Telegram Web
🌾 ከኢስላም መርሆች...

﴿أَطْعِمُوا الْجَائِعَ، وَعُودُوا الْمَرِيضَ، وَفُكُّوا الْعَانِيَ﴾

“የተራበን መግቡ፣ የታመመን ጠይቁ፣ እስረኛን ፍቱ።”
@ychanut
🌾 መልካም ሰዎች የቱንም ያህል መጥፎ ለመሆን ቢጥሩ አይሳካላቸውም ምክንያቱም በውስጣቸው ያለው መልካምነት መጥፎ ከመሆን ይከለክላቸዋልና።
@ychanut
🌾አስተግፊሩሏህ
ሱብሐነላህ
አልሐምዱ ሊላህ
አሏሁ አክበር
ላ ኢላሀ ኢልለሏህ
@ychanut
🌾 በድቅድቅ ሌሊት፣
በባህር ጨለማ፣
በዓሳ ሆድ ዉስጥ ተሁኖም ጭምር የተስፋ ጭላንጭል አለ።
ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ።

@ychanut
🌾መክፈል የማይቻሉ ብድሮች አሉ!! በህይወት ዘመናችን ፈፅሞ የማንከፍላቸው።
@ychanut
🌾 ጀሊሉ ወደ ጀልባው ከመራህ እንዳትሰምጥ መቅዘፉ ያንተ ድርሻ ይሆናል። አስተንትን...
@ychanut
🌾 አምስት ናቸው!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿حَقُّ المُسْلِمِ على المُسْلِمِ خَمْسٌ: رَدُّ السَّلامِ، وعِيادَةُ المَرِيضِ، واتِّباعُ الجَنائِزِ، وإجابَةُ الدَّعْوَةِ، وتَشْمِيتُ العاطِسِ﴾

“ሙስሊም በሙስሊም ላይ ያሉት መብቶች አምስት ናቸው። ሰላምታ ባቃረበልህ ግዜ ሰላምታውን ልትመልስለት፣ ሲታመም ልትጠይቀው፣ ጀናዛውን ልትሸኝ፣ ለግብዣ ጥሪ ባደረገልህ ግዜ ልትሄድ። አስነጥሶት አላህን ካመሰገነ ‘አልሀምዱሊላህ ካለ’ ምህረት ልትጠይቅለት።”
@ychanut
🌾 አንዳንድ ሰዎች እንደ ሲጋራ ናቸው የወደዳቸውን የሚገሉ። ወዳጅ ተወዳጅ ሁናችሁ ዝለቁልኝ👏
@ychanut
🌾ማጣት ማለት ሙታኖችን ማጣት ነው እንጂ
በህይወት ያሉትማ ይተካካሉ ።
@ychanut
🌾«ለምትጎነጨው ውሃ እንኳን ቢሆን ከሰዎች ፈላጊ ሆነህ በቀረብካቸው ቁጥር፤እነርሱ ዘንድ የሚኖርህም ክብር በዚያው ልክ ይወርዳል»።

ሸይኩል ኢስላም ኢብን ተይሚያ (ረሂመሁላህ)
@ychanut
🌾ከሞት ይልቅ መኖር የሚያስፈራበት ግዜ ላይ ደርሰናል። ግና አብሽሩ መሽቶ አይቀርም ይነጋል።
@ychanut
🌾 አልሓምዱሊላህ!!
@ychanut
🌾በቸገረህ ጊዜ ሰዎች ከጎንህ ላለመቆም ምክንያት እየደረደሩ ሲሸሹህ አብሽር እኔ ከጎንህ ነኝ አለሁልህ ያለህን ሰው ፈፅሞ አትርሳ እርሱ እውነተኛ ወዳጅህ ነውና።
@ychanut
🌾"ልብህ እንዲለሰልስ ከፈለክ የተቸገሩትን መግብ የየቲሞችን እራስ ዳብስ።" (የውዱ ነብይ መልእክት)
@ychanut
🌾“ልብ የልብን ጠረን ያሸታል” ይላሉ ኢብነል ቀይዪም። አንዳንዴ መውደድ የልብ ትውውቅ ነው። ብዙ ያላወራኸውን፣ ብዙም የማታውቀውንና ምንም ያላደረገልህን ሰው እንዲሁ ትወደዋለህ። "ለምን ወደድከኝ?” ብለህ ምክንያት ብትጠይቅ ምክንያት የማይነግርህ ብዙ ወዳጅ አለ።
@ychanut
🌾ለሰዎች ጥላቻን ማሳየት ከጀመርክ በቃ ተሸንፈሃል።
@ychanut
🌾ዓለም ሁሉ የሱ ነች።
እኛም ባሮቹ ነን።
ከቁጣህ አይሁን እንጂ
ጌታዬ እንደሻህ አርገን።
@ychanut
🌾ይቅርታው ይፀናል፤ ግና ወዳጅነቱ እንደነበር እንዴት ሊመለስ ይችላል??

#ይቅርታ ቢደረግም ወዳጂነትን ቀድሞ እንደ ነበረ መመለስ ግን አይቻልም!!
@ychanut
🌾“ጌታዬ! ኃጥያት ባይኖርብኝ ቅጣትህን አልፈራም ነበር። ቸርነትህን ባላውቅ ኖሮ ደግሞ ምንዳህን አልከጅልም ነበር።”
ወደድኩት ይህን ዱዓ…
@ychanut
🌾"ስታድግ ይገባሃል" ከተባለከው ውስጥ ስንቱ ገብቶሃል?? ካልገባህ ገና አላደክም።
@ychanut
2025/02/25 19:31:17
Back to Top
HTML Embed Code: