Telegram Web
ዛሬ ማለዳ የከተማችንን የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ማካሄድ ጀምረናል ።

(ጥቅምት 8/2018 ዓ.ም) በግምገማ መድረኩ በሩብ ዓመቱ የታቀዱ እና የ90 ቀን አበይት ተግባራት የደረሱበት የአፈፃፀም ደረጃ ይገመገማል። መድረኩ የተገኙ ዉጤታማ አፈፃፀሞችን ይበልጡን አልቀን በማስቀጠል እና የታዩ ጉድለቶችን በማረም እንዲሁም ትኩረት እና የተለየ ርብርብ የሚሹ ተግባራትንም ለይተን ቀጣይ አቅጣጫ የምናስቀምጥበት ይሆናል ።

ፈጣሪ ኢትዮዽያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
36👍5🤮3
የአዲስ አበባ ከተማ አስትዳደር በሩብ ዓመቱ ምገባን በተመለከተ ካከናወናቸው ተግባር ውስጥ:-

👉 የተማሪዎች የዩኒፎርም ስርጭትን በተመለከተ በበጀት ዓመቱ ከ1,029,090 በላይ በነፃ ለተማሪዎች ዪኒፎርም ማቅረብ ተችሏል ፡፡

👉 የተማሪ መማሪያ ደብተር ከ8 ሚሊይን በላይ በነፃ ለተማሪዎች ማቅረብ ተችሏል፡፡

👉 የመምህራን ጋዋን ስርጭት 52,603 የመምህራን ጋዋን ለማሰራጨት በእቅድ ተይዞ ሙሉ ለመሉ ተፈጽሟል፡፡

👉 የተማሪዎች ምገባ አገልግሎት ሽፋንን ወደ 976,702 በማሳደግ ተማሪዎች በምገባ ፕሮግራሙ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ አፈፃፀሙም ከባለፈዉ ተመሳሳይ ወቅት ከነበረዉ በ136,117 ተማሪዎች ብልጫ ያሳያል፡፡

👉በተጨማሪም በ26 የምገባ ማዕከላት በቀን አንድ ጊዜ መመገብ የማይችሉ ዜጎችን በቀን ከ36,600 በላይ ሰዎችን እየመገበ ይገኛል::
62👍32👏6🦄3🥰1
2025/10/20 08:25:41
Back to Top
HTML Embed Code: