Telegram Web
🍂🍂🍂

"...ክርስቲያኖች ግን ክርስቲያኖች ለመኾናቸው መታወቅ የሚገባቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥተው ምሥጢራትን ሲቀበሉ ብቻ ሳይኾን የትም ቦታ በሚኖሩት የቅድስና ሕይወት ነው፡፡ በአፍአ የከበሩ ሰዎች በአፍአ ከሚያሳዩት ምልክት እንደሚታወቁ ኹሉ፥ እኛም ልንታወቅ የሚገባን በነፍሳችን ክብር ነው፡፡ በሌላ አገላለጥ አንድ ክርስቲያን መታወቅ ያለበት በተሰጠው ልጅነት ብቻ ሳይኾን ለልጅነቱ እንደሚገባ በሚያሳየው አዲስ ሕይወትም ጭምር ሊኾን ይገባል፡፡ ይህ ክርስቲያን ለዓለም ብርሃንና ጨው ሊኾን ይገባዋል፡፡ ለዓለም ብርሃን መኾንህስ ይቅርና ለራስህ እንኳን ብርሃን መኾን ካልተቻለህ፣ የሚሰፋ ቁስልህን በዘይት ማሰርም ካቃተህ፥ ክርስቲያን መኾንህን የምናውቀው እንዴት ነው? ወደ ተቀደሰው ውኃ ገብተህ በመጠመቅህ ነውን? በዚህስ አይደለም ! ይህስ እንዲያውም ዕዳ ፍዳ ይኾንብሃል [እንጂ ክርስቲያን መኾንህን እንድናውቅህ አያደርገንም]፡፡ ይህ ሀብት (ልጅነት) ታላቅ ነውና ለዚህ ሀብት እንደሚገባ ለማይኖሩት ሰዎች ዕዳ ፍዳ መጨመሪያ ነው፡፡

አዎን፥ ክርስቲያን ለዓለም ብርሃኑን ማብራት ያለበት ከእግዚአብሔር በተቀበለው ጸጋ ብቻ ሳይኾን እርሱ ራሱም ድርሻውን በመወጣት ነውና፡፡ ክርስቲያን ካልኾኑት ይልቅ በኹለንተናው በአረማመዱ፣ በአተያዩ፣ በአለባበሱ፣ በአነጋገሩ ብልጫ ሲኖረው ነውና፡፡ ይህንም የምለው ልጅነትን የተቀበሉ ክርስቲያኖች ልጅነትን ተቀበሉ በመባል ብቻ ሳይኾን የሌሎች ሰዎች ረብ ጥቅም ይኾን ዘንድ ለተቀበሉት ልጅነት የሚገባና ሥርዓት ያለው ሕይወት እንዲኖሩ ስለምሻ ነው፡፡

🍂🍂
አሁን ግን ከሌሎች ከማያምኑት ብልጫ ኖሮህ እንዳየው በምፈልገው ሕይወት፥ በኹሉም ረገድ ተቃራኒ ኾነህ አይሃለሁ፡፡ ለምሳሌ ከቦታ አንጻር፥ ቀኑን ኹሉ የፈረስ እሽቅድምድምንና ተውኔትን፣ ነውርን የተሞሉ ትርኢቶችንና የክፉዎችን ማኅበር፣ ርኵሰትንም የተሞሉ ሰዎችን ስትመለከት እንደምትውል አይሃለሁ፡፡ ከፊትህ አንጻር፥ ዘወትር ያለ ልክና እንደ አመንዝራ ሴት ስትስቅ እመለከትሃለሁ፡፡ ከአለባበስህ አንጻር፥ ከተዋንያንና ጠቢባን ነን ከሚሉ ሰዎች ምንም እንደማትለይ አስተውልሃለሁ፡፡ ከሚከተሉህ ሰዎች አንጻር፥ ብዙ ውዳሴ ከንቱንና ሽንገላን እንደምትሻ አይሃለሁ፡፡ ከንግግርህ አንጻር፥ ምንም ደኅና ነገር፣ በቁዔት ያለው ቃል፣ ለሕይወታችን የሚረባ ንግግር እንደሌለብህ አደምጣለሁ፡፡ ከማዕድህ አንጻርም ከዚያ ጽኑዕ የኾነ ወቀሳ የሚያመጣብህ እንደ ኾነ አያለሁ፡፡

ታዲያ እስኪ ንገረኝ ! ክርስቲያንን ክርስቲያን ከሚያስብሉት ነገሮች እጅግ የራቅህ ኾነህ እያለ፥ ክርስቲያን መኾንህን መለየት የምችለው በምንድን ነው? ክርስቲያን መባልህስ ይቅርና፥ ሰው ብዬ ልጠራህ የምችለውስ እንዴት ነው? እንደ አህያ ትራገጣለህና፤ እንደ ኮርማ ትሴስናለህና፤ እንደ ፈረስ ከሴቶች ኋላ ኾነህ ታሽካካለህና፤ እንደ ድብ ሆዳም ነህና ፤ ሥጋህን እንደ በቅሎ ሥጋ ትሰገስጋለህና፤ እንደ ግመል ቂም ትይዛለህና፤ እንደ ተኵላ ትነጥቃለህና፤ እንደ እባብ ትቈጣለህና፤ እንደ ጊንጥ ትናደፋለህና፤ እንደ ቀበሮ ተንኰለኛ ነህና፤ እንደ እባብ ወይም እንደ እፉኝት በጕረሮህ መርዝ አለና፤ እንደ ክፉ ጋኔን ከወንድምህ ጋር ትጣላለህና፡፡

ታዲያ ክርስቲያን የሚለውስ ይቅርና፥ በምንህ ሰው ብዬ ልጥራህ? ሰው የሚያስብል ምልክት ሳይኖርህ እንዴት ብዬ ከሰው ዘንድ ልቊጠርህ? የንኡሰ ክርስቲያኖችና የክርስቲያኖች ልዩነት ባሰብሁ ጊዜ ልዩነቱ የሰውና የአርዌ ገዳም ያህል ይኾንብኛል፡፡ ታዲያ ምን ብዬ ልጥራህ? አርዌ ገዳም ብዬ ልጥራህን? እንዲህስ አልልህም፤ ጭካኔህ ከአራዊተ ገዳም በላይ ነውና፤ [በሌላ መልኩ ደግሞ እነርሱ እንደዚያ የኾኑት ከተፈጥሮአቸው የተነሣ እንጂ እንደ አንተ ወደውና ፈቅደው አይደለምና፡፡] ታዲያ ምን ብዬ ልጥራህ? ጋኔን ልበልህን? እንዲህስ አልልህም፤ ጋኔን የሆድ ባሪያ አይደለምና፤ ፍቅረ ንዋይም የለበትምና፡፡ ታዲያ ከአራዊተ ገዳምም ከአጋንንትም የሚብስ ክፉ ግብር ከያዝህ፥ ንገረኝ - ሰው ብዬ እጠራህ ዘንድ ይገባኛልን? ሰው ለመባል እንኳን የሚበቃ ምግባር ከሌለህስ፥ ክርስቲያን ብለን ልንጠራህ የምንችለው እንዴት ነው?"

📚 የማቴዎስ ወንጌል ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደተረጎመው 
ድርሳን 4፥14-15 ገጽ 80-82
📝በገብረ እግዚአብሔር ኪደ የተተረጎመ


🍂🍂🍂
🥰6
📣 ልዩ የጥያቄና መልስ ውድድር ! 📣

በየሳምንቱ ዓርብ ዕለት በተለመደው ሰዓት

በውድድሩ እየተሳተፋችሁ መንፈሳዊ እውቀትን በመገብየት የጥያቄ እና መልስ መርሐ ግብሩ ተሳታፊ እንድትኾኑ በአምላከ ቅዱስ ያሬድ ስም እንጋብዛለን።

መልካም ተሳትፎ እንመኛለን።
🙏4
🎲 Quiz '🎲 Quiz 'ጥያቄ እና መልስ ወርኃ የሰኔ 27'
👉"Start the quiz "  የሚለውን ይጫኑ  👉"I am ready" የሚለውን ሲጫኑ ጥያቄ እና መልሱ ይጀመራል::  ጥያቄዎችን ሲመልሱ የቴሌግራም ቦት (ሲስተም) ይመዘገባል::  🔔መልካም ዕድል 🔔
🖊 5 questions · 45 sec
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿

እንኳን #ለእስክድርያ (ለግብጽ) አገር ሊቃነ ጳጳሳት ሠላሳ ሦስተኛ ለሆነው ሃያ ስምንት ዓመት ሙሉ በስደትና በመከራ ላሳለፈ ለታላቁ አባት #ለአባ_ቴዎዶስዮስ_ለዕረፍት_መታሰቢያ በዓልና #ለአባ_ያዕቆብ_እል-በረዲ_ለመታሰቢያ በዓሉ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰብ፦ #ከቅዱስ_ባስልዮስና_ከቢፋሞን#ከባሊዲስና #ከኮቶሎስ_ከአርዳሚስ_ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።

🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿
🙏7
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿

እንኳን #ለንጉሥ_ዳዊት_ልጅ_ለኢትዮጵያዊው ንጉሥ #ለጻድቁ_ለቅዱስ_ቴዎድሮስ_ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል፣ #ለኢትዮጵያዊው_ጻድቅ ለከበረ #ለቅዱስ_ዐምደ_ሚካኤል_ለሥጋው_ፍልሰት እግዚአብሔር አምላክ በሰላም በጤና አደረሰን።
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿
🙏7
የምሽቱ ጥያቄ ከነ ምላሹ  | ሰኔ 27 /2017 ዓ.ም

ጥያቄ ከነ መልሱ

1. በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ውስጥ ሐዋርያት የተሰበሰቡበት ከአህዛብ የተለወጡትን እና የሙሴን ሕግ በተመለከተ የተወያዩበት ጉባኤ የትኛው ነው?
ሀ. የአንጾኪያ ጉባኤ ለ. የኤፌሶን ጉባኤ ሐ. የኢየሩሳሌም ጉባኤ መ. የቆሮንቶስ ጉባኤ

ሐ. የኢየሩሳሌም ጉባኤ

2. ጳውሎስ ለገላትያ ሰዎች መልእክት የጻፈበት ዋና ምክንያት ምን ነበር?
ሀ. አንድነታቸውን ለማመስገን ለ. የገንዘብ ልገሳን ለማበረታታት
ሐ. ህግን ከሚያራምዱ አይሁዳውያን ለማስጠንቀቅ መ. የጣዖት አምልኮን ለመፍታት

ሐ. ህግን የሚያራምዱ የአይሁድ እምነት ተከታዮችን ለማስጠንቀቅ

3. በሐዋርያት ሥራ 2፣ መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ላይ በጰንጠቆስጤ ከወረደ በኋላ ምን ሆነ?
ሀ. የፈውስ ተአምራትን አድርገዋል ለ. በማያውቁት ቋንቋዎች (ልሳኖች) ሰበኩ
ሐ. ለአብያተ ክርስቲያናት ደብዳቤ ጻፉ መ.እንደገና ተጠመቁ

ለ.በማይታወቁ ቋንቋዎች (ልሳኖች) ሰበኩ

4. በሐዋርያት ሥራ ውስጥ የተጠቀሰው የመጀመሪያው ሰማዕት ማን ነው?
ሀ.ጴጥሮስ ለ. እስጢፋኖስ ሐ. ጄምስ መ. በርናባስ

ለ. እስጢፋኖስ

5. በሐዋርያት ሥራ 6 ላይ ሰባቱን ዲያቆናት ሲሾሙ ሐዋርያት ቅድሚያ የሰጡት ምንድን ነው?
ሀ. የፋይናንስ እውቀት እና የመናገር ችሎታ ለ. ሀብት እና ማህበራዊ ተጽእኖ
ሐ. መልካም ስም፣ በመንፈስ እና በጥበብ የተሞላ መ. የዕብራይስጥ ወጎች እውቀት

ሐ. መልካም ስም፣ መንፈስ እና ጥበብ የሞላበት



👏👏👏 መልሶቻቸውን የላኩልን ተሳታፊዎች እናመሰግናለን🙏🙏🙏

👉 ወዳጆችዎን ወደ ቻናላችን ይጋብዟቸው። @wuludeyared
🙏2
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿

እንኳን #ለነቢዩ_ለሰማዕቱ_ለካህኑ_ለሐዋርያው #ለመጥምቀ_መለኮት_ለቅዱስ_ዮሐንስ_ለተወለደበት_ለልደት_በዓልና #በሕንደኬ_ካሉ_ደሴቶቸ በአንዲቱ ውስጥ ለሚኖር ለገድለኛ ለሆነ #ለአባ_ጌራን_ለዕረፍት_መታሰቢያ_በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱሳን_ማርያና_ከማርታ_ከመነኰስ #ገብረ_ክርስቶስ_ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿
🙏7👍2
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

📣በክፍላት መካከል የሚደረግ
መንፈሳዊ ጥያቄ እና መልስ📣

በክፍላት መካከል የሚደረግ መንፈሳዊ ጥያቄ እና መልስ
በክፍላት መካከል የሚደረግ መንፈሳዊ ጥያቄ እና መልስ የመጀመሪያ ዙር ውድድር በእለተ ማክሰኞ ከ12:00 ጀምሮ ይጀመራል።እርስዎም ተሳታፊ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል።

መልካም ተሳትፎ እንመኛለን።

📣አድራሻ፦ በሰንበት ት/ቤት አዳራሽ
👍2
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿
እንኳን ሰማዕት ለሆነች ሰውነቷን ለእግዚአብሔር ለሰጠች #ለቅድስት_ድንግልና_ለመስጋድልት_ለቅፍሮንያ_ለዕረፍቷ_መታሰቢያ_በዓልና #ለቅዱሳን_መስተጋድላን #ብዮክና_ብንያሚን_ለዕረፍታቸው_መታሰቢያ_በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከሮሜ_ሊቀ_ጳጳሳት_ከክልዮስና #ከበርተሎሜዎስ #ከጻድቁ_ከገብረ_መድኅንም_ከዕረፍታቸው መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿
🙏9🥰3
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

📣በክፍላት መካከል የሚደረግ
መንፈሳዊ ጥያቄ እና መልስ📣

በክፍላት መካከል የሚደረግ መንፈሳዊ ጥያቄ እና መልስ
በክፍላት መካከል የሚደረግ መንፈሳዊ ጥያቄ እና መልስ የመጀመሪያ ዙር ውድድር በእለተ ማክሰኞ ከ12:00 ጀምሮ ይጀመራል።እርስዎም ተሳታፊ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል።

መልካም ተሳትፎ እንመኛለን።

📣አድራሻ፦ በሰንበት ት/ቤት አዳራሽ
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁
እንኳን #ከዐሥራ_ሁለቱ_ሐዋርያት ለአንዱ ግመልን በመርፌ ቀዳዳ ላሳለፈ #ለሐዋርያው_ለቅዱስ_ታዴዎስ ለዕረፍቱ በዓል መታሰቢያ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁
🙏13🥰1
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁

እንኳን #ለእስክድርያ_ሃያ_አራተኛ_ሊቀ_ጳጳስ ለአምደ ሃይማኖት መናፍቁ ንስጥሮስ በጉባኤ ኤፌሶን ተከራክሮ ረቶ ላወገዘው ለታላቁ #ለአቡነ_ቄርሎስ_ለዕረፍት መታሰቢያ በዓልና ከእርሱ በፊት ለነበረው ሊቀ ጳጳሳት ዮናክንዲኖስ ደቀ መዝሙሩ ለነበረው #ለሮሜ_ሊቀ _ጳሳት_ለቅዱስ_አባት_ለአባ_ክልስቲያኖስ_ለዕረፍት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን።
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿
👍1🙏1
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

«ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው በሸመገለ ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም» ምሳሌ 22፥6


የሰንበት ት/ቤት አገልግሎት እየሰፋ እና ተልእኮው ጥልቅ እየሆነ የመጣበት ጊዜ ነው። ከተሰጠው ተልዕኮ ውስጥ ወሳኙ ነገ ቤተክርስቲያንን እና ሀገርን ተረካቢ ትውልድ የሆኑትን ሕጻናት ልጆቻችን የሚመለከት ነው። በእምነታቸው ፣ በምግባራቸው ፣ በጥበብ ፣ በጽድቅ እና በክርስቲያናዊ እሴት እንዲያድጉ ማድረግ ከእግዚአብሔር የተሰጠን አደራ እና ግዴታችን ነው። ይህንን ተገንዝበን በትጋት በማስተማር ፣ በመምራት እና ተረካቢ እንዲሆኑ ማድረግ ከእኛ ይጠበቃል።

በመሆኑም ይህንን ታላቅ ተልዕኮ ለማከናወን ሰንበት ት/ቤታችን ታታሪ እና ቁርጠኛ የሆኑ አባላቶቿን ለሕጻናት ክፍል አገልግሎት ትፈልጋለች። በተለየ በክረምት ወቅት ካሉን መደበኛ ሕጻናት እጥፍ ልጆችን ስለምንቀበል በማስተማርም ይኹን በማስተባበር ጊዜ አቅም ያላችኹ አባላቶችን እንፈልጋለን::

የአገልግሎት ጊዜያት ለመደበኛ ሕጻናት
🗓አርብ ከ11:30-12:30
🗓ቅዳሜ 08:00-12:00
🗓 እሁድ 04:00-07:00
ለክረምት አዲስ ሕጻናት ማክሰኞ እና ሐሙስ
🕔ጠዋት ከ 03:00 - 06:00 ሲኾን

ይህንን የሰንበት ት/ቤት ታላቅ የአገልግሎት ጥሪ የተቀበላችሁ በሰንበት ት/ቤት አባላት ጉዳይ ክፍል በአካል በመገኘት ወይም በመደወል እንድትመዘገቡ ይሁን።

ለበለጠ መረጃ፡
ስልክ ቁጥር
 
📲 09-19-15-34-23
📲 09-13-7015-50
📲09-10-71-25-44

ለልጆቻችን ዛሬውኑ ይድረሱ!!

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ት/ቤት ሕጻናት ክፍል
እግዚአብሔር አገልግሎታችንን ይባርክ!! በጻድቁ ቅዱስ ያሬድ ጸሎት ይማረን!! አሜን


🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
👍2
🌴🌴🌷🌷🌴🌴🌷🌷🌴🌴🌷🌷🌴🌴

አበው ስለ እመቤታችን እንዲህ አሉ

"አምላክ ከንጉሥ ሔሮድስ ሴት ልጅ ቢወለድ ኖሮ አልጋ ወራሽ በሆነና ባልተሰደደ ነበር። እርሱ ግን የድሆች ልጅ የሆነችውን ድንግል መረጠ"
*አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ*

"ታላቁ ተራራ ሆይ ታናሽዋ ብላቴና የተሸከመችህ ራስህን በሚቻላት መጠን አድርገህላት ነው ፣ ታላቁ እሳት ሆይ ታናሽዋ ብላቴና ተሸክማህ ያልተቃጠለችው ኃይልን ትችል ዘንድ አጽንተሃት ነው " 
*ቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ*

"ይህ ዓለም የእግዚአብሔርን ልጅ በቀጥታ ከእግዚአብሔር አብ እጅ ለመቀበል የተገባ ሆኖ ስላልተገኘ ፣ ዓለም ከእርስዋ ይቀበል ዘንድ አንድያ ልጁን ለድንግል ማርያም እናት ትሆነው ዘንድ ሠጣት"
*ቅዱስ_አውግስጢኖስ*

"ጌታ ሆይ እናትህን ማን ብለን እንጥራት? እናት ብቻ እንዳንላት ድንግል ሆና አገኘናት ፣ ድንግል እንዳንላት ልጅ ታቅፋ አየናት። ጌታ ሆይ እናትህን ለመጥራት እንዲህ የሚያስቸግር ከሆነ አንተን ከቶ ምን ብለን እንጠራሃለን??"
*ቅዱስ_ኤፍሬም*

🌴🌴🌷🌷🌴🌴🌷🌷🌴🌴🌷🌷🌴🌴
🥰13
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁
እንኳን #ለዐሥራ_ሁለቱ_ደቂቅ_ነቢያት ለመታሰቢያ በዓላቸውና ከእነርሱ አንዱ ለሆነው ለሴዴቅያስ ልጅ ለጎዶልያ ልጅ ለኩሲ ልጅ #ለነቢዩ_ለቅዱስ_ሶፎንያስ_ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ #ከቅዱሳን_አቡቂርና_ዮሐንስ ከሥጋቸው ፍልሰት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁
🙏3👍1
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿


«ልጅን በሚሄድበት መንገድ ምራው በሸመገለ ጊዜ ከእርሱ ፈቀቅ አይልም» ምሳሌ 22፥6



የአገልግሎት ጊዜያት ለመደበኛ ሕጻናት
🗓አርብ ከ11:30-12:30
🗓ቅዳሜ 08:00-12:00
🗓 እሁድ 04:00-07:00
ለክረምት አዲስ ሕጻናት ማክሰኞ እና ሐሙስ
🕔ጠዋት ከ 03:00 - 06:00 ሲኾን

ይህንን የሰንበት ት/ቤት ታላቅ የአገልግሎት ጥሪ የተቀበላችሁ በሰንበት ት/ቤት አባላት ጉዳይ ክፍል በአካል በመገኘት ወይም በመደወል እንድትመዘገቡ ይሁን።

ለበለጠ መረጃ፡
ስልክ ቁጥር 
📲 09-19-15-34-23
📲 09-13-7015-50
📲09-10-71-25-44

ለልጆቻችን ዛሬውኑ ይድረሱ!!

ውሉደ ያሬድ ሰንበት ት/ቤት ሕጻናት ክፍል
እግዚአብሔር አገልግሎታችንን ይባርክ!! በጻድቁ ቅዱስ ያሬድ ጸሎት ይማረን!! አሜን

🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
🙏5
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿
እንኳን #ለብርሃናተ_ዓለም_ለቅዱስ_ጴጥሮስ#ቅዱስ_ጳውሎስ_በጫካኙ ንጉሥ በኔሮን ቄሳር እጅ #ሰማትነት_ለተቀበሉበት_ለዕረፍታቸው_መታሰቢያ ዓመታዊ በዓል፣ ለመላእክት አለቃ #ለቅዱስ_ሳቁኤል_ለበዓሉ_መታሰቢያ#ለሰባ_ሁለቱ_አርድእት_ለመታሰቢያቸው_በዓላቸው#ለአባታችን_ለአቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ_ዓመታዊ የመታሰቢያ በዓላቸውና ለሐዋርያት (ለሰኔ) ፆም ፍቺ እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን። በተጨማሪ፡በዚች ከሚታሰቡ፦ በጋዛ ሰማዕት ከሆነ #ከይስሐቅና_ከደብረ_ዓሣ_ጻድቃንም ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿
🙏5
🌿🌿🌿🌿🌿
እንኳን ለክቡራንና ዐበይት አባቶቻችን ሐዋርያት ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ጳውሎስ የሰማዕትነት መታሰቢያ በዓላቸው አደረሳችሁ
🌿🌿🌿🌿🌿

‹‹ጴጥሮስ ኰኵሐ ሃይማኖት ወጳውሎስ ልሳነ ዕፍረት፥ በበዓልክሙ እምርት ንሥኡነ ዐሥራተ ምሕረት፥ ሰላም ለክላሌክሙ በዛቲ ዕለት።

ትርጉም:-

ቅዱስ ጴጥሮስ የሃይማኖት ዐለት ነው፤ ቅዱስ ጳውሎስ ልሳነ እፍረት ነው፤ (የተመረጠ ዕቃ)
በታወቀችው በዓላችሁ የምሕረት ዐሥራታችሁን ያዙ፤ በዚች ዕለት ለተሰየፈችው አንገታችሁ ሰላም ይሁን።››

         ባሕረ ጥበባት ቅዱስ ያሬድ

ከቅዱስ ጴጥሮስና ከቅዱስ ጳውሎሰ ረድኤትና በረከት ያድለን!

🌿💫🌿💫🌿💫🌿💫🌿💫🌿💫🌿💫
🙏10
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁

እንኳን እንደ እርሱ ያሉ #ኤልያስና_ኄኖክ ወደ አሉበት ብሔረ ሕያዋን ለተሰወረው #ለነቢዩ_ለቅዱስ_ዕዝራ_ሱቱኤል_ለዕርገቱ_በዓል እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረሰን።
🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁🌿🍁
🙏1
2025/07/13 03:59:28
Back to Top
HTML Embed Code: