Telegram Web
የቢሮ አጠቃላይ ካውንስል አባላት የስራ ክፍሎችን የ15 ቀን እቅድ አፈጻጸም ግምገማ በመቀጠል በዛሬው እለት የትምህርት ቤት መሻሻል ዳይሬክቶሬትን አፈጻጸም ገምግመዋል።


(ጥቅምት 5/2018 ዓ.ም) በመርሀግብሩ የአጠቃላይ ካውንስል አባላቱ የትምህርት ቤት መሻሻል ዳይሬክቶሬት በ15 ቀናት በቁልፍ ተግባራት አመላካች እና በሪፎርም ስራዎች ያከናወናቸው ተግባራት ሪፖርት በዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ ቀጸላ ፍቅረማርያም ቀርቦ ውይይት አካሂደዋል።



የትምህርት ቤት መሻሻል ዳይሬክቶሬት የትምህርት ቤቶች ደረጃ ተሻሽሎ ተማሪዎች ምቹ በሆነ የመማሪያ ቦታ ትምህርታቸውን መከታተል እንዲችሉ የተለያዩ ተግባራትን የሚያከናውን የስራ ክፍል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ ጠቁመው ዳይሬክቶሬቱ በ15 ቀናት ያከናወናቸውን ውጤታማ ተግባራት በተለይም መልካም አስተዳደርን ከማስፈን ፣ አገልግሎት አሰጣጥን በቅልጥፍና ከመስጠት ፣ ብልሹ አሰራርን ከማስወገድ ረገድ የሰራቸውን መልካም ተግባራት አጠናክሮ በማስቀጠል እና በአፈጻጸም የተስተዋሉ ክፍተቶችን በማረም በቀጣይ ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል።


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ በበኩላቸው የቢሮው አጠቃላይ ካውንስል አባላት የስራ ክፍሎችን አፈጻጸም በየ15 ቀኑ በመገምገም በቀጣይ ውጤታማ እንዲሆኑ አቅጣጫ በማስቀመጥ ላይ መሆናቸውን ገልጸው የትምህርት ቤት መሻሻል ዳይሬክቶሬት በትምህርት ተቋማት አከባቢ የሚገኙ አዋኪ ተግባራት እንዲወገዱ ያደረገው ድጋፍና ክትትል የሚበረታታ መሆኑን በመጥቀስ ዳይሬክቶሬቱ በቀጣይ የትምህርት ቤቶች ደረጃ እንዲሻሻል ከባለድርሻሻል አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባው አመላክተዋል።
54👍4🥰1😈1
የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የተዘጋጀውን ስትራቴጂ ተግባራዊ ለማድረግ በተዘጋጀ የማላቅ ስትራቴጂ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።


(ጥቅምት 6/2018 ዓ.ም) በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት እና የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች የተሳተፉ ሲሆን በመርሀግብሩ የማላቅ ስትራቴጂው በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በከተማ አስተዳደሩ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ውጤታማ እንዲሆን ቢሮው አራት ተግባራትን ያካተተ ስትራቴጂ አዘጋጅቶ ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ መሆኑን ገልጸው የማላቅ ስትራቴጂው ስትራቴጂውን በአግባቡ ተግባራዊ ማድረግ እንዲቻል መዘጋጀቱን አስረድተዋል።

ኃላፊው አያይዘውም በከተማ አስተዳደሩ የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከሚፈተኑ ተማሪዎች መካከል 60 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በቀጥታ እንዲገቡ በስትራቴጂው መቀመጡን ጠቁመው የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች ስትራቴጂው በአግባቡ ተግባራዊ ሆኖ የሚፈለገው ውጤት እንዲመዘገብ ወላጆችን ጨምሮ ሁሉንም ባለድርሻ አካል በማስተባበር ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

ስትራቴጂው መሰረት በየክፍለ ከተማው በሚቋቋሙ የክላስተር ማዕከላት የመንግስትና የግል ትምህርት ቤት ተማሪዎች ብቁ በሆኑ መምህራን የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠትን ጨምሮ በስትራቴጂው የተቀመጡ ሌሎች ተግባራትን በአግባቡ በመተግበር ተፈታኝ ተማሪዎቹን ውጤታማ ለማድረግ እንቅስቃ ሴ መጀመሩን የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጥላዬ ዘውዴ የማላቅ ስትራቴጂውን ባቀረቡበት ወቅት አመላክተዋል።
31
በ2018 ዓ.ም 1ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ከክፍለከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡


(ጥቅምት 6/2018 ዓ.ም) በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈንታሁን እያዩ የ2018 ትምህርት ዘመን 1ኛ ሩብ ዓመት የቁልፍና አበይት ተግባራት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተካሂዱዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር ቢሮው ቀደም ሲል ሪፖርቱን በማኔጅመንት እንዲሁም በአጠቃላይ ካውንስል አባላት እና የተቋሙ ሰራተኞች በተገኙበት መገምገሙን ገልጸው በትምህርት ሴክተሩ በዝግጅት ምዕራፍ የሚከናወኑ ተግባራት በተግባር ምዕራፍ የሚከናወኑ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ መሰረት የሚጥሉ በመሆናቸው ክፍለከተሞች በሩብ አመቱ የነበራቸውን አፈፃፀም በመገምገም በቀጣይ የተሻለ ስራ መስራት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡

በመርሀግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳምሶን መለሰ የ2018 ዓ.ም የተማሪ ምዝገባ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተካሂዱዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
42👍6
2025/10/19 19:41:18
Back to Top
HTML Embed Code: