Telegram Web
«ካባዬ»
(ከለእርቃን ሩብ ጉዳይ መፅሐፍ)

ክፍል አንድ

------------
ይሄንን ኮንዶሚኒየም ቤት ለማግኘት ከሦስት ወር በላይ ተንከራትቻለሁ።

ኪራይ ነው።
ዛሬ ዛሬ አዲስአበባ ላይ ፍላጎትንም፣ አቅምንም አጣጥሞ የሚገኝ የኪራይ ቤት
ማግኘት ሕልም ነው። እኔ ደግሞ የብር ችግር እንደሌለበት ሰው ስመርጥ ዐይን
የለኝም። ሀብታም ስላልሆንኩ ጠባብ ቤት መኖር ይፈረድብኝ፣ ግን ጠባብም
የተግማማም መሆን አለበት?



የለበትም።
ለዚህ ነው ይህንን አራተኛ ፎቅ ላይ የሚገኝ በጣም ጠባብ ግን ንጹህና ሰላማዊ
ስቱዲዮ ኮንዶሚኒየምለማግኘት ሦስት ወራት የፈጀብኝ። ከንጽሕናው ፀጥታው፣
አራተኛ ፎቅ ጥግ ላይ ክትት ብሎ መገኘቱ ማረከኝና ተከራየሁት።


ግን ይሄ ታሪክ ስለ ተከራየሁት ስቱዲዮ ኮንዶሚኒየም አይደለም።
ስለንጽሕናውና ስለፀጥታውም አይደለም። ስለሰፈሩ ከተማ መሀል መገኘትም
አይደለም። ስለ አዲሷ ጎረቤቴ እትዬ እማዋይሽ ነው።


ታኅሳስ ላይ ቤቱን ቀለም አስቀብቼ፣ እቃዎቼን ሸክፌ ገባሁ።


በገባሁ ዕለት ነው እትዬ እማዋይሽን ያገኘኋት እና የተዋወቅኳት።

ቅዳሜ ነበር። ከቀኑ ዘጠኝ ሰዐት ይሆናል።

እሷ፣ ፎቁን እያረፈች እንደወጣች በሚያስታውቅ ሁኔታ ትንፋሽዋ ቁርጥ ቁርጥ እያለና እያለከለከች በሬ አጠገብ የሚገኘው በሯ ጋር የቤቷን ቁልፍ እያንቀጫቀጨች ስትደርስ፣ እኔ ደግሞ ውስጥ ያለውን እስካስተካክል ውጪ የተውኳቸውን ኮተቶቼን ወደ ቤት ለማስገባት ስወጣ ነው፣ ፊት ለፊት የተገጣጠምነው።

እንዳየኋት የተሰማኝ ነገር ያለቦታዋ የምትገኝ ሰው መምሰሏ ነበር።

በዕድሜ ስልሳ ቤት ትሆናለች።

ነገር ግን ሙሉ በሙሉ የሸበተው ጸጉሯ ብዙ ጊዜ ዕድሜያቸው የሄደ ሰዎች ላይ እንደማየው ስስና እንክብካቤ ያጣ አልነበረም። ዘንፋላና በሥነ-ሥርአት የተተኮሰ ነበር። አለባበሷ አሁንም በእሷ ዕድሜ ያሉ ሴቶች እንደሚዘወትሩት ሰፊ ልብስ ላይ ሌላ ሰፊ ልብስ፣ ግራጫ ቀለም ላይ ቡናማ፣ ወፍራም ሹራብ ላይ ወፍራም የአንገት ልብስ ዓይነት አልነበረም።
ደልደል ያለና ውብ ሰውነት አላት።

በልኳ ግን ሳይጠብ የተሰፋ ቆንጆና ደማቅ ቢጫ ቀሚስ፣ አጠር ካለ ሰማያዊ ክፍት ሹራብ ጋር ለብሳለች። ተረከዙ አጭር፣ ፊቱ ሹል ጥቁር ጫማ አድርጋለች። የምታምር ትንሽዬ ቡናማ ቦርሳ አንግታለች።

ደርባባ ነች። ዘንጣለች።

“እንዴት ዋልሽ ልጄ?” ስትለኝ ነው ዕድሜዋን ከዝነጣዋ ያስታረቅኩት።

“ደህና ይመስገን” አልኩኝ ፈጠን ብዬ።

“ጎረቤትሽ ነኝ… እንኳን ደህና መጣሽ… እማዋይሽ እባላለሁ”
“አመሰግናለሁ… ኤደን እባላለሁ” መለስኩላት።
“ሳናግዝሽ ገባሽ… አሁን ምን ልርዳሽ?” አለች ዐይኖቿን ተመሳቅለው
የተኮለኮሉት ውጪ የተዘረገፉ እቃዎች ላይ አሳርፋ።

“ግዴለም ብዙ አይደለም ጨርሻለሁ” አልኩ አሁንም ፈጥን ብዬ።

“በይ ስትረጋጊ ቤቴ ነይና ቡና ጠጪ” አፈር አልኩና፣

“አይ…. እሱ እንኳን ሌላ ቀን” አልኩ። እያግደረደረችኝ ከሆነ መግደርደሬ ነበር።

“ኖንሴንስ… እያግደረደርኩሽ አይደለም… ጎረቤት መተዋወቅ አለበት። ቡና
ማፍላቴ ስለማይቀር እቃሽን ቦታ ቦታ አስይዢና እንጠጣለን”

አሁን ጥያቄ አልነበረም።

ትልቅ ሰውም ስለሆነች፣ ጥያቄም ስላልነበር ምርጫ አጥቼ እሺ አልኳት።
ዐሥራ አንድ ሰዐት ገደማ ላይ የብረት በሬ ተንኳኳች።

እማዋይሽ ነበረች።

“ነያ ቡናው ደርሷል” አለችኝ።

በሬን ቆልፌ ተከትያት ቤቷ ገባሁ።

ቤቷ፣ አዲስ በተቆላ የቡና ጠረንና ለአፍንጫ በሚጥም ዕጣን ጭስ ተጨናንቃ
ተቀበለችኝ።

ረከቦትና ስኒዎቹን በዐይኔ ብፈልግ የሉም። ዕጣን ማጨሻውን ለማግኘት ብሞክር
አልቻልኩም።

ከመቀመጤ፣ “ዛሬ ገብተሽ መቼስ ምግብ አልሠራሽም” ብላ ምን የመሰለ
ፍርፍር አበላችኝ።

ጎንደር ያለችውን ባለሙያ እናቴን አስታወሰኝ።

(ይቀጥላል)

By Hiwot Emishaw


@wegoch
@wegoch
@paappii
< "እናርግ" አለኝ እኮ፣ ያ ውሻ >

ምናለበት እሺ ብትዪው ? ምትወጂው ከሆነ ስሜቱ ለጋራ ነው ፣ አይደለም እንዴ?

< አንተ ሐይሚን አርገሀታል? ንገረኝ። >

"አድርገሀታል" ማለት? ምን አደረኳት? "

< ሒይ ! እያወክ አትገግም። >

"በድተሀታል ወይ ? ማለት ፈልገሽ ከሆነ ፣ በድቻታለሁ። ብድትድት ነው ያረኳት። ካንቺ ጓደኞች ያልበዳሁት የለም። "

< እህ ? ውሻ! ውሻ ነህ ።>

አዎ ነኝ ! ዉው ዉው ኣዉዉዉዉዉ ። ሀያትንም በድቻታለሁ።

ሀያት ነች ያስተዋወቀችን። ሀያት የጥቁር ቆንጆ ፣ እንደ እሳት ቅልብልብ ፈጣን ውልብልብ እጅግ ብልህና በትምህርትም ጎበዝ ተማሪ የነበረች ናት። ኤለመንተሪ ከሀያት ጋር ስንማር ጥያቄ ና መልስ ውድድር እኔና እሷ ከፍላችንን እየወከልን ዞረናል። ሀይስኩል እንደገባን ሀያት ናት ከዚህችኛዋ አለም ጋር ያስተዋወቀችን። ከአስረኛ ክፍል በሁዋላ ሀያት የት እንደገባች አናውቅም። እኔና አለም ግን አስር አመት ሆነን። በጓደኝነት። ንፁህ የሚባለው አይነት ጓደኝነት።

*_*_*_*_*_*_*_*_*_*_*_*_*_*

አለም

< ወዬ >

" አለም የሚል ስም ይዘሽ እንዴት መንፈሳዊት አማኝ ሆንሽ ? "

< አንተማ ለይቶልሀል። >

ሁሌም ከፍቅረኞቿ ምትለያየው የወሲብ ጥያቄ ሲያቀርቡላት ነው። እሷ "ከጋብቻ በሁዋላ" ትላቸዋለች። እነሱ ጥለዋት ሲሄዱ መጥታ እኔ ላይ ታለቅስብኛለች። ይበዳኛል ብላ ሰግታ አታውቅም።

እኔ ብበዳሽስ ? እላታለሁ።

ሁሌም < ሐይሚን አርገሀታል? እስካሁን ስንት ሴት አወጣህ? > ትለኛለች።

"ስንቷን ሴት ስንት ስንት ጊዜ እንዳወጣሁ ልንገርሽ ? ሐይሚን ...ሐያትን ደሞ እእእ ?"

< ኡህ! አንተስ ባልገሀል >

ትለኛለች።

*_*_*_*_*_*_*_*_*_*_*_*_*_*

በስጋ እናትም አባትም። ቤተሰቦቿ አሳዳጊዎቿ ናቸው። እና እኛ። እኛ ማለት እኔና ሌላ ማላውቃቸው ጓደኞቿ።

< አንተ ቤተሰብ ስላለህ እድለኛ ነህ > ትለኛለች።

" እኔ ቤተሰብ እዳ ነው " እላታለሁ።

*_*_*_*_*_*_*_*_*_*_*_*_*_*

ያኔ ሐያት ከእሷ ጋር ካስተዋወቀችን ማግስት ወደኔ ክላስ እየተጎተተች መጣች። ፀይም ነበረች ግን አመዳም። ፀጉሯ ረጅም ነው፣ ግን ደረቅ ነው። ጥቁር ሻርፕ አንገቷ ላይ ጣል ታደርጋለች ፣ ለምን እንደምታደርግ አይገባኝም። እናም ያግባባን ብቸኛ ነገር እኔ ብልህ እንደሆንኩ ማሠቧ ና እሷ ብርቱ ስለሆነች ከእሷ ጋር እንደምስማማ ስለምታስብ ነው።

እኔስ ? እኔ ትምህርት ላይ እየቀነስኩ አሪፍ መስሎ መታየት ላይ እየበረታሁ ነበረ። ቀንደኛ ቀልደኛ ሚባሉት ተማሪዎችን ጎራ ተቀላቀልኩ። ሁሉም ጓደኞቼ ድንግል ሆነው ሳሉ ቀድሜ ገርልፍሬንድ ያዝኩ፣ ቆንጆ ሴት፣ ከሌላ ክፍል፣ ሐይማኖትን ። በርግጥ ኤለመንተሪ እያለሁ የሔርሜላን አንገት ስሜያለሁ። ከነሱ መፍጠኔ ለእኔ አይገርመኝም።

እና ይህቺ አለም < ትምሕርትህ ይበጅሀል። እሷን ተዋት። ገና ልጅ ነህ። ደግሞም ቆንጆ አይደለችም።> ትለኝ ነበረ።

ግን ሁለታችንም በእድሜ እኩያሞች ነን። እሷን መካሪ እኔን ተመካሪ ያደረገን እሷን ለይቶ የመከራት ኑሮ ነው።

ኑሮ ያስተማራትን ትምህርት በደንብ ይዛዋለች። ፈተናውንም አልፋዋለች። አሁን ዘናጭ ነች። ፀይም መልኳም ፀጉሯም ወዝ ኖሮታል። ለስራ ሌላ ሀገር የሄደች ጊዜ ገንዘብ እኔ አበድራት ነበረ። ሁለት ጊዜ ሌባ ሙልጭ አድርጎ ዘርፏታል። አሁን እኔ ገንዘብ ሲቸግረኝ ከእሷ ነው የምበደረው። የወር ገቢዋ ከእኔ የወር ደመወዝ አስር እጥፍ ነው።

*_*_*_*_*_*_*_*_*_*_*_*_*_*

አስረኛ ክፍል ተዋወቅን ፣ አስር አመት አብረን አሳለፍን ። አሁን ልታገባ ነው። ሰርጓ በቅርብ ነው።

<አንተ መቼ ነው ምታገባው ? >

ብዙ ፍቅረኞች አሉኝ ። የቷን ላግባ?

< ባለጌ

ሐይሚን አሁን ብታገኛትስ ? >

አስር አመት ሙሉ ሐይሚን ያልረሳሻት ለምንድን ነው ?

< ሐይሚን አይደለም ያልረሳሁት። ያንን የግቢውን ቆንጆ፣ ብልህና ትንሽዬ ልጅን ልረሳው ያልቻልኩት። የአስራስድስት አመቱን ያንን ናሁ መሆን እፈልግ ነበር። አሁን ላይ ግን እዚህ ሆነን ደግሜ እሱ ራሱን ሆኖ ማየት እመኛለሁ >

" እመኚኝ። እኔ ምንም ከስሬ አላውቅም። እናም የራሴን መንገድ አገኛለሁ። ሚስትም አገባለሁ።

አንቺ ትንሽ ቀደም ብለሽ ሒጂ። አግቢ። እኔ ባንቺ መንገድ አልሄድምና። መልካም መንገድ። መልካም ጋብቻ።

ለባልሽ የምነግረው ነገር አለኝ ፦ " እሷን እቅፌ ላይ ለብዙ ቀን እንዳሳደርኳትና ከእሷ ገላ ላይ የወሰድኩት ምንም ነገር እንደሌለ ነው።

ስላልፈለኩ። ወይ ፈልጌ ስላልቻልኩ። ወይ ችዬም ታማኝ ሆኜ ይሆናል።

እኔ ባለቤቷ ነኝ። አሁን አንተ ባሏ ልትሆን ነው። ይትባረክ"


By Nahu senay

@wegoch
@wegoch
@paappii
የሄደበትን የመጨረሻ ቀን አስባለሁ።

ኩራቱን ተገፎ ሀፍረትን ተከናንቦ እርቃኑን እንደቆመ ሠው ዐይኔን ሽሽት አንገቱን ደፍቶ መሬት መሬት እያየ "እሜትዬ በድዬሻለሁ…" ያለበትን ቃና እሰማለሁ። ምህረት ፍለጋ ለይቅርታ አልመጣም ነበር። አንዳንድ ሀጥያቶች ስርየት የላቸውም፤ ስለአንዳንድ በደሎቻችን ከራሳችንም እርቅ አይኖረንም። ለዋለው ክህደት ይቅርን አልፈለገምና የኔ ይቅር ማለት ትርጉም አልነበረውም። የኔ ምህረት መስጠት ኩራትና ክብሩን ከወደቀበት ሊያነሳለት አቅም አልነበረውም። አንገቱን ደፍቶ በገባበት በር አንገቱን ደፍቶ ሲወጣ ቃል አልወጣኝም። አልተከተልኩትም በዐይኔ አልሸኘሁትም። ልቤ መመለሱን ቢሻ ከበደሉ ሊያልቀው ግን አልተቻለውም። በሰው ለውጦሻል ተይው ይሂድ አለ፡፡ ተውኩት፣ ሄደ…አልተመለሠም ።

ዘመናቶቼ መኸል ግን እጠብቀው ነበር። አንዱን ቀን ይመጣል ብዬ በር በሩን አማትሬያለሁ። ወሬውን ፍለጋ ጆሮዎቼ እልፍ ጊዜ ቆመው የደጁን ድምፅ ሲቃርሙ ኖረዋል። ብዙ ጠብቀዋል፤ ለማንም ሳልነግር በደሉን ውጫለሁ። ባሻዬ ከዳኝ ሳልል ይቅር ብዬ ነበር። ፍለጋ ባልወጣ የት ሄደ ባልል በልቤ በእየዕለቱ 'አንተ ትሻላለህ፤ ተመለስ ግድ የለም' እል ነበር።

እወደው ነበር፤ ኩራት በሸበበው ፈገግታ ቢደበቅም ቅሉ ሳየው ልቤ የፈካ ቀለምን ትፈነጥቅ ነበር። እንደነዛ የመጀመሪያ ቀናት ጠጁን እየተጎነጨ ጓዳውን ሲያማትር በዐይኑ ሲፈልገኝ ትንሿ ልቤ በመጋረጃ ተከልላ እያየች ትደልቅ እንደነበረው፤ እንዲያ…እንዲያ እወደው ነበር። እነዛ ጊዜ ሸምኗቸው ጋቢ ሆነው የለበሳቸው የጥጥ ማጎች ስለሱ እያሠብኩ ሳሾራቸው፤ ተበጥሰው እንደተንከባለሉ ስንት ወድቀው ስንት እንደተነሱ፤ ስንት እንዝርት እንደሰበሩ አያውቅም፤ አልነገርኩትም ለፍቅር ሰነፍ ነበርኩ ።

By Beza Wit

@wegoch
@wegoch
@paappii
አገባሁ...ወለድኩ...ደገምኩ...ሠለስኩ:: እሱን እያፈቀርኩ ከወንድሙ ሦስት ልጆች ወለድኩ:: እሱን እየተመኘው ወንድሙን አገባሁ:: ካሳለፍናቸው 3 የUniversity ጓደኝነት አመታት በኃላ እንደተመረቅን ነበር ላገኘው እንደምፈልግና ብቻውን እንዲመጣ የነገርኩት ገና ተደላድሎ ከመቀመጡ ነው " አፈቅርሀለው" ያልኩት ::ሳቀ በሀይል ሳቀ
"አንቺ ያምሻል እንዴ ለቁም ነገር ነው ምፈልግህ ስትይኝኮ ምን ሆነች ብዬ ስንት ነገር ነው ጥዬ የመጣሁት ትቀልጃለሻ አንቺ ሆሆ " አየሁት .. እነዛ መጀመሪያ ካየዋቸው ቅፅበት ጀምሮ ራሴን ያሳጡኝን አይኖቹን ትኩር ብዬ አየዋቸው ::ሚያረገው እየጠፋው ሁሌ እንደሚጠራኝ
" ቃሊ የምርሽን ነው እንዴ "
"አዎ አፈቅርሀለው" ፊቱን በአንዴ ወደ ግራ የተገባ ፊት ቀይሮ " ከመቼ ጀምሮ ቃሊ?"
"ከመጀመሪያው የሁለተኛ አመት የትምርት ቀናችን ከማክሰኞ ከመስከረም 22 ጀምሮ" ደነገጠ " ቃሊ please አታሹፊብኝ " ፊቱ ሲቀላ እየታወቀኝ መጣ
"ምንም እንድትለኝ አይደለም ብንጋባ ብታፈቅረኝ ምንምን በደስታ ልሞትብህ ስለምችል አላቅም ግን እህቴ ነሽ ምናምን እንዳትለኝ ደሞ" መንተባተብ ጀመርኩ ::
"ቃሊ"
"ወዬ" ልቤ በፍጥነት ስትመታ ይታወቀኛል
"ኤላኮ ያፈቅርሻል" ፊቱ ማላቀውን እሱን ሆነብኝ..ውስጤ ሲፈረከስ ተሰማኝ ኤላ ማለት? ኤላ የሱ ወንድም? ማለት መንታ ወንድሙ ኤላ ? ኤላ ጓደኛዬ? ኤላ ኤላ ውስጤ ተተራመሰ.....በመልክም በአመልም ምንም አለመመሣሠላቸው ሲገርመኝ ነበር ሶስቱን የጓደኝነት አመታት ያሳለፍነው :: ሁሌም አብረን ነበርን እሱም..ኤላም...እኔም :: በሁለት መንታ ወንድማማቾች መሀል ያለው ብቸኛ ጓደኛቸው በመሆኔ ጊቢ ውስጥ እንደኔ ደስተኛ ሰውም የነበረ መኖሩን እኔንጃ እኔን መሀል አርገው ሲተራረቡ መስማት...ሲበሻሸቁ...አንዳቸው እንዳቸው ላይ ሲቀልዱ ...እጄን የኔው ተፈቃሪ እንደቀልድ በቦክስ ሲመታኝ ኤላ ሲቆጣው...ተሸክመውኝ ሲሯሯጡ ላየን 3 መንታዎች እንጂ ማልዛመዳቸው መሆኔን ማንም አይጠረጥርም አንዳንዶቹ ደሞ የማንኛው ናት እንደሚሉም አቃለው :: የጊቢው ሴቶች ደሞ ኤላን ይወዱት ስለነበር እንዳጣብሳቸው ሚወተውቱት እኔን ነው ኤላ ግን ወይ ፍንክች ስለሚል ማጣበሱ አልተሳካልኝም ነበር :: ሲፈጥረኝ ከሴት አትዋደጂ ያለኝ ይመስል ከልጅነቴ ጀምሮ ሴት ጓደኛ ኖሮኝ አያውቅም ጊቢ ገብቼም የመጀመሪያውን freshman አመት ከማንም ጋር አልግባባም ነበር ከዛ ግን ሁለተኛ አመት ላይ ምንማረውን ትምርት መርጠን ስንመደብ እነሱን አገኘው ለዛም ነበር በጓደኝነታችን ደስተኛ የነበርኩት :: ከ6ኪሎ ጊቢ በታች ያሉ ማሚ ቤቶች ሄደን ምሳ ስንበላ በእጄ ከአንድ ጉርሻ በላይ ስጎርስ አላስታውስም በሁለቱ የፉክክር ጉርሻ ነበር ጠግቤ ምነሣው በዛ ላይ ሳየው ገና ልቤ የደነገጠለት ልጅ ጓደኛ ሆኜ ስስቅ መዋል ..ደስታ ማለት እኔ ነበርኩ:: "ጉድና ጅራት ወደ ኃላ ነው" አሉ....ያን ቀን "ኤላኮ ያፈቅርሻል " ሲለኝ ጉሮሮዬም ልቤም አይምሮዬም ደረቀብኝ ጎኔ ያለውን ግማሽ ኮካ አንስቼ ጨለጥኩት ::
"ኤላ የቱ" አይኖቼ ሲፈጡ ይታወቀኛል
"ቃሊ ኤላ የኛ ነዋ "ፊቱ የማላቀው ቋንቋ ፅሁፍ ሆነብኝ አየዋለው አይገባኝም ::
"ከመቼ ጀምሮ?" እሱ እንዳለኝ እኔም አልኩት ማወቄ ይቀይረው ያለ ነገር ይመስል
"ካየሽ ቀን ጀምሮ ቃሊ ትዝ ይልሻል class እንደጀመርን ካፌ አጊኝተንሽ ብቻሽን ከምትበዪ ከኛ ጋር ምሳ አብረን እንብላ ብዬሽ አብረሽን የዋልሽ ቀን " እንዴት እረሳዋለው ያን ቀን በአይን ካፈቀርኩት ሰውጋር አምላክ አገናኘኝ ብዬ በደስታ ስፈነድቅ ነበር የነጋው :: ፀጥ ብዬ ሳየው ወሬውን ቀጠለ "ያን ቀን ማለት ኤላ ካላስተዋወከኝ ብሎ ሲለምነኝ ነበር ታውቂያለሽ ቃሊ ኤላን ከማህፀን ጀምሮ ሳውቀው ከአፉ ወቶ ሚያውቀው የሴት ስም ያንቺ ብቻ ነበር :: ቃሊ ኤላ አንቺን ስለማግባት ካንቺ ስለመውለድ ብቻ ነውኮ ሚያልመው ደሞ እሱም ከዛሬ ነገ እነግራታለው እያለ ነውኮ የተመረቅነው ቃሊ ኤላን ያዢው ወንድሜ እስከነፍሱ የሚያፈቅራት ሴት ታፈቅረኛለች ብሎ ማሰቡ ለኔም በሽታ ነው ቃሊ ደና ዋይ ኤላን ያዢው" ብሎኝ ነበር በተቀመጥኩበት ጥሎኝ የሄደው "ኤላን ያዢው" ይሄን ነበር ያለኝ :: .....እኔም ኤላን በእጄ በልቤ እሱን ይዤ ይኸው ሶስተኛ ልጃችንን ወለድን:: .....ኤላ ህልሙን ኖረ እሺ እኔስ?? የሱ ህልም ማስፈጸሚያ ልሆን ነበር የተፈጠርኩት? ያፈቀሩትን ስለማግኘት ኤላ ያሟላው እኔ ያጎደልኩት መስፈርትስ ምን ነበር??? ልጆቼስ አጎታቸውን በልቤ አግብቼ እንደምኖር ያወቁ እንደሆነ እንዴት ይዳኙኝ ይሆን ? እንጃ....ሁሉም ያፈቀረውን አያገባም..ልክ እንደኔ::


By ቃል_ኪዳን


@wegoch
@wegoch
@paappii
God,have mercy! This woman is so obsessed with her life. With her home and her family.

በጠዋት ትነሳለች ቁርስ ትሰራለች ቤተሰቦቿን ታበላለች ታጠጣለች መጥገባቸውን ታረጋግጣለች ከዛም ወደየሚሄዱበት ትሸኛቸዋለች። ቀጥላ ወደቤቷ ጽዳት ፣ ወደእንጀራ ጋገራ ፣ ምሳ ማሰናዳት ወዘተ.... አቤት ያላት ፅናት! ለጉድ ነው! ቤት ጠርጋ ወልውላ አጫጭሳ ልብሶች አጥባ እቃዎቹ ታጥበው ደርቀው በየቦታቸው ተደርድረው።
ወጡ ችክን ብሎ ተሰርቶ፣ ቡናው ትክን ብሎ ፈልቶ እጣኑ እየጤሰ ምሳ 'ሳት ይደርሳል። በር በሩን እያየች የቤተሰቧን መምጣት ትጠብቃለች ሲመጡላት በሚገባ ታስተናግዳቸዋለች።

በፈገግታ እና በምግብ ከፈወሰቻቸው በኋላ መልሰው ወደየሩጫቸው! "አመሠግናለሁ"ን እንኳን ሳትጠብቅ በሳቅ በፈገግታ ሸኝታ ወደቤቷ! የተበላበትን የተጠጣበትን እቃ አጥባ፣ የተዝረከረከውን ቤት አበጃጅታ ስታበቃ ደግሞ ለእራት ዝግጅት ጉድ-ጉድታዋን ትጀምራለች። ጣፋጭ ምግብ አብስላ፣ ሙቅ ሾርባ ሰርታ ቤቷን አሟሙቃ ትጠብቃለች። ወዳሞቀችው ጎጆ ይሰበሰባሉ ከእጇ ፍሬም ይበላሉ።

ይሔ ብቻ አይደለም she is psychiatrist ,she is economist, she is event organizer, she is expert in negotiation and an incredible socialist!

ይህች ሴት እናቴ ናት❤️

ምኞትሽ ምንድነው ብባል " እንደሷ መሆን" እላለው።


By Magi

@wegoch
@wegoch
@paappii
የምወደው ልጅ ነበር ። እርጋታው ህልሙ መልኩ ሁኔታውን
እወደዋለሁ ስህተቱን ድክመቱን ሳይቀር ነበር የምታገሰው ።

ብጥር ...ብጥር... ከኔ ጋ ማቆየት አልቻልኩም ።

ጊዜ ሄደ ...

እኔም ሄድኩኝ

ሌላ መስመር ሌላ ኑሮ ሌላ ጠዓም አየሁኝ እሱ
ዘግይቶ ወደ ምፈልገው መንገድ መጣ

ዳር ዳር አለ እንዳልገባኝ ሆንኩኝ እብረን እንድንሆን ጠየቀኝ ..ዋጋሽ ገብቶኛል ወድጄሻለሁ አለኝ ።

አልታበይኩም አልጎረርኩም ሰነፍ ነው ቀድሞ ደርሶ ባረፈደ የሚያሾፈው ። ብስለት የሚለካው የሆነልን ሲመስለን በያዝነው አቋም እና ሁኔታ ነው ።

በትህትና አልችልም አልኩት ።

Timing is every thing ፀሎቴ ውስጥ ህልሜ ውስጥ ቅዠቴ ውስጥ ማሳካት የምፈለገው ውስጥ እምይዘው አቋም ውስጥ እሱ ነበር ። ጊዜ ሁኔታ አጋጣሚ ተደራረበ እና አንዱም ውስጥ ጠፋ !!

ምንም ስላላዋጣ ግዜ ልቤ ውስጥ የተወለደውን ፍቅር አደብዝዞት ነበር ። ልቤ ውስጥ የተከማቸውን ፍቅር ስላልወደደው ፍቅሬን ፊት ነስቼው በግዜ ብዛት ተነነ ።

ብቻ መወደድ ከብዶኝ ስለነበር ሳስታውሰው እረፍት አይሰማኝም ነበር ። እረፍት የሌለው ፍቅር ምኑን ፍቅር ነው ??

ናፍቆኝ ጓጉቼ ሳገኘው አይኑ ለኔ ስሜት አልባ እንደሆነ ስለሚነግረኝ ናፍቆቴ ወደ ድብርት ይቀየራል ።

የሚለኝን ያደረገውን የሆነውን ሁኔታውን ትርጉም አየሰጠው ስቀምር የማድር እንደነበርኩ እኔን ካልሆነ አይገባውም !!

ዛሬ ሁኔታሽ አንቺነትሽ ሁሉ ትርጉም ሰጠኝ አብረን እንሁን አለኝ ። ዘግይቶ ነበር Timing is every thing

እንደማይሆን እያወኩ ፍላጎት እንዳለኝ ምልክት ሰጥቼ አልበድለውም !!

" አልችልም" አልኩት

ቁርጣችንን አልነግር እያሉ እንደሚበድሉን መሆን አልፈለኩም ተፈላጊ የመሆኔን እርሃብ ለማስታገስ ወለም ዘለም እያልኩ አልበድለውም

በትህትና " አልችልም ሌላ የህወት መንገድ ላይ ነኝ " አልኩት ። እየመከርኩ አልተመፃደኩም ። መልካሙን ሁሉ እንዲገጥመው ግን በልቤ ተመኝቼለታለሁ ።

ትክክለኛ ነገር ትክክለኛ የሚያደርገው timing ነው !
timing is every thing እንዲሉ አበው!!

By Adhanom Mitiku

@wegoch
@wegoch
@paappii
አልዋሸሁም

==============

22 ማዞሪያ፡፡

መንገዱ በሰው ተወሯል፡፡

ለታክሲ በተሰለፉ መአት ሰዎች፣ ከጣሪያ በላይ እየጮሁ ይሄንንም ያንንም በሚሸጡ ነጋዴዎች፣ አጎንብሰው ከነጋዴዎቹ ጋር በሚከራከሩ ገዢዎች፣ በሁሉም አቅጣጫ በቀስታ፣ ቶሎ ቶሎ በሚራመዱ እግረኞች፡፡ ቆመው ስልክ በሚያወሩ ሰዎች፡፡

እኔስ ምን እያደረግሁ ነው?

እየሮጥኩ ነው፡፡ በፍጥነት፡፡ ጠና ካለች ሴትዮ ነጥቄ የያዝሁትን ቅንጡ ቦርሳ በቀኝ እጄ ደረቴ ላይ አጣብቄ ይዤ በግራ እጄ አየሩን እየቀዘፍኩ እሮጣለሁ፡፡

ሁኔታዋ ደህና ብር እንደያዘች ነግሮኛል፡፡

ልክ ኦሎምፒክ ላይ ቀነኒሳ የሐይሌን መቅረት ባለማመን አስሬ ወደ ኋላ እየተገላመጠ እንዳየው አንድ ሁለቴ ዞር ብዬ የተከተለኝ ሰው አለመኖሩን እያየሁ ነው የምሮጠው፡፡

ቦርሳዋን የነጠቅኳት ሴት እንጥሏ እስኪቃጠል እየጮኸች ነበር፡፡

አንድ ወጠምሻ እየተከተለኝ ነበር፡፡ በጎ አድራጎት መሆኑ ነው፡፡ እኔ የምለው…ሰዉ ግን ለምን የራሱን ኑሮ አይኖርም…? ምነው በየጎዳናው የበጎ ሰው ሽልማት ካልሸለማችሁኝ ባዩ በዛ፡፡ ሆ!

ዞር አልኩ፡፡
የለም፡፡
ኡፎይ፡፡

ወያላ ‹‹ፒያሳ በላዳ!›› እያለ ከሚጮህላቸው ተደርድረውና በር ከፍተው ከሚጠብቁ ላዳዎች አንዱ ጋር ስደርስ የሁዋላ ወንበሩ ላይ ገብቼ ዘ---ፍ እንዳልኩኝ እዛው አገኘኋት፡፡

ቦርሳዋን የወሰድኩባት ሴትዮ አይደለችም፡፡ የፊዚክስ ህግ እዚህ ቀድማኝ እንድትገኝ አይፈቅድላትም፡፡

ግን እሷ ብትሆን ይሻለኝ ነበር፡፡

ሳሮን ነበረች፡፡ ሳሮን ገላልቻ፡፡ የሃይስኩል ጓደኛዬ፡፡ የሃይስኩል ፎንቃዬ፡፡ ከአስር ዐመት በላይ ያላየኋት፣ ዛሬም በሚያፈዝ ሁኔታ የምታምረው ሳሮን፡፡

በቁልቢው! ካልጠፋ ቀን፣ ካልጠፋ ሰዐት፣ ካልጠፋ ቦታ ዛሬ፣ እዚህ፣ እንዲህ ላግኛት?

የሰረቅኩትን ቦርሳ ኪሴ ውስጥ አጣጥፌ አስቀምጬው የነበረ ጥቁርና ከውጪ የማያሳይ ፌስታል ውስጥ በፍጥነት ጎሰርኩና ፊት ለፊት ገጠምኳት፡፡

ሳቀች፡፡

‹‹ኤርሚዬ! እውነት አንተ ነህ?›› ብላ አቀፈችኝ፡፡
ስታምር፡፡ መአዛዋ ሲጥም፡፡
አዬ መከራዬ!

ደማቅና ሞቅ ያለ ሰላምታ ተለዋውጠንና ላዳው ሞልቶ መንገድ ስንጀምር ዛሬ ስላለንበት ሁኔታ ማውራት ጀመርን፡፡

‹‹እሺ…ሳሮንዬ እንደተመኘሽው አሪፍ ዶክተር ሆንሽ…?›› አልኳት ፌስታሉን ጠበቅ አድርጌ እየያዝኩ፡፡

በጣም እንዳላበኝ ያስተዋለች አትመስልም፡፡ ምናልባት ከረጅም ጊዜ በኋላ በድንገት በመገናኘታችን የደነገጥኩት መስሏት ይሆናል፡፡

‹‹ሃሃ…አዎ…ጎንደር ዩኒቨርስቲ ህክምና ተምሬ ዶክተር ሆኜልሃለሁ›› አለች ያንን የሚያምር ፈገግታዋን ይበልጥ አድምቃ፡፡

ሆኜልሃለሁ፡፡ ግራ እጇን የጋብቻ ወይ የቃልኪዳን ቀለበት ለማግኘት በአይኖቼ ፈተሸኩ፡፡

ባዶ፡፡
ልቤ ቀለጠ፡፡ የባሰ አላበኝ፡፡

ሹፌሩ ጋቢና የተቀመጠውን ተሳፋሪ ሂሳብ ሰብሳቢ አድርጎ እንደሾመ ቶሎ ብዬ ብር አወጣሁና የእሷንም ከፈልኩ፡፡ ሳትግደረደር ፈገግታዋን ለገሰችኝ፡፡

መልስ ተቀብዬ አየት አደረግኋትና ልክ እንደእሷ ፈገግ ለማለት እየጣርኩ፣

‹‹ጠብቄ ነበር፡፡ ትዝ ይለኛል ባይሎጂ ላብ ስንገባ እነዚያን ምስኪን እንቁራሪቶች እየሳቅሽ ስትሰነጣጥቂያቸው፡፡ ሌሎቻችን ላለማስመለስ ስንታገል አንቺ ግን ደስ ይልሽ ነበር …›› አልኩ፡፡

በጣም ሳቀችና ‹‹አንተስ ኤርሚዬ? ሁሌ እንደምልህ ህግ አጠናህ አይደል?›› አለችኝ፡፡

ጥያቄዋ የጥፊ ያህል አመመኝ፡፡

እዚህ ላዳ ውስጥ ዘልዬ ከመግባቴ በፊት፣ እሷን ከማግኘቴ በፊት የተፈጠረው ነገር ሁሉ ልክ እኔ ሳልሆን ሌላ ሰው ሲያደርገው ቆሜ የታዘብኩ ይመስል ትእይንቱ በዐይኔ ላይ ዞረ፡፡

ይህቺ የልጅነት ህልምና ተስፋዬን የምታውቅ፣ ግን ደግሞ ያለፉት አስር አመታት እንዴት አድርገው ተስፋዬንም ህልሜን እንደቀሙት የማታውቅ ከድሮ ሕይወቴ በድንገት ተወንጭፋ የመጣች ልጅ ጥያቄዋ አሳመመኝ፡፡

ስሰርቅ ዛሬ የመጀመሪያዬ ሆኖ አይደለም፡፡

ስርቆትን መቁጠር እስካቆም፣ የጥፋተኝነት ስሜት ሽው እንኳን እስካይለኝ ለአመታት ሰልጥኜበታለሁ፡፡

አሁን ግን፣ ያኔ ማንም ሳያየኝ በፊት አይታኝ፣ ‹‹ኤርሚዬ አንተ ንግግርና ክርክር ላይ…ቋንቋ ላይ ጎበዝ ስለሆንክ አሪፍ ጠበቃ ወይ ዳኛ ይወጣሃል፡፡ ህግ ነው ማጥናት ያለብህ›› ካለችኝ ልጅ ጋር ተቀምጨ የሆንኩትን ነገር ሳስበው ሃፍረት ወረረኝ፡፡

ቢሆንም ፈገግ አልኩና ‹‹ አዎ…ህግ አካባቢ ነኝ›› አልኳት፡፡

መልሴን አጢኖ ለመረመረው አልዋሸኋትም፡፡

By Hiwot Emishaw

@wegoch
@wegoch
@paappii
የእኛ ሰፈር ስለት ርዕሱ ነው:-

አንዴ እንደማመጥ እንደማመጥ አሉ የሰፈሩ አድባር ሽማግሌ።ሁሉም የሰፈር ሰው ፀጥ አለ።
እህህ እህህ ያው በየ አመቱ እንደምናደርገው መጠጡ ተአቅማችን በላይ ሆኖ ታለ አቅማችን ከርሞ ማቅረብ የማንችለውን ስለት እንዳንሳል ይሄኔ ወደ ሞቅታ እየገባን እያለ በየተራ እየተነሳን ስለታችን እንሳል ወንዶች በጭብጨባ ሴቶች በእልልታ ቸር እንመኛለን።

እሺ ቀጥይ እሟሃይ አስረበብ:-

#እማሆይ:-የዛሬ አመት ሁላችንም ከቁጥር ሳንጎድል እንዲሁ እንዳለን በሰላም ከደረስነ አስር እንጀራ

እልልል ጨብጨብጨብ

አጉረምራሚው ጀማ:-አይ እሟሃይ አልሳልም አይሉም እንዴ ከቁጥር ሳንጎድል የሚሉ አሁን በለጠ ሊከርም ነው ኤዲሱና ትቪው እያጣደፈው እስከ ተሳስም በባጄ

ቀጥል አቶ አስማማው።

#አስማማው:-የዛሬ አመት ጦርነቱ አቁሞ የሰላም አየር ከተነፈስነ ሁለት ካሳ ቢራ

እልልል ጨብጨብጨብ

አጉረምራሚው ጀማ:-ልጁ ሚኒሻ ስለሆነ ነው እንጂ አሁን አስሜ የአገሩ ሰላም አሳስቦት አሄሄ ስለቱ ቢደርስስ የሁለት ካሳ ቢራ የት ሊያገኝ ነው ቂቂቂ የአረቄ እዳ አለበት እያለች አስካለ ስትፈልገው አደል የምትውል ክክክ

ወዘሮ ብርቄ ቀጥይ:-
#ብርቄ:-አዲሳባ ያለችው ልጄ ቤቷ እስከ ከርሞ ካልፈረሰ አንድ ዶሮ

እልልል ጨብጨብጨብ

አጉረምራሚው ጀማ:-ያቺ እንግዳ ሲሄድባት ፊቷ የማይፈታው ናት?አይደለም የእሷማ ፈርሶባት አረብሀገር ሄዳለይ አሉ የትንሽቱን ነው እንጂ

አቶ ዘነበ ቀጥል:-
#ዘነበ:-ጅማ ያለው ልጄ እስከ ዛሬ አመት ወረሞ ከሆነ አንድ ጠቦት በግ አስገባለሁ

እልልል ጨብጨብጨብ

አጉረምራሚው ጀማ:-አቶ ዘነበ ደሞ ወጉ ሁሉ ግራ ነው ባለፈው መጥቶ እያለ ሀጠራው አካምጅርታ እያለ አልነበር ተያ በላይማ ከወረመ ይኦንግበታል ኪኪኪ ኧረ እንዳይሰማ ቀስ በሉ

ቀጥል ልጅ ኩራባቸው:-

#ኩራ:-የዛሬ አመት ከመካከላችን ስድስት ሰው ብቻ ከሞ ተ አንድ በግና አራት ካሳ ቢራ

የሰፈሩ ሰው:- ኤድያ እንደው ይሄ ደግሞ አንድ ቀን ከአፉ ደና ነገር ሳይወጣው እንዲህ እንዳለ አረጀ

ምኑ ሟርተኛ ነው በእንድማጣው

እናቱ በአራስነቱ ጥላው ወጥታ ነው አሉ እንዲህ ቡኖ የቀረ

አይ ኩራ አረቄ ከቀመሰ በቃ አፉ ድሮን ነው ጥሩ ነገር አይወጣውም

ቆይ እንጂ ልጁን ውሻ አታርጉት እውነቱን ነውኮ

ሲጀመር አምና የተሳለውን ሳያመጣ ለምን እድል ሰጣችሁት አስወጡት

ሂድ ተኛ ሂድ ተኛ አስወጡት ይሄንን ጅል


By Koan AD


@wegoch
@wegoch
@paappii
ነገረ ጠንቋይ. . .

ባልና ሚስት ሶስት ልጆች ወለዱ። ሶስቱም ባልጩት የመሰሉ ጥቁር ነበሩ። ቢቸግራቸው መፍትሔ ፍለጋ ጠንቋይ ቤት ሄዱና ችግራቸውን ነገሩ። ቀይ ልጅ መውለድ ነው ፍላጎታችን አሉት።

ጠንቋዩም "አክራብ አክራብ ኩርማንኩር ወዘተመረ ለቀጨነ" አለና "የምላችሁን ካደረጋችሁ ቀይ ልጅ ለመውለድ ቀላል ነው የናንተ መፍትሔው" አላቸው። "ምን እናድርግ?" አሉት።

"ይኸውላችሁ፣ ስትዳከሉ አቶ ባል የቸንቸሎህን ጫፍ ጫፉን ብቻ አስገባ። ከዚያ የሚወለደው ልጅ ቀይ ነው የሚሆነው" አለ አቶ ጠንቋይ። ባልና ሚስት አመስግነው፣ እጅ ስመውና ከፍለው ወደቤታቸው ሄዱ።

ማታ ላይ ስራ ተጀመረ። ባል በታዘዘው መሠረት በጫፍ በጫፉ 🙈 መደከል ጀመረ! (ቱ! ለኔ)

ሚስት በመሀል "ውዴ!" አለች

ባል "ወዬ!"

ሚስት "ልጁን ትንሽ ብናጠይመውስ?"

ባል 😊😊 ግማሽ ግማሹን ሰደደ (🙈🙈🙈)

ከደቂቃ በኋላ ሚስት አሁንም "ማሬ!"

ባል "ወዬ!"

ሚስት "እኔ የምልህ. . . ልጅ አይደለ? ቢጠቁር ምን ይሆናል?"

* * *

By Gemechu merera fana


@wegoch
@wegoch
@paappii
Forwarded from ግጥም ብቻ 📘 (Leul Mekonnen)
እናንተ የምወድዳችኹ ፤
ስነ-ፅሁፍን የምትወድዱ ፤
የግጥም ነፍስ ያላችኹ ፤
ወንድሞቼ ፤ እህቶቼ ፤ ወዳጆቼ ፤ ታላላቆቼ እና በደስታዬ ደስ የሚላችኹ የዘመን ተጋሪዎቼ ኹሉ ፤ ይቺን የመጀመሪያ ስራዬን ቅድሚያ ገዝታችሁ ፤ ከጓዳ ወደ አደባባይ እንድትሸኙልኝ ስል ፤ የተወደደ የወዳጅነት ግብዣዬን እጋብዛችዃለሁ ።

ከወዲኹ ...
እጅግ እጅግ አመሰግናችዃለሁኝ
ኑሩልኝ !
ቴዎድሮስ ካሳ

____

የመፅሐፍ ቅድመ ሽያጭ ማስታወቂያ
Reserve yours now—it's on pre-order!

ርዕስ /Title - የዱር አበባ / Wild Flower
ዘርፍ / Genres - ስነ-ግጥም /Poetry
ዋጋ/ price - 300 ብር/ birr

የባንክ ቁጥር / Bank Accounts :
ቴዎድሮስ ካሳው አስረሴ
Tewodros Kassaw Asresse
ንግድ ባንክ / CBE - 1000360039847 ወይም 1000292025185 (ናትናኤል እሸቱ)
አዋሽ ባንክ /Awash Bank - 01320885596200
ሲቢኢ ብር / CBE Birr - 0972338625
ቴሌብር/ Tellebirr - 0972338625

[ ማሳሰብያ : ዃላ ለማስታወሻ ይረዳኝ ዘንድ Screenshot አንስታችሁ በውስጥ በሜሴንጀሬ አልያም በቴሌግራም አድራሻዬ @Poet_tedi መላኩን እንዳትረሱት ይሁን ።]
ይኸውልህ ሉሌ ፤ ለአንዳንድ ስራዎች ውሏችንም አመሻሻችንም ሃያ ሁለትና አከባቢው ነው። የኔ ጎደኛም(ባለ ታሪኩ ማለት ነው) አውራሪስ አከባቢ ትልቅ የግል ድርጅት አለው። እንደነገርኩህ ሃያ ሁለት በምንውልበት ሰዐት ብዙውን ስራችን በስልክ እየተደዋወልን ስለምንሰራው፣ የሆነች ድራፍትም ይሁን ቢራ የሚሸጥበት ቤት ገብተን ምሳችን በልተን እየጠጣን ውለን ነበር ምናመሸው።

አንድ ቀን በአዲሱ አስፖልት አከባቢ የሆነች አዲስ ቤት አግኝተን እዛው ስንጫወት ውለን አመሸን። ባለቤቲቷ በጣም ጥሩ ጨዋና ስርዓት ያላት ሴት ነበረች። እቤቱ ውስጥ ምታስተናግድና ሂሳብ ምትሰራ ልጅም ነበረች። የታላቅ ወንድሟ ልጅ እንደሆነችና እሷ እንዳሳደገቻት አወራችን። ያስተናገደችን ልጅ ውበቷ ልዩ ነው ፤ ትከየፍባታለህ ። ጓደኛየም ልጅቷን ደስ ብላው ስለ ነበር እየተመላለስን በቃ በዛው ከስተመር ሆንና ፤ ተዛመድን። በሂደትም ከልጅቷ ጋር ክንፍ ያለ ፍቅር ውስጥ ወደቁ። (በነገራችን ላይ ጓደኛየ ባለ ትዳር ነው።)

ከልጅቷ ጋር በፍቅር ላይ እያሉ ለሁለት አመት ግዜ ያህል ከአገር የሚያስወጣ ጉዳይ (በጦርነቱ ግዜ ትግሬ ሲሳደድ ግዜ) ይገጥመውና እስከ ሙሉ ቤተሰቡ ካናዳ ይከርማል። እኛ ጓደኞቹም የምንሰራው ስራ ብዙ ግዜ የሱ ስለነበረ እሱ ከተለየን ቡሃላ መገናኘታችን እየቀዘቀዘ ወደ ሃያ ሁለት የሚያስኬደን ጉዳይም ብዙ ስላልነበር ጀምዓው ተበተነ።

ከሁለት አመት ቡሃላ ፤ ነገር ሲረግብ ፥ ፍሬንድ ሚስትና ልጁን እዛው ትቶ ተመልሶ መጣ። ጀምዓውም እንደገና መሰባሰብ ጀመረ ። አንድ ቅዳሜ ተደዋውለን ምሳ እንብላ እንባባልና አሹ ስጋ ቤት እንሰባሰባለን። እዛው ስንጫወት ዋልን። በግምት ከምሽቱ ሁለት ሰአት አከባቢ ሲሆን መበታተን ጀመርን።ከአሹ እየወጣን እያለ 'ጓደኛየ ምናወራው ነገር ስላለ ግማሽ መንገድ ልሸኝህና ከዛ RIDE ትይዛለህ' ብሎኝ እሱ መኪና ውስጥ ገባሁ።

በጉዞ ላይ አትላስ መብራት ልንደርስ ስንል በተቃራኒው መንገድ Street ላይ የሆነች ልጅ አይቶ ዳር ይዞ "ቲና" እያለ ይጣራል። ልጅቷም ተሻግራ ስትመጣ ያቺ ከሁለት አመት በፊት በፍቅር ክንፍ ያለላት አስተናጋጅ ልጅ ነበረች።( የመጣ ሰሞን ሲፈልጋት ነበር፣ አጋጣሚ የነበረችበት ቤት ሄደን ሌሎች አዳዲስ ሰዎች ናቸው የሚሰሩበት) እኔም ወርጄ አቅፌ ሰላም አልኳት። ወደ መኪናው ግቢ አላት። ገባች።

መኪናውን ከአትላስ ወደ መድሃኔአለም አቅጣጫ እያሽከረከረ ይዞን ሄደ። (ልጅቷ በወቅቱ የStreet ስራ ጀምራ ነበር። የዚ ታሪክ ረጅም ነው ፤ ይቅርብህ )። በቃ ፥ በዚህ አጋጣሚ ጨዋታውን አስቀጥለነው እናመሻለን አለን። እኔና ቲናም በሃሳቡ ተስማምተንና ግብዣውን ተቀብለን ሶስታችን አንድ ላይ አልኮል ስንጠጣ አመሸን። የለሊቱ ከሰዐት አከባቢ ስለደከመኝ ወደቤት ልግባ ብየ RIDE ጠራሁ። ሁለቱም ተያይዘው የነበርንበት አካባቢ Room ይዘው አደሩ።

ከዛ ቡሃላ በተደጋጋሚ የተለያዩ ጊዚያቶች እኔ ባልኖርም እዛች አትላስ ያገኘናት አከባቢ ሄዶ ፒክ ያረጋትና አብረው አምሽተው ያድራሉ። የሆነ ግዜ ግን በተደጋጋሚ ቢሄድም ሊያገኛት አልቻለም። የሚገርምህ ፤ ስልኳ አልነበረውም ፤ እዚህ ስትመጣ ታገኘኛለህ ነበር መልሷ እሱ እንደነገረኝ)

የዚህ ሁሉ ታሪክ አስገራሚውም አስደንጋጩም ነገር የሚፈጠረው እዚህ ላይ ነው።ያቺ ሚስኪን ጨዋ ትሁት የሬስቱራንቱ ባለቤት ፣ የልጅቱ አክስት የነበረችው ሴት ጉርድሾላ Century Mall ለሆነ ስራ ጓደኛየጋ ሄደን በሩ አካባቢ አገኘናት። ትንሽ ጉስቁልቁል ብላለች ወዟም ጠፍቷል። ሰላምታ በደንብ ከተለዋወጥን ቡሃላ ...

"ምነው ታመሽ ነበር እንዴ?"አልኳት

"እረ ደህና ነኝ። ከወንድሜ ልጅ ሞት ቡሃላ ልክ አደለሁም። አጋዤን፣ ያሳደግኳት ልጄን ካጣኋት ቡሃላ መኖር ሁሉ አስጠላኝ ወይኔ ቲናየ" ብላ እምባዋን ታዘራው ጀመር።

"እንዴ ቲና ምን ሆነች? መቼ? ምናምን እያልን መንተባተብ ስንጀምር ...

"ኣጣኋት ። መኪና በላብኝ። አንተ ውጭ ልትሄድ ከተሰናበትከን ቡኋላ በሶስተኛው ወሩ አካባቢ ቦሌ ርዋንዳጋ ልጄ መኪና በላት" ብላ አምርራ ለቅሶውን አቀለጠችው። የዛኔ ድብልቅልቅ አለብኝ። ታድያ ከውጭ ከመጣ ቡሃላ ያገኘናት ማናት????????????!!!

እንደምንም ብየ ሊፈነዳ ያለውን ጭንቅላቴን አረጋግቸ ፤ እሷን መጠየቅ ጀመርኩ ። መች አደጋ እንደደረሰባት? የፖሊስ ምርመራ ሪፖርት መኖሩና አለመኖሩ?የሆስፒታል የሞት ሰርተፊኬት? የት እንደተቀበረች? የመሳሰሉት ግራ እየተጋባችም ቢሆን ጠየቅናት። ሰኀሊተ ምህረት እንደተቀበረች፤ ኧረ ያንን ቀን ወስዳ መቃብሯ ሁሉ አሳየችኝ።

ታድያ ጓደኛየ ከካናዳ ከተመለሰ ቡሃላ ያቺ በተደጋጋሚ ስትገናኘው የነበረችውና አሁን የተሰወረችው 'ቲና' ማናት??? Right now, my friend is not normal, ሉሌ. He already got insane. አልኮል ውስጥ እራሱ ደብቋል ።

ለልዕል ተወልደ የተላከ

@wegoch
@wegoch
@paappii
Gize Wegoch, [Oct 21, 2024 at 8:57 PM]
አይጠሩ
...........

   በአማት መወደድ ለጥቂት ዕድለኛ ኢትዮጵያውያን ብቻ የተሰጠ ፀጋ ይመስለኛል።በተለይ ደግሞ በቁመት የምትበልጥህን ሴት ልታገባ እየተዘጋጀህ ከሆነ!ነፍሳቸውን ይማርና ጎረቤታችን አብዬ በላቸው
"ፍቅር ምን ድረስ ክፉ ነው?"ተብለው ሲጠየቁ
"እኔና ሰዋለምን እስቲያጋባን ድረስ" ይሉ ነበረ አብረው ሲቆሙ በጡታቸው ትክክል የሚሆኑትን ሚስታቸውን እያሰቡ።የሞቱት አብሯቸው የኖረው አስም በሌሊት አፍኗቸው ነው ቢባልም የመንደራችን 'ፓፓራዚዎች' እንደሚሉት ከሆነ ግን ለሞት ያበቃቸው አስሙ ብቻ ሳይሆን በባለቤታቸው ጡቶች መሃል አፍንጫቸው መታፈኑ ነበር።
እሰቡት 1.50 ሆኜ 1.75 የምትረዝም እጮኛ ስይዝ! አብዬ በላቸው ከነሚስታቸው ድቅን ይሉብኛል። ከመጋባታችን አንድ ወር አስቀድማ ከቤተሰቦቿ ጋር አስተዋወቀችኝ።ያደገችው ከአሽሙረኛ እናቷና ከጉልቤው ወንድሟ ጋር ነው።ውበቷን ያየ የእናቷን ወግ አጥባቂነት እና የወንድሟን ኃይለኝነት መገመት አያቅተውም።ልታስተዋውቀኝ ቤቷ የወሰደችኝ ቀን እናቷ እትየ ዘውዴ ከእግር እስከራሴ አልቢን በሚያስንቅ አይናቸው እንደሽንኩርት ከላጡኝ በኋላ የሚያበሽቅ ሳቃቸውን አስከትለው
"እንዴት ያለ ኮረሪማ አግኝተሻል ሚጡ!ና እስቲ ሳመኝ"ብለው ሱባኤ እንደገባ ገዳምተኛ ወገባቸዉን በነጠላቸዉ አሰሩና ከምድር ወገብ የሚሰፋ ሽክርክሪት መቀነታቸዉን እየቋጩ ጎንበስ አሉ። መና እንደወረደለት ሰዉ ወደ ላይ ቀና  ስል ከመቅፅበት ትከሻዬን እንደቅቤ ቅል እየናጡ አገላብጠው ሳሙኝ።ልጃቸው በሷ እንደወጣች ቁመታቸው ይናገራል።ከፊት ለፊታቸው ስቆም ከአይናቸው ይልቅ ከጡታቸው ጋር ነው የምፋጠጠው።ጃንሆይም እንደሳቸው ጡት መውደቃቸውን እጠራጠራለሁ።እንኳን የሳቸው ጡት ሁለት ልጅ የጠባው ይህች ጉደኛ ሀገር ራሷ ደርግ አይጥ እንደቀመሰው ካልሲ ቦትርፏት፣ኢህአዴግ እንደ ገና ዳቦ በላይ በታች አንድዷት፣የአሁኑ ጉድ በወሬ ፓትራ እስከጥግ ነፋፍቷት...የሳቸውን ጡት ያህል ዝቅ አላለችም።

  ሳሎናቸው ግድግዳ ላይ የተሰቀለውን የቤተሰብ ፎቶ ሳይ "አቤት ግጣም በልክ ሲገኝ!" አሰኘኝ።ባለቤታቸው ከእሳቸው የበለጡ ብቅል አውራጅ ቢጤ ናቸው።ወንዱ ልጃቸው ከሚጡ ትንሽ ይረዝማል።ደፍሬ ሳሎናቸውን የረገጥኩ የመጀመሪያው ስንዝሮ እኔ ሳልሆን አልቀርም።

ወደ ምግብ ጠረጴዛው ስናዘግም አሽሙር የተካነ አፋቸውን አሸራመው እየቃኙኝ
"ሶፋው ላይ እንሁን መሰል ጠረጴዛው አለቅጥ ረጅም ነው" አሉኝ።ጠረጴዛው የረዘመብኝ እንደሁ ሌላ ዝርጠጣ ስለሚከተለኝ ጥያቄአቸውን ተቀብዬ ወደ ሶፋው አመራን።ከመቀመጣችን ሌላ ብቅል አውራጅ ባልቴት እየተንጎማለሉ ዘለቁ።ሚጡ ወደ ጆሮዬ ጠጋ ብላ
"አክስቴ ናት ኃይልሻ" አለችኝ።
እትየ ዘውዴ
"ህብስቴ መጣሽ?ቀረሽ ብየ ነበር'ኮ እመዋ" አሉና አገላብጠው ከሳሟቸዉ በኋላ አቆልቁለው እያዩኝ
"ነይ ሳሚው የሚጡን ባል...እየውልሽ እንዴት ያለውን ምጥን የወንድ አውራ እንዳመጣችው"
"ኧግ!የቢያዝኔ ምትክ...እምጷ...የአባቷ ምትክ...እምጷ...የት አገኘሃት?... እምጷ ይችን መለሎ...እምጷ"
የሞት ሞቴን  ፈገግ ብዬ ከመቀመጤ በእህታቸው እግር ተተክተው ይወጉኝ ገቡ።
"ዋዋዋዋዋ...እንደው ከየት አገኘሃት?ማነበር ያልከኝ ስምህን"

"ኃይሌ"
"ምንድን ነዉ ስራህ?"
 'ገጣሚ ነኝ' ልላቸው ፈለኩና የዘመኔ ገጣምያን  በህሊናየ ድቅን አሉብኝ።
በእዉቄ እንኳን ቁመቱ ጊዜ ጠብቆ የሚጨምረዉ ግጥም ወይም ወግ ሲያነብ ብቻ ነዉ። ምክንያቱም ተመልካቹ ሁሉ ተቀምጦ ስለሚያዳምጠው።
ብዙዎችን በአይምሮዬ ማሰላሰል ስጀምር ገጣሚነቴ ተኖ ጠፍብኝ ።
"ምን አልከኝ ?"ሲሉኝ
"እ የዩኒቨርሲቲ መምህር ነኝ" አልኳቸዉ በደባልነት የያዝኩትን ሙያዬን።
"እ...መምህርነት ሸጋ ነው!...እና ከየት አገኘሃት በል ይችን መለሎ?"
"እህ...ህ...ህ...ትውውቃችን እንኳን ከድሮም ነው...ከትምህርት ቤት"
"ኧረግ ኧረግ ኧረግ ኧረግ!!...መቸም ተፊት ተቀምጣ እየከለለችህ አስቸግራህ ነው እሚሆን...እሂ...ሂ...ሂ...ሂ"
'ጥርስዎት ለሙቅ አይትረፍ!ድዳም'

"ኧረ በነገር አትያዣቸው ህብስቴ ምሳው ይቅረብ" አሉና አማቴ ሰፋ ባለ ትሪ ዶሮ ወጣቸውን በአይብ አጅበው አቀረቡት።
'ሰው ከረዘመ ሞኝነት አያጣውም' የሚለው አባባል እዚህ ቤት አይሰራም።እንደውሃ ሙላት እያሳሳቁ መግደልን ተክነውበታል።

ህይወቴ በረጃጅም ሴቶች ዙሪያ እንዲሽከረከር ማን እንደፈረደብኝ ባላውቅም 8ኛ ክፍል እያለን በደብዳቤ የጠየቅኋት መለሎዋ ማህሌት ራሱ  ደብዳቤውን ለስም ጠሪ ሰጥታ ተማሪዎች ፊት ከማስነበብ የከፋ አልጨከነችብኝም። የልብ ስእል ለመሳል የቀደድኩትን ወረቀት እናቴ ሰብስባ ሶስት እንጀራ ከነ ካሲናዉ እንዳወጣችበት ሳስታዉሰዉ ይደንቀኛል።
በጦር ተወግቶ ለሚደማው ልቤ ማሳያ ይሆነኝ ዘንድ አባቴ በፀሀፊነት ከሚያገለግልበት የሰፈሩ እድር የተቀበለውን ብቸኛ ቀይ እስኪብሪቶ በማገንፈሌ አንድ ፌርሜሎ ከሰል ተቀጣጥሎ ለሳምንት ወጥ መስሪያ የሚሆን በርበሬ ታጥኜ ነበር።ይህን ሁሉ መስዋዕትነት ከፍዬ
"ያም አለ ያም አለ የአተር ገለባ ነው
ሰው ይዋደድ እንጅ ቁመት ለአገዳ ነው" ብዬ መጻፌን ሳስታውስ እንደቂል በራሴ እስቃለሁ።

  ዶሮው ተበልቶ ሲያበቃ ያመጣሁት ውስኪ ተከፈተና አንድ ሁለት እያልን ጨዋታ ቀጠልን።በመሃል አማቴ ግድግዳ ላይ የተሰቀለውን የባለቤታቸውን ፎቶ አዩና አንደ መሳቅም እንደማልቀስም እያደረጋቸው

"አየ....የ...የ...ቢያዝኔ ዛሬ ነው  የሞትክ!አየ የኔ ጠምበለል!"ወዲያው ወደ ሚጡ ዞረው
"አይደለም እንዴ አንች?ዛሬ አይደለሞይ የሞተው?እንዲህ አለምሽን ሳያይ...አይ ቢያዝኔ!" ብለው በተቀመጥኩበት ከአፈር የሚደባልቅ አስተያየት አከሉልኝ።

የቁመቴን ማጠር የኪሴ መወፈር አካካሰው እንጂ እናትየው የዛኑ ቀን ከኔ በሚረዝም በቡሀቃ ማማሰያቸው እያጠደፉ ቢያባርሩኝ እንዴት ደስ ባላቸው!ባስተዋወቀችን በሳምንቱ የኔዋ ጉድ ከሰርጉ በኋላ የምንገባበትን ቤት እናቴ ካላየችው ብላ እየጎተተች አመጣቻቸው።ሳሎኑን በገረፍታ አዩና ምኝታ ቤት ዘው ብለው ገቡ።አልጋው ላይ አፍጥጠው
"ምነው እንዲህ ሰፋ?በራይ ልትወጡበት ነው?ባይሆን ቁመቱን ጨምሩት!" አሉ።የልጃቸውን ቁመት ያህል በእግዚሀሩ እንኳን መመካታቸውን እንጃ!

  ሰርጉ ሳይሰረግ እንዲህ የቋንጃ እከክ የሆኑብኝ ከተሰረገ ወዲያ ሊኖረኝ የሚችለውን ህይወት ሳስበው ሚጡን ማውራት እንዳለብኝ ተሰማኝ።
"እትየ ዘውዴ ከሰርጉ በኋላ ለበዓል ካልሆነ እንዲመጡ አልፈልግም!"አልኩ ምርር ብዬ

"ምን ማለትህ ነው ኃይልሻ?እናቴ'ኮ ናት!"

"ለኔ ደግሞ አማቴ ናቸው!የማይወዱኝ አማቴ!ጣልቃ ገብነትም'ኮ ልክ አለው።አንቺ ለምታገቢኝ የሳቸው አቃቂር አውጭነት ምን ይሉታል?"

"ኢሂ...ሂ...ሂሂሂ...እማዬ'ኮ ተጫዋች ስለሆነች ነው...ደግሞም የምትወደው ሰው ላይ ነው የምትቀልደው...አትቀየማት"ብላ በጥርሷ አዘናጋችኝ።

ሰርጉ 3 ቀን ሲቀረው ለንቦጯን ጥላ መጣች።
"ምን ሆነሽ ነው?" ዝም

"አንቺ ሚጡ ምን ሆነሽ ነው?" ዝም

"አትናገሪም እንዴ?"

"ከእማዬ ጋር ተጣላን"ብላ ለንቦጯን ይብስ ዘረጋችው።

"በምን?ምን ተፈጠረ?"

የስልኳን ፎቶ ማከማቻ ከፍታ አንድ ሂል ጫማ አሳየችኝና
"ይሄን ጫማ ለሰርጌ አደርገዋለሁ ብዬ የዛሬ ወር ነው የገዛሁት።ትናንትና ማታ አይታው 'የዘውዴ መቃብር ሳይማስ ይኸን ለብሰሽ አትሞሸሪም!' " አለችኝ።
Gize Wegoch, [Oct 21, 2024 at 8:57 PM]
'ለምን' ብዬ ልጠይቅ ከማሰፍሰፌ ምክንያታቸው ተገለጠልኝና አስችለኝ ብዬ
"ታዲያ ከሳቸው ደስታ የሚበልጥ ምን አለ ሚጡዬ?በቃ የመረጡልሽን አድርጊ እናትሽ አይደሉ?" ብዬ አባበልኳትና አቅፌአት የጨጓራዬን ጭስ ወደ ባዶው አየር ለቀቅሁት።

የመሞሸሪያችን ቀን እሳቸውን የቻለ ትዕግስቴን ጎረቤቶቻቸውና ወዳጆቻቸው ሲፈታተኑት ዋሉ።እዮብም እንዲህ መፈተኑን እንጃ!ታላቅ ወንድሟ ካሳሁን ጓደኞቹን ሰብስቦ ሰርጌን የጀማሪ ክብደት አንሺ የቅርፅ ዉድድር አስመሰሉት።   በሌባ ጣቱ መሬቱን እየጠቆመ
"ሎ...ሎጋው  ሽቦ...ቦ" ሲል
"ኧረ የምን ሎጋው ሽቦ?እስቲ ሌላ ትከሻ እሚፈትን ዘፈን አምጡ"አሉ  ጎረቤታቸው እትየ አስካል።የቀለም ትምህርቱም ሆነ ህይወት ራሷ ባስተማረችኝ ልፈታው ያልቻልኩት ትልቁ እንቆቅልሽ ሴት ስታርጥ ለምን አሽሙረኛ እንደምትሆን ነው።አዛውንቱን ቀርቶ ወጣቱን የሚያስት ጥርሳቸውን ብልጭ እያደረጉ ያቀነቅኑ ገቡ።
አንች የኔ አበባ ነሽ የኔ አበባ...
አንች የኔ አበባ ነሽ የኔ አበባ(ተቀባይ)
....
መላ ነው ነይ መላ
እነው መላ መላ(ተቀባይ)(2x)
የዘውድነሽን ልጅ ነይ መላ
እነው መላ መላ(ተቀባይ)
ወዴት አገኛት       "      "
አለ እናቷ ጓዳ      ''      "
መታያም የላት      "      "
የኔማ ዘውድነሽ       "        "
እጇ ያረፈበት           "        "
ለአልፎ ሂያጅ ይበቃል  "       "    
ማጠር አያውቅበት  "     "
እየው እየው መላ

አሉና ለ ሁለት ደቂቃ ያህል ትከሻቸው እስኪገነጠል ተንዘፍዝፈው ከከበባቸው ተቀባይ መሃል ወጡ።የሳቸውን መንዘፍዘፍ ተከትሎ አማቴ በኩርፊያ ተነፋፍተው ወደ ጓዳ እያቶሰቶሱ ሲገቡ ታዝቤ ነበር።
በነጋታው  የተከራየነዉን ቬሎ መልሰን በአማቴ ሰፈር በኩል አለፍን...ሰይጣን ሹክ ብሎን ነው መቼስ!እትየ ዘውዴ ቤት ስንደርስ በርከት ያለ ሰው ተሰብስቦ ስላየን  ጠጋ አልን።አማቴ እያማረሩ ለተሰበሰበው ህዝብ ስሞታ ያቀርባሉ።

"ምነው ነገር በኔ መግነኑ?አጭር አምቻ በኔ አልተጀመረ!ምነው ዘቢዳር በርጩማ እሚያህል አምቻ ስታመጣ ምን ተባለ?ደሞ ደግሸ ባበላሁ እኔ ላይ አሽሙር አስካል?እኔ ላይ?... ቁመት ቢረዝም ምን ሊረባ??በቁመት የጎዳውን በጠባይ ክሶት የለ?...እንደአንች አምቻ ነጋ ጠባ ከሚጎረጉጫት ኧረ የሽቶ ጠርሙስ አክሎ መኖር በስንት ጣዕሙ?..."እያሉ የጥያቄ ናዳ ሲያዥጎደጉዱ እትየ ዘቢዳር የተሰበሰበውን ሰው እየገፈታተሩ እትየ ዘውዴ ላይ ደረሱ

"እከከከከከከ!ይች ናት ዘቢዳር!የማን አምቻ ነው በርጩማ አንች?የኔን አምቻ ነዋ ምሽቱ ብብትና ብብቱን ይዛ አልጋ ላይ እምታሰቅለው!አልሰማንም'ኮ አሉ...አልሰማንም...አሁን ማን ይሙት ከአንች አምቻ የሚወደለው እንቅፋት ሆኖ የሰው ጥፍር አይልጥም? " እያሉ ሲውረገረጉ
ሹልክ ብዬ ወጣሁና ከጥቂት እርምጃ በኋላ ያገኘኋቸውን አንድ የኔ ቢጤ አባት ሰላም ብዬ ጥያቄዬን አስከተልኩ።

"አባቴ እንደው መዘጋጃ ቤቱ በየት በኩል ይሆን?"
"ማን ሞቶ ነዉ?" ደንገጥ ብለው ጥያቄዬን በጥያቄ መለሱት።
ቃል አጠሮኝ ጉዞየን ቀጠልኩ።ለካ ፍታትና ቀብር ለሞተ ብቻ ነዉ።

ዘማርቆስ

@wegoch
@wegoch
@paappii
Forwarded from Studio Anaya (Ribka Sisay)
አዲስ አበባ የምትገኙ ብቻ ከትምህርት ጋር የተገናኙ ማስታወቂያዎችን ለመስራት ከ10-15 አመት ያሉ ሴት እና ወንድ ካስቶች እየመለመልን ስለሆነ 3 የተለያዩ ፎቶዎችን ወላጆች ከስልካቹ ጋር @Ribki30 ላይ ላኩልን።
እማማ አፀደ የሚባሉ ጎረቤት አሉን የእናቴ ጓደኛ ናቸው። እማማ አፀደ አመም አድርጓቸው ህመማቸው በባሰ ቁጥር እናቴን ጠሏት።

ይሰድቧታል ሌባ ናት ይላሉ።
መሰሪ ናት ይላሉ።
ልትገለኝ ትፈልጋለች ይላሉ።
መርዝ አበላቺኝ ይላሉ ። አትምጣብኝ ብለው ስሞታ ይናገራሉ ሌሊት እቤቴ ልትገባ ነበር ይላሉ ።

ሰው እንዳትመስላችሁ ይላሉ ። እናቴ ቤታቸው መሄድ አቆመች ።

ከቤት መውጣት እያቆሙ ግቢያቸው መዋል ጀመሩ ....

እናቴ እሷ መሆኗን አትንገሩ ብላ ፤ ምግብ ትልክላቸዋለች ። በእህታቸውን ልጅ ፤ ምን ጎደለ ጤናቸው እንዴት ነው እያለች ትሰልላቸዋለች...

ንዴት ሊገድለኝ ይደርሳል ። እቆጣታለሁ << ስምሽን እያጠፉሽ እየሰደቡሽ እየጠሉሽ አትተያቸውም ወይ?>> እላታለሁ!!

<<ጭንቅላታቸው እጢ ወጥቶባቸዋል እሱ ነው ትንሽ ቀየር ያደረጋቸው እንጂ ፤ እሳቸው እንኳን ሳልበድል ብበድላቸው እንኳን በክፉ አያነሱኝም>> ትለኛለች።

ምግብ ትልክላቸዋለች ። በእህታቸው ልጅ በኩል የሚያስፈልጋቸውን መድኃኒት መግዣ ከኛ ወስዳ ... ተበድራም ቢሆን ትገዛላቸዋለች ። እሳቸው ያቺ ምናምንቴ ፣ ድግምታም ያቺ ነጠላ እያሉ ጮክ ብለው እናቴን ሲሰድቧት ይውላሉ ።

ጠላኋቸው !!

አንድ ቀን ለምን ግን እንዲ ስምሽን እያጠፉ እየጠሉሽ እያልፈለጉሽ አልጠላሻቸውም? ብዬ እናቴን ጠየቅኋት።

<<ጓደኛዬ ናቸው! እዚህ ሰፈር ስመጣ እሳቸው ናቸው ያለመዱኝ ። እድር ያስገቡኝ ፥ የሌለኝን እቃ ያዋሱኝ ፥ የተቆረቆሩልኝ ፥ የአረሱኝ ፣የመከሩኝ...

እንዲህ አይባልም እያሉ መንገድ ያሳዩኝ እርሳቸው ናቸው ። ድንገት ታመው ነው የተቀየሩት ።ከሁሉም ጋር ነው መጣላት የጀመሩት እኔ ላይ ትንሽ ጠንከር አሉ እንጂ ...

በክፉ ግዜ እንኳን ወዳጅ ላይ ጠላት ላይ አይጨከንም!!

የጨዋ ሰው ልክ የሚታየው ሲጣሉት ነው ። በፍቅር ግዜ ሰው አይመዘንም ክፉ ግዜ ነው ሰው የሚያጠለው ....

አፀዱ እንዴት አይነት ጥሩ ሰው መሰሉህ ዛሬ ህመም ተጣብቷቸው እን'ጂ ። ስንት ቀን መሰለህ እጦት በሳቸው ሳብያ ከቤታችን የተባረረው ።
አፀደ ደግ 'ሩህሩህ ናቸው...

እናንተ ሳትወለዱ ማንም ሳይኖረኝ ነው ከኔ ጋር የነበሩት...

የአፀደ ውለታ አለብኝ !>>

By Adhanom Mitiku

@wegoch
@wegoch
@paappii
ያከሸፈቻቸው ያከሸፏት አገር!
(አሌክስ አብርሃም)

የ8ኛ ክፍል ተማሪወች እንደነበርን ነው። አንድ ቀን የሆነ አስተማሪ ቀረ። በዛ ክፍት ክፍለጊዜ ሁላችንም ደስ ያለንን ስንሰራ (አብዛሀኞቻችን ወሬና መንጫጫት) አንድ ምስጋናው? የሚባል የክፍላችን ልጅ ብላክቦርድ ላይ በወዳደቀ ቾክ ሁለት ሰወችን ሳለ። ስዕል ስላችሁ ይሄ ዝም ብሎ የልጅ ስዕል አይደለም፣ ባስታወስኩት ቁጥር የሚገርመኝ የግንባራቸው መስመር፣ ፊታቸው ላይ ያረፈው ጥላ ልብሳቸው ላይ ያለው ፓተርን ሳይቀር ፎቶ የሚመሳስሉ ፖርትሬቶች። ደግሞ የሳለው ምንም እያየ አልነበረም። እማሆይ ቴሬሳ ሁለት እጆቻቸውን እንደህንዶች ሰላምታ አገናኝተው ግንባራቸውን እንዳስነኩ እጃቸው መሀል መቁጠሪያ ተንጠልጥሎ፣ እንዲሁም ቀዳማዊ ሀይለስላሴ ከነንጉሳዊ ልብሳቸው። ወደጎን ዞር ብለው። ሁላችንም ተገረምን ተደነቅን። የስእሎቹ መጠን የእውነት ሰው ያክሉ ነበር።

ቀጣዮ ክላስ ጅኦግራፊ ነበር። ኮስታራው አስተማሪያችን ገባና ስዕሎቹን አየት አድርጎ "ማነው የሳለው?" አለ ። በአንድ አፍ "ምስጋናው" አልን በአድናቆት ጭምር። ራሱ ወደምስጋናው ወንበር ተራምዶ የያዘው ልምጭ ተሰባብሮ እስከሚያልቅ ቀጠቀጠው። እና በቁጣ "ይሄ የተከበረ የትምህርት ገበታ ነው ! ማንም እየተነሳ የሚሸናበት አይደለም ደደብ" ብሎ ደነፋ። ዳስተሩን አንስቶ አንዴ እጁን ሲያስወነጭፈው ሀይለስላሴን ለሁለት እማሆይ ቴሬሳን አናታቸውን ገመሳቸው። አጠፋፍቶ ማስተማሩን ቀጠለ። ምስጋናው ከዛ በኋላ እንኳን ሰሌዳ ላይ ወረቀት ላይ ሲስል አላስታውስም።

ብዙ ዓመታት አለፉ። አንድ ቀን አዲስ አበባ ፒያሳ መርከብ የምትባል ምግብ ቤት ምሳ በልተን ስንወጣ በር ላይ አንድ የጎዳና ተዳዳሪ በፌስታል ፍርፋሪ ሲበላ አየሁ ምስጋናው ነበር። ቢጎሳቆልም አልጠፋኝም። ዛሬ በምን አስታወስኩት? አንድ አሜሪካዊ ህፃን ሰሌዳ ላይ በቾክ የሳለው ስእል በአስተማሪዎቹና በትምህርት ቤቷ ርዕሰ መምህር ስለተደነቀ በቀስታ ሰሌዳውን አንስተው አንድ ቢሮ ግድግዳ ላይ እንደሰቀሉት አነበብኩ። ስዕሉ ለዓመታት እንዲቆይ የሆነ ነገር እናስደርጋለን ብላለች ርዕሰ መምህርቷ። አገር ባከበረቻቸው ትከብራለች ባከሸፈቻቸው ትከሽፋለች። ይህ ሒሳብ የገባቸው ብፁአን ናቸው። ለትውልድ ፍቅር ያወርሳሉና።

@wegoch
@wegoch
@paappii
Poem.ogg
2.1 MB
#yohabi ደብዳቤ
የማይድን ናፍቆት.... 'የተረሳው ክፍል'

"ስትሄድ ያልከኝን መርሳት አቅቶኛል"

@wegoch
@wegoch
@paappii
አልቃሽና አጫዋች
(በእውቀቱ ስዩም)

ቦጋለ በሚባል ስም የሚታወቁ ሁለት ስመጥር ሰዎችን አውቃለሁ፤ የመጀመርያው የ”ፍቅር እስከመቃብሩ” ገበሬ፥ ቦጋለ መብራቱ ነው፤ ሁለተኛው በገሀድ ኖሮ አልፏል፤ድሮ በጎጃም ሽማግሌዎች ክፉ ሰው ሲራግሙ፥ “ ቦጋለ ያይኔ አበባ ስምህን ይጥራው “ይሉ ነበር ይባላል፤

ቦጋለ ያይኔ አበባ ስመጥር አልቃሽ ነበር፤ የጥንት አልቃሾች ቀላል ሰው እንዳይመስሏችሁ፤ በለቅሶ ወቅት የሚታየውን ትርምስ እና ጫጫታ ወደ ኪነጥበብ ትርኢት የሚቀይሩበት ተሰጥኦ ነበራቸው ::

ቦጋለ ያይኔ አበባ በወጣትነቱ ያገሩን መሬት አርሷል፤ እንዲሁም ያገሩን መሬት በእግሩ አዳርሷል፤ ወደ አልቃሽነት ሙያ እስኪገባ ድረስ ግን የረባ ስኬት አላገኘም ነበር፤ ይህንን በማስመልከት፥ እንደ ግለ-ታሪክ እና Cv በምትቆጠርለት እንጉርጉሮው እንዲህ ብሎ ነበር፤

“አርሼም አየሁት ፥
ነግጄም አየሁት
አልሰሰመረም ሀብቴ
አልቅሼ እበላለሁ እንደ ልጅነቴ “

ቦጋለ ያይኔ አበባ ከዘመናት ባንዱ ወግ፥ ደርሶት ሴት ልጁን ዳረ፤ እንጀራ ሆኖት የቆየው ሞት አሁን በሌላ ገጹ ተከሰተ፤ ሙሽሪት በሰርጓ በሳምንቱ ተቀጠፈች፤ እልልታው ወደ እሪታ የተቀየረበት ቦጋለ በተሰበረ ልብ ይቺን ውብ እንጉርጉሮ ወረወረ፦

“እንዲህ ያለ አምቻ፥ ክብሩን የዘነጋ
በፈረስ ሰጥቼው ፥ መለሰልኝ ባልጋ”

ኪነጥበብ ፥ አስቀያሚ መከራን ወደ ውበት መቀየር እንደምትችል ይቺ እንጉርጉሮ ምስክር ናት፤

ከሞት ሁሉ ቅስም ሰባሪው የልጅ ሞት ይመስለኛል ፤ ከወሎ የፈለቀች ከወዳጄ የሰማሁዋት ፥አንድ ጨዋታ ትዝ ትለኛለች፤ አያ ሙሄ የተባለ ገበሬ ልጁ ሞቶበት ፥ጎጆው በርንዳ ላይ ከርትም ብሎ ይቆዝማል ፤ ባለንጀራው አዋ ይመር አጠገቡ ተቀምጧል፤ አዋ ይመር ወዳጁን በቃል ማጽናናት በቂ ሆኖ አላገኘውም ፤ የወዳጁን ልጅ የቀሰፈውን ፈጣሪ ለመበቀል ስለፈለገ ፥ ጠመንጃውን አነጣጥሮ ወደ ሰማይ ተኮሰ፤

ተኩሱ በረድ ሲል አዘንተኛው አያ ሙሄ ወዳጁን እያየ እንዲህ አለ፤

“ካገኘከው ገላገልኸን፤ ከሳትኸው ግን አስፈጀኸን”🙂

@wegoch
@wegoch
@paappii
ቀልድ
*

ልጅቷ ለትምህርት ቻይና ሄዳ ( በርግጥ አንዳንዶች ለንግድ ነውም ይላሉ፤ እኛ ለምን ለካራቴ ውድድር አትሄድ ምንም አያገባንም) ... ቻይና ሄዳ አንድ ቻይናዊጋ ጾታዊ ፍቅር መጀመር ከዛ በቃ ተጋቡ

ሀገር ቤት ይዛው ስትመጣ እናቷ ማመን ያቃታቸው ቻይናዊ የማግባቷ ነገር ሳይሆን የቀለቡ ነገር ነው

ቢያዩ ጊንጥ፤ ቅንቡርስ በረሮ የጉንዳን ቆሎ ወዘተረፈ

አንድ ቀን እነዚህን ነገሮች ይዞ መጥቶ ይሰራልኝ አለ

እናትየው: እውውይይ እንደው አደራ የውሻው አጥንት በሚቀቀልበት ድስት ስሩለት የኔን እቃ እንዳታነካኩ😂

የቻይናው ምግብ በኮረሪማ በበሶብላ የመሳሰሉት ቅመሞች አብዶ ተሰራለት እና ጣቱን እስኪቆረጥም አነከተ

ሆንቾፖ ኪሊቾቺቿቶኮዃ ሲንፊቻቹዎ አላቸው

እናትየው: ምንድን ነው የሚለኝ ሰውዬሽ

ልጅቷ: እማዬ ጣት ያስቆረጥማል በጣም አመሰግናለሁ ነው ያለሽ

ሾሆ ሲጆቾ ፖጂሊሃኪቾ ቺኒማማ

ኧረረረረ በቃ ምንም አይናገር አፉን እንደቆረበ ሰው አፍኖ ይቀመጥ ፌንጣዎቹ ዘለው እንዳይወጡ ይተወኝ ዝም ይበል ምስጋናው በቃኝ

ልጅቷ: አይ እማዬ እሱማ እያለ ያለው በጣም ጠግቤአለሁ የተረፈውን ከድናችሁ አስቀምጡልኝ በኋላ እበላዋለሁ

🧐: ኧ? ከድናችሁ? ምን እንዳይ ገባበት? በረሮው ውስጥ በረሮ እንዳይገባ ነው? ጊንጣ ጊንጥ ውስጥ ጉንዳን እንዳይገባ ነው?

🙄

በማስተዋል አሰፋ የተፃፈ

@wegoch
@wegoch
ጥገኛን ተውና ታታሪውን አሳድገው!

የሆነ ጊዜ የዩናይትድ አረብ ኤመሬትስ መስራች ሼህ ረሺድን ኢንተርቪው አድርጌው ነበር። ስለነገዋ ዱባይ ስጠይቀው የሰጠኝ መልስ አስገርሞኝም አስደንቆኝም ነበር

ምን አለ?

"አያቴ ግመል ይጋልብ ነበር፣ አባቴም ግመል ይጋልብ ነበር፣ እኔ ደግሞ መርሰዲስ እየነዳሁ ነው። የኔ ልጅ ላንድሮቨር ይነዳል። የልጅ ልጄም እንደዚያው ላንድሮቨር ይነዳል። የልጅ ልጅ ልጄ ግን ግመል መጋለቡ አይቀሬ ነው!"

"ለምን ?"
ለምን ካልከኝማ!

"ክፉ ጊዜ ጠንካራ ሰዎችን ይፈጥራል። ጠንካራ ሰዎች ደግሞ ሁሉ ነገር ቀላል የሆነበትን ጊዜ ይፈጥራሉ።ቀላል ጊዜያት በተራቸው ደካማ ሰዎችን ይፈጥራሉ። ደካማ ሰዎች ደግሞ ክፉ ጊዜን መልሰው ያመጡታል። ብዙዎች አይገነዘቡት ይሆናል ፣ ነገር ግን ይህ እንዳይመጣ ታታሪዎችን ማሳደግ አለብን። ያ ሲሆን ጥገኞች አይፈጠሩም።"

By Melaku Berhanu

@getem
@getem
@paappii
2024/11/18 00:34:04
Back to Top
HTML Embed Code: