Telegram Web
ፍቅር

በአንድ ወቅት ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ቢላል ኢብኑ ረባህን ከኃላው በፍቅር ስሜት እቅፍ አድርገው ይይዙትና ድምፃቸውን ቀይረው...

❤️ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) :- "እኔ ማን ነኝ"?

ቢላል (ረ.ዐ) :- ዑመር (ረ.ዐ) ነህ?

❤️ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) :- አይደለሁም

ቢላል (ረ.ዐ) :- አቡብክር (ረ.ዐ) መሆን አለብህ?

❤️ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) :- አሁንም ተሳስተሃል

ቢላል (ረ.ዐ) :- በቃ ዑስማን (ረ.ዐ) ነህ?

❤️ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) :- አላወቅከኝም

ቢላል (ረ.ዐ) :- ዓሊ (ረ.ዐ) ነህ ማለት ነው...
እያለ ያቀፈውን ሰው ማንነት ሲጠይቅ ይቆያል።

ከዚያም ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ለቀቅ አደረጉትና ከፊት ለፊቱ በመምጣት

"ቢላል ሆይ! እውነት እኔ መሆኔን አላወቅክም ነበር እንዴ"? ሲሉ ጠየቁት

ቢላልም "የአላህ መልእክተኛ ሆይ!" በደንብ አውቄዎታለሁኝ ነገር ግን ለረጂም ጊዜ እንድታቅፉኝ ስለፈለኩኝ እንጂ ሲል መለሰላቸው።

❤️ሰለዋቱ ረቢ ወሰላሙ አለይከ ያ ረሱሊላህ❤️

@yasin_nuru @yasin_nuru
ስለ ቻይና ሙስሊሞች 10 ነገሮች

🔷 ኢስልምናን ለመጀመሪያ ጊዜ ቻይና የደረሰው በዑመር (ረዐ) ኸሊፋነት ዘመን በታላቁ ሰሃባ ‹‹ሰዓድ ኢብን አቢ-ወቃስ›› (ረዐ) እንደሆነ ይነገራል።

🔷 በቻይና የመጀመሪያውን መስጂድ ያሰራውም ሰዓድ ሲሆን ‹‹ሑዓሼንግ›› የሚባልና አሁንም በይዞታ የሚገኝ የ1300 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ መስጂድ ነው።

🔷 በአገሪቱ 80 ሚሊዮን የሚገመቱ ሙስሊሞች እንዳሉ የሚገመት ሲሆን ከህዝቡን 2% ገደማ ይሸፍናሉ።

🔷 ሙስሊሞቹ በብዛት የሚኖሩበት ቦታ ‹‹ዢንጂያንግ›› ሲባል ከአፍጋስታን፣ ፓኪስታን፣ ህንድ፣ ታጃኪስታን እና ሌሎች ጋር የሚዋሰን ሰፊ ግዛት ነው።

🔷 ‹‹ዢንጂያንግ›› ቀድሞ የዑስማያ ኸሊፌት የተርኪስታን ግዛት የነበረ ሲሆን ኸሊፋው ከወደቀ በኋላ በ1949 ቻይና በሐይል ልትወስደው ችላለች። ግዛቱም ከቻይና ሰፊው ሲሆን በማዕድን የበለፀገ ነው።

🔷 ቻይና ውስጥ ሁለት አይነት ነገድ ያላቸው ሙስሊሞች ያሉ ሲሆን ‹‹ሐም›› እና ‹‹ኡግሁር›› ይባላሉ። ሐሞች ቻይናዊ ሲሆኑ ኡግሁር ደግሞ በመልካቸውም የተለዩ የመካከለኛው ኤዥያ ዝርያዎች እንደሆኑ ይታመናል።

🔷 በቻይና ሁሉም ሙስሊሞች መድሎ ቢደርስባቸው ከፍተኛ በደል የሚፈፀምባቸው ግን የኡግሁር ሙስሊሞች ናቸው።

🔷 የኡግሁር ሙስሊሞች ከሌላው በተለየ በደል የሚደርስባቸው አንደኛው በዘራቸው ቻይናዊ ስላልሆኑ ሁለተኛው ደግሞ አካባቢው በማዕድን የበለፀገ ስለሆነ መንግስቱ ህዝቡን የማጥፋት ዕቅድ እንዳለው ይነገራል።

🔷 ቻይና በኡግሁር ሙስሊሞች ላይ ከምትፈፅመው ግፍ መካከል  ወላጅና ልጅን መነጣጠል፣ በማጎሪያ ካምፖች ማሰር፣ አካላቸውን መበለት፣ ሰላት፣ ፆምና ቁርኣን መከልከል፣ አልኮል ማስጠጣት፣ የአሳማና ውሻ ስጋ ማስበላት፣ መግደል እና ሌሎችንም ይፈፅማሉ።

🔷 የቻይና መንግስት ይህን ሁሉ አሰቃቂ ግፍ እየፈፀመ ድርጊቱ ‹‹ሽብርተኝነት›› አልተባለም።

👉 በዑመር (ረዐ) ዘመን የቻይና መንግስት ለፋርስ ንጉስ መጠጊያ እንኳን ለመስጠት ኸሊፋውን በመፍራት እንቢ ማለቱ ይነገራል። ዛሬ የሙስሊም አገራት የኡግሁር ሙስሊሞች አሰቃቂ ግፍ እየተፈፀመባቸው እያዩ ከቻይና ጋር የንግድ እንቅስቃሴያቸውን እንኳን ማቆም አልቻሉም።

‹‹አይሁዶችንና እነዚያን ያጋሩትን ለእነዚያ ለአመኑት በጠላትነት ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ የበረቱ ሆነው በእርግጥ ታገኛለህ።››
(ማዒዳህ 82)

© ሰል ማን

@yasin_nuru @yasin_nuru
ገንዘብ ደስታን አይፈጥርም ብላችሁ ካሰባችሁ



ብሩን ወደ አካውንቴ ላኩልኝ አለ አንዱ😁

ኧረ አልሃምዱሊላህ እንበል

@yasin_nuru @yasin_nuru
🛤በውስጥ መስመር የተላከልኝ ማስታወሻ
- ስሞት አላስብም፣ አልጨነቅም፣

- ገላዬ ፈራሽ ነውና ምን አሳሰበኝ

ሙስሊም ወንድሞቼ መደረግ ያለበትን ሁሉ ያደርጉልኛል፡፡

1- ልብሴን ያወልቃሉ፣

2- ያጥቡኛል፣

3- ይከፍኑኛል፣

4- ከቤቴ ይዘውኝ ይወጣሉ፣

5- ወደ አዲሱ ቤቴ (መቃብር) ይወስዱኛል፣

6- ብዙዎች ጀናዛዬን ለመሸኘት ይመጣሉ፣

7- እኔን ለመቅበር ሥራቸውንና ቀጠሯቸውን ሁሉ ትተው የሚመጡ አሉ፡፡

ቀጠሯቸ መካከል ምናልባት ላንዳፍታ እንኳን ስለኔ አስበው የማያውቁ ብዙ ናቸው፡፡

8- ቤተሰቦቼ እኔን ላለማስታወስ ያለኝን ነገር ሁሉ አውጥተው ይጥሉ ይሆናል፤ አሊያም በኔ ሥም ይመፀውቱ ይሆናል

- ቁልፎቼ 🔑🗝

- መጽሐፎቼ 📚

- ጫማዎቼ 👟

- ልብሦቼ 👖👔…..

በአንድ ነገር ግን እርግጠኛ ሁኑ፡፡

- በመሞቴ ይህች ዱንያ ሐዘኗ አልበዛም፣ አለች አልፈረሠችም፣

- የዓለም 🌍 እንቅስቃሴም ላፍታ አልቆመም፣

- የኢኮኖሚው 💰 ቀውስም አልተፈጠረም፣

- በሥራ ቦታዬ ላይ ሰው ለመቅጠር ማስታወቂያ🧾 ይወጣል፣

- ንብረቴ 💸🏠🚘 የወራሾቼ ይሆናል፣ በትንሽ በትልቁም ኦዲት የምደረገው ግን እኔ ነኝ፣

- ስሞት መጀመሪያ ከኔ የሚገፈፈው ስሜ ነው፡፡ በሥሜ መጠራቴ ይቀራል፤

- ጀናዛው የታለ እባላለሁ፡፡ ጀናዛውን ዉሰዱ፣ አምጡ እንስገድበት፣ ጀናዛውን እንቅበር … ይባላል

- ሥልጣኔ፣ ከተከበረ ቤተሰብ መሆኔ፣ ጎሳዬ … ሁሉ ዋጋ ያጣል፤



ዱንያ ይህን ያህል ቀላልና ተራ ነገር ነች፤ የምንሄድበት ዓለም ግን አቤት ክብደቱ! ማስፈራቱ! …

በሕይወት ያለህ ወዳጄ ሆይ! በመሞትህ ሦስት ዓይነት ሐዘን አለ

1- የሚያውቁህ ዋ ያ ሚስኪን እኮ ሞተ! ይላሉ

2- ባልደረቦችህ ለሰዓታት አለያም ለቀናት ያዝኑና ወደ ሳቅና ጨዋታቸው ይመለሳሉ፣

3- ትልቁ ሐዘን ያለው ቤትህ ነው፣ ቤተሰብህ ጋ … ሁሌም ያስታውሱህ ይሆናል፣

የዱንያ ታሪክህ በዚህ መልኩ አበቃ ፤ የመጨረሻው ዓለም ታሪክህ ተጀመረ

ሁሉ ነገርህ ተወሰደ፣ ፈረሠ፣ አለፈ፣ ጠፋ!!!

1- መልክህ፣

2- ሀብትህ፣

4- ጤናህ፣

5- ልጅህ፣

6- ቪላህ፣

7- ዝናህ፣

8- ሚስትህ/ባልሽ

ካንተ ጋር ሥራህ ብቻ ቀረ

እውነተኛው ሕይወት ተጀመረ፡፡

እዚህ ላይ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ/ሽ

ለአኺራህ ምን አዘጋጀህ!! እስቲ በጥልቀት አስብ፡፡

እናም በርታ፣ በርቺ እህቴ

1- በግዴታዎች፣

2- በሱንና ነገሮች፣

3- በድብቅ መፅውት፣

4- መልካም ሥራ አብዛ፣

5- ሌሊት ተነስተህ ስገድ፣

ትድን ዘንድ ጠንክር፣ ይሳካልህ ዘንድ በርታ፡፡

መልካም ንግግር ምጽዋት ነው፡፡ ምንም የለኝም አትበል፡፡ ሌላ ነገር ብታጣ ይህችን በእጅህ የገባችውን ፅሑፍ መጽውት፣ ምንም ጉልበትና ጊዜ አይወስድብህምና አታመንታ፡፡

ለወዳጅ ዘመዶ ሼር ሼር ሼር .....✔️

#Copied

@yasin_nuru @yasin_nuru
ብስክሌት ጠጋኝ የነበረው የአሁኑ
ኮንትራክተር ጓደኛዬ እንዴት ሰለመ ??
===============
T.me//yeyasine_wedaje
ከጓደኝነታችን በፊት ክርስቲያን የነበረው ጓደኛዬ በጣም የሚገርም አስደናቂ ባህሪ እንደ ነበረው ከበፊት ጓደኞቹና ጎረቤቶቹ ሰምቻለሁ ። በፊት የነበረው መልካም ባህሪውና ቆራጥነቱ  ዛሬ ላይ በእስልምና ውስጥ የበለጠ ውበት አጎናፅፎታል ።
_
ይህ ሰው  ከጎረቤቶቹ መካከል አንድ እግረ  ሽባ የሆኑ ሙስሊም ሰው ነበሩ ። እኚህ ሰው ሁሌም ባይሆን ለጁምዓ ሰላት ከመስጅድ አይቀሩም ነበር ።

ይህ ጎረቤቱ አርብ አርብ ሁሌም እየተንፏቀቁ ወደ መስጅድ ሲሄዱና ሲመጡ ሲመለከት በውስጡ ያስጨንቀው ጀመረ ።
_
አንድ ቀን በውስጡ ይህን ሰው በብስክሌቱ ወደ መስጅድ ማድረስና ከሰላት ቡሃላ ጠብቆ መመለስ እንዳለበት ወሰነ ። ይህን ሀሳብ ለሰውዬው ሲያማክራቸው እሳቸውም በጣም በመደሰት ዱዓ አድርገውለት በሀሳቡ ተስማሙ ።
_
የመጀመሪያውን ጁምአ ለሰላት አድርሷቸው ከመስጅድ ቅጥር ግቢ ውጪ ሆኖ ከኹጥባ በፊት በሼኽ ኢብኑ ዩሱፍ የሚደረገውን የኹጥባ ተፈሲርና በኢማሙ እርጋታ የሚነበበውን የአርብኛ ኹጥባ በድምፅ በማጉያ ሲያዳምጥ የማያውቀው ስሜት ልቡን ተቆጣጠረው።
_
የሁለተኛው ጁምዓ እስኪደርስ ጨነቀው ቀኑም ደረሶ የመስማት እድል አግኝቶ አዳመጠ  እንዳባለፈው ጁምዓም የሰማው ነገር ሁሉ ልቡን አሸብሮታል ። ጉዳዩ ወደ ሌላ ምእራፍ ተሻገረ ። ደገመ ደጋገመ ። ደካማን በመርዳት እዝነት የጀመረችው ልቡ የአላህንና የሩሱለላህን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ንግግር ለመስማት በፍቅር ተጠለፈች ።
_
የተወሰነ ሳምንታት ከተመላለሰ ቡሃላ እሱን ወደ መስጅድ እንዲመላለስ ሰበብ የሆኑት ሰውዬ በሁለት ጁምዓ መሃል ወደ አኺራ ሄዱ ።
_
ይህ ሰው ውስጡ ሀዘን ቢኖርም በየጁምዓው ከመስጅድ ቅጥር ግቢ ውጪ በመሆን ውስጡን የማረከውን ኹጥባ ለማዳመጥ መመላለሱን አላቋረጠም ።
_
አንድ ቀን ለይለተል ጁምዓ በመናም በህይወቴ አይቼ ማላውቀው በጣም የሚያምር ሰው እጄን ይዞ መስጅድ አብረን ገባን ኹጥባም ሰማሁ ሰላትም ስግጄ ከመስጅድ እየወጣን ሳለ ከእንቅልፍ ነቃሁኝ  የመጀመሪያው የሱብሂ አዛን  ወአሽሃዱ አነ ሙሀመደን ረሱለላህ እያለ ነበር የነቃሁት ።
_
ታዲያ ይህንን መናም ለማስፈታት ማንም ጋር መሄድ አልፈለገም የጁምዓ ሰላት ወቅትን ጠብቆ እንደበፊቱ ሰው ሊያደርስና ኹጥባ ሊሰማ ሳይሆን ከሙስሊሞች ጋር
የሚቀላቅለውን ሰው ለመፈለግ ነበር የወጣው ።
_
በመጨረሻም ከሰፈራቸው አንድ ሻይ ቤት የነበረው መሀመድ የሚባል ሰው ጋር በመሄድ ወደ መስጅድ  ይዞት እንዲሄድ ሲጠይቀው ሙሀመድም በመጀመሪያ ሸሃዳ
መያዝ እንዳለበት ይነግረዋል ።
_
እሱም ሸሃዳ ምንድነው ቢለው << አሽሃዱ አንላ ኢላሀ ኢለላህ ወአሽሃዱ አነ ሙሀመደን ረሱለላህ >> ብለህ ትመሰክራለህ ሲለው ይህንንማ ማታ ያ ሚያምር ሰው አስብሎኛል ብሎ ማታ ያየውንና የሰማውን  ነገረው ።
_
ሙሀመድም እየተገረመ ወደ መስጅድ በመውሰድ ከኡለሞች ጋር በማገናኘት የነገረውን ሲነግራቸው ኡለሞቹም እኛ ረሱለላህ ያሰለሙትን ሰው ደግመን አናሰልምም ባይሆን ደስ እንዲለን እስቲ ያሉህን ንገረን አሉት ።
_
ጓደኛዬም የመጨረሻውን ምእራፍ እነዚያ ከመስጅድ ቅጥር ግቢ ውጪ ሆኖ በፍቅር ምክራቻውን ሲሰማ ልቡን በፍቅር ያሸበሩትን  ኡለሞችን ፊት ፊታቸውን እያየ የሰማውን ሸሃዳ ለኡለሞች አስደምጦ …………… ገቢ ሆነ ።
_
በሰአቱ ቦታው ላይ የነበሩት ኮሚቴዎች ህዝብ ፊት ቆሞ መስለሙን እንዲገልፅና ህዝቡም  የደስታ መገለጫ ስጦት እንደሚሰጡት ሲነግሩት እሱ ግን መስለሜን መናገር እችላለሁ ። ግን ስጦታ ያላቹትን ግን ማርያምን አለፈልግም ሲል የኮሚቴዎች ሳቅ መልሶ እሱንም አስቆት እስላምን መኖር ከጀመረ ይኸው ሁለት አስር አመታቶች አለፉት ።
==============
_
ረሱለላህ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሰዎችን ወደ ኢስላም ያስገቡት በዳእዋ ፣ በዱዓ ፣ በኢክራም ፣ በኢኽላስና በአኽላቅ ሲሆን አብዛኛው ሶሀባ ኢስላምን የተቀበሉት በአኽላቃቸው ነበር ።
_
ኢማናችን፣ተቅዋችን ፣ኢኽላሳችን፣እንዲሁም ኢባዳዎቻችንን ለሌሎች አይታያቸውም ነገር ግን  አኽላቃችንን ነው የሚመለከቱት ።

አላህ ያግራልን !!

Jan 31 2020

@yasin_nuru    @yasin_nuru
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የ2ኛው አለም አቀፍ የቁርአን እና የአዛን ውድድር የመክፈቻ ስነ ስርዓት በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ
♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️
በዘይድ ኢብኑ ሳቢት የቁርአን ማህበር አዘጋጅነት በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የበላይ ጠባቂነት በመጭው እሁድ በአዲስአበባ ስታዲየም የሚካሄደው ሁለተኛው አለም አቀፍ የቁርአን እና አዛን ውድድር የመክፈቻ ስነ ስርዓትና የማጣሪያ ውድድር በዛሬው ዕለት በኢሊሌ ሆቴል እየተካሄደ ይገኛል።

የማጣሪያ ውድድሩ ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ60 የተለያዩ ሀገራቶች የመጡ ተወዳዳሪዎች የሚሳተፉበት ሲሆን የዛሬውን የማጣሪያ ውድድር ያለፉ ተወዳዳሪዎች በመጭው እሁድ በአዲስአበባ ስታዲየም የፍፃሜ ውድድር ተፋላሚ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

በዛሬው ዕለት በኢሊሌ ሆቴል እየተካሄደ በሚገኘው የማጣሪያ ውድድር የመክፈቻ ዝግጅት ላይ የፌዴራል እና የአዲስአበባ መጅሊስ አመራሮች ፣ አለምአቀፍ የቁርአን ውድድር ዳኞች ፣ ከተለያዩ ሀገራት የተጋበዙ ሊቃውንት ፣ኡለማኦች ኡስታዞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

2ኛው አለም አቀፍ የቁርአን እና የአዛን ውድድር የማጣሪያ ውድድር!

ቀጥታ ስርጭት ከአዲስአበባ

https://www.facebook.com/haruntube/videos/1758213854960067/?app=fbl



@yasin_nuru @yasin_nuru
ረመዷን 30 ቀን ቀረው!😍😍

30 days until Ramadan!

اللهم بلغنا رمضان
ይቅርታ 31 ቀን ነው የቀረው

@yasin_nuru
ከእለታት አንድ ቀን የአላህ መላክተኛ (ሰ ዐ ወ) መንገድ ላይ ሳሉ አንዲት በእድሜ የገፉ ሴት እቃ ተሸከመው ይመልከቱና፤ወደሴትዬዋ ጠጋ በማለት እናቴ እቃውን ላግዞት በማለት ይጠይቃሉ?!

ሴትዮዋም የአላህ መላክተኛ ስለመሆናቸው የሚያቁት ነገር አልነበረም፤እቃው ከራሳቸው ላይ አውርደው ሰጧቸው፤የ አላህ መላክተኛም
(ሰ ዐ ወ) እቃውንም ተሸክመው እስከ በር ድረስም አደረሱላቸው።

ሴትዮዋ ትንሽ ጠብቀኝ ብላቸው ወደቤት ገቡ፤
የአላህ መላክተኛ (ሰ ዐ ወ) ሴትዮዋ እስኪመጡም ጠበቁ፤ ሴትዮዋም ከቤት በመውጣት እንዲህም አሉ፦
ሊጄ ምክር ብሰጥህ ትቀበለኛለህ አሉ?የአላህ መላክተኛም (ሰ ዐ ወ) እንዴት አልቀበልም ሲሉ መለሱ፤ሴትዮዋም ልጄ እኔ አደራ የምልህ
የሙሀመድን እምነት እንዳትከተል ነው አሉ፤
የአላህ መላክተኛም(ሰ ዐ ወ) እንዲህም አሉ እኔ ሙሀመድ ከሆንኩኝስ አሉ?!ሲሉ ጠየቋቸው!

ሴትዮዋም አንተ ሙሀመድ ከሆንክማ ከአላህ ሌላ አምላክ የለም ሙሐመድም የአላህ መላክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለው አሉ፤

እንዲህ ነበር የአላህ መላክተኛ (ሰ ዐ ወ)አለምን በፀባያቸው የገዙት!!!

እህት ወንድሞቼ እኛስ እውን ባህሪያችን ስራችን ምን ይመስላል?!!

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ ዐ ወ) ለአለም የበሩ ብርሃን ናቸዉ!!

@yasin_nuru @yasin_nuru
Forwarded from ISLAMIC SCHOOL️ (ᴇᴢᴇᴅɪɴ)
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን

የቀሳሞች ጦር መሪ ሙሐመድ ደይፍ ወደማይቀረው አለም መሸጋገሩን አቡ ዑበይዳ በይፋ አስታውቋል።

በሐማስ ስር የሚገኘው ቀሳም የቡድኑ ዋና የጦር አዛዥ ሙሐመድ ደይፍ እና ምክትሉ መርዋን ዒሳን ጨምሮ  የቡድኑ የጦር አመራሮች መሰዋታቸውን ዛሬ ገልጿል።

@islam_in_school
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#በጣም_ልብ_የሚነካ_ታሪክ_ነው

☞በአረብ አለም የሚኖር አንድ የአሥር አመት ታዳጊ ነው

ይህ ታዳጊ የሰራው ነገር ግን ሠውን አጃኢብ አስኝቷል።

ነገሩ እንዲህ ነው: ይህ የአስር አመት ህፃን ዘውትር በሠላት ወቅቶች ከመሥጂድ ይታደማል

ሠላቱም በጀመዓ ይሠግዳል ድምፅ ከፍ ተደርጎ በሚሰገድባቸው ሦስት ሠላቶች ላይ ታዲያ ኢማሙ ፋቲሀን ቀርቶ ሲጨርስ ማለትም ወለዷ ሊን ሲል ሠጋጁ በአንድነት አሚን ሢል ይህ ልጅ ድምፁን ከፍ አድርጎ ከጀመዓው ተነጥሎ ብቻውን አሚን ይላል....

ይህ ነገር በመደጋገሙ ኢማሙን እጅግ ያበሳጨው ነበር ቢያየው ቢያየው ልጁ ሊያቆም ስላልቻለ አንድ ቀን ከመግሪብ ሠላት በኃላ ንዴቱን መቆጣጠር ያቃተው ኢማም ይህን ልጅ እንቅ አድርጎ አንጠልጥሎ ያምባርቅበታል!

ለምንድነው ምትረብሸው ከጀመዓው ጋር አብረህ ለምን አሚን አትልም እና መሰል ነገሮችን ይህን ህፃን ልጅ ተናገረው😡😡

ይህ ታዳጊ በፍርሃት በተሸበሸቡት ልብሶቹና
ቲማቲም በሚመሥሉ ጉንጮቹ እምባ ያቀረሩ አይኖቹ ያንን ኢማም በሥሥት እየተመለከቱ...

«እኔ ምጮህው አለ......
እኔ ምጮህው እቤታችን መስጂዱ አጠገብ ነው አባቴ ደሞ ሠላት አይሰግድም ምናልባት የኔን ድምፅ ሢሠማ ደስ ብሎት አልያም ተደንቆ ከመጣና ከሠገደ ብዬ ነው ያ ኢማም» ብሎ መለሰለት🥺🥺

ይህን ጊዜ ኢማሙ ሚናገረው ጠፋው ሠውነቱ ተርገፈገፈ😔😔

የአከባቢውን ሠው አፈላልጎ ይህን ለአባቱ አደረሠው አባቱም በልጁ ተግባር እጅግ ተደንቆ ወደ ጌታው እያለቀሰ ተውበት በማድረግ ሠላቱን ጀመረ።

ሰዎችን አይተን ብቻ በችኮላ አንፍረድ። ይህን ለመስራት ያበቃቸው ምን ምክንያት ሊኖር ይችላል ብለን ኡዝር እንፈልግላቸው ምናልባት መጥፎ ሥራ የሚሰሩ መስሎን ሲፈተሽ ግን በጣም የሚደንቅ ሊሆን ይችላል!!   

ሱብሃን አላህ

Darul

@yasin_nuru     @yasin_nuru
ነገ ጠዋት ከማለዳው 12:30 ጀምሮ አዲስ አበባ

ነገ እሁድ በአዲስ አበባ ስታዲየም የቁርኣንና የአዛን ውድድር ይካሄዳል።

እንዳትቀሩ!

@yasin_nuru
ጥር 25፣ 2017 ዓ.ል | ሻዕባን 3፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የበላይ ጠባቂነት የሚካሄደው 2ኛው ዙር ዓለም አቀፍ የቁርአን እና የአዛን የፍፃሜ ውድድር በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚካሄድ ሲሆን የውድድሩ ታዳሚዎች በብዛት ወደ ስታዲየሙ እየገቡ ነው።

ዝርዝር መረጃውን እየተከታተልን እናቀርባለን።

••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
የኢት/እ/ጉ/ጠ ምክር ቤት ሕዝብ ግንኙነት።

@yasin_nuru
ጥር 25፣ 2017 ዓ.ል | ሻዕባን 3፣ 1446 ዓ.ሒ
بِسْمِ ٱللَّهِ ٱلرَّحْمَٰنِ ٱلرَّحِيمِ            
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
2ኛው ዙር ዓለም አቀፍ የቁርአንና የአዛን ውድድር ተጠናቀቀ።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••••
አዲስ አበባ |

በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የበላይ ጠባቂነት በዘይድ ኢብኑ ሳቢት የቁርአን ማህበር አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው ዓለም አቀፍ ሁለተኛ ዙር የቁርአንና የአዛን ውድድር ተጠናቀቀ።

በቁርአን ሂፍዝ፣ በቁርአን ቲላዋና በአዛን ዘርፍ አሸናፊዎች በዳኞች አማካኝነት ይፋ ሆኗል።

በወንዶች በቁርአን ሂፍዝ አሸናፊዎች
1ኛ. ሙሐመድ ፉዓድ … ከሊቢያ
2ኛ. ዩሱፍ አሺር … ከኳታር
3ኛ. አህመድ በሺር …ከአሜሪካ

በሴቶች የቁርአን ሂፍዝ ውድድር አሸናፊዎች
1ኛ. ሩቅያ ሳላህ … ከየመን
2ኛ . ነሲም ጀናዉጃ … አልጄሪያ
3ኛ.  ቀመራ ወሊዩ መሐመድ … ከኢትዮጵያ

በአዛን ውድድር አሸናፊዎች
1ኛ ሙሀመድሻን አቡበከር … ከኢንዶኖዢያ
2ኛ ኡመር ዱራን … ከቱርኪዬ
3ኛ አደም ጅብሪል … ከኢትዮጵያ

በወንዶች የቁርአን ቲላዋ የአሸናፊዎች ዝርዝር
1ኛ አብዱራዛቅ አል ሸሀዊ  …ከግብፅ
2ኛ ከራር ለይስ … ከኢራቅ
3ኛ አንጀድ ካምዳን … ከየመን 

ጥር 21 ተጀምሮ ዛሬ በተጠናቀቀው ሁለተኛ ዙር ዓለም አቀፍ የቁርአንና የአዛን ውድድር ላይ ከ60 በላይ ሀገራት ተሳትፈውበታል።

ውድድሩ እንዲሳካ በሁሉም የውድድር ሂደት ጥረት ላደረጉ ዓሊሞችና የውድድሩ ዳኞች መቀመጫቸውን አሜሪካ ባደረጉት ፈርስት ሂጅራና ተቀዋ ሐበሻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው 2ኛው ዙር የቁርአንና የአዛን ዓለም አቀፍ ውድድር ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የኡለማዕ ጽህፈት ቤት፣ የአዲስ አበባና የኦሮሚያ እስልምና  ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤቶች ስራ አስፈፃሚዎች፣ ዲፕሎማቶች እና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍል ተወካዮች የታደሙ ሲሆን ይህ ዓለም አቀፍ የቁርአን መድረክ በቁርአን ተከፍቶ በቁርአን ተዘግቷል።

@yasin_nuru @yasin_nuru
🔰 ለእያንዳንዱ ሙስሊም በጀነት 72 ሚስት ይኖረዋልን??🔰
➸ አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ በዚህ ቅርቢቷ ዓለም የፈጠረን እሱን ብቻ አምልከን ጀነት እንድንገባ ነው።

➸ አላህ እንዲህ ይላል👇
"ጋኔንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡
(📗ሱረቱ አል-ዛሪያት - 56)

➸ ከሴትና ከወንድ በአላህ አምኖ አላህን ብቻ የሚያመልክና  መልካም ስራ የሚሰራ ሰው በጀነት አይን አይታው፣ጆሮ ሰምታው፣ልብ ላይ ውል ብሎ የማያውቅ ትልቅ ፀጋ ያገኛሉ።
(📗ሱረቱ አል-ሰጅዳህ፣ - 17)
[📚ኢማም ቡኻሪይ ሐዲስ 3244]
እነዚህ ፀጋዎች ለሁለት ይከፈላሉ
1. መንፈሳዊ ፀጋ ሲሆን ጀነት ውስጥ ከሚያገኛቸው ፀጋዎች ትልቁ ፀጋ  የአላህን ፊት ማየት ነው።
2. ሥጋዊ ጸጋዎች ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ደግሞ አላህ ለምዕመናን ያዘጋጀላቸውን (ታይተውም ሆነ ተቀምሰው) የማይታወቁትን ፍራፍሬዎች መብላት፣ ከሚስታቸው ጋር የመኖር ፀጋ ወዘተ ናቸው።
ዛሬ የምናየው የጀነት ሰዎች ስለሚያገኟቸው የጀነት ሚስቶች ነው።
ለሴቶችስ ምን አለላቸው ለሚለው ጥያቄ በኡለሞች የተሰጠውን መልስ👇👇
https://www.tgoop.com/iwnetlehullu1/357
☝️☝️ ተጭነው ይመልከቱ☝️☝️
ስለ ሌላ ዝርዝር ነገሮች ሌላ ግዜ እናያለን ኢንሻአላህ  አሁን ለእያንዳንዱ ወንድ 72 ሚስት ይሰጠዋል ስለሚለው እናያለን ኢንሻአላህ።
➸ሀዲሱ ኢብኑ ማጃህ ላይ የሚገኝ ሲሆን አላህ እያንዳንዳችሁን 72 ሚስት ያጋባችኃል ይላል።
ይሄ ሀዲስ በትክክል ከነቢያችን ﷺ ተረጋግጧል ወይስ ዶዒፍ(ደካማ) ሀዲሰ ነው የሚለውን እናያለን

➸በሀዲስ ጥናት ላይ ጎልተው ከወጡት እና ከሱ በኃላ አምሳያው እንዳልተነሳ የሚመሰከርለት ሀፊዝ ኢብኑ ሀጀር የሶሂሁልቡኻሪይ ሸርህ በሆነው ፈትሁል ባሪ ኪታባቸው ላይ
"እያንዳንዱ ሙእሚን 72 ሚስቶች ይሰጠዋል፣ከመቶ ሴቶች ጋር ይገናኛል፣5000 ወይም 4000ሚስቶች ወዘተ የሚሉ ሀዲሶችን እየጠቀሰ ሀዲሶቹ ሰነዳቸው ላይ ችግር ድክመት ስላለባቸው ዶዒፍ(ደካማ) መሆናቸውን ጠቅሷል። ደካማ የሆኑበትን ምክንያት እዛው ጠቅሷል።
ወደ 4000 ወይም 5000 ሚስቶች የሚለው ደግሞ በሰነዱ ላይ ስሙ ያልተጠቀሰ ዘጋቢ ስላለ ዘገባው ዶዒፍ ደካማ ነው።
ከዚያ በኃላ የታላቁ ኢማም ኢብኑል ቀይም ንግግር አስከትሎ አመጣና
ኢማሙ " የጀነት ሰዎች በጀነት ሚስቶች አሏቸው ከሚለው ሀዲስ ውጭ ከሁለት ሚስት በላይ ይሰጣቸዋል የሚል ሶሂህ(ትክክለኛ) የሆነ ዘገባ የለም። 
- ትክክለኛው" ለእያንዳንዱ ሙእሚን ሁለት ሚስት አለው የሚለው ነው። ብለዋል
📚ፈትሁልባሪ ሸርህ ሶሂህ አልቡኻሪይ ቅጽ 7 ገፅ 544

ሐፊዝ አቡ ኑዐይም አልአስባሃኒይ
"72 ሚስት ያገኛሉ የሚለው ሀዲስን በጠቀሰበት ላይ ሀዲሱ የመጣበት ሰነድ(ሰንሰለቱ) ላይ ኻሊድ ኢብኑ የዚድ የሚባል ዶዒፍ(ደካማ) የሆነ ዘጋቢ ስላለበት ሀዲሱ ضعيف جدا በጣም ዶዒፍ ነው።የሚል እናገኛለን
📚 ሲፈቱ ሶላት ሊአቢ ኑዐይም አልአስባሃኒይ ገፅ 205 ሀዲስ 370

ከኪታቡ በቀጣይ ገፁ ላይ "73 ሚስት ያገኛሉ የሚለውን በጠቀሰበት ላይ ሀዲሱ የመጣበት ሰነድ(ሰንሰለቱ) ላይ ሐጃጅ ኢብኑ አርጠአህ የሚባል ስህተተ ብዙ እና ሙደሊስ የሆነ ዘጋቢ ስላለበት የሀዲሱ ሰነድ ضعيف ዶዒፍ ደካማ ነው። ኢማሙ ዘሀቢይ "ዘጋቢው ሙንከር የሆኑ(በጣም ደካማ የሆኑ) ሀዲሶችን የሚዘግብ ነው። የሚል እናገኛለን
📚 ሲፈቱ ሶላት ሊአቢ ኑዐይም አልአስባሃኒይ ገፅ 206 ሀዲስ 372
➸ ታላቁ የሀዲስ ሊቅ ኢማሙል አልባኒይ የሶሂህነት መስፈርት ያላሟሉ(ዶዒፍ ሀዲሶችን በሰበሱበት ኪታቦቻቸው ላይ
" 72 ሚስት የሚለውን ሀዲሱን ከጠቀሱ በኃላ "ሀዲሱ ضعيف جدا በጣም ደካማ የሆነ ሀዲስ ነው" ብለዋል
📚 ሲልሲለቱል አሃዲስ አድዶዒፋህ ወልመውዱዓህ ቅጽ 9 ገፅ 456 ሀዲስ 4473
በኢብኑ ማጃህ የተዘገበው 72 ሚሰት የሚለውን ሀዲሱን ዶዒፍ ብለውታል
📚 ዶዒፍ ሱነን ኢብኑ ማጃህ ገፅ 364 ሀዲስ 5002
➸ ታላቁ ኢማም ኢብኑል ቀይም በኪታባቸው ላይ 
- ስለ 72 ሚስት የሚያወራው ሀዲስ የመጣበት ሰነድ(ሰንሰለት) ላይ ኻሊድ ኢብኑ ዘይድ የሚባል ዘጋቢ አለ።
ይህን ዘጋቢ ከሰለፎች ታላላቅ ኡለሞች ዶዒፍ(ደካማ) መሆኑን ተናግረዋል።
*ያህያ ኢብኑ መዒን* ደካማ ነው
*ኢማሙ ነሳኢይ* ታማኝ አይደለም ብሏል።
*ኢማሙ አድዳረቁጥኒይ* ዶዒፍ ነው ብሏል።
* ኢብኑ ዓዲይ" ደግሞ ይሄ ስለ 72 የሚወራው ሀዲስ ሙንከር ተደርጎበታል ብሏል።

-73 ሚስት ይሰጣቸዋል የሚል ሀዲስ ላይ ደግሞ አሕመድ ኢብኑ ሐፍስ የሚባል ዘጋቢ አለ። ይሄ ዘጋቢ ብዙ ሙንከር(ተቀባይነት የሌላቸው) የሆኑ ዘገባዎች አሉት
📚ሐዲ አልአርዋሕ ኢላ ቢላዲል አፍራሕ ገፅ 501-502

- በቀን መቶ ሴትን ይገናኛሉ የሚለው ሀዲስ ሰነድ ላይ ሑሴን አልጁዕፊይ የሚባል ዘጋቢ አለ። ይህንን ሀዲስ ኡለሞች ኢንካር ያደረጉበት የሆነ ሀዲስ ነው። ኢማም ኸጢብ አልበግዳዲይ ሀዲሱ ዶዒፍ ነው ብሏል
📚 ሐዲ አልአርዋሕ ኢላ ቢላዲል አፍራሕ ገፅ 503
☝️ኢማም ኢብኑል ቀይም እነዚህ ሀዲሶች ዶዒፍ መሆናቸውን ከጠቀሱ በኃላ
"ትክክለኛ ዘገባ የመጣው ሁለት ሚስት እንደሚሰጣቸው ነው ከሁለት ሚስት በላይ ይሰጣቸዋል የሚል ሶሂህ(ትክክለኛ) የሆነ ዘገባ የለም። 
📚 ሐዲ አልአርዋሕ ኢላ ቢላዲል አፍራሕ ገፅ 505

➸ ከዚህ ምንረዳው ካፊሮች እያንዳንዳችሁ 72 ሚስት ታገኛላችሁ እያሉ የሚያመጧቸው ሀዲሶች ዶዒፍ ደካማ መሆናቸውን እንረዳለን። ያመጧቸው ሀዲሶች ለነሱ ማስረጃ ሊሆኑላቸው አይችሉም። ምክንያቱም ሀዲስን ማስረጃ አድርጎ ለማቅረብ ያ ሀዲስ ከነቢዩ ﷺተረጋግጦ የመጣ መሆን አለበት
📚 ሸርህ መንዙመቱል በይቁንያህ ኢብኑ ዑሰይሚን ገፅ 21

ከላይ እንዳየነው ሀዲሶቹ ዶዒፍ(ደካማ) ናቸው።
ባለፈው ርዕሳችን ላይ እንዳየነው ሰለፎች ዘንድ ዶዒፍ የሆነን ሀዲስ ማስረጃ ሊደረግ እንደማይችል አይተናል።
በተጨማሪ👇
📚ሸርህ መንዙመቱል በይቁንያህ ኢብኑ ዑሰይሚን 60
📚 ሙስጠለሁል ሀዲስ ኢብኑ ዑሰይሚን ገፅ 16
ለእያንዳቸው ከ 2 በላይ ሚስቶች ይሰጣቸዋል የሚለው ሀዲስ ዶዒፍ(ደካማ) ከሆነ ስንት ነው የሚሰጡት ከተባለ👇
ኡለሞች ትክክለኛነቱ ላይ የተስማሙበት የሆነ በቡኻሪይ እና ሙስሊም ሌሎች ኪታቦች ላይም በተዘገበ ሀዲስ ላይ
" ለእያንዳንዳቸው ሁለት ሚስት ይሰጣቸዋል"
📚ሶሂህ አልቡኻሪይ ሀዲስ 3245 እና ሀዲስ 3246
e፣ ሶሂህ ሙስሊም 2834 መፅሐፍ 53, ሀዲስ 20
የሚል ሶሂህ ሀዲስ እናገኛለን።
➸ አንዳንድ 72 ሚስት የሚለው ሀዲስን ሶሂህ ያደረጉ ኡለሞች ሁለት ሚስት የተባለው ከዱንያ(ከዚህ ዓለም) የሆኑ ሴቶች ሲሆኑ ሰባዎቹ ደግሞ ከሁረል ዓይን ናቸው ቢሉም ይሄ አያስኬድም። ምክንያቱም ሶሂህ በሆነ ሀዲስ ላይ
" ለእያንዳንዳቸው ከሁረል ዓይን የሆኑ ሁለት ሚስቶች ይሰጣቸዋል"
📚ሶሂህ አልቡኻሪይ ሀዲስ 3254
የሚል ስላለ ትክክለኛው እና ሶሂህ ማስረጃዎች የሚደግፉት ለእያንዳንድ ሙዕሚን ሁለት ሚስቶች ይኖረዋል የሚል ነው።

ኢብኑ ረጀብ ረሂመሁላህ እንዲህ ይላሉ
"ለእያንዳንዱ ሰው ሁለት ሚስት ይሰጣቸዋል። በደረጃቸው ልክ ከሁለት በላይ የሚኖራቸው ቢኖሩም ( 72፣73፣100 እንደሚባለው) የሴቶቹ ብዛት በቁጥር የሚገድብ ሶሂህ የሆነ ማስረጃ የለም
📚 አትተኽዊፍ ሚን አንናር ገፅ 268
➤አልሃምዱሊላሂ ረቢል ዓለሚን➤

ከላይ የጠቀሰኳቸውን ማስረጃዎች ከኪታብ በማስረጃ ከፈለጉ ይህንን ይጫኑ👇👇
https://www.tgoop.com/iwnetlehullu1/460
☝️☝️☝️☝️☝️
አስራሚ እውነተኛ ታሪክ
የታሪኩ ረእስ የተቅዋ ጠቀሜታ

አንድ እውቀት ፈላጊ ተማሪ እና እርሱን የሚያስተምሩት አንድ አሊም ነበሩ። እኝህ አሊም ከለታት አንድ ቀን ለዚህ ተማሪና ለጎደኞቹ የሚከተለውን ምክር መከሯቸው ከሰው ዘንድ ለማኝ ከጃይ እንዳትሆኑ። አሊም የሆነ ሰው እሲ ስጡኝ ብሎ እጁን ወደሰው የሚዘረጋ ከሆነ ምንም ኸይር አያገኝም። ለራሱም ለድኑም ውርደት ነው የሚከናነበው። ስለዚህ እናነተ ወዳባቶቻችሁ ሂዱና አባቶቻችሁ የሚሰሩትን ስራ ስሩ ወይም አግዞቸው። ታዳ በምትሰሩት ስራ ሁሉ አላህን ፍሩ። ከዚህ ቡሀላ ተማሪወቹን ወደ የጉዳያቸው አሰናበቱአቸው።
ይህ ወጣት ተማሪ ወደ እናቱ ሄደና አባቴ የሚሰራው ምን አይነት ስራ ነበር ብሎ ጠየቃት። እናቲቱም የአባቱን ስራ ለመንገር በጣም ተቸገረች። እንደገና ቡሀላ አባት ወደ አኼራ ሂዲአል የእርሱ ስራ ላንተ ምን ያደርግልሀል አለችው። ልጁ ካልነገርሽኝ ብሎ አስጨነቃት። ጥያቄ ሲያበዛባት አባትህ ሌባ ነበር አለችው።

ልጅየውም ሸይኻችን አባታችን የሚሰራውን ስራ እንድንሰራ ነገር ግን አላህ መፍራት እንዳለብን መክረውናል አላት። እናቲቱም ምን ማለትህ ነው? እየሰረክ እንዴት ነው አላህን የምትፈራው? ስትል የግርምት ጥያቄዋን ጠየቀችው። እናትና ልጅ በሀሳብ ሳይግባቡ ተለያዩ። ልጁ ግን ወደ አንድ ቦታ ሂዶ የአሰራረቅ ዘደወችን ተማር።

በሌብነት ስልቶች ከተካነ ቡሀላ ትምህርቱንም የሸህየውን ምክርም ተግባራዊ ለማድረግ ወሰነ። የኢንሻን ሶላት ሰግዶ ሰው እስኪተኘ ድረስ አድፍጦ ጠበቀ። ከዚያም ከቤቱ ወጣ በቅድሚያ ወደአንድ ጎረቢት ቤት ወስጥ ገብቶ ለመስረቅ ነበር ያሰበው። ነገር ግን የሸህየውን አላህ ፍሩ ተግሳጽ  አስታወሰ ጎረቢትን ማስቸገር አላህ ከመፍራት አይደለም አለና ይህንን ቤት አልፎ ወደሌላ ቤት ተሻገረ። ይህ ቤት ደግሞ የየቲሞች ነው ለነፍሱም ይህ ቤት የየቲሞች ቤት ነው። አላህ ደግሞ የየቲሞችን ገንዘብ መብላት እርም ( ሀራም) አድርጎታል አለ።

ይህንኛውንም ቤት ትቶ ወደቀጣዩ ቤት አለፈ። እንድህ እንድህ እያለ ወደ አንድ ሀብታም ነጋደ ቤት ደረሰ ቤቱም ዘበኛ አልነበርውም ።  ይህ ሀብታም ብዙ ገንዘብ እንዳለው ሰው ሁሉ ያውቃል ከአስፈላጊ በላይ ትርፍ ገንዘብ እንዳለው ይታወቃል እዚህ ቤት ነው መግባት ያለብኝ ብሎ በተመሳሳይ ቁልፍ በሩን ከፍቶ ወደ ቤት ውስጥ ገባ።
ሰፊ ግቢና ብዙ ክፍሎች ያሉት ቤት ነው። ወደዋናው ቤትም ገብቶ ካዝናውን ከፍቶ ሲመለከት,,,,,


ወርቅ እና አልማዝ እንድሁም ብዙ ገንዘብ አገኘ። ያገኘውን እቃ ይዞ ለመውጣት ሲል ሁሉንም መውሰድ የለብኝም ምክንያቱም ሽይሀችን አላህ ፍሩ ብለውናልና ምን አልባት ይህ ነጋዴ ዘካ ያላወጣ ከሆነ መጀመሪያ ከገንዘቡ ዘካ ማውጣት አለበት አለ ።

ካዝናው አጠገብ ተቀምጦ ያገኘውን መዝገብ ፊኖስ አብርቶ መመርመር ጀመረ። እንዳጋጣሚ በሂሳብ ጎበዝ ነበርና ገንዘቡን ቆጥሮ ዘካውን አሰበ። ሂሳቡን ሲያሰላ ብዙ ሰአት ወስዶበት ኖሮ የፈጅር (የሱብሂ) ሶላት ደርሷል። አላህን የመፍራት መጀመርያው ሶላት መስገድ ነውና ወደመታጠቢያ ክፍል ውስጥ በመግባት ውዱእ አደረገ። ለሶላት አዛን አደረገ።

የቤቱ ባለቤት አዛን በቤቱ ውስጥ ሲሰማ ግራ በተጋባ ስሜት እና ድንጋጤ ተነሳ ሚስቱም ተከትላዋለች። የሚያስገርም ነገር ነበር የተመለከተው ፋኖሱ በርቱአል የገንዘብ ማስቀመጫው ሳጥኑ ወለል ብሎ ተከፍቷል በአቅራቢአው አንድ ሰው አዛን ይላል። ሚስቱ በአላህ እምላለሁ እየሆነ ያለው ነገር ምንም አልገባኝ አለች። አዛኑን ከጨረሰ ቡሀላ ሰውየው ወደልጁ ቀርቦ ሰውየው ምን አይነት ጉደኛ ነህ ማነህ አንተ ሌባ አለው።

ልጁም ፈርጠም ብሎ መጀመርያ ሶላት እንስገድና ከዛ ቡሀላ እናወራለን ይለዋል። ባለቤቱም ውዱእ አደረገ ልጁም ለባለቤቱ በል ቅደም ቅደምና አሰግደን ኢማምነት ለባለቤት ነውና አለው። ባለቤቱም ምን አልባት መሳርያ ይኖረዋል ብሎ ስለፈራ ኢማም ሁኖ አሰገደ። እንደት እንደሰገደ ግን አላህ ብቻ  ነው የሚያውቀው። ሶላት ሰግደው እንደጨረሱ ባለቤቱ ወደልጁ በመዞር ማነህ ምን እያደረክ ነው ያለኸው? ጉዳይህ ምንድነው ሲል የጥያቄ ውረጅብኝ አወረደበት። ልጁም,,,,,,,,,,


ልጁም ያላወጣኸውን የዘካ ገንዘብ ሂሳብ እያሰላሁልህ ነበር የስድስት አመት ዘካህን አስቤ ጨርሸልሀለሁ ይህን የዘካ ገንዘብ ለሚገባቸው ሰወች እንድትሰጣቸው ለብቻ አስቀምጨልሀለሁ አለው።

ባለቤቱም በመገረም ሌላ ጥያቄ ጠየቀ ለመሆኑ አንተ እብድ ነህ? ልጁም ይህን ያደረገበትን ምክንያት ከመጀመርያው ጀምሮ ለባለቤቱ አጫወተው። ነጋደውም የልጁን ታሪክ ካደመጠ ቡሀላ ሂሳቡ ትክክል እና ምንመ ያልጎደለው መሆኑን አረጋግጦ ወደሚስቱ ሄደ። የልጁንም ታሪክ በዝርዝር አጫወታት።

ይህ ነጋዴ አንድት ልጃገረድ ልጅ ነበረችውና ወደሌባው ልጅ ተመልሶ እንድህ አለው : ልጀን ብደርህና  እና የሂሳብ ሰራተኛየና ፀሀፊየ ባደርግህ እናትህንም ደግሞ እኔ ጋር ባስቀምጣት እንድሁም አንተን በተጨማሪ በንግድ ሽርክና ባስገባህ ደስ ይልሀል? ልጁም እሽ እቀበላለሁ አለ። እንደነጋም ነጋዴው ምስክሮችን ጠራና ኒካሁን አሰር የጋብቻ ስነስረአት ተደረገ። የነጋደው ሴት ልጅና ሌባው ተጋቡ።

አላህን በቁረአኑ አላህን የፈራ እሱ መውጫ ያበጅለታል። እርዚቅም ካላሰበበት ያመጣለታል ይለናል። ለዚህም ነው ይህ ወጣት አላህን ፈራ ካላሰበበት እርዚቅ አመጣለት። በማጭበርበር በስርቆት በማታለል እሚመጣ ነገር የለም ቢመጣም ለግዜው ይመስለናል እንጅ መጨረሻው ውርደት ነው አላህ የተቅዋ ሰወች ያድርገን


ፀሀፊ አረቡ ዩሱፍ

       ምንጭ ቀሶስ ኢማኒያት ከሚለው
                     መፅሀፍ የተወሰደ

#ረመዳን_23_ቀን_ቀረው🥰


@yasin_nuru    @yasin_nuru
2025/02/07 00:11:22
Back to Top
HTML Embed Code: