✨✨✨🍂✨🍂
በሰንበት ት/ቤታችን 2ኛ ዙር የወላጆች ጉባኤ ተካሄደ።
በጉባኤው ላይም ከሰሚት መካነ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሰላም ሰንበት ት/ቤት ወላጅ ኮሚቴዎች ልምዳቸውን አካፍለዋል።

🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿
እንኳን #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ አስቀድሞ ገዳይ ቀማኛ፣ ዘማዊና ያላመኑ ለነበሩ በንስሐ ተመልሰው በአባ መቃርስ እጅ ከተጠመቁ ከመነኰሱ በኋላ በግብፅ በአስቆጥስ ገዳም ታላቅ ተጋድሎ አድርገው በሰማዕነት ለዐረፉ #ለአባ_ሙሴ_ጸሊም_ለዕረፍቱ በዓል መታሰቢያ፣ ለአባታችን ለአቡነ ተክለ ሃይማኖትና ለእናታች ለቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ለወራዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን።

🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁
እንኳን #ከሰባ_ሁለቱ_አርድእት አንዱ ለሆነው #የጌታችን_ወንድም_ለተባለው ለፀራቢው ለዮሴፍ ልጅ #ለሐዋርያው_ለቅዱስ_ይሁዳ_ለዕረፍት_በዐል፣ ለእስክድርያ አርባ አራተኛ ሊቀ ጳጳስ #ለአባ_ጴጥሮስ ለዕረፍት በዓልና #ለክረምት_መግቢያ_ቀን በሰላም አደረሰን። ከእነዚህ ቅዱሳን እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

✨✨✨🌴️️️️️️🌴️️️️️️🌴️️️️️️✨✨✨🌴️️️️️️🌴️️️️️️🌴️️️️️️✨✨✨🌴️️️️️️🌴️️️️️️🌴️️️️️️
በደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ቤተ ክርስቲያን
ውሉደ ያሬድ ሰንበት ት/ቤት
ለ 2 ወር የሚቆይ መንፈሳዊ ትምህርት
የሚሰጡ ትምህርቶች
✨ ትምህርተ ሃይማኖት
✨ ክርስቲያናዊ ሥነምግባር
✨ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን
ትምህርቱ የሚሰጠው
🗓ሰኞ እና ሐሙስ
🕕ከምሽቱ 12:00 - 2:00
ትምህርቱ ሐምሌ 3 ይጀመራል
የምዝገባ ቦታ በሰንበት ት/ቤቱ ትምህርት ክፍል
ለበለጠ መረጃ
📞09411-05-73-30
📞0947-34-74-99
✨✨✨🌴️️️️️️🌴️️️️️️🌴️️️️️️✨✨✨🌴️️️️️️🌴️️️️️️🌴️️️️️️✨✨✨🌴️️️️️️🌴️️️️️️🌴

🌿🍁🌿🍁🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿
እንኳን ለከበረ ለመላእክት አለቃ #ለቅዱስ_ገብርኤል_ለበዓሉ_መታሰቢያ እንዲሁም ኔቅሎን በሚባል አገር በፍዩም ገዳም ቤተ ክርስቲያኑ ለተከበረችበትና #ለታላቁ_ነቢይና_መስፍን ለነቢያት አለቃ #ለቅዱስ_ሙሴ ደቀ መዝሙር ለነዌ ልጅ #ለቅዱስ_ኢያሱ_ለዕረፍቱ_መታሰቢያ_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።

🌴🌷🌴🌷🌴🌷🌴🌷🌴🌷🌴🌷🌴🌷🌴🌷
ዐስሩ አሸናፊዎች
የአስሩ ምሳሌያት ነገር ይህ ነው ። አንዱም ከአንዱ ይልቅ ያሸንፋል ፤ አንዱም እንዲሁ ሌላውን ድል ይነሳዋል ።
ጽኑ ብረትን እሳት ያሸንፈዋል ፤ ጽኑ እሳትን ውኃ ያሸንፈዋል ፤ ጽኑ ውኃን ደመና ይሸከመዋል ፤ ጽኑ ደመናን ጽኑ ነፋስ ይበትነዋል ፤ ጽኑ ነፋስን ምድር ያሸንፈዋል ፤ ጽኑ ምድርን የአዳም ልጆች ያሸንፏታል ፤ ኃያላን የአዳም ልጆችን ኀዘን ያሸንፋቸዋል ፤ ጽኑ ሐዘንን ጥዑም ወይን ያሸንፈዋል ፤ ጽኑ ወይንን እንቅልፍ ይሽረዋል ፤ ከዚህ ሁሉ ይልቅ ሴት በድል ነሺነት በልጣ ትገኛለች ።
(መጽ.ምሳሌ 6:27-29)
ሚስትህን ከወንድ ጋር ትቀርብ ዘንድ አምነህ አቲሰናብታት ። እሳትን እንጨትን ጠብቅልኝ ብሎ የሚያምነው አለን ? ሰሎሞንም እሳትን በጉያው ይዞ የማይቃጠል ማነው ? በፍህም ላይ የሚራመድ እግሮቹስ የማይቃጠሉ ማን ነው ? ከወንድ ሚስትም ሒዶ ንጹሕ ኾኖ የሚመለስ የለም አለ ።
መጽሐፈ ወግሪስ ገጽ 48

እንኳን #ከሰባ_ሁለቱ_አርድእት_አንዱ ለሆነው ሐዋርያው #ቅዱስ_ጳውሎስን_ላጠመቀው #ለሐዋርያው_ቅዱስ_ሐናንያ_ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል፣ ሰንደላት ከሚባል አገር ለሆነ #ለቅዱስ_ቶማስ፣ ከእርሱም ጋር አብረው ሰማዕትነት ለተቀበሉ ለሰባት መቶ ወንዶችና ዘጠኝ ሴቶች ለዕረፍታው መታሰቢያ በዓል፣ ጌታችን ስለ እርሱ ቅዱስ ሉቃስ በጻፈው በቅዱስ ወንጌል ለተናገረለት #ለድኀው_ለቅዱስ_አልዓዛርም_ለመታሰቢያው በዓሉና #ለመድኃኔዓለም_ለስቅለቱ_ለወራዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከማማስና_ከሲላስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

✨✨✨🍂✨🍂✨🍂
"...ክርስቲያኖች ግን ክርስቲያኖች ለመኾናቸው መታወቅ የሚገባቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥተው ምሥጢራትን ሲቀበሉ ብቻ ሳይኾን የትም ቦታ በሚኖሩት የቅድስና ሕይወት ነው፡፡ በአፍአ የከበሩ ሰዎች በአፍአ ከሚያሳዩት ምልክት እንደሚታወቁ ኹሉ፥ እኛም ልንታወቅ የሚገባን በነፍሳችን ክብር ነው፡፡ በሌላ አገላለጥ አንድ ክርስቲያን መታወቅ ያለበት በተሰጠው ልጅነት ብቻ ሳይኾን ለልጅነቱ እንደሚገባ በሚያሳየው አዲስ ሕይወትም ጭምር ሊኾን ይገባል፡፡ ይህ ክርስቲያን ለዓለም ብርሃንና ጨው ሊኾን ይገባዋል፡፡ ለዓለም ብርሃን መኾንህስ ይቅርና ለራስህ እንኳን ብርሃን መኾን ካልተቻለህ፣ የሚሰፋ ቁስልህን በዘይት ማሰርም ካቃተህ፥ ክርስቲያን መኾንህን የምናውቀው እንዴት ነው? ወደ ተቀደሰው ውኃ ገብተህ በመጠመቅህ ነውን? በዚህስ አይደለም ! ይህስ እንዲያውም ዕዳ ፍዳ ይኾንብሃል [እንጂ ክርስቲያን መኾንህን እንድናውቅህ አያደርገንም]፡፡ ይህ ሀብት (ልጅነት) ታላቅ ነውና ለዚህ ሀብት እንደሚገባ ለማይኖሩት ሰዎች ዕዳ ፍዳ መጨመሪያ ነው፡፡
አዎን፥ ክርስቲያን ለዓለም ብርሃኑን ማብራት ያለበት ከእግዚአብሔር በተቀበለው ጸጋ ብቻ ሳይኾን እርሱ ራሱም ድርሻውን በመወጣት ነውና፡፡ ክርስቲያን ካልኾኑት ይልቅ በኹለንተናው በአረማመዱ፣ በአተያዩ፣ በአለባበሱ፣ በአነጋገሩ ብልጫ ሲኖረው ነውና፡፡ ይህንም የምለው ልጅነትን የተቀበሉ ክርስቲያኖች ልጅነትን ተቀበሉ በመባል ብቻ ሳይኾን የሌሎች ሰዎች ረብ ጥቅም ይኾን ዘንድ ለተቀበሉት ልጅነት የሚገባና ሥርዓት ያለው ሕይወት እንዲኖሩ ስለምሻ ነው፡፡
🍂✨🍂
አሁን ግን ከሌሎች ከማያምኑት ብልጫ ኖሮህ እንዳየው በምፈልገው ሕይወት፥ በኹሉም ረገድ ተቃራኒ ኾነህ አይሃለሁ፡፡ ለምሳሌ ከቦታ አንጻር፥ ቀኑን ኹሉ የፈረስ እሽቅድምድምንና ተውኔትን፣ ነውርን የተሞሉ ትርኢቶችንና የክፉዎችን ማኅበር፣ ርኵሰትንም የተሞሉ ሰዎችን ስትመለከት እንደምትውል አይሃለሁ፡፡ ከፊትህ አንጻር፥ ዘወትር ያለ ልክና እንደ አመንዝራ ሴት ስትስቅ እመለከትሃለሁ፡፡ ከአለባበስህ አንጻር፥ ከተዋንያንና ጠቢባን ነን ከሚሉ ሰዎች ምንም እንደማትለይ አስተውልሃለሁ፡፡ ከሚከተሉህ ሰዎች አንጻር፥ ብዙ ውዳሴ ከንቱንና ሽንገላን እንደምትሻ አይሃለሁ፡፡ ከንግግርህ አንጻር፥ ምንም ደኅና ነገር፣ በቁዔት ያለው ቃል፣ ለሕይወታችን የሚረባ ንግግር እንደሌለብህ አደምጣለሁ፡፡ ከማዕድህ አንጻርም ከዚያ ጽኑዕ የኾነ ወቀሳ የሚያመጣብህ እንደ ኾነ አያለሁ፡፡
ታዲያ እስኪ ንገረኝ ! ክርስቲያንን ክርስቲያን ከሚያስብሉት ነገሮች እጅግ የራቅህ ኾነህ እያለ፥ ክርስቲያን መኾንህን መለየት የምችለው በምንድን ነው? ክርስቲያን መባልህስ ይቅርና፥ ሰው ብዬ ልጠራህ የምችለውስ እንዴት ነው? እንደ አህያ ትራገጣለህና፤ እንደ ኮርማ ትሴስናለህና፤ እንደ ፈረስ ከሴቶች ኋላ ኾነህ ታሽካካለህና፤ እንደ ድብ ሆዳም ነህና ፤ ሥጋህን እንደ በቅሎ ሥጋ ትሰገስጋለህና፤ እንደ ግመል ቂም ትይዛለህና፤ እንደ ተኵላ ትነጥቃለህና፤ እንደ እባብ ትቈጣለህና፤ እንደ ጊንጥ ትናደፋለህና፤ እንደ ቀበሮ ተንኰለኛ ነህና፤ እንደ እባብ ወይም እንደ እፉኝት በጕረሮህ መርዝ አለና፤ እንደ ክፉ ጋኔን ከወንድምህ ጋር ትጣላለህና፡፡
ታዲያ ክርስቲያን የሚለውስ ይቅርና፥ በምንህ ሰው ብዬ ልጥራህ? ሰው የሚያስብል ምልክት ሳይኖርህ እንዴት ብዬ ከሰው ዘንድ ልቊጠርህ? የንኡሰ ክርስቲያኖችና የክርስቲያኖች ልዩነት ባሰብሁ ጊዜ ልዩነቱ የሰውና የአርዌ ገዳም ያህል ይኾንብኛል፡፡ ታዲያ ምን ብዬ ልጥራህ? አርዌ ገዳም ብዬ ልጥራህን? እንዲህስ አልልህም፤ ጭካኔህ ከአራዊተ ገዳም በላይ ነውና፤ [በሌላ መልኩ ደግሞ እነርሱ እንደዚያ የኾኑት ከተፈጥሮአቸው የተነሣ እንጂ እንደ አንተ ወደውና ፈቅደው አይደለምና፡፡] ታዲያ ምን ብዬ ልጥራህ? ጋኔን ልበልህን? እንዲህስ አልልህም፤ ጋኔን የሆድ ባሪያ አይደለምና፤ ፍቅረ ንዋይም የለበትምና፡፡ ታዲያ ከአራዊተ ገዳምም ከአጋንንትም የሚብስ ክፉ ግብር ከያዝህ፥ ንገረኝ - ሰው ብዬ እጠራህ ዘንድ ይገባኛልን? ሰው ለመባል እንኳን የሚበቃ ምግባር ከሌለህስ፥ ክርስቲያን ብለን ልንጠራህ የምንችለው እንዴት ነው?"
📚 የማቴዎስ ወንጌል ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደተረጎመው
✨ ድርሳን 4፥14-15 ገጽ 80-82
📝በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ

🎲 Quiz '🎲 Quiz 'ጥያቄ እና መልስ ወርኃ የሰኔ 27'
👉"Start the quiz " የሚለውን ይጫኑ 👉"I am ready" የሚለውን ሲጫኑ ጥያቄ እና መልሱ ይጀመራል:: ጥያቄዎችን ሲመልሱ የቴሌግራም ቦት (ሲስተም) ይመዘገባል:: 🔔መልካም ዕድል 🔔
🖊 5 questions · ⏱ 45 sec

እንኳን #ለእስክድርያ (ለግብጽ) አገር ሊቃነ ጳጳሳት ሠላሳ ሦስተኛ ለሆነው ሃያ ስምንት ዓመት ሙሉ በስደትና በመከራ ላሳለፈ ለታላቁ አባት #ለአባ_ቴዎዶስዮስ_ለዕረፍት_መታሰቢያ በዓልና #ለአባ_ያዕቆብ_እል-በረዲ_ለመታሰቢያ በዓሉ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰብ፦ #ከቅዱስ_ባስልዮስና_ከቢፋሞን፣ #ከባሊዲስና #ከኮቶሎስ_ከአርዳሚስ_ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

እንኳን #ለንጉሥ_ዳዊት_ልጅ_ለኢትዮጵያዊው ንጉሥ #ለጻድቁ_ለቅዱስ_ቴዎድሮስ_ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል፣ #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ለከበረ #ለቅዱስ_ዐምደ_ሚካኤል_ለሥጋው_ፍልሰት እግዚአብሔር አምላክ በሰላም በጤና አደረሰን።

የምሽቱ ጥያቄ ከነ ምላሹ | ሰኔ 27 /2017 ዓ.ም
ጥያቄ ከነ መልሱ
1. በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ሐዋርያት የተሰበሰቡበት ከአህዛብ የተለወጡትን እና የሙሴን ሕግ በተመለከተ የተወያዩበት ጉባኤ የትኛው ነው?
ሀ. የአንጾኪያ ጉባኤ ለ. የኤፌሶን ጉባኤ ሐ. የኢየሩሳሌም ጉባኤ መ. የቆሮንቶስ ጉባኤ
✅ሐ. የኢየሩሳሌም ጉባኤ
2. ጳውሎስ ለገላትያ ሰዎች መልእክት የጻፈበት ዋና ምክንያት ምን ነበር?
ሀ. አንድነታቸውን ለማመስገን ለ. የገንዘብ ልገሳን ለማበረታታት
ሐ. ህግን ከሚያራምዱ አይሁዳውያን ለማስጠንቀቅ መ. የጣዖት አምልኮን ለመፍታት
✅ ሐ. ህግን የሚያራምዱ የአይሁድ እምነት ተከታዮችን ለማስጠንቀቅ
3. በሐዋርያት ሥራ 2፣ መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ላይ በጰንጠቆስጤ ከወረደ በኋላ ምን ሆነ?
ሀ. የፈውስ ተአምራትን አድርገዋል ለ. በማያውቁት ቋንቋዎች (ልሳኖች) ሰበኩ
ሐ. ለአብያተ ክርስቲያናት ደብዳቤ ጻፉ መ.እንደገና ተጠመቁ
✅ ለ.በማይታወቁ ቋንቋዎች (ልሳኖች) ሰበኩ
4. በሐዋርያት ሥራ ውስጥ የተጠቀሰው የመጀመሪያው ሰማዕት ማን ነው?
ሀ.ጴጥሮስ ለ. እስጢፋኖስ ሐ. ጄምስ መ. በርናባስ
✅ለ. እስጢፋኖስ
5. በሐዋርያት ሥራ 6 ላይ ሰባቱን ዲያቆናት ሲሾሙ ሐዋርያት ቅድሚያ የሰጡት ምንድን ነው?
ሀ. የፋይናንስ እውቀት እና የመናገር ችሎታ ለ. ሀብት እና ማህበራዊ ተጽእኖ
ሐ. መልካም ስም፣ በመንፈስ እና በጥበብ የተሞላ መ. የዕብራይስጥ ወጎች እውቀት
✅ ሐ. መልካም ስም፣ መንፈስ እና ጥበብ የሞላበት
👏👏👏 መልሶቻቸውን የላኩልን ተሳታፊዎች እናመሰግናለን🙏🙏🙏
👉 ወዳጆችዎን ወደ ቻናላችን ይጋብዟቸው። @wuludeyared

እንኳን #ለነቢዩ_ለሰማዕቱ_ለካህኑ_ለሐዋርያው #ለመጥምቀ_መለኮት_ለቅዱስ_ዮሐንስ_ለተወለደበት_ለልደት_በዓልና #በሕንደኬ_ካሉ_ደሴቶቸ በአንዲቱ ውስጥ ለሚኖር ለገድለኛ ለሆነ #ለአባ_ጌራን_ለዕረፍት_መታሰቢያ_በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱሳን_ማርያና_ከማርታ_ከመነኰስ #ገብረ_ክርስቶስ_ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።