“በዙፋንም የተቀመጠው፦ እነሆ፥ ሁሉን አዲስ አደርጋለሁ አለ።" (ራእይ 21፥5)
#ውድ_የተዋህዶ ልጆች_የቻናሎቼ_ተከታዮች
እንኳን ከዘመነ ዮሐንስ ወንጌላዊ ወደዘመነ ማቴዎስ ወንጌላዊ በሰላም እና በጤና አሸጋገራችሁ::
ቀን እና ሌሊትን
ሳምንታትን እና ወራትን
አመታትን እና አዝማናትን እያፈራረቀ በዕድሜያችን ላይ ዕድሜን ጨምሮ ለአዲሱ ዘመን ያደረሰን ከዘመናት በፊት የነበረ ዘመናትንም አሳልፎ የሚኖር ለህላዌው ዘመን የማይቆጠርለት ቸሩ አምላካችን መድኃኔዓለም ስለማይነገር ስጦታው እስከዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን::
አዲሱ አመት ዘመን የምንቀይርበት ብቻ ሳይሆን እኛም ተቀይረን ለክብር የምንበቃበት ይሁንልን።
ብዙዎች ይቺን ቀን ለማየት ናፍቀው ያላዩ በሞት የተጠሩ አሉ።
ብዙዎች በህመም በየ ሆስፒታሉ በየፀበሉ ያሉ አሉ።
በመከራ በስቃይ በችግር ውስጥ ያሉ አሉ እኛን ግን እግዚአብሔር ነብዩ 'በቸርነትህ' አመታትን ታቀዳጃለህ'' (መዝ 65:11) ብሎ አንደተናገረው በስራችን ሳይሆን በቸርነቱ አዲሱን አመት ያሳየን ቸሩ አምላካችን የተመሰገነ ይሁን።
ቅዱስ ጴጥሮስ በመጀመርያው መልእክቱ ምዕራፍ 4-3 ላይ
“የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል።”
ብሎ ባለፈው ዘመን ከኖርንበት የኃጢአት መንገድ እንድንመለስ ያስተምረናል::
እኛም ከክፋት፣ከተንኳል፣ከመከፋፈል በጠቃላይ ከክፉ ተግባር ርቀን እግዚአብሔርን የምናስደስትበት ዘመን ያድርግልን።
ዲ/ን ተረፈ ተስፋዬ ነኝ።
@ty1921
@webzema @menefesawinet @kinexebebe @yedawit_begena @amantaakoo @yeberhanljoche @esxifanose

ጥቅምት 14/2017 #ሐዋርያዉ_ቅዱስ_ፊልጶስ
#ፃድቁ_ገብረ_ክርስቶስ
👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን አምላካችን መድኃኒታችን #ኢየሱስ_ክርስቶስን በቅዱሣኑ ስም ለምናመሰግንበት ቅዱሳኑን በምልጃ ፀሎታቸው እንዲራዱን ለምንማፀንበት አመታዊ የእረፍት በአላቸዉ እንኳን አደረሰን
👉ሐዋርያዉ #ቅዱስ_ፊልጶስ በጋዛ ምድር ኢትዮጵያዊውን ጃንደረባ #ባኮስን ያጠመቀው ረድኡ ሐዋርያ #ቅዱስ_ፊልጶስ ዕረፍቱ ነው ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ባለውለታችን ነዉ
👉 #በእግዚአብሔር ፈቃድ ሰማያዊውም ሆነ ምድራዊውን ውለታ የዋለልን የኾነውና ለመጀመሪያ ጊዜ በሐዲስ ኪዳን #የእግዚአብሔርን_ቃል የተናገረን የክርስትና ጥቀምት አባትና አጥማቂያችን ከ72ቱ አርድዕት አንዱ የኾነው ቅዱስ ሐዋርያው ፊልጶስ በሀገራችን ብቸኛ የሆነውና በ አ.አ ኮልፌ አጠና ተራ በሚገኘው ደብረ ምጥማቅ ቅዱስ ፊሊጶስ ቤተክርስቲያን በዓለ ዕረፍቱ ይከበራል
እነሆ በውሀ እንዳልጠመቅ የሚከለክለኝ ምንድን ነው የሐዋርያት ሥራ 30÷56
👉 #ቅዱስ_ገብረ_ክርስቶስ አባቱ የቁስጥንጥያ ገዢ የነበረው ንጉሥ ቴዎድዮስ እናቱ የቁስጥንጥንያ እመቤት መርኬዛ የሚባሉ ሲሆኑ ጥቅምት አስራ አራት በዓለ ዕረፍቱ ነዉ ደጋግ የሆኑት በሀይማኖት በምግባር ፀንተው #እግዚአብሔርን በመፍራት የሚኖሩ ቤተሰቦቹ ልጅ አልነበረቻውምና ኢየሩሳሌም ድረስ ሄደው በስለት ያገኙት ልጃቸው ነው
👉በስለት ያገኙትም ስለሆነ በግዕዙ #ገብረ_ክርስቶስ በአማርኛ የአምላክ አገልጋይ
👉በማለት ስሙን አውጥተውለታል የንጉስ ልጅ እንደ መሆኑ በጥበብ በዕውቀት #አግዚአብሔርን በመፍራት አሳድገውታል ለአካለ መጠን በደረሰም ሥልጣኑን የሚረከብ ነውና ለሮሜው ንጉስ ልጅ ከሆነችው ጋር አጭተው በስርዐታቸው አጋብተዋቸዋል
👉በምድራዊ ሕይወት ሰማያውያን መላእክትን በሚያስመስለው በድንግልና ሕይወት ይኖር ዘንድ ውሳኔው ነውና ይህንን ነገር ለሙሽሪት አስረድቷት #እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ይሁን ብሏት #የክርስቶስ ሙሽራ ሆኖ በሌሊት ከጫጉላው ወጥቶ በመርከብ ተሳፍሮ ርቆ ሄዷል
👉አባቱም በወታደሮቹ ቢያስፈልገው ሊያገኘው አልቻለም እርሱ ግን በእንዲት #ቤተክርስቲያን_አፀድ ስር ከነዳያን ጋር ተቀምጦ እራሱን ሰውሮ 15 ዓመት ያህል ኖሯል በኋላም ለአንድ መነኩሴ የእርሱ ነገር ተገልፆለት ለህዝቡ ቢናገርበት ታወቀብኝ ብሎ ርቆ ሄዷል
👉 #በእግዚአብሔርም ፍቃድ ወደ አባት እናቴ ቤት ሄጄ በዚያ እየተመፀወትኩ እኖራለው ብሎ ሂዷል በዚያም ትራፊ አየተደፉበት ውሾች እንዲበሉት አጥንት ቢደፉበትም ፤ውሾቹ ግን የእግሩን ቁስል ይልሱለት ነበር በዚህም ሕይወት 15 ዓመት ያህል ኑሯል
👉ቅዱሱም የ30 ዓመት የሕይወቱን ዜና በክርታስ ይፅፍ ነበር እና ጥቅምት 14 ቀን በንጽሕና በቅድስና ሕይወት #የክርስቶስ ሙሽራ እንደሆነ ነፍሱ ከስጋው ተለይታለች
👉የፃፈውም ተነበበ በቤተ መንግስቱም ታላቅ ሀዘን ተደረገ በዚያኑም ቀን በክብር ገንዘው ቀብረውታል በዚያም ጊዜ ብዙ #ድውያነ_ስጋ_ተፈውሰዋል ህዝቡም ከሚገባው በላይ በዝቶ ነበርና ንጉሡ የወርቅ ገንዘብን እየበተነ ህዝቡ ገንዘቡን ሲለቅም በዚያኑ ባረፈበት ቀን ጥቅምት 14 ቀን ሊቀ ጳጳሱ በተገኙበት ስረዓተ ቀብሩ ተፈፅሟል
👉በግንቦት 14 ቀን #ከጫጉላ_ቤት_የመነነበት በስሙ በታነፀ ቤተክርስቲያን በድምቀት ይከብራል ወረሐዊ መታሰቢያውም በ14 ነው
👉የሐዋርያው #ቅዱስ_ፊልጶስ የፃድቁ #ገብረ_ክርስቶስ ምልጃና ፀሎት ሁላችንንም ይጠብቀን ረድኤት በረከታቸው አይለየን "አሜን"✝️ 💒 ✝️
@yeberehanljoche

ራስን መግዛት እንዴት ?
መንፈሳዊው ሰው ካሉት ብቃቶች መካከል አንዱና ዋነኛው ራስን መግዛት ነው፡፡ እርሱ ራሱን ለሥጋ ምኞትና ለፍላጎቶቹ አሳልፎ አይሰጥም፡፡ ሕሊናው የኃጢአትን ምኞት ሲናፍቅ ይህን አሳቡን በመቃወም መንፈሱ እንድትመራው በማድረግ ራሱን አጥብቆ ይገዛል:: መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል:- «በመንፈሱ ላይ የሚገዛ (መንፈሱን የሚገዛ) ከተማ ከሚወስድ ይበልጣል፡፡» ምሳ. 16፥32
እንደ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ትምህርት ራሱን የሚገዛ ወይም የሚመራ ማለት ሥጋው የጠየቀውን ሁሉ የማይሰጥ ይልቁኑ የሚቃወም ማለት ነው:: «ነፍሱን የሚወድ ያጠፋታል፤ነፍሱን በዚህ ዓለም የሚጠላ ለዘላለም ሕይወት ይጠብቃታል፡፡» ዮሐ. 12፥25።
ራስን መግዛት በውስጡ የተለያዩ ክፍሎች እንዳሉት እርግጥ ነው፡፡ እነርሱም፤-
1. #ምላስን_መግዛት፡፡
2. #አሳብን_መግዛት::
3. #ልብን_መግዛት፡፡ (ፍላጎትንና ምኞትን በመግዛት)
4. #ስሜትን_መግዛት::
5. #ሆድን_መግዛት (ምግብን በተመለከተ) ናቸው፡፡
ራሱን የሚመራ ሰው እርሱነቱን ለእሴትና ለዓላማ እንዲሁም ለሕግና ደንብ ያስገዛል፡፡ ራሱን መምራት የማይችል ሰው ግን በእርግጥ እርሱነቱን ለጥፋት ይጋብዛል፡፡ ራሱን የሚገዛ ሰው ነፍሱን በእውነተኛ ፍቅር ይወዳታል:: ራሱን የሚያቀናጣ ግን ነፍሱን ከማጣቱም በላይ ሌሎችም ከእርሱ ጋር አብረው እንዲጠፉ ያደርጋል፡፡ ራሱን አጥብቆ የሚጠብቀው በትጋቱ ነፍሱን ስለሚጠብቃትና በመልካም ሁኔታ ስለሚይዛት ያድናታል፡፡ አልፎ ተርፎም ሌሎችን ለማዳን ምክንያት ይሆናል፡፡ የራሱን አመለካከትና ግንኙነት በቅደም ተከተል ያደራጃል፡፡ በመጀመሪያ እግዚአብሔርን ያስቀድማል፤ በመቀጠል ሰዎችን ያስከትላል፤ በመጨረሻም ራሱን።👉
#ምላስን_መግዛ፡
መንፈሳዊው ሰው ቃላት ወይም አሳቦች ያቀበሉትን ወደ አእምሮው የመጡትን ሁሉ በአንደበቱ አይናገራቸውም፡፡ እያንዳንዱን ቃል ከአንደበቱ ከማውጣቱ በፊት ይመዝናል:: የእርሱ ሚዛን የሚለካው የቃሉን ፍሬ ነገር ብቻ ሳይሆን ትክክል መሆኑንና አለመሆኑንም ጭምር ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የእርሱ ዋና ዓላማው ቃሉ በሌሎች ሰዎች ላይ የሚያመጣውን ተጽዕኖ፣አፀፋና ውጤቱን ጭምር ነው::
የምላስ ወይም የአንደበት ስህተት ውጤት ሥጋን ማሳደፉንና የፍጥረትንም ሩጫ ማቃጠሉን የሚያውቅ ሰው ከመናገሩ በፊት ከፍተኛ ጥንቃቄ ያደርጋል:: ያዕ. 3፥5-6:: ከነቢዩ ከዳዊት ጋር ሆኖም:- «አቤቱ ለአፌ ጠባቂ አኑር፤ የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ፡፡» ይላል፡፡ እርሱ አንዴ ከአፉ የወጣው ቃል ተመልሶ ሊገባ እንደማይችል ያውቃል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ከአፉ የወጣው ቃል አድማጮቹ ጆሮ ከደረሰ በኋላ የተናገረውን መልሶ ሊውጠው፣ ወይም ይቅርታ ሊያገኝበት እንደማይችል አስቀድሞ ያውቃል:: ከዚህ በኋላ ስህተቱን ለማስተካከል ቢጥርም ጥፋቱ በእርሱ ላይ ዕዳ ሆኖ እንደሚቆጠር አጥብቆ ይረዳል፡፡ ከሁሉ በላይ ደግሞ ጌታ እንደተናገረው እንደሚኮነንበት ያውቃል፡ . . . ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህና፤ ከቃልህም የተነሣ ትኮነናለህ፡፡» ማቴ. 12፥37::
(#በብፁዕ_አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
#መንፈሳዊ_ሰው_መጽሐፍ ገጽ 122-128
#በአያሌው_ዘኢየሱስ_የተተረጎመ

ባስልዮስ ሆይ! ንገረኝ...
በዚህ ዓለም የሥራ መስክ ገበሬ መርከብ ለመንዳት የማይነሣው፣ ወይም ወታደሩ የግብርናን ሥራ የማይሠራው፣ ወይም ሙያው መርከብ ነጂ የኾነ ሰው ጦር እንዲመራ እልፍ ጊዜ ቢጎተትም እንኳ እሺ የማይለው ለምንድን ነው? እያንዳንዱ ያለችሎታው ቢሰማራ የሚከተለውን አደጋ አስቀድሞ ስለሚያይ አይደለምን? ታዲያ ጥፋቱ ቁሳቁስና ንብረት በሚኾንበት ኹኔታ አስቀድመን ብዙ የምናስብና ግፊትና ግዴታን የማንቀበል ኾነን ሳለ፥ ክህነትን እንዴት እንደሚይዙትና እንደሚያገለግሉበት ለማያውቁ ቅጣቱ ዘለዓለማዊ በኾነበት ኹኔታ ግን ያለብዙ ማሰብና ማሰላሰል እንዲሁ በዘፈቀደ ወደዚህ ዓይነት ታላቅ አደጋ ውስጥ ዘለን እንገባለንን? የሌሎች ሰዎች ግፊትስ ምክንያት ሊኾነን ይችላልን? አንድ ቀን ፈታሒ በጽድቅ ኰናኒ በርትዕ የኾነው እግዚአብሔር ይጠይቀናል፡፡ ይህ ሰበብም አያድነንም፡፡
ከምድራዊ ነገሮች ይልቅ በመንፈሳዊ ነገሮች ላይ ይበልጥ ጠንቃቆች ልንኾን ይገባናልና፡፡ በትንንሽ ነገሮች ላይ ጠንቃቆች ስንኾን እንታያለንና፡፡ እስኪ ንገረኝ! አንድ ሰው የቤት ሥራ ሙያ ሳይኖረው ብትሠራልን ስንለው እሺ ብሎ ቢመጣና ከዚያ በኋላ ግን ዕንጨቱንና ድንጋዩን ቢያበላሽና የሠራው ነገር ወዲያውኑ ተበታትኖ ቢወድቅ በራሱ ፈልጎ አለመምጣቱና በሌሎች ግፊት ሥራውን መጀመሩ በቂ ምክንያት ሊኾነው ይችላልን? በጭራሽ! የሌሎችን ግፊትና ጥሪ አልቀበልም ማለት ነበረበትና በርግጥም ተጠያቂ ነው፡፡
ታዲያ እንዲህ እንጨትና ድንጋይ ለሚያበላሽ ሰው በጥፋቱ ከመጠየቅና ከመቀጣት ለመዳን ምንም ምክንያት ከሌለው፥ ነፍሳትን የሚያጠፋ፣ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በግድየለሽነት የሚያንጽ ሰው’ማ እንዴት? የሌሎች ግፊትና ማስገደድ በቂ ምክንያት ይኾነኛል ብሎ ሊያስብ ይችላልን? እንዲህ ብሎ ማሰብስ ሞኝነት አይደለምን?
ፈቃደኛ ያልኾነን ሰው ማንም ሊያስገድደው እንደማይችል ለማሳየት ብዬ ሐተታ መስጠት አያስፈልገኝም፡፡ ነገር ግን ከዚህ በፊት እንደ ተናገርኩት ይህ ፈቃደኛ ያልኾነ ሰው እጅግ ተጭነዉትና ግድ ብለዉት ሌሎች ብዙ መንገዶችንም ተጠቅመው ወደዚህ ኃላፊነት አመጡት እንበል፡፡ ታዲያ ይህ ከቅጣት ሊታደገው ይችላልን? እማልድሃለሁ፤ በፍጹም ራሳችንን አናታልል! ሕፃናት ሳይቀሩ በቀላሉ በሚያውቁት ነገር ላይ እንደማናውቅ ኾነን አናስመስል፡፡ እንደማናውቅ ማስመሰላችን በዚያች ዕለት ላይ በእውነት ያለ ሐሰት ምንም አይጠቅመንምና፡፡
https://www.tgoop.com/yeberhanljoche

††† እንኳን ለዓለም ሁሉ መምሕር ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እና ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ለቤተ ክርስቲያን የብርሃን ምሰሶ ስለሆነላት ስለ ታላቁ ሐዋርያዊ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? እንደ እኔ ያለ ኃጥእ: ለባሴ ሥጋና ገባሬ ንስሃ ስለሱ ሊናገር አይቻለውምና:: አባቶቻችን እንደ ነገሩን ስለ አፈ ወርቅ ለመናገር አፈ ወርቅ መሆን ያስፈልጋል:: እስኪ በቅዱሱ አባት ምልጃ ጥቂት ልሞክር::
††† ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ማን ነው?
††† ነገዱ ከሶርያ: የተወለደው በ347 ዓ/ም በእስክንድርያ ሲሆን አባቱ አስፋኒዶስ እናቱ ደግሞ አትናስያ ይባላሉ:: እነርሱ ደግ ቢሆኑ ይህንን እንቁ ልጅ እግዚአብሔር ሰጣቸው:: ዮሐንስ ለክርስቲያን እንደሚገባ በትምሕርትና በጥበብ አደገ:: ገና በሕጻንነቱ ወደ ግሪክ ሔዶ የዘመኑን ሳይንስ (ፍልስፍና) ከአፉ እስከ ገደፉ ተምሮ ተመልሷል::
ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅን ለየት ከሚያደርጉት ነገሮችም አንዱ ይሔው ነው:: በዘመናዊም ሆነ በመንፈሳዊ ትምሕርት ይህ ቀረህ የማይሉት ሊቅ የሆነው ገና በ15 ዓመቱ ነበር:: በ2 ወገን የተሳለ ሰይፍ በመሆኑ ስንኩዋን በሕይወተ ሥጋ እያለ ዛሬም ለንፉቃን ትልቅ የራስ ምታት ነው::
ቅዱሱ ገና በ16 ዓመቱ ሃብት: ንብረት: ውበት: ክብርና እውቀት የሞላለት ቢሆንም ያለውን ሁሉ ለነዳያን ሰጥቶ መጻሕፍትን ብቻ ሰብስቦ ከባልንጀራው ቅዱስ ባስልዮስ ጋር በርሃ ገባ:: ሰውነቱን በጾምና በጸሎት እየቀጣ በበርሃ ሲኖር ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስና ሊቀ ሐዋርያት ቅዱስ ዼጥሮስ ወደ እርሱ መጡ:: ሊቀ ሐዋርያት የመንግስተ ሰማያትን መክፈቻ ስልጣን ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌሉን ሰጥተው ተሰወሩት::
ከዚህች እለት በሁዋላ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ባሕረ ምስጢራት ሆነ:: ብሉይ ከሐዲስ: ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ ራዕየ ዮሐንስ ድረስ በአንድምታ ትርጉዋሜ ተነተናቸው:: በተለይ ሐዲስ ኪዳንን እየመላለሰ አመሰጠረው:: ቅዱስ ሕሊናው ሳይታክት: ንጹሕ እጆቹ ሳይዝሉ የጻፋቸው ድርሳናት: መልዕክታትና ትርጉዋሜያት ቢቆጠሩ አሥር ሺህ ሞሉ:: በእውነት ለዚህ አንክሮ ይገባል! የሚገርመው ይህን ሁሉ ሲሰራ እድሜው ገና ለጋ: ማዕርጉም ዲቁና ነበር::
ከዚህ በሁዋላ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ቅስና ተሹሞ በስብከተ ወንጌል ብዙ ቦታዎችን አዳረሰ:: በቅድስናው ወደውታልና የቁስጥንጥንያ ፓትርያርክ አድርገው ሾሙት:: አፈ ወርቅ ሲናገርም ሆነ ሲያስተምር እንኩዋን የሚያወራ ኮሽ የሚል የለም:: ከጣዕመ ትምሕርቱ የተነሳ ሕዝቡ በተደሞ ይሰሙት ነበር:: ሲያስተምር ምድራዊው ሰው ይቅርና ልዑላኑ መላእክት ተሰብስበው ያደንቁት ነበር:: አንዴም እመቤታችን በሕዝብ መካከል አፈ ወርቅ ብላ ጠርታዋለች:: ለዛም ነው አፈ ወርቅ የሚባለው:: ቅዱሱ በሥልጣነ ቃሉ መልዐከ ሞትን ገስፆ 10 ዓመት አቁሞታል::
ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ለሰው ፊት አያደላም:: በርሱ ዘንድ ንጉሥና ደሃ ነዳይ እኩል ነው:: ለሞት ያበቃውም ይሔው ነበር:: ምክንያቱም የወቅቱ ንግስት አውዶክስያ ያንዲት ድሃ መበለትን መሬት ቀምታ አልመልስም በማለቷ መክሮ አወገዛት:: እርሷ ግን ከኃጥአንና መናፍቃን ጋር መክራ 2 ጊዜ አጋዘችው:: በተሰደደበት ሃገር ፍሬ አፍርቶ: አስተምሮና አሳምኖ በ407 ዓ/ም አርፏል:: ቤተ ክርስቲያንና ምእመናን ሳይጠግቡት እንደናፈቁት በ60 ዓመቱ አጡት:: በወቅቱ ታላቅ ሐዘንና ለቅሶ ተደረገ::
አንድ ቀን የዘመኑ ደግ ንጉሥ አርቃድዮስ ግብር አገባ:: (ግብዣ አዘጋጀ) በዚያች ሌሊት ደግሞ ቅዱሱ ሊቅ ታጥቆ ሲጸልይ ሳለ: አባ ማርዳሪ የሚባል ጻድቅ ደግሞ 12ቱ ሊቃነ መላእክት (እነ ቅዱስ ሚካኤል) ከሰማይ በግርማ ሲወርዱ ተመለከተ::
ደንግጦ "ወዴት ናችሁ ጌቶቼ" ቢላቸው "ቁስጥንጥንያ: ወደ ዮሐንስ አፈ ወርቅ እንሔዳለን:: እርሱ እመቤታችንን እንደሚያመሰግናት ጌታ ነግሮናልና" አሉት:: "እባካችሁ እኔም የአፈ ወርቅ ምስጋናው እንዲገለጥልኝ መርቁኝ" አላቸው:: ሊቃነ መላእክቱም መርቀውት ጐዳናቸውን ቀጠሉ::
በማግስቱ በቤተ መንግስት ውስጥ ሊቃውንቱ: መሳፍንቱ: ዻዻሳቱ: ሕዝቡ ሁሉ ተሰብስበው ከድግሱ በሉ:: ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ግን በመንበሩ ተቀምጦ ነበር እንጂ አልበላም:: ድግሱ ሲጠናቀቅ ንጉሡ አርቃድዮስ ሊቁን "ጥያቄ አለኝ" ብሎ በጉባኤ መካከል ጠየቀው::
"ምነው ወንጌላዊ ማቴዎስ 'ኢያዕመራ ዮሴፍ እስከ አመ ወለደት ወለደ ዘበኩራ - የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም' ማለቱ (ማቴ. 1:25) ስለ ምን ነው?" ቢለው ቅዱሱ ተነስቶ: በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ይተረጉምለት ጀመር::
"ድንግል ማርያም ንጹሕ ብርሌን ትመስላለች:: ብርሌ የተለያየ ቀለም ያለው ፈሳሽ ቢያስገቡበት ቀለሙ አብሮ ይቀያየራል:: እመቤታችንም ጌታን ጸንሳለችና ሕብረ መለኮቱ ሲለዋወጥ መልኩዋ አብሮ ሲለዋወጥ እያየ ዮሴፍ ይደነግጥ ነበር::
'እርሷ ማን ናት? በማሕጸኗ ያለውስ ማን ነው?' እያለ ይጨነቅ ነበር:: ጌታን ከወለደች በሁዋላ ግን አንድ ሕብረ መልክ ሆናለችና:: አስቀድሞ ማን እንደ ነበረች አላወቀም::
አሁን ግን እርሷም ወላዲተ አምላክ: ልጇም አምላክ ዘበአማን መሆኗን አወቀ ማለት ነው" እያለ ሲተረጉም ሰምተው ሁሉም ሲያደንቁ: በዚያ የነበረች ስዕለ አድኅኖ "አፈ ወርቅ! ልሳነ ወርቅ! አፈ በረከት!" ስትል ተናገረች::
ያን ጊዜ አርቃድዮስ የወርቅ ልሳን በሊቁና በስዕሏ ላይ አደረገ:: አፈ ወርቅ ግን ባጭር ታጥቆ "እሰግድ ለኪ! እሰግድ ለኪ! ወእዌድሰኪ . . ." ብሎ ዛሬ በተአምረ ማርያም የምናውቀውን ምስጋና ሰተት አድርጐ አደረሰላት:: ይህንን ምስጋናም ሊቃነ መላእክቱ ሰምተው እያደነቁ ወደ ሰማይ ወጥተዋል::
ሊቁ ባረፈ በ35 ዓመቱ በትንሹ ቴዎዶስዮስ ዘመን: በዚህ ቀን ሥጋው ፈልሷል:: ወደ ቁስጥንጥንያ ሲደርስም ከናፍቆት የተነሳ ታላቅ ዝማሬና እንባ ተደርጉዋል:: አፈ ወርቅም ቀና ብሎ ሕዝቡን ባርኩዋል::
††† ቅዱሱ ሲጠራ እንዲሕ ነው:-
*ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
*አፈ በረከት
*አፈ መዐር (ማር)
*አፈ ሶከር (ስኩዋር)
*አፈ አፈው (ሽቱ)
*ልሳነ ወርቅ
*የዓለም ሁሉ መምሕር
*ርዕሰ ሊቃውንት
*ዓምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ)
*ሐዲስ ዳንኤል
*ሊቀ ዻዻሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው)
*መምሕር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ
*ጥዑመ ቃል - - -
††† ቅድስት ወለተ ጴጥሮስ ኢትዮጵያዊት †††
††† ቆራጧ እናታችን ቅድስት ወለተ ዼጥሮስ ለእኛ ለኢትዮዽያውያን የተዋሕዶ አማኞች ሞገሳችን ናት:: እጅግ የሚደነቅ መንፈሳዊ አርበኝነትን በካቶሊኮች ላይ አሳይታለችና::
ቅድስት ወለተ ዼጥሮስ የተወለደችው በ16ኛው መቶ ክ/ዘመን በምሥራቅ ኢትዮዽያ ዳውሮ አካባቢ ነው:: ወላጆቿ ባሕር አሰግድና ክርስቶስ ዕበያ ይባላሉ:: ክርስትናን በሚገባ አጥንታ አድጋ: በወላጆቿ ፈቃድ በሥርዓቱ ባል አገባች:: ግን ወዲያው አፄ ያዕቆብ ገደሉባት::

ወላጆቿም ግድ ብለው ስዕለ ክርስቶስ የተባለ የሱስንዮስን የጦር መሪ አጋቧት:: እስከ 24 ዓመቷም ልጆችን ወለደች:: በዚህ ሁሉ ጊዜ የጾምና የጸሎት ሰው ነበረች:: አፄ ሱስንዮስ ተዋሕዶን ክዶ ካቶሊክ በሆነ ጊዜ ባሏ ወደ ንጉሡ እምነት ገባ::በዚህ ስታዝን ይባስ ብሎ ጠዳ ላይ የአቡነ ስምዓን (ዻዻሱን) ልብስ ግዳይ ይዞ ቀረበ:: እርሷም ልቧ ቆረጠ:: ፈጣሪ 3ቱን ልጆቿን አከታትሎ ወሰደ:: ደስ ብሏት ጠፍታ ሳጋ (ዛሬ ገዳሟ ያለበት) ገባች:: ቀጥላም መነኮሰች::
ከዚህ በሁዋላ እየዞረች መናፍቃን ስታሳፍር: ሕዝቡን ስታጸና ዓመታት አለፉ:: በሷ ስብከትም ብዙ መነኮሳትና ምዕመናን ሰማዕት ሆኑ:: እሷም በየገዳማቱ ተንከራተተች:: በደዌ ተሰቃየች:: በንጉሡ ተይዛ 2 ጊዜ ወደ በርሃ ተሰደደች::
ፋሲል ነግሶ: ሃይማኖት ተመልሶ ሃገር ሲረጋጋ ወደ ምጽሊ: ከዚያም ወደ መንዞ መጥታ ገዳም መሥርታ: መናንያንን ሰብስባ: ስታጽናና ኑራለች:: በተወለደች በ50 ዓመቷም በ1630ዎቹ መጨረሻ አካባቢ ዐርፋ ተቀብራለች:: የተጋድሎ ዘመኗም 26 ዓመታት ናቸው:: ቅድስት ወለተ ዼጥሮስ ሰማዕትም ጻድቅም ናት::
††† የጥቡዓን አምላክ የሊቁን ምሥጢር: የቅድስቷን መጨከን: ከበረከታቸውም ይክፈለን::
††† ኅዳር 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ (ፍልሠቱ)
2.ቅድስት ወለተ ዼጥሮስ ኢትዮዽያዊት
3.አባ ሲኖዳ (ዘደብረ ጽሙና - ጐጃም)
4.ጻድቃን እለ ወጺፍ
5.ቅዱሳን አብርሃምና ሐሪክ
6.ቅድስት ወለተ ዻውሎስና ወለተ ክርስቶስ
††† ወርኀዊ በዓላት
1.እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት
2.ያዕቆብ ሐዋርያ
3.መክሲሞስና ዱማቴዎስ
4.አባ ገሪማ
5.አባ ዸላሞን
6.አባ ለትጹን
7.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ
††† "በድካምና በጥረት: ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት: በራብና በጥም: ብዙ ጊዜም በመጦም: በብርድና በራቁትነት ነበርሁ . . . የቀረውን ነገር ሳልቆጥር ዕለት ዕለት የሚከብድብኝ የአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሳብ ነው::" †††
(2ቆሮ. 11:23)
††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
@yeberhanljoche

faaruu haraa Glataan Dhiyeessaa f/taa Yoobsan mokoonon (@FaaruuTube400 ...
https://youtube.com/watch?v=FBx4zl28ayc&si=lxcD8YWj4moW5sWu

YouTube
faaruu haraa Glataan Dhiyeessaa f/taa Yoobsan mokoonon (@FaaruuTube400 @Faaruu @FaaruuDaawit
#oromo #faarfannaa_afaan_oromoo #faaruuortodoksii #ማህቶት #ethiopia #ተዋህዶ #ሰይፉ_ሾው #ሰይፉ_ፋንታሁን #ዶንኪቲውብ
ከ20 k በላይ member ያላቸውን መንፈሳዊ ቻናሎች መግዛት የሚፈልግ ካለ
በ👉 @Yene_mareyam አናግሩን።
በ👉 @Yene_mareyam አናግሩን።