው ቮልታ) ትቶ የሚመጥናትን አፍሪካዊ ስም ቡርኪና ፋሶ አላት። ቡርኪና ፋሶ "የሀቀኛ ሰዎች ምድር" ማለት ነው።
ዜጎቿም ቡርኪናቤ ተባሉ።

ሳንካራ ፀረ―ኢምፔሪያሊዝም ስርአት መሰረተ። ከነጮች የእርዳታ ፍርፋሪ መቀበል አቆመ። ከሱ በፊት የነበሩ ስርአቶች የወሰዱትን የውጪ ብድር አሰረዘ("የስርአቱ እንጂ የቡርኪናፋሶ ብድር አይደሉም" ብሎ)  የሃገሪቱን መሬት እና የማእድን ሃብት የሕዝቦች የጋራ ንብረት አደረገ። ከአለም ባንክ እና የገንዘብ ድርጅት መመሪያ መቀበል አቆመ። በኢኮኖሚው የመሬት ስሪትን አስተካክሎ እርሻ በማስፋፋት እራሷን በምግብ የምትችል ሃገር ፈጠረ። የስንዴ ምርት በእጥፍ ጨመረ።  ረሃብን አስቀረ። በትምህርት ሚሊየን ቡርኪናውያንን ከመሃይምነት ጨለማ አላቀቀ። በጤና ሚሊየን ህፃናትን በመከተብ የማህበራዊ ጤና ስርአትን ዘረጋ። አስር ሚሊየን ዛፎችን ተከለ።(Now, that's a number that is sound) 350 ማህበረሰቦች በራሳቸው ጉልበት ትምህርት ቤት እንዲሰሩ አደረገ። ሃገሪቷን የሚያስተሳስር የመንገድ እና የባቡር ሃዲድ ስርአት ዘረጋ። የሴቶችን መብት አከበረ።

በአጠቃላይ ሳንካራ ለጥቁሮች በራሳቸው እግር የመቆም ጉልበት አለምአቀፍ ምልክት ሆነ። ሳንካራ በአብዛኛው ህዝብ ቢወደድም ጥቂት ጠላቶች ነበሩት። በተለይም ጥቅማቸው የተነካባቸው የመካከለኛው መደብ አባላት እና ፈረንሳይ። እነዚህ ጠላቶቹ ተባብረው በመፈንቅለ መንግስት ከሥልጣን አስወገዱት፤ በጥይት ስጋውን ከነፍሱ ለዩዋት። አሁንም ጥቁር ተኳሽ ነጭ አስተኳሽ ነበሩ።

ለምንድነው እንደዚህ አይነት ታሪኮች መጨረሻቸው ሁሌም አንድ አይነት ነው!

ሳንካራ ከመሞቱ ከጥቂት ሳምንታት በፊት እንዲህ ብሎ ነበር፦

"አብዮተኞች እንደ ግለሰብ ሊገደሉ ቢችሉም፣ ማንም ሃሳብን መግደል አይችልም!"

፨፨፨፨

ጥቁሮች ያለ ማንም እርዳታ ተአምር መስራት ይችላል። የተረጂነት ስነልቡና ከበታችነት ስነልቡና ጋር በጥብቅ የተሳሰረ ነው።

#ገጣሚአበበተሾመ@tztbt
#ኤልሻዳይ@tztbt
አንድ ሰው ሚስትና ውሽማ ነበሩት እና የትኛዋን መምረጥ እንዳለበት ግራ ገብቶት ነበር። በመጨረሻም ለችግሩ መፍትሄ ፍለጋ ወደ አንድ ጠቢብ ሰው ዘንድ ለመሄድ ወሰነ። ጠቢቡንም "ከሚስቴ ወይስ ከውሽማዬ ጋር መሆን አለብኝ?" ብሎ ጠየቃቸው።

ጠቢቡም ሰውየውን ተመልክተው ሁለት የአበባ ማስቀመጫዎችን በእጃቸው ያዙ፤ በአንደኛው ጽጌረዳ በሌላኛው ደግሞ ቁልቋል ነበር። ከዚያም እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፦

"ከእነዚህ ሁለት ማስቀመጫዎች አንዱን እንድትመርጥ ብነግርህ የቱን ትመርጣለህ?"

ሰውየውም "በእርግጥ ጽጌረዳዋን እመርጣለሁ!" ሲል በችኮላ መለሰ።

ጠቢቡ በስሱ ፈገግ አሉና እንዲህ አሉት፦ "አንተ ምን ያህል ችኩልና በውጫዊ ውበት የምትታለል ሰው መሆንህን አረጋገጥክ። ስለዚህ ከሁለቱ አንዱንም አትገባም፤ ጽጌረዳ ያለበትንም ሆነ ቁልቋል ያለበትን።

አንዳንድ ወንዶች በውበትና በማህበራዊ ገጽታ ተገፋፍተው በውጭ የሚያብረቀርቀውን ይመርጣሉ። ጽጌረዳ ውብ ናት ነገር ግን ቶሎ ትጠወልጋለች። ቁልቋል ግን በመጀመሪያ እይታ ያን ያህል ባይማርክም፣ በማንኛውም የአየር ንብረት ውስጥ ሳይለወጥ እንደሆነው ይኖራል። ሁሌም ጥቁር አረንጓዴና እሾሃማ ነው፤ ነገር ግን ሲያብብ ልዩና ውብ አበባን ይሰጥሃል።

ሚስትህ ድክመቶችህን፣ ጉድለቶችህንና ስህተቶችህን ሁሉ ታውቃለች፤ ከነሙሉ ስብዕናህም ትወድሃለች። ውሽማህ ግን የምትፈልግህ ሙሉውን አንተነትህን ሳይሆን ውብ የሆነውን ገጽታህን ብቻ ነው፦ ፈገግታህን፣ ድሎችህን፣ ደስታህንና እንክብካቤህን። ሚስትህ ግን እንባህንና ሽንፈቶችህን ሁሉ አቅፋ በክፉም በደጉም ከጎንህ ናት።

አስቸጋሪ ጊዜ ሲመጣ ውሽማህ ትታህ ትሄዳለች፤ ሌላም ሰው መፈለግ ትጀምራለች። ሚስትህ ግን ከጎንህ ጸንታ ትቆማለች። ነገሮች ሁሉ መልካም በሚመስሉበት በዚህ ሰዓት ብቻ አትፍረድ። ነገሮች ሁሌም እንዲህ አይቀጥሉም።

ላንተ አሁን ጊዜው በጣም ረፍዷል። ጽጌረዳዋን ለማግኘት ቁልቋሉን ንቀሃልና ሁለቱንም አታገባም። ነገር ግን ስህተትህን የምትረዳበት ጊዜ እንደሚመጣ እወቅ፤ በዚያን ጊዜ ግን ሁሉም ነገር አልፎ ይሆናል።"

ቤትህ ያለውን አልማዝ ትተህ የጎዳና ላይ ድንጋይ ለመልቀም አትሩጥ::

#ገጣሚአበበተሾመ@tztbt
ጽጌረዳዋ ወይስ ቁልቋሉ? (The Rose or the Cactus?)

አንድ ሰው ሚስትና ውሽማ ነበሩት እና የትኛዋን መምረጥ እንዳለበት ግራ ገብቶት ነበር። በመጨረሻም ለችግሩ መፍትሄ ፍለጋ ወደ አንድ ጠቢብ ሰው ዘንድ ለመሄድ ወሰነ። ጠቢቡንም "ከሚስቴ ወይስ ከውሽማዬ ጋር መሆን አለብኝ?" ብሎ ጠየቃቸው።

ጠቢቡም ሰውየውን ተመልክተው ሁለት የአበባ ማስቀመጫዎችን በእጃቸው ያዙ፤ በአንደኛው ጽጌረዳ በሌላኛው ደግሞ ቁልቋል ነበር። ከዚያም እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፦

"ከእነዚህ ሁለት ማስቀመጫዎች አንዱን እንድትመርጥ ብነግርህ የቱን ትመርጣለህ?"

ሰውየውም "በእርግጥ ጽጌረዳዋን እመርጣለሁ!" ሲል በችኮላ መለሰ።

ጠቢቡ በስሱ ፈገግ አሉና እንዲህ አሉት፦ "አንተ ምን ያህል ችኩልና በውጫዊ ውበት የምትታለል ሰው መሆንህን አረጋገጥክ። ስለዚህ ከሁለቱ አንዱንም አትገባም፤ ጽጌረዳ ያለበትንም ሆነ ቁልቋል ያለበትን።

አንዳንድ ወንዶች በውበትና በማህበራዊ ገጽታ ተገፋፍተው በውጭ የሚያብረቀርቀውን ይመርጣሉ። ጽጌረዳ ውብ ናት ነገር ግን ቶሎ ትጠወልጋለች። ቁልቋል ግን በመጀመሪያ እይታ ያን ያህል ባይማርክም፣ በማንኛውም የአየር ንብረት ውስጥ ሳይለወጥ እንደሆነው ይኖራል። ሁሌም ጥቁር አረንጓዴና እሾሃማ ነው፤ ነገር ግን ሲያብብ ልዩና ውብ አበባን ይሰጥሃል።

ሚስትህ ድክመቶችህን፣ ጉድለቶችህንና ስህተቶችህን ሁሉ ታውቃለች፤ ከነሙሉ ስብዕናህም ትወድሃለች። ውሽማህ ግን የምትፈልግህ ሙሉውን አንተነትህን ሳይሆን ውብ የሆነውን ገጽታህን ብቻ ነው፦ ፈገግታህን፣ ድሎችህን፣ ደስታህንና እንክብካቤህን። ሚስትህ ግን እንባህንና ሽንፈቶችህን ሁሉ አቅፋ በክፉም በደጉም ከጎንህ ናት።

አስቸጋሪ ጊዜ ሲመጣ ውሽማህ ትታህ ትሄዳለች፤ ሌላም ሰው መፈለግ ትጀምራለች። ሚስትህ ግን ከጎንህ ጸንታ ትቆማለች። ነገሮች ሁሉ መልካም በሚመስሉበት በዚህ ሰዓት ብቻ አትፍረድ። ነገሮች ሁሌም እንዲህ አይቀጥሉም።

ላንተ አሁን ጊዜው በጣም ረፍዷል። ጽጌረዳዋን ለማግኘት ቁልቋሉን ንቀሃልና ሁለቱንም አታገባም። ነገር ግን ስህተትህን የምትረዳበት ጊዜ እንደሚመጣ እወቅ፤ በዚያን ጊዜ ግን ሁሉም ነገር አልፎ ይሆናል።"

ቤትህ ያለውን አልማዝ ትተህ የጎዳና ላይ ድንጋይ ለመልቀም አትሩጥ::

#ገጣሚአበበተሾመ@tztbt
#elshaday@tztbt
1
#SouthEthiopia

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን ኪንዶ ኮይሻ ወረዳ የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የማሽንጋ ወንዝ በመሙላቱ በተከሰተ ጎርፍ የሁለት ሰዎች ሕይወት መጥፋቱን የወላይታ ዞን አደጋ ስጋትና ስራ አመራር ኃላፊ አቶ ዳዊት ደሳለኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ወደ ገበያ እየሄዱ የነበሩ አራት አርሶአደሮችን የዉሃ ሙላቱ  ወስዷቸዉ እንደነበር የገለፁት አቶ ዳዊት ሁለቱ በሕይወት መትረፋቸውን ሁለቱ ደግሞ ህይወታቸው ማለፉን ገልፀዋል።

በአንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች በመሬት ናዳ ሰዎች እንደሞቱ ተደርጎ እየተሰራጨ ያለዉ መረጃ ከእዉነት የራቄ ነዉ ያሉት ኃላፊዉ ከሰሞኑ በዞኑ በየትኛውም ቦታ በመሬት ናዳ የሞተ ሰዉ አለመኖሩን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ፤ በዛው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ደቡብ አሪ ዞን ሳላማጎ ወረዳ ዲሜገሮ ቀበሌ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ምሶሶ ለመትከል በቁፋሮ ላይ የነበሩ ሰራተኞች ላይ አፈር ተደርምሶ ሦስት ወጣቶች ወዲያውኑ መሞታቸውን የወረዳዉ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ግዳጁ ጨነቀ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አደጋዉ የደረሰዉ በአከባቢው የከፍተኛ ኤሌክትሪክ መስመር ተሸካሚ ታዎር ለመትከል DCGG በተባለ ኮንትራክተር አማካኝነት በተቆፈሩ ጉድጓዶች የዝናብ ዉሃ መሙላቱን ተከትሎ ዉሃዉ በጄኔሬተር ፓንፕ እንዲወጣ ተደርጎ ሰራተኞች ግንባታ እየሰሩ በነበረበት የአፈር መደርመስ ተከስቶ እንደሆነ አስረድተዋል።

በአደጋው ሦስት ወጣቶች ሲሞቱ በሁለቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን አስታዉቀዋል።

የሦስቱ ወጣቶች አስከሬን በእስካቫተር ተቆፍሮ መዉጣቱንም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

#ገጣሚአበበተሾመ@tztbt
ቴዲ አፍሮ እስካሁን ካወጣቸው ሙዚቃዎች መካከል "ማ ዘንድ ይደር.." የሚለው ሙዚቃውን የሚያህል የለም። All Teddy Afro musics are great but "ማ ዘንድ ይደር" Hits different. ለእኔ የምንጊዜም ምርጥ ሙዚቃ ነው። ግጥሙ፣ ዜማው እንዲሁም ቅንብሩ ያላቸው ውህደት = perfection. ግጥሙ በተለያየ መንገድ Interpret ሊደረግ ይችላል ፤ በተለያየ መንገድ [ አተያይ ] ብዙ ትርጉም ነው ያለው። እማ ዘንድ ይደር ማን ዘንድ ይደር and so on. ግጥሙ ለሁለቱም ትርጓሜዎች ተስማሚ የሆነ ግጥም ነው። ለሀገር፣ ለእናት.. ለሚስት..! ግጥሙ በሶስቱም Angle ብታስቡት ስክት የሚል ነው። የዚህ ግጥም ከፍታ ሁልጊዜ እንዳስደመመኝ ነው..!
.
.
እማ ዘንድ ይደር ፡ ሄዶ ጎኔ
ሰው አልሆንም ፡ ካላንቺ እኔ
ማ ዘብ ኖሮ ፡ ለኔ ገላ
ደግሞ አያለሁ ፡ ካንቺ ሌላ
.
ልምጣ ወይ ልቅር ፡ ምን ይሻለኛል
ከፍቅርሽ የሚያስጥል ፡ ማን ዘንድ ይገኛል
ስለት አለብኝ ፡ ከርቤ እና እጣን
ለመተያየት ፡ እንዲያበቃን
የጠቢቡ ሰው ፡ የሊቁን ቅኔ
ህልሜ አይፈታም ፡ ሳላይሽ ባይኔ
.
እማ ዘንድ ይደር ፡ ሄዶ ጎኔ
ሰው አልሆንም ፡ ካላንቺ እኔ
ማ ዘብ ኖሮ ፡ ለኔ ገላ
ደግሞ አያለሁ ፡ ካንቺ ሌላ
.
የብራና ስእል ፡ አይነ ጎላዬ
መልከ ማክዳ ፡ ሳባ መሳዬ
የሸማሽ ጥለት ፡ ቀልሞ ሰንደቄ
ያስታውሰኛል ፡ ላንቺ መውደቄ
.
ልቤ አምሮህ ሌላ ፡ ዝቅ አትበል ይቅር
ሀገር ያህላል ፡ ከፍ ያለ ፍቅር
ማ ዘንግ ይዞ ፡ ገብቶ ገዳም
ያገናኘው ፡ ፍቅርን ከአዳም
ማ ፆም ይዞ ፡ ቆጥሮ ጠጠር
ባሳከለው ፡ ፍቅርን ሀገር..!

ማ ዘንድ ይደር ፡ ማ ዘንድ ይደር
ሰው አሳዝኖ ፡ ሰው ላይሆን ነገር
ምን አስጀመረው ፡ የማይሆን ነገር
ልቤ አንቺን ትቶ ፡ ከማን ዘንድ ይደር
.
ልማልልሽ ወይ ፡ በ "ቶ" መስቀሌ
ከራሴ ጋር ነው ፡ ብጣላሽ ጥሌ
.
ማ ዘንድ ይደር ፡ ማ ዘንድ ይደር
.
ድር ተርታሪ ፡ ጥልፍ የጠለፈው
አስዋብኩሽ ብሎ ፡ ምን አስጎበረው
ሸማ ተጊጦ ፡ ቀለም ቢነከር
ልብስ አያምርበት ፡ ያ'ራቁት ሃገር
.ልምጣ ወይ ልቅር ፡ አጣሁ መንገድ
እግሬ እንዴት ይጥፋው ፡ ቆርጦ መሄድ
እይ ሰው ሲወጣ ፡ እይ ሰው ሲወርድ
እንዲህ አይደለም ወይ ፡ መራመድ
ይህ አይደለም ወይ ፡ መራመድ
ዘንድ ይደር ፡ ዘንድ ይደር
እማ ዘንድ ይደር..!
#ገጣሚአበበተሾመ@tztbt
1
2025/07/14 05:08:54
Back to Top
HTML Embed Code: