የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከስፕላሽ ኢንተርናሽናል ጋር ውይይት አካሄደ፡፡
(መስከረም 29/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከስፕላሽ ኢንተርናሽናል ከመጡ ልኡካን ቡድን አባላት ጋር ውይይት አካሄደ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በውይይቱ ላይ እንዳሉት የትምህርት ጥራትና ምቹ የመማሪያ አካባቢን ለመፍጠር ቢሮው እያከናወነ ያለውን ስራ የሚደግፍ በርካታ ስራዎች በስፕላሽ ኢንተርናሽናል በኩል ሲሰራ መቆየቱን ገልጸው በቀጣይም ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
በውይይቱ ቢሮው ከስፕላሽ ኢንተርናሽናል ጋር በጋራ ሲሰሩ የቆዩ ስራዎች ላይ ግምገማ ያካሄደ ሲሆን ቀጣይ ስራዎችን በጋራ ለመፈጸም የሚያስችሉ ዋና ዋና ተግባራት ላይ የጋራ ውይይት አካሂደዋል፡፡
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc

❤22
38ኛውን የአለም የቱሪዝም ቀን ምክንያት በማድረግ በትምህርት ተቋማት ሲካሄድ የቆየው ተንቀሳቃሽ አውደ ርዕይ በቦሌ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተጠናቀቀ።
(መስከረም 29/2018 ዓ.ም) በማጠቃለያ አውደ ርዕዩ የቱሪዝም ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር እንደገና አበበን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ እና የትምህርት ቤቱ አመራሮች እንዲሁም መምህራን እና ተማሪዎች ተገኝተዋል።
የኢፌድሪ ቱሪዝም ሚኒስቴር ዴኤታ ዶክተር እንደገና አበበ በማጠቃለያ አውደ ርዕዩ ባስተላለፉት መልዕክት ተንቀሳቃሽ አውደ ርዕዩ ተማሪዎች በሀገራቸው የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎችን አውቀው ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ማስተዋወቅ እንዲችሉ ታስቦ ከቱሪዝም ኮሚሽን እና ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ጋር በጋራ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ በበኩላቸው ተማሪዎች የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎቹ የት እንደሚገኙ እና ለሀገሪቱ እያበረከቱ የሚገኘው ፋይዳ ምን እንደሆነ እንዲገነዘቡ በማሰብ ተንቀሳቃሽ አውደ ርዕዩ ቀደም ሲል በዳግማዊ ሚኒሊክ፣በጥቁር አንበሳ እና በጄነራል ታደሰ ብሩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለእይታ ቀርቦ በዛሬው እለት በቦሌ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መጠናቀቁን ገልጸው ቢሮው በቀጣይ ከቱሪዝም ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን ተማሪዎች የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎቹን የሚጎበኙበት እድል የሚመቻች መሆኑን አመላክተዋል።
በአውደ ርዕዩ እድሳት የተደረገላቸው ታሪካዊ የቱሪዝም ስፍራዎች ፣አዳዲስ መዳረሻዎች እና በዩኔስኮ የተመዘገቡ የቱሪዝም መዳረሻዎች ለተመልካች ለዕይታ ቀርበዋል።

❤23
የከንቲባ ፅ/ቤት ድጋፍና ክትትል ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ድጋፍና ክትትል አካሄደ::
(መስከረም 29/2018 ዓ.ም) የከንቲባ ፅ/ቤት ድጋፍና ክትትል ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በመገኘት በ2018 የዝግጅት ምዕራፍ KPI አፈፃፀምና ትግበራ፤ ቅንጅታዊ ሥራዎች ከተግባር ልየታ እስከ አፈፃፀም እንዲሁም በመልካም አስተዳደር የተሰሩ ሥራዎችና የተፈቱ ችግሮች አፈፃፀም ላይ ትኩረት ያደረ ክትትልና ድጋፍ አካሄደ::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ የከንቲባ ፅ/ቤት በየጊዜው እያደረገ ያለው የድጋፍና ክትትል ሥራ ለቢሮው ውጤታማነት ትልቅ አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑን ገልፀው የድጋፍና ክትትል ቡድኑ ቀጣይ ለስራችን ስኬት የሚያነሳሳ ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን እንጠብቃለን ብለዋል::
የተቋማት ቅንጅታዊ ሥራ ክትትል ድጋፍ ፕላንና መሰረተ ልማት ቡድን መሪ አቶ ሰለሞን ሀይሉ ከንቲባ ፅ/ቤት ድጋፍና ክትትል ቡድን በከተማ አስተዳደሩ ስር የሚገኙ ቢሮዎች ላይ የክትትል: ድጋፍና ማስተባበር ሥራዎች የሚሰራ መሆኑን ገልፀው፤ በትምህርት ቢሮ በመልካም አስተዳደርና ቅንጅታዊ ሥራዎች እንዲሁም ቅሬታ አቀራረብ ላይ መሰረት አድርጎ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ አመላክተዋል::

❤44
ሀገር አቀፉን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ለማሻሻል በተዘጋጀ ስትራቴጂ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።
(መስከረም 29/2018 ዓ.ም) ውይይቱ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሚያስፈትኑ የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች ከተውጣጡ ርዕሳነ መምህራን ጋር የተካሄደ ሲሆን የቢሮው የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጥላዬ ዘውዴ ስትራቴጂውን አቅርበው ውይይት ተካሂዷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት በየአመቱ መሻሻል እያሳየ ቢገኝም ከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ሴክተሩ ከሚያወጣው ኢንቨስትመንት አንጻር ውጤቱ በሚፈለገው ደረጃ ባለመሆኑ ስትራቴጂው መዘጋጀቱን ጠቁመው ስትራቴጂው በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆን የርዕሳነ መምህራን አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ የዛሬው ውይይት መዘጋጀቱን አመላክተዋል።
ኃላፊው አያይዘውም በስትራቴጂው ከተካተቱ ተግባራት መካከል በአቅራቢያ ከሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ቅዳሜ ሙሉ ቀን እና እሁድ ግማሽ ቀን በየክላስተር ማዕከላቱ በጋራ እንዲማሩ ምቹ ሁኔታ መፍጠርን ጨምሮ በየትምህርት ቤቱ ከመደበኛ የትምህርት ሰአት ውጭ በሳምንት ሶስት ቀን የማጠናከሪያ ትምህርት እንዲሰጥ ማድረግ በስትራቴጂው መቀመጡን ገልጸው ስትራቴጂው የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ እንዲችል ከወላጆች ጋር በጋራ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ስትራቴጂው በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆን መመሪያ የሚያዘጋጁ አካላት የተመረጡ ሲሆን መመሪያው ተዘጋጅቶ ሲጠናቀቅ ለትምህርት ቤቶች የሚላክ መሆኑን በውይይቱ ተገልጿል።

❤31