ተወዳጆች
ቅዱስ አትናቴዎስ
ሐዋርያዊ ይህን መሠረታዊ ጉዳይ በአርዮሳውያን ላይ በጻፈው ጥልቅና ሰፊ ትምህርቱ ላይ እንዲህ ሲል ያብራራዋል-
ቃል ፍጡር ቢሆን ኖሮ ይህ [የእኛ መዳን] ተፈጻሚ ሊሆን አይችልም ነበር፤ ፍጡር ቢሆን ኖሮ ዲያብሎስም ራሱ ፍጡር ስለሆነ ትግሉን ይቀጥልበት ነበር፤ ሰውም በሁለቱ መካከል ሆኖ ከእግዚአብሔር ጋር የሚዋሐድበትና ከፍርሃት ነጻ የሚወጣበት መንገድ አጥቶ ሕይወቱ ሁል ጊዜ በአደጋ ውስጥና በጥፋት ላይ እንደ ሆነ ይቀጥል ነበር፡፡
ስለዚህም በእውነት የእኛ የሆነውን ሰውነትና ባሕርይ ነሣ (ገንዘብ አደረገ)፡ ይህም ባሕርያችንን እርሱ ፈጣሪውና አስገኚው እንደ መሆኑ በእርሱ በራሱ ያከብረው ዘንድ፣ በዚህም በእርሱ መሪነትና አርአያነት ወደ መንግሥተ ሰማያት ያገባን ዘንድ ነው::'™ የሰው ባሕርይ (ትስብእት) የተዋሐደው ከፍጡር ጋር ቢሆን ኖሮ፣ ወይም ወልደ እግዚአብሔር እውነተኛ እግዚአብሔር ባይሆን ኖሮ የእኛ ባሕርይ የጸጋ አምላክነትን አያገኝም ነበር፤ የእኛን ሥጋ የለበሰው የእርሱ (የእግዚአብሔር] እውነተኛና የባሕርይ ልጁ ባይሆን ኖሮ ሰው ወደ እግዚአብሔር ዘንድ ከፍ ከፍ ሊልና ሊቀርብ አይችልም ነበር፡፡ (ትምህርት በእንተ አርዮሳውያን፣ ትምህርት 2፣ ቁ. 43)

(ቅዱስ አግናጥዮስ፣ መልእክት ኀበ ፊልጵስዮስ፣ ምዕ. 4)
እንዳለው
“ሰይጣን በአንዳንዶች መስቀሉን ይክዱ ዘንድ በእነርሱ ላይ ሥራውን ይሠራል
የጌታችንን ሕማማቱንና ሞቱን እንዲያፍሩበትና ምትሐት ነው እንዲሉ በውስጣቸው ይሠራባቸዋል
ከድንግል መወለዱንና ሥጋ መልበሱን፣ እንዲሁም የእኛን ባሕርይ ርኩስ እንደ ሆነ አድርጎ ይነቅፋል፡፡
ከአይሁድ ጋር ደግሞ ሰዎች መስቀሉን እንዲክዱ ቤተ ክርስቲያንን ይዋጋታል፤ ከአሕዛብ ጋር ደግሞ ድንግል ማርያምን ይነቅፋሉ፣ ያክፋፋሉ፡ ክርስቶስ ከእርሷ ባሕርይዋን ገንዘቡ አድርጎ እንዳልተወለደ አድርገው ይናገራሉ፡፡
የክፋት ሁሉ መሪና ፍታውራሪ የሆነው ዲያብሎስ አሠራሩ ብዙ ዓይነት ነውና፣ እርሱ የሰዎች ፈታኝና አታላይ እንደ መሆኑ ሰዎችን በተለያዩ መንገዶች ከእውነት ይለያቸው ዘንድ ይፈትናቸዋል፡፡”

ቅዱስ አግናጥዮስ፣ መልእክት ኀበ ሰብአ ጥራልያን፣ ምዕ. 10
👉የማምነውና ተስፋ የማደርገው በምትሐት ወይም በማስመሰል ሳይሆን ስለ እኔ በእውነት ሰው በሆነውና በሞተው በኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡
👉ሐሰት የሆነ ነገር ለእውነት አስጸያፊ ነውና፡፡ ስለሆነም የማምነው ድንግል ማርያም የፀነሰችውና የወለደችው እግዚአብሔር ቃል የተዋሐደውን ሥግው ቃልን ነው፡፡
👉 የእግዚአብሔር ቃልም የእኛን ባሕርይ ገንዘቡ አድርጎ በእውነት ከድንግል ማርያም ተወልዷል፡፡
👉ሰዎችን ሁሉ በማኅፀን የሚፈጥረውና የሚቀርጸው እርሱ ራሱ ከድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ በድንግልና በማኀፀኗ ተፀንሶ ኖሯልና፡፡

ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
ደናግል ሆይ
የሰማያዊ ሕይወት አርኣያና አምሳል የሆነችው
የድንግል ማርያም ሕይወት ይኑራችሁ፡፡
እርስዋ ለክርስቶስ እናት ለመሆን
በምንም የምታንስ አልነበረችም'
ደናግል ሆይ
የሰማያዊ ሕይወት አርኣያና አምሳል የሆነችው
የድንግል ማርያም ሕይወት ይኑራችሁ፡፡
እርስዋ ለክርስቶስ እናት ለመሆን
በምንም የምታንስ አልነበረችም'
ተወዳጆች
መኝታውን በወርቅ ያጌጠ ማድረግ ሲችል
በግርግም ውስጥ ማድረግን መረጠ
እናቱንም ከንግሥታት አንዲቱን ማድረግ ሲችል
አላደረገም ብሏል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ❤️
ድንግል ማርያም እንዲህ ናት::
ታላላቅ ሀብታትን ሳትጠይቅ የተቀበለች ፣
ሳትለምን የተመረጠች ፣ ሳታገባ የፀነሰች ፣
ሳታምጥ የወለደች ፣ ድንግልናዋን ሳታጣ እናት የሆነች ፣
አንዳች ሳትሻ ሁሉን ያገኘች
የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ እርስዋ ናት፡፡
መኝታውን በወርቅ ያጌጠ ማድረግ ሲችል
በግርግም ውስጥ ማድረግን መረጠ
እናቱንም ከንግሥታት አንዲቱን ማድረግ ሲችል
አላደረገም ብሏል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ❤️
ድንግል ማርያም እንዲህ ናት::
ታላላቅ ሀብታትን ሳትጠይቅ የተቀበለች ፣
ሳትለምን የተመረጠች ፣ ሳታገባ የፀነሰች ፣
ሳታምጥ የወለደች ፣ ድንግልናዋን ሳታጣ እናት የሆነች ፣
አንዳች ሳትሻ ሁሉን ያገኘች
የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ እርስዋ ናት፡፡
ውድ ቤተሰቦቼ እንደምን አላችሁልኝ በጣም ነው ሁለችሁንም የምወዳችሁ ፈጣሪ በመልካም ምግባር ያኑርልኝ 💖💖❤️❤️
ድንግል ሆይ
ቤተ ክርስቲያን ታመሰግንሻለች!!!
"ያዘነች ስትሆን በልጅሽ በወዳጅሽ ትንሣኤ የተጽናናችው፡፡
የተዋረደች ስትሆን በድንግልናሽ ቡቃያ መውጣት ከፍ ከፍ ያለችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታመሰግንሻለች፡፡
በዕለተ ዓርብ ከልጅሽ ቀኝ በፈሰሰው ውሀ ተጠምቃ የውግታቱን ደም ተቀብታ ቅድስት ቤተክርስቲያን ታመሰግንሻለች።
የልዑል እግዚአብሔር በግ የተባለ ልጅሽ ዐማኑኤልየተሞሸረባት መርዓዊ ሰማያዊ የተባለባት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታመሰግንሻለች"
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ❤️

መላእክት ሁሉ ይዘምሩላታል
❝ በሰማያት ኵሎሙ መላእክት ይኬልልዋ… ወበምድርኒ ኵሎሙ ቅዱሳን ይቄድስዋ... እስመ ወለደት ወልደ ዘበኵራ ያፈቅርዋ እንዘ ንጽሕት በድንግልና… አልባቲ ሙስና ፤ ❞
ትርጉም ፦ በሰማያት መላእክት ሁሉ ይዘምሩላታል ፣ … በምድርም ቅዱሳን ሁሉ ያመሰግኗታል ፣ … በድንግልናዋ ንጽሕት ስትሆን የበኵር ልጇን ወልድን ስለወለደች ይወዷታልና ፣ … እሷ ርኵሰት የሌለባት ናት"
[ ቅዱስ ያሬድ ]

ወረብ ፭ኛ ናሁ ተፈፀመ የ፩ኛ ዓመት የ፮ኛ እሁድ ጽጌ
#መዝሙረ_ማኅሌት #
ናሁ ተፈጸመ ተፈጸመ ናሁ ማኀሌተ ጽጌ ሥሙር ተፈጸመ ናሁ/፪/
አስምኪ ቦቱ አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት/፪/
ተፈጸመ ናሁ #ማኅሌተ_ጽጌ_ሥሙር፥ አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር፥ ከመ በሕጽንኪ ያሰምክ ፍቁር፡፡” — “ንጹሕ የተዓምርሽ ቀስት (5 ቀስተ ደመና የማርያም መቀነት) እንደ ብር ገንቦ ጌጥ፥ በአረንጓዴ ቢጫና ቀይ ዐይነት በወርቅ አምሳል የተሠራ ነው፥ የሰማይና የምድር #ንግሥት ኾይ! የተወደደ የጽጌ ምስጋና ተፈጽሟልና፥ የቀጣዩን ዓመት ምስጋና በሰላም አቅርቢልን።”
እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ🙏

እመቤታችን በጣም በጣም ችግሮቻችንን ትመለከታለች
ድካም ትረዳለች እናታችን ናት
እመቤታችን ጥቃቅን የሰው ችግር አይሰወራትም
ሁሉን ማየት ትችላለች ለዚህ ነው እርግበየ መደምደሚያየ የምንላት
ለሁሉም የምትበቃ እናት እመቤታቸን ናት
እኔ እናቴ ልታበላኝ ትችላለች ልታድነኝ ግን አትችልም
በነፍሴ ብታሰር ግን ልታስፈታኝ አትችልም
እመቤታችን ለሁሉም ምትብቃ ናት
ርዕሰ ሊቀውንት አባ ገብረ ኪዳን❤️

ሰው ፍለጋ እግሩን የሚያደክም ሰው
ልቡ ይወልቃል እንጂ ሰው አያገኝም
የራስን ልብ እራስን ማስተካከል ነው
ሰውን ከማስተካከል እራስን ማስተካከል
ሰውን ለማስተካከል መድከም በፍፁም አይቻልም
እሚቻለው እራስን ማስተካከል ነው
ተስፋ የቆረጡ ሰዎች ይሄን ሁሉ አልፈው
ከተስፋ መድረስ እንደሚቻል የምታሳይ
ብቸኛዋ የቤተክርስቲያን ተስፋ ምልክት
እመብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም ነች።
እግዚአብሔርን ለያዘ ብቸኝነት የለበትም።
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ❤️
ልቡ ይወልቃል እንጂ ሰው አያገኝም
የራስን ልብ እራስን ማስተካከል ነው
ሰውን ከማስተካከል እራስን ማስተካከል
ሰውን ለማስተካከል መድከም በፍፁም አይቻልም
እሚቻለው እራስን ማስተካከል ነው
ተስፋ የቆረጡ ሰዎች ይሄን ሁሉ አልፈው
ከተስፋ መድረስ እንደሚቻል የምታሳይ
ብቸኛዋ የቤተክርስቲያን ተስፋ ምልክት
እመብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም ነች።
እግዚአብሔርን ለያዘ ብቸኝነት የለበትም።
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ❤️
የዓለም ሁሉ መድኃኒት የምትሆን ብላቴና እግሯ የተመላለሰበቱን ምድር እስም ዘንድ ማን በከፈለኝ
ይቅርታን የምታሰጥ ብላቴና ጥላዋ ይነካኝ ዘንድ ማን በከፈለኝ የብርሃን ልጅ ወደሄደችበት እከተላት ዘንድ ማን በከፈለኝ የእግሯንም ጫማ እሸከም ዘንድ ማን በከፈለኝ።
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ

ድንግል ማርያምን የያዘ ሰው የክርስቶስ በግ ነው ።
ምልክት የሌለው የላባ ነው ማለት
ምልክቲቱ ድንግል ማርያም ናትና
ድንግል ማርያም የሌለቻቸው ሰዎች የዲያብሎስ ናቸው ።
የክርስቶስ በጎች አይደሉም አንዱ ምልክታችን መስቀል ነው።
መስቀል የላቸውም አያምኑትም ይክዱታል።
ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይላል ።
እኔ ከክርስቶስ መስቀል በቀር በምንም ባንዳች አልመካም ።
ድንግል ማርያምን የያዘ ሰው የክርስቶስ በግ ነው ።
ምልክት የሌለው የላባ ነው ማለት
ምልክቲቱ ድንግል ማርያም ናትና
ድንግል ማርያም የሌለቻቸው ሰዎች የዲያብሎስ ናቸው ።
የክርስቶስ በጎች አይደሉም አንዱ ምልክታችን መስቀል ነው።
መስቀል የላቸውም አያምኑትም ይክዱታል።
ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ ይላል ።
እኔ ከክርስቶስ መስቀል በቀር በምንም ባንዳች አልመካም ።
Forwarded from Quality button