ከኃጢአት ቀጥሎ ኃፍረት አለ። ከንስሓ ቀጥሎ በጌታ የሆነ ደስታ አለ። ነገር ግን ሰይጣን ይህን ቅደም ተከተል አዛብቶብን በኃጢአት ስንደሰት በንስሓ እናፍራለን።
- ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
- ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
+ የቅዱስ ዮሴፍ የማደጎ ሕፃናት ሥልጠና ተካሔደ +
ጃንደረባው ሚድያ
ሰኔ 2017 ዓ.ም. አዲስ አበባ
በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ ትውልድ ጃን ቂርቆስ 3 ንዑሳን ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ በሆነውና በማደጎ ሕፃናት ላይ በሚሰራው የቅዱስ ዮሴፍ ንዑስ ፕሮጀክት በኩል የተዘጋጀ የመጀመርያ ዙር ስልጠና ልጆችን በማደጎ ወስደው ማሳደግ ለሚፈልጉ እና የማደጎ ሕፃናትን ወስደው በማሳደግ ላይ ላሉ ወላጆች ተሰጠ።
መረጃዎች እንደሚያሳዩት ወላጆቻቸውን በተለያዩ ምክንያቶች የሚያጡ በርካታ ጨቅላ ሕፃናት በየእለቱ ወደሕፃናት ማሳደግያ ይገባሉ። ወደ ማሳደጊያ የሚገቡት እነዚህ ሕፃናት በማሳደጊያ ውስጥ ሙሉ ሆነው እንዲያድጉ የሚያስችላቸው ሁኔታ ባለመኖሩ አካላዊ፣ አእምሯዊ፣ ማኅበራዊ እና መንፈሳዊ እድገታቸው የተሟላ አይሆንም።
በመሆኑም በሁሉም ሁኔታ ውስጥ ያሉ ሕፃናት ሁለንተናዊ እድገታቸው ተሟልቶ እንዲያድጉ የሚሰራው የጃን ቂርቆስ ፕሮጀክት የማደጎ ሕፃናት ላይ የሚሰራ ንዑስ ፕሮጀክት በመቅረፅ ለሕፃናቱ ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል። ንዑስ ፕሮጀክቱ ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች መሀል ሕፃናትን በማደጎ ወስዶ በማሳደግ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ግዴታን መወጣት በሚኖረው ጠቀሜታ ዙርያ የማሳወቅ ስራ መስራት፣ ሕፃናትን በማደጎ ወስደው ማሳደግ ለሚፈልጉ ወላጆች በማደጎ ልጆች አስተዳደግ ዙርያ ስልጠና መስጠት፣ በሕፃናቱ አስተዳደግ ዙርያ ቀጣይነት ያለው ማማከር እና ክትትል ይጠቀሳሉ።
ስልጠናው በማደጎ ሕጋዊ አሰራሮች እንዲሁም በማደጎ ወላጅነትና ተያያዥ ጉዳዬች ዙሪያ ያተኮረ ሲሆን ተሳታፊዎች ባነሷቸው ጥያቄዎች ላይም በባለሞያዎች የታገዘ ውይይት ተደርጓል ። በተጨማሪ በስልጠናው ላይ ልጆችን በማደጎ ወስደው በማሳደግ ላይ ያሉ ወላጆች፣ ልጆች ወስደው ለማሳደግ ህጋዊ ሂደት የጀመሩ እና በማደጎ ልጆችን የመውሰድ ሃሳብ ያላቸው ወላጆች የተገኙበት በመሆኑ በተሳታፊዎች መካከል የልምድ ልውውጥ ማድረግ ተችሏል።
በቀጣይም ወላጆቻቸውን አጥተው በማሳደግያዎች ውስጥ የሚገኙ ሕፃናት እናትና አባት አግኝተው እድገታቸው የተሟላ እንዲሆን ለማስቻል በስፋት ለመስራት እቅድ ተይዟል።