Telegram Web
የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት አስተርዮ ማርያም 🙏🙏🙏 ዓመታዊ የንግሥ በዓል በምስጋና ደብራችን በደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ በታላቅ ድምቀት እንዲኽ ተከብሯል።

እመ ብዙኃን እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የዓመት ሰው ትበለን። አሜን!🙏🙏🙏
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁



እንኳን ለሊቀ መላእክት ለቅዱስ ዑራኤል ለሢመቱ (ለተሾመበት) ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን።


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁



እንኳን ከሰባ ሁለቱ አርድእት ለአንዱ ለሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ደቀ መዝሙሩ (በመንፈስ ልጁ) ለሆነው ለቅዱስ ጢሞቴዎስ ለዕረፍት በዓልና ለጻድቁ ንጉሥ ለቴዎዶስዮስ ለመታሰቢያ በዓሉ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከከበሩ ሰማዕታት ከቅዱሳን ጌርሎስና አትናቴዎስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
📣 ልዩ የጥያቄና መልስ ውድድር ! 📣

በየሳምንቱ ዓርብ ዕለት በተለመደው ሰዓት

በውድድሩ እየተሳተፋችሁ መንፈሳዊ እውቀትን በመገብየት የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብሩ ተሳታፊ እንድትኾኑ በአምላከ ቅዱስ ያሬድ ስም እንጋብዛለን።

መልካም ተሳትፎ እንመኛለን።

"ጽዮንን የሚወዳት አይደክምም"
ቅዱስ ያሬድ
🎲 Quiz 'ጥያቄ እና መልስ ወርኃ ጥር  ፳፫'
👉"Start the quiz "  የሚለውን ይጫኑ  👉"I am ready" የሚለውን ሲጫኑ ጥያቄ እና መልሱ ይጀመራል::  ጥያቄዎችን ሲመልሱ የቴሌግራም ቦት (ሲስተም) ይመዘገባል::    🔔መልካም ዕድል 🔔
🖊 5 questions · 30 sec
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁

እንኳን ለታላቁ አባት ለሐዲስ ሐዋርያ ለፀሐይ ዘኢትዮጵያ ለአቡነ ተክለሃይማኖት በቁመትና በጸሎት ብዛት አንዲቱ የእግሩ አገዳ ለተሰበረበት (ለስብተ አፅማቸው) ዓመታዊ መታሰቢያ በዓልና ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ እንደ ነዳይ ሆነው ለምነው ያገኙትን ለጦም አዳሪዎች በመመጽወት ለሚታወቁት ለአቡነ እጨጌ መርሐ ተክርስቶስ (ዘሸዋ) ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን።


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
🍁️️️️🍁️️️️🍁️️️️🌿🌿🌿🍁️️️️🍁️️️️🍁️️️️

እንኳን ለታላቁ አባት ለሐዲስ ሐዋርያ ለፀሐይ ዘኢትዮጵያ ለአቡነ ተክለሃይማኖት በቁመትና በጸሎት ብዛት አንዲቱ የእግሩ አገዳ ለተሰበረበት (ለስብተ አፅማቸው) ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን።

🍁️️️️🌿
የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ስብተ አፅም፦
"...ከበዐቱ ሳይወጣ ሌሊትና ቀን ቆመ። አልተቀመጠም ወደ ግራና ወደ ቀኝም አልተንቀሳቀሰም። ውኃም ቅጠልም ቢሆን ከቅዳሜና ከእሑድ በቀር በዚያ ወራት ምንም ምን አልቀመሰም። እህል ግን ከመነኰሰ ጀምሮ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ አልቀመሰም። ፀሓይንም ጨረቃንም ከዋክብትን በጋና ክረምትንም ቡቃያና አበባንም ፍሬውንም አላየም። ዓይኖች ሳሉት እንደ ዕውር ጆሮዎች ሳሉት እንደ ደንቆሮ የሚናገር የተከናወነ አንደበት እያለው እንደ ዲዳ ሆነ። ከምስጋና በቀር ምንም ምን አይናገርም። ሌሊትና ቀንም እግዚአብሔርን አመሰገነ። ዓለምንም እንደ ትቢያና እንደ ጉድፍ ቆጠረው ከክርስቶስ ጋር እንደተሰቀለ ሆነ ልቡናውም ዘወትር ወደ ዓየር የተመሰጠ ነበር። እንዲህ ባለም ገድል ብዙ ዘመን (22ዓመታት) ኖረ። ቁመትንም ካበዛ ወዲህ አንዲቱ የእግሩ አገዳ ተሰበረች ደቀ መዛሙርቱ አንሥተው አክብረው በሰበን ጠቅልለው ከመንበሩ እግር በታች ቀበሯት። ከዚህም ባንዲት እግሩ ሰባት ዓመት ቆመ። ከነዚህም አራቱን ዓመት ውሃው አልጠጣም"።


ገድለ ተክለ ሃይማኖት ምዕ53፥8-11።

🍁️️️️🍁️️️️🍁️️️️🌿🌿🌿🍁️️️️🍁️️️️🍁️️️️
2025/02/01 23:31:37
Back to Top
HTML Embed Code: