Telegram Web
📚ተቅሪቡ ተድሙሪያህ፡ የመጨረሻው ክፍል
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
Forwarded from فوائد مدنية (محمد الرحيلي)
‏المدافعون عن الوطن وولاة الأمر والكاشفون لأعدائه من الظاهرين والمتسترين والمتلونين مجاهدون في سبيل الله وقائمون على ثغر عظيم نرجو لهم من الله الأجر العظيم وحقهم علينا أن ندعو لهم ونؤازرهم ، وليس غريبا أن يقوم الحزبيون بتشويه سمعتهم ووصفهم بالألقاب المنفرة وتحريك رجالهم للنيل منهم



الشيخ أ.د/سليمان الرحيلي | تويتر


📌قناة فوائد الشيخ أ.د. سليمان الرحيلي

www.tgoop.com/Drsuleiman
Ibnu aliy @wsu:
ኢድ ሙባረክ

በመላው አለም ለምትገኙ ሙስሊም ወንድም እና እህቶቼ እንኳን አላህ ለ1441ኛው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል በሰላም አደረሰን ፤አደርሳችሁ ለማለት እወዳለሁኝ

ተቀበለሏሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊኸል ዓዕማል


🌹عيد مبارك 🌹
كل عام وانتم بخير
تقبل الله منا ومنكم صالح الاعمال
ኢንሻኣ አሏህ ከዚህ በኋላ የአቂደቱል ዋሲጢያ የኡሰይሚን ሸርህ እና የመንዙመቱል በይቁኒያ ደርስ ይለቀቃል!!!
መንሀጀ-ሠለፍን እንዴት ተረዳሀው/ሽው?!
……  …… መንሀጀ-ሰለፍን በትክክል እንገንዘብ!!

🔹 መንሀጀ-ሠለፍን በትክክል ከተረዳን የሁሉንም ነገር ልክና ድንበር እናውቀዋለን።

መንሀጀ ሰለፍ ማለት:- ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለምን) እና ባልደረቦቻቸውን ጨምሮ እነሱንም በትክክል የተከተሉ የደጋግ ቀደምቶች መንገድ ማለት ነው።

መንሀጀ ሰለፍ ማለት:- አንዳንዶች እንደሚያስቡት ልክ እንደ ሌሎች የጥመት አንጃዎች ራሱን የቻለ አንጃ ሳይሆን ትክክለኛ (ንፁህ) ያልተበረዘው እስልምና ማለት ነው። ትክክለኛውና (ንፁህ) እስልምና ማለት ደጋግ ቀደምቶች ባመኑበት መልኩ ማመን ነው!።

አምላካችን አላህ በተቀደሰው ቃሉ እንዲህ ብሏል:-

فَإِنْ آمَنُوا بِمِثْلِ مَا آمَنتُم بِهِ فَقَدِ اهْتَدَوا ۖ وَّإِن تَوَلَّوْا فَإِنَّمَا هُمْ فِي شِقَاقٍ ۖ فَسَيَكْفِيكَهُمُ اللَّهُ ۚ وَهُوَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ

«በርሱ ባመናችሁበት ብጤ ቢያምኑ በእርግጥ ተመሩ፡፡ ቢዞሩም እነርሱ በጭቅጭቅ ውስጥ ብቻ ናቸው፡፡ እነርሱንም አላህ ይበቃሃል፤ እርሱም ሰሚው ዐዋቂው ነው፡፡» አል_በቀረህ 137

ትክክለኛ ሠለፊይ ማለት ደግሞ:- እነዚሁ ደጋግ ቀደምቶች ባመኑበት መልኩ አምኖ በአካሄድም ሆነ በአኽላቅ፣ ከከሀዲዎችና ከጥመት አንጃዎች ጋር በሚኖረን ግንኙነትም ሆነ በሌላ ደጋግ ቀደምቶችን በመልካም ሁኔታ ተከትሎ መጓዝ ማለት ነው።

ሠለፊይነት ማለት:- የመልካም ቀደምቶችን መንገድ ለራስህ ዝንባሌ በሚመችህ መልኩ ሳታሰናዳው አጥብቀህ በመልካም ሁኔታ መከተል ነው።

አምላካችን አላህ እንዲህ ብሏል:-

وَالسَّابِقُونَ الْأَوَّلُونَ مِنَ الْمُهَاجِرِينَ وَالْأَنصَارِ وَالَّذِينَ اتَّبَعُوهُم بِإِحْسَانٍ رَّضِيَ اللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا عَنْهُ وَأَعَدَّ لَهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي تَحْتَهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا ۚ ذَٰلِكَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ

«ከስደተኞቹና ከረዳቶቹም ሲሆኑ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሏቸው አላህ ከእነሱ ወዷል ከእርሱም ወደዋል፡፡ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲኾኑ ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ ይህ ታላቅ ዕድል ነው፡፡» አል_ተውበህ 100

መንሀጀ ሰለፍ ማለት:- የፖለቲካው ሁኔታ ሲቀያየር የምትቀያይረው ማለት አይደለም!!

መንሀጀ ሰለፍ ማለት:- የአንድ ሰሞን የግርግር አቋም አይደለም!!።

መንሀጀ ሰለፍ ማለት:- በዱኒያዊ ጉዳይ ከተወሰኑ የጥመት አንጃዎች (የቢድዐ) ሰዎች ጋር ስትገናኝ ለዱኒያዊ ጥቅም አልያም አንዳች ለዲን ይጠቅማል ብለህ ምታስበው ነገር እንዳይቀርብህ ብለህ በማላላትም ይሁን በማጥበቅ የምትቀያይረው አቋም ሳይሆን የትም ሆነህ በየትኛውም ሁኔታህ እስከ እለተ ሞትህ አጥብቀህ የምትይዘው የማይቀያየር የደጋግ ቀደምቶች መንገድ ነው።

መንሀጀ ሰለፍ ማለት:- ከሆኑ ግለሰቦች ጋር በዱኒያዊ ጥቅምም ይሁን በስነ-ምግባር ስላልተጣጣምክ ለመወነጃጀል ያህል የምትጠቀምበት አይደለም!!

መንሀጀ ሰለፍ ማለት:- ቢደላህም ቢቸግርህ፣ ከሆኑ ግለሰቦች ጋር በዱኒያዊ ጥቅማ ጥቅምም ሆነ በሌላ ብትጋጭም ሆነ ብትዋደድ፣ እስከ እለተ ሞትህ በክራንቻ ጥርስህ አጥብቀህ የምትይዘው የደጋግ ቀደምቶች መንገድ የሆነው ንፁህ እስልምና ነው!!

መንሀጀ ሰለፍ ማለት:- ሞቅ ሲልህ ምታወልቀው ሲበርድህ አንስተህ የምትለብሰው ጃኬት አይደለም!! ይልቅ ሞቅታህም መቀዝቀዝህም ትክክል ይሁን አይሁን የምትለካበት ትክክለኛው መነፅር ነው።

ስትቀዘቅዝ ለምን ቀዘቀዝኩ? ብለህ እንደ ሸሪዓ ራስህን የምትገመግምበት መንገድ ነው።

ሞቅ ሲልህ ደግሞ ይህ እንደ ሸሪዓ (እንደ ቀደምቶች አቋም) ተገቢ ነው አይደለም? ብለህ ራስህን ፈትሸህ ምታስተካክልበት ምንጊዜም ሊለይህ የማይገባ የደጋግ ቀደምቶች መንገድ እንጂ ሞቀኝ ብለህ አውጥተህ የምታስቀምጠው ልብስ አይደለም!!

ሠለፊይ (ሱኒይ) የሆነ ሰው የማይሳሳት ፍፁም አይደለም!!።
አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ሲሉ ይደመጣሉ:- “ሰለፊይ ነው ብዬ ፂሙን አስረዝሞ፣ ሱሪውን አሳጥሮ፣ እንዲህ ሲያደርግ አይቼ ሰለፊይነት አስጠላኝ… ኒቃቧን ለብሳ እንዲህ አድርጋ እንዲህ ስትል… ደግሞ በዛ ላይ ቀሪኣ ነች (የቀራች ናት) ከዛ በኋላ አስጠሉኝ…” ወዘተ ይላሉ።
ሆነ ብለውም ይሁን አይሁን እንዲህ መሰል ፀያፍ ቃላቶችን በሰለፊይ ወንድምና እህቶች ላይ ከምላሳቸው የሚያወጡ ሰዎች አሉ።

እንዲህ የሚሉ ሰዎች ሶስት ነገሮችን ዘንግተዋል:-
1ኛ, ዲናችን የሚለካው በቁርኣንና በሀዲስ እንጂ በሰዎች እንዳልሆነ ዘንግተዋል።

2ኛ, እነዚህ ኢስላማዊ ምልክት የሚታይባቸውን ሰዎች ሰው መሆናቸውን ዘንግተው ልክ ምንም የማይስቱ እንደ መላኢካ (ፍፁም) አድርጎ መሳል አለ።

3ኛ, አንዳንዴም እነዚህ ሰዎች ጥፋት ነው ብለው የሚያስቡት ነገር በሆነ ባህል ተፅእኖ ወድቀው ስህተት መስሎ የታያቸው ነገር ግን ደግሞ እንደ ሸሪዓ ችግር የሌለው ነገር በመሆኑ ሌሎች ቀለል አድርገው ተግብረውት ይሆናል።

የሆነው ሆኖ ብቻ ግን አንድ መታወቅ ያለበት ነገር ቢኖር ሰለፊይ የሆነ ሰው ፍፁም አይደለም!! ይሳሳታል ከስህተቱ ግን ቶሎ ይመለሳል። እንዲሁም መንሀጀ ሰለፍ በሰዎች ሳይሆን የሚለካው ሰዎች ናቸው በመንሀጀ ሰለፍ የሚለኩት!!

ፈተናዎች በሚደራረቡበት ጊዜ እና የጥመት አንጃዎች ማእበል በሚበረታበት ወቅት እውቀት ያለው እንኳን ከመንሀጀ ሰለፍ ሲንገዳገድ ካየህ በጭላንጭል እውቀት መንሀጀ ሰለፍን የያዙ ሰዎች እንዴት ይሆኑ ይሆን?! ብለህ እንድታስብ ያደርግሃል።

መንሀጀ ሠለፍን በትክክለኛ እውቀትና በትክክለኛ ማስረጃ በሚገባ ተገንዝቦ መያዝ ግዴታ ነው!!

አለያ ግን ልክ ባህሩ በማእበል ሲናወጥ የጀልባዎች ሁኔታ እንደሚያሳስበው ሁሉ፣ በትክክለኛ እውቀት መንሀጀ ሰለፍን አጥብቀው ያልያዙ ሰዎች ሁኔታ አሳሳቢ ነው!!

ሳጠቃልል ሠለፊነት ማለት:- ቁርኣን እና ሐዲስን በደጋግ ቀደምቶች ግንዛቤ መገንዘብ ማለት ነው። እንዲሁም ደጋግ ቀደምቶች በተጓዙበት መጓዝና በቆሙበት መቆም ነው።
✍🏻ኢብን ሽፋ: (www.tgoop.com/ibnshifa)
የተለያዩ ት/ቶችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችን ⤵️ #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://www.tgoop.com/IbnShifa
https://www.tgoop.com/IbnShifa
Forwarded from 🎤 ሸምሱ ጉልታ (አቡ ሀመዊየህ)  (أبو حموية)
👉 አጭር መልስ ለኢብኑ ሙነወር

➲ ኢብኑ ሙነወር ሶሞኑን ባነሳቸው ሶስት ነጥቦች ላይ አጠር ያለ ምላሽ ለመስጠት ወደድኩኝ። ሁለቱ ከኔ ጋር የሚገናኙ ሲሆኑ አንዱ ከሸይኽ ዐ/ ሐሚድ ጋር የሚገናኝ ነው።
ከኔ ጋር በሚገናኙት ላይ ምላሽ የምሰጠው ከራሴ ለመከላከል ብዬ ሳይሆን ኢብኑ ሙነወር ውሸት ውሸት የሚለው ራሱ ውሸት መሆኑን ለምስኪን ተከታዮቹ ግልፅ ለማድረግ ነው
እነዚህ ሶስቱ ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፦
1ኛ የሸይኽ ዐ/ሐሚድ ከየመን አስጠንቅቋል የሚለው የሸይኽ ረሻድ ክስና ስሜታዊ መልስን የሚመለከት
2ኛ እነ ኢብኑ ሙነወር ከሸይኽ ባሙሳ ጋር ከተገናኙ በኋላ ነው አቋማቸውን የቀየሩት የሚለው
3ኛ ባሕሩ ፉሪ አቡበከር መስጂድ ላይ እገሌ የሚባል ግለሰብ በሚያስተምርበት መስጂድ ነው የሚያስተምረው የሚሉት ናቸው
መልሱ እንደሚከተለው ይሆናል፦
1ኛ ኢብኑ ሙነወር ሸይኽ ዐ/ሐሚድ የመን ከሚገኙ የተወሰኑ ተቋማት ካስጠነቀቁ በኋላ መካ ላይ ከሸይኽ ባሙሳ ጋር ተገናኝተው ስለተጠቀሱት ተቋማት ከገለፁላቸው በኋላ መግባባት ላይ እንደ ደረሱ ከሸይኽ ባሙሳ ፁሑፍ  ጠቅሶ ከፃፈ በኋላ ሸይኽ ዐ/ሐሚድ በሸይኽ ባሙሳ ፊት ያመኑት ስህተት ባደባባይ አምነው እርምት መስጠት ነበረባቸው ይህን ባለማድረጋቸው ሸይኽ ረሻድ ጠንከር ያለ ምላሽ ሰጥቷል። በዚህ ሊንክ ታገኙታላችሁ ብሎ ረዱን ጋበዘ
ልብ በሉ ሸይኽ ባሙሳ እዚህ ከመጡ በኋላ ስለዚህ ጉዳይ ተጠይቀው በጣም በሚገርምና ሌላን የማክበር ስሜት በሚታይበት መልኩ ከሸይኽ ዐ/ሐሚድ ጋር ተነጋግረን ነበር አንዳንድ ነገሮች ግልፅ አድርጌለት ተግባብተናል ብለው አላህን ያመሰግናሉ

ኢብኑ ሙነወር የሚያስተዋውቀው የሸይኽ ረሻድ ምላሽ ግን አንድ ወደ ዒልም ራሱን ካስጠጋ ሰው በማይጠበቅ መልኩ ስሜታዊ ሆኖ ቲፎዞዎችን በሚያስጮህ መለኩ ከሸይኽ ዐ/ሐሚድ ንግግር ጋር የማይገናኝ ከዳዕዋው ይልቅ ለየመን መቆርቆር በሚመስል መልኩ ወሰን ያለፈ መልስ ነው።

ሸይኽ ዐ/ሐሚድ ስለተጠየቁት መርከዞች እኔ እንደሰማሁት ብለው ስለሰለፍዮች ግን አላውቅም ወዳዛ ሂዱ አልልም ይህን አልወድም ነው ያሉት
–  ሸይኽ ረሻድ ግን ሸይኽ ዐ/ሐሚድ ከየመን አስጠንቅቋል
– የሸይኽ ሙቅቢልን ልፋት መና አስቀርቷል
– ሰዎችን ከአላህ መንገድ ከልክሏል
– ራሱን የሰለፍያ መሪ አድርጓል
– ልኩን አላወቅምና የመሳሰሉ በጣም የሚገርሙ ትችቶችን ሰንዝሯል።
የሸይኹ ንግግር የመን ሙሉ በሙሉ በሸይኽ ሙቅቢል ዳዕዋ ላይ ያለች ነው የሚያስመስለው
– ሸይኹ የሸይኽ ሙቅቢልን ዳዕዋ ዋጋ ስላሳጣው የሕያ አል ሐጁርይ ምንም አላነሳም
– ደማጅን ስላፈረሱት ሺዓዎች ቃል አልተነፈሰም
– የመንን ለሁቲ ሺዓዎች አሳልፈው ስለሰጡት ኢኽዋኖች ምንም አላለም
የሰለፍይ መሻኢኾችን ከፊሎቹ እንዲሰደዱ ከፊሉቹ ተደብቀው እንዲኖሩ አድርገው ስለሚያሰቃዩት እነዚህ አንጃዎች ሰውነቱ እየተንቀጠቀጠ አልተናገረም
ይልቁንም ተናዶ ፍርድ መስጠት የከለከለውን ሸሪዓችንን ባላገናዘበና ዲን መመካከር ነው የሚለውን ታላቅ መርህ በጣሰ መልኩ የሰማሁት ድምፅ አናዶኝ ነው ብሎ አላህ ፊት የሚያስጠይቅ ንግግር ነው ያደረገው
ታዲያ ኢብኑ ሙነወር ሆይ ይህ ፍትሀዊ ነው ብለህ ነው ስሙት ያልከው ወይስ ዝንባሌህን ስለሚደግፍልህ?  ለምን የሸይኽ ባሙሳን መልስ ሰዎች እንዲያዩት አላደረግህም? መልሱን ላንተው ትቼዋለሁ

2ኛ እነ ኢብኑ ሙነወር "ከነ ሸይኽ መሐመድ ባሙሳ ጋር ከተገናኙ በኋላ ነው አቋም የቀየሩት" ባህሩ ስሜን ጠቅሶ በተናገረው ላይ እኔ ከሸይኽ ባሙሳ ጋር አልተገናኘሁም ውሸት ነው ብዬ መልስ ሰጥቼ ነበር። ይኸው አሁን ሰው በተሰበሰበበት ኢብኑ ሙነወር የቱነው ብሎ ጠይቆ... እያለ አለመገናኘቱን ለማረጋገጥ ብዙ ከለፋ በኋላ" አስባችሁም ይሁን ገምታችሁ ከመዋሸት እንድትጠነቀቁ ነው" ይላል

መልስ፦
በመጀመሪያ ደረጃ በ "እነኢብኑ ሙነወርና በ ኢብኑ ሙነወር" መካከል ያለው ልዩነት አማርኛ ሶስተኛ ቋንቋው ለሆነ እንኳን ይከብዳል ብዬ አላምን ማለትም እኔ ኢብኑ ሙነወር ከነሸይኽ ባሙሳ ጋር ከተገናኘ በኋላ አይደለም ያልኩት
እነ ኢብኑ ሙነወር ከሸይኽ ባሙሳ ጋር ከተገናኙ በኋላ አቋማቸውን መቀየራቸውን ሸይኽ ባሙሳ ለነ ኡስታዝ ሻኪር፣ ሸይኽ ዐ/ሐሚድና ሸይኽ ሑሰይን ሸይኹን ሊዘይሩ በሄዱበት ጊዜ የነገሯቸው መሆኑን ነግረውኛል ነው ያልኩት። ሸይኽ ሑሴይን ይህ ትክክል መሆኑን በሰጠው ምላሽ ጠቅሷል።
የባህሩ ውሸት የቱ ጋር ነው? እነዚህ ነግረውኛል ማለቱ ነው?
ሌላው እነ ኢብኑ ሙነወር ማለት የሚፈለግበት እሱና በሱ ስር ያሉት ሰዒድ ሙሳ፣ ፉአድ ሙሐመድ፣ ሳዳት ከማል፣ ሙሐመድ ሲራጅና ሌሎችም ነው
እነዚህ በኔ ስም መጠራት የለባቸውም ከሆነ አጥፍቻለሁ ካልሆነ ግን እነ ኢብኑ ሙነወር ሲባል የሱ መገኘት ግዴታ አይደለም። በእነ ኢብኑ ሙነወር የተሰየመ የክስ ፋይል 10 ሰዎች ያሉበት ቢሆንና ከ10ሩ አራቱ ብቻ ቀርበው እነ ኢብኑ ሙነወር ሲባል ቀርቧል ቢባል አሁን በምትከራከረው መልኩ ትከራከራለህ ማለት ነው?
ዋነኛው አጀንዳ የናንተ አቋም መቀየር ሆኖ ሳለ ለምን እኔ ከባሙሳ ጋር አልተገናኘሁም ወደሚል ለመቀየር እንደፈለክ አልገባኝም። ለምን አው ቀይረናል አይ አልቀየርንም አትልም? አልቀየርንም ከሆነ እጄ ላይ የሚገኙትን የድምፅና የፁሑፍ ፋይሎችን አሁን መዘርገፍ አልፈልግም። ከጭፍን ሙሪድነት ወጥቶ መስማትና ማንበብ ለሚፈልጉ ከዛሬ ሶስት አመት በፊትና በኋላ ያሉትን ድምፅና ፁሑፎችን ቻናሎቻችሁ ላይ ገብተው እንዲሰሙና እንዲያነቡ ተከታዮቻቸውን እጋብዛለሁ

3ኛ "ባህሩ የሚያስተምረው እገሌ የሚባል ግለሰብ በሚያስተምርበት መስጂድ ነው" የሚለው ነው
መልስ፦
ይህን የሚለው ከአመት በፊት ወራቤ ላይ የኢኽዋኖች መስጂድ ላይ ዳዕዋ ማድረጋቸውንና በአሁኑ መሻኢኾቹን ይዘው ወደ ሙመዪዓዎች መስጂዶች መሄዳቸውን አስመልክቶ በተነሳው ተቃውሞ ነው
በመጀመሪያ ደረጃ አሁንም ዋናው አጀንዳ የአቋም መውረድ ከሌለ እንዴት ፈቀዱላችሁ ነው እንጂ መስጂዶቹ ላይ ለምን ዳዕዋ አደረጋችሁ አይደለም።
ኢብኑ ሙነወር ሆይ ወራቤ ላይ  ኢኽዋኖች ያኔ ለኢብኑ መስዑዶች" ኢኽዋን ሲዘፍን ካላጨበጨብኩኝ ማለት ምንድነው"

"ደመረኩለሙላህ" በምትል ጊዜ ይፈቅዱልህ ነበርን? ሙመዪዓዎችስ ያ ሁሉ የስድብ ናዳ ስታወርድባቸው ይፈቅዱልህ ነበር? አንተስ ወደእርነሱ ትሄድ ነበር? አሁን እንዴት ፈቀዱልህ? እንዴትስ ሄድክ? ፉሪ አቡበከር መስጂድንስ ከእነዚህ ጋር እንዴት አገናኘኸው? እናንተ በተጠቀሱት መስጂዶች ላይ እኔ አቡበከር ላይ ያለኝ አይነት መብት አላችሁን? አቡበከር መስጂድ ላይ የጠቀስከው ግለሰብ ብቻ አይደለም ያለው የናንተ ተልእኮ ተቀብለው የባህሩን ተማሪዎች ለመበታተንና ባህሩን ለማስወጣት ቀና ደፋ የሚሉ አንድ ስንዝር መራመድ ያልቻሉ ብዙ ሰዎችም ጭምር ነው ያሉት። እነርሱ በሚርመሰመሱበትም መስጂድም ነው የማስተምረው።

አቡ በከር መስጂድ ላይ የናንተ ከአቋም መንሸራተት የኢብኑ መስዑዶች በዲን መነገድ በአደባባይ እናገራለሁ። ይህ የእግር እሳት ሲሆንባችሁ ተማሪው እንዲበተንና ለቅቄ እንድሄድ ለአመታት ለፋችሁ አልሳካ ሲላችሁ አሁን በአደባባይ ይፋ አወጣችሁት። በቁጭታችሁ ሙቱ እንጂ ለቅቄ አልወጣም።

የኔ አቡበከር መስጂድ ላይ ያለውን ማስተማር የናንተ አሸዋ ሜዳ ጀማል ያሲን በሚያስተምርበት መስጂድ ከማስተማራችሁ ጋር ብታመሳስል ፍትህ ነበር። ግን በሱ የወቀሳችሁ የለም። ያውም በድሮ አቋማችሁም ላይ ሆናችሁም። ለማንኛውም ከአጀንዳ እየወጣህ ሰዎችን ግራ አታጋባ እላለሁ።
  አበቃሁ
https://www.tgoop.com/bahruteka
የዳር አስ-ሱንና
የደርስ ፕሮግራሞች

ማሻሻያና በተጠናቀቁ ኪታቦች ቦታ የተተኩ ኪታቦችን ለማወቅ ዝርዝሩን ይመልከቱ

👉 ልብ ይበሉ! በተቋሙ ለእውቀት ፈላጊዎች እድሉ እጅግ በጣም ሰፊ ነው!

ቀናት:-
1ኛ, ሰኞ፣ ማክሰኞ፣ ረቡዕ፣ ሐሙስ
ሰኣት:- ከፈጅር (ሱብሂ) ሶላት በኋላ
ኪታብ:- ቡሉግ አል-መራም ሚን አዲለቲ'ል አህካም

ለሴቶች
ከ3:00 እስከ 5:45 ድረስ
በያኑ ማፊ ነሲሀቲ ኢብራሂም አር-ሩሀይሊ…፣ ነሲሀቲ ሊኒሳእ፣ ሸርህ አል-ቀዋዒዱ'ል ሙስላ (በሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን)
ተጨማሪ:- ቁርኣን በነዞር ከቃዒደቱ ኑራኒያ ጀምሮ እራሱን የቻለ ሴቶች በሴቶች

ለወንዶች
ከዐሱር በኋላ ደዓኢሙ ሚንሃጅ አን-ኑቡወህ (ሊሸይኽ ረስላን)
ተጨማሪ:- ሙሉ የልጆች ቂርኣት ሴቶች በሴቶች ወንዶች በወንዶች

2ኛ, ቅዳሜና እሁድ
ሰኣት:- ከፈጅር በኋላ
ኪታብ:- ኑኽበቱል ፊከር (ፊ ሙስጦላሁል ሀዲስ)

3ኛ, ጁምዓ እና ቅዳሜ
ሰኣት:- ከ3:00 እስከ 4:30
ኪታብ:- ሸርህ አስ-ሱንና (በሸይኽ ፈውዛን) ሸርህ፣ ነሲሀቲ ሊኒሳእ

4ኛ, ሰኞና ማክሰኞ
ሰኣት:- ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
ኪታብ:- በያኑ ማፊ ነሲሀቲ ኢብራሂም አር-ሩሀይሊ

5ኛ, እሮብና ሐሙስ
ሰኣት:- ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
ኪታብ:- መጅሙዐቱ ሶርፍ (ከቢናእ የተጀመረ)

6ኛ, ጁምዓ፣ ቅዳሜና እሁድ
ሰኣት:- ከመግሪብ እስከ ዒሻእ
ኪታብ:- በዐቂዳ ዙሪያ 200 ጥያቄና መልስ (በሸይኽ ሃፊዝ አል-ሀከሚ የተዘጋጀ)

7ኛ, ሰኞ፣ ማክሰኞ፣ እሮብ
ሰኣት:- ከዒሻእ ሶላት በኋላ
ኪታብ:- ሱል-ለም አል ኡሱል (ሊሸይኽ ሃፊዝ አል-ሀከሚ)

8ኛ, ሐሙስ፣ ጂምዓ፣ ቅዳሜ
ሰኣት:- ከዒሻእ ሶላት በኋላ
ኪታብ:- ሸርህ ዐቂደቱ ሰፋሪኒየህ (በኢብኑ ዑሰይሚን ሸርህ)

9ኛ, ቅዳሜና እሁድ
ሰኣት:- ከ8:20 እስከ 9:30
ኪታብ:- ቡሉግ አልመራም እና ሒጅራኑ አህሊ'ል ቢድዐህ (ሊሸይኽ አቡዘር)

እሁድ ቀን:-
ከ3:30 እስከ 5:50 ድረስ
አል-ኢርሻድ… (ሊሸይኽ ሷሊህ አል-ፈውዛን)
እና ሪያዱ ሷሊሂን
ከዐሱር በኋላ ሸርህ ከሽፍ አሽ-ሹብሃት (በኢብኑ ዑሰይሚን)
እና ኩን ሰለፊየን…

ከአላህ ጋር በተግባር እርምጃዎችን ወደፊት…

ዳር አስ-ሱንና የሸሪዓ እውቀት ማዕከል
አዲስ አበባ አለምባንክ

የዳር አስ-ሱንና የቴሌግራም 👇👇 ቻናል #join በማድረግ ይቀላቀሉ
https://www.tgoop.com/DarASSunnah1444
https://www.tgoop.com/DarASSunnah1444
አል-ኢርሻድ.pdf
4.8 MB
ተለቀቀ‼️

📌📚📖አዲስ መፅሐፍ 📖📚📌

"አል ኢርሻድ - ወደ ትክክለኛ እምነት መምራትና በማጋራትና በጥመት ባለቤቶች ላይ ምላሽ መስጠት"


الإرشاد إلى صحيح الإعتقاد والرد على أهل الشرك والإلحاد

በሸይኽ ዶክተር/ሷሊሕ ብን አል'ፈውዛን ሐፊዞሁሏህ ተዘጋጅቶ

በአቡ ዓብዲልዓዚዝ/ዩሱፍ አሕመድ ሐፊዞሁሏህ ወደ አማርኛ የተመለሰ

በዚሁ ቻናል በPDF ተዘጋጅቶ ለአንባቢያን የሚተላለፍ ይሆናል ተብሎ ቃል በተገባው መሰረት እነሆ የአላህ ፈቃድ ሆኖ ለአንባቢያን ቀርቧል‼️

ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን‼️
አላህ አንብበው ከሚጠቀሙት ያድርገን‼️
የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ

كن على بصيرة

https://www.tgoop.com/alateriqilhaq
2025/07/14 10:57:33
Back to Top
HTML Embed Code: