Telegram Web
ስምና ኩነኔ
"""""""""'''''''
ለውሸትሽ ድጋፍ፥
በ.ማ.በ.ል.ሽ አፋፍ፥
እውነትን ቀብተሽ
በማስመሰል አንባ፥መዝለቅሽ ቢሰምርም፤
ስም ያለው ሞኝ ነው
'ክህደት' ባልኩኝ ቁጥር፥"ወይታሽ" አይቀርም...

አይቀርም

አክብሩልኝ ካለው
ከአስርቱ ትዕዛዝ፥ህግጋት ተላልፎ፤
እንዳትነኩ ካለው
ገነት ከፀደቀው፥እፀ በለስ ቀጥፎ፤
የውሸት ቅኔ ዘርፎ...
የሰው ልጅ በድክመት
በህይወቱ ምላስ፥ኃጥያትን ቢቀስም፤
ዘላለም አለሙን
"እመት'' ሲል ይኖራል
ተደባልቀውበት፥መኮነኛው ከስም!

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
ለሌሎች ምርጥ🤌👌 ግጥሞች join በሉ....👇👇👇

@HAKiKA1
@HAKiKA1
Forwarded from አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ) (አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ))
የቆጥ ውበት
"""""""""""""""
ከውበትሽ፥
ከስብዕናሽ፥
ቅልውጥ ሄጄ ስስቀመቀም፤
ነግሰሽብኝ፥
ከልቤ ላይ፥
ማርከሻሽን ከምን ልልቀም...?

የአንጀት ደዌ
ልክፍት ነው
መወደድሽ ውስጥ ይንጣል፤
ሚቆጠቁጥ፥
የሰማይ ቆጥ፥
ሽቅብ ላይ ነው ልብሽ አይጣል፤
የሾህ ብቃይ፥
ሊሆን ስቃይ፥
በውበትሽ ጅራፍ ቀጣን፤
በአንቺ ሚዛን
ሲወዳደር
ክፉ አይደለም ከቶ ሰይጣን..!

አጃኢብ ነው
ፍቅርሽ ሲጥል
አይፎክርም... አያቅራራ፤
ማስታገሻ
ከቶ የለም
ሲፈጥርሽም እፁብ ስራ፤
ስንቱ አዳም
ለአንቺነትሽ እሱነቱን እየሰዋ፤
የብብቱን ክብር ጣለ
.....ለውበትሽ ሲንጠራራ!

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@HAKiKA1
@HAKiKA1
Forwarded from አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ) (አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ))
ሽውርር ተስፋ
"""""""""""""""""
ያለፈው ክፋት ነው
የሚመጣው እንጃ፤
ዛሬን መዳከር ነው
የሀገሬው ፍርጃ...

ትላንትም ግፍ ነበር
የህይወት ልቅምቅም፤
ከገር ፊታችን ላይ
እንባን የሚያስለቅም...

ይመሻል?..... አናውቅም
ይነጋል?.....አናውቅም፤
ተስፋችን ቢቀበር
አይገርምም አይደንቅም፤
አሁን ሰላም ካለ
ነገን አ'ናፍቅም...
.
እንግዲህ
.
ልቦናህን መርምር
እርምጃህ ቀስ በቀስ፤
ልቦናሽን እዪ
መንገድሽን ቀነስ፤
የቂም ሾተል ይዞ
"ነገን አንጋ" ብሎ
በፀሎት ጌታ ፊት የምን ማለቃቀስ?

አንቅረው ሴራህን
ሽልሽን አራግፊ ክፋት ይጨናገፍ፤
ይህንን አርጎ ነው
ለአዲስ ንጋት ጀንበር አጥብቆ መንሰፍሰፍ...
.
አልያማ
.
በሆድ ክፉ አርግዞ
የነገር ሽል ይዞ
ከነፍስና ስጋ ሳይጠፋ በቅጡ፤
ለፍቅርና ሰላም
በህልም ቅዠት አድረው
በተስፋ ዓለም ላይ ነገን ቢቋምጡ፤
የነገ ቀን ነግቶ
ማርያም ማርያም ቢባል የሰይጣን ነው ምጡ፤
ስህተት ነው ንጋቱ...!

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)

@HAKiKA1
@HAKiKA1
Forwarded from አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ) (አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ))
የክብ.....ካብ
"""""""''''''''''''''""
እንጀራችን ክቡ፥
ዕድላችን ክቡ፥
መንገዳችን ክቡ...
በመከበብ ዕጣ፥ዕድል ተለውሶ፤
ከቶ አይደርስም ያሉት
እየተቃበዘ ይመጣል መልሶ...

በል ስራህን መርምር
አላማህን መትር እጆችህን አጥና፤
አርምጃህ ሀቅ ይሁን
ከሰው ጫንቃ ውረድ ውልህ ይሁን ቀና...

ዕቅድህን እየው...

ዕቅድህን እየው
አይምሮህን ቃኘው
በማጥ አትዳክር ህልም አለምህ ጠቦ፤
ህይወት አዙሪት ነው
የግፍ እንባ እንደ እባብ ይመጣል ተስቦ...

ተው
ተው እስቲ እረፍ
ነፍስያህን በእውነት ግረፍ

አትድንም
አትተርፍም
ከህዝብ ዕንባ ከሰው ደም ጦስ፤
ቢታጠብስ መቼ ፀዳ
ከኢየሱስ ደም ያ ጲላጦስ?

አፅዳ...
ፈትግ....
አንፃ ሀሳብህ ህሊናህን ቃኘው፤
ባሰብከው ልክ ነው
የሰማይ ቤት ዕዳህ ፍርድህ የሚዳኘው....

አስብ አለምህን
አስብ ህይወትህን
አስብ እምነትህን
አስብ...
አስብ...
አስብ...
ከመኖርህ ጉድጓድ መልካምነት ሰብስብ...!
ሸፍን ገመናህን
ህሊናህን ገንባ በፍቅር ምሰሶ፤
የክብ ነው ነፍስህ
የሰራኸው ሁሉ ይደርሳል መልሶ!

#አስብ!

አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)

@HAKiKA1
@HAKiKA1
https://www.tgoop.com/HAKiKA1

ምርጥ እንድትቀላቀሉት የምጋብዛችሁ ቻናል......join ብለው የጥበብ ስራዎችን ይታደሙ
@HAKiKA1
ለግጥም አፍቃሪዎች 🙌

ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን የስነ ግጥም ቻናሉን join ብለው እንዲቀላቀሉ እጋብዛለሁ።
በብዙ ይዝናኑበታል ያተርፉበታልም።
join👇😊👇
አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ)
@HAKiKA1
@HAKiKA1
@HAKiKA1
@HAKiKA1
በ TikTok መጥተናል follow አድርጉ....

አብርሃም ፍቅሬ(የቅዳስ ልጅ)

👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://vm.tiktok.com/ZMNwnsXCs/
#አበባ_አየሁ

©ሲራክ ወንድሙ

እሩቅ ለሩቅ ሆነን
ይጠባል መስከረም ፥ ይታጠናል ህዳር
ፀደይ እየዳኸ
ክረምት ይጋልባል ፥ ተስፋዬን ሳሳምር

አምና በዚህ ሰዓት ፥ ጠበቅኩሽ በውርጩ
እስኪያልፍብኝ ሀሩር ፥ ወፎች እስኪንጫጩ

ጠበቅኩሽ ፥ ጠበቅኩሽ
የሌት ውብ እንቅልፌን ፥ በናፍቆት መጅ ድጬ
በመምጣትሽ እርሾ ፥ ልቤን አሳብጬ።

የአንቺ ሀገር ወዴት ነው የአድማስሽ አቀበት ?
እግሬን ላወላዳ ፥
ይቆምልኝ እንደው የልቤ ትኩሳት
ተይ ንገሪኝ ባክሽ ፥ ወዴት ነው ባዕቱ
ካቻምና ላይ ቆሜ ፥ መነነ ዘመኑ ከነፈ ጊዜያቱ

የተራራው ደረት በአደይ ፂም ጎልምሶ
የሀምሌ ጨለማ
ባባረረው ብርሃን ፥ ሲሄድ ተለሳልሶ
እንደው ለአዲስ ዓመት ፥ ትጋቴን አስታውሰሽ
ናፍቆት ፣ ተስፋ ፣ ፍቅርን - አንድ ላይ ታቅፈሽ
በሬን ከፍተሽ ግቢ ፥ አበባ - አየሁ ብለሽ
....
©ሲራክ @siraaq
https://www.tgoop.com/yegetem32
join this poetic Channel😊
👇👇👇👇
@HAKiKA1
Forwarded from Abrham F. Yekedas
አንዳንዴ ህይወት በምን በኩል እንደምታስቀምጠን አይታወቅም ..... እኔም ደሞ የበኩላችሁን እንድትደግፉኝ ብዬ ፊታችሁ ቆሜያለሁ።

ይህ ከታች የምትመለከቱት ምስል አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ከምትማር አንድ የ Class ጓደኛችን የተላለፈ ታምሜያለሁና ከዚህ ጭንቅ ገላግሉኝ አግዙኝ የሚል ይዘት ያለው text ነው። ሶስት አመት አብረን ስንማር ከህመሟ ጋ እየታገለች እንደነበር፤ አሁን ግን እሷም ቤተሰቧን ይህንን ወጪ መቋቋም እንዳልቻሉ አስረዳችን። በፊት ስንማርም በየፈተናዎቹ ራሷን እየሳተች ስትወድቅ የሚጥል በሽታ እንጂ እኛም እንዲ የከፋ ነገር ነው ብለን አላሰብንም ነበር።

እኛ የተቻለንን ብናደርግም ነገሩ በእኛ ብቻ ልንቋቋመው አልቻልንም።

በአንዳንድ ትንሽ የግጥም ሙከራዎቼ የምታውቁኝ የ Social media ጓደኞቼ እና የማታውቁኝም በሙሉ....ይቺን እህታችንን ብናግዛት ብዬ በተማፅኖ እጠይቃችኃለው..!

የውሀ ጠብታዎች ጥርቅም ወንዝ ይሆናል ....አደራ ለምታደርጉት ማንኛውም ድጋፍ አነሰ ብላችሁ ለበጎ ተግባራችሁ ልጓም እንዳታበጁለት🙏

CBE
1000349400859 Samrawit Bedilu

1000391441425 Wesentelsh Tsegaye(her mother's account)

ንግድ ባንክ የሚያስቸግራችሁ

0908720710 በእኔው Telebirr Account  ትችላላችሁ።

ያደረጋችሁትን ድጋፍ Screenshot እያደረጋችሁም በ inbox ብትልኩልኝ ሁላችሁንም ለማመስገን ይረዳኛል።

#ጓደኝዬን_አግዙልኝ
Forwarded from አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ) (Abrham F. Yekedas)
እየገዛችሁ...

ክንፋም ከዋክብት የግጥም መፅሀፍ የህትመት ሂደቷን እንደ ምጥ ቀን ቆጥራ ከተገላገለች እነሆ ሳምንትን አሳልፋለች.... ጥቅምት 16 2017 ዓ.ም በዋልያ መፅሀፍ መደብር አንጋፋ አርቲስቶች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተመርቃለች።

ያሉ ቀሪ መፅሀፎችን እጃችሁ ማስገባት የምትፈልጉ @Run_Viva_Run ላይ አውሩኝ። እንቀባበላለን።

@HAKiKA1
Forwarded from አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ) (Abrham F. Yekedas)
ትውስታ አይለቀኝም። ለእያንዳንዱ ትውስታ ደግሞ ታሪክ ነውና ዋጋ እሰጣለሁ። ዋጋ ያለውን ነገር ዋጋ ስሰጥ ደግሞ እንደዛ የሆነልኝን ሰው ስወድ ከልቤ ነው። መወደድ ደግሞ አንዳንዴ ለተወዳጁ ሰው አጉል ኩራትን ይሰጣል። አጉል ኩራት ንቀት ናት። ንቀት ደሞ የትዕቢት እናት ናት። ትዕቢት ሰይጣናዊ ነው ፍቅርን አያሳይህም። ፍቅር ከተከለለብህ ደሞ ወዳጅህ የሚታይህ ላንተ ጥቅም አልባ ሆኖ ነው። ወዳጅህን "ዞር በልልኝ" ትለዋለህ። "ለምን ምን አጠፋሁ?" ይልሀል። ምክንያት መስጠት ሲያቅትህ ትናደድና የባሰ ትጠላዋለህ "በቃ ከመንገዴ ዞር በል" መልስህ ይሆናል። ተገርሞ/አዝኖ/ተናዶ ዞር  ይልልሀል። ደግ ወዳጅንና/ደግ ባልንጀራን ማጥበቅ በፈጣሪ የተወደደ ሆኖ ሳለ፤ ሰይጣናዊ አስተሳሰቦች በአይምሮዋችን ሲንከላወሱ ፍቅርንም ወዳጅንም ያሳጡናል። "ሰውን መውደድ ስህተት እንደሆነ" ውስጥህ ከነገረህ...ያውልህ ሰይጣን በግራህ በኩል እየተደሰተ፤ ፈጣሪ በቀኝ በኩል በእዝነት እየተመለከተህ ...

#ሰው_ሲወዱት_ያብዳል

Abrham F. Yekedas

@HAKiKA1
Forwarded from አብርሃም ፍቅሬ (የቅዳስ ልጅ) (Abrham F. Yekedas)
ህይወት ከሱ ውጪ እንዴት ነው?...አላውቀውም። ነፍስና ስጋዬ በእሱ ምህዋር ላይ እየተሽከረከሩ ነበር። አንድ ቋሚ ላይ እንደተንጠለጠለ የቴዘር ኳስ... እኔም እንደዛ ነበርኩ። ቋሚው እልም ብሎ ቢጠፋብኝ ወደየትም የምሽቀነጠር አይነት ሰው... ከእሱ ውጪ ማንም ከምንም እንደማይቆጥረኝ አውቃለሁ።

ከወላጅ አልባ ህፃናት ማሳደጊያ ዕድሜዬ ደርሶ እንደወጣሁ ያወቅኩት እሱን ብቻ ነው። ሰው ያስፈራኝ ነበር። እሱ ግን እንዴትም ብሆን የማልፈራው...እንዴትም ብፈነጥዝበት የሚችለኝ የህይወት መስኬ ነበር። በቃ የኔ ዓለም እሱ ላይ ነበር። ተቆጥቶኝ እንኳን ኩርፊያዬ ይጨንቀዋል...እጅግ አድርጎ ያባብለኛል። ተቆጥቶ መልሶ እንዲያባብለኝ አጠፋ ነበር። ይቆጣኛል፣ ይመክረኛል መልሶ እንደ ህፃን ያባብለኛል።እሱ መሬት ከቻለችኝ እኩል ተሸክሞ ችሎኛል፣ ሁንልኝ ያልኩትን ሆኖልኛል፣ አርግልኝ ያልኩትን አድርጎልኛል፣ ባለው ነገር ሁሉ አቅብጦኛል፣ ትኩረቱ ከኔ ተለይቶ አያውቅም፤ ግን ካለሱ መኖርን አላሳወቅኝም። ትንሽ እንኳን ጉድለት አሳይቶኝ አያውቅም ። ትንሽ እንኳን...ትንሽ ክፍተት...አለ አይደል እሱን የምቀየምበት እርሾ እንዴት አያስቀምጥልኝም?... "ከእሱ ውጪም እኮ ህይወት አለ?" የምልበት ሀሳብ እንዴት ውል እንዲልብኝ አላደረገም? ለእኔ እሱ ፍፁም ነበር። ለእኔ በእሱ ልክ የሚለካ ምን ፍጡር አለ?

ማታ እኮ ያለኝ "ትንሽ አሞኛል..." ብቻ ነበር።....እንዳልሰጋበት ይሆን?....ዓይኑን አይቼ እንኳን "በጣም አሞትስ ቢሆን"  አላልኩም። እሱ ራስ ምታቴ እንኳን የሚያስጨንቀው ሰው ነው። ህም አንዴ አፍንጫዬን ቢያፍነኝ አይደል በሰው አጥር ላይ ከፍ ብሎ የሚታይ ደማከሴ ሲቆርጥ ከግቢው ከባለቤቶች ጋ የተጣላው... "እግዜር ላበቀለው መድኃኒት እንዲ ይሁኑብኝ" እያለ ነበር ሲኒው ላይ ደማከሴውን የጨመቀው፣ እየተቆጣ በመዳፉ ላይ ያለውን የደማከሴ ፈሳሽ ፊቴን አሻሸልኝ...ያሻሸውን ደማከሴ ጦስሽን ብሎ ከቤት አውጥቶ ወረወረው፣ እየተቆጣ ሲኒው ላይ ያለውን የደማከሴ ጭማቂ በአፍንጫዬ ግቶ እንዳስነጥስ አደረገኝ....ያፋፈነኝ ሁላ ለቀቀኝ። በንጋታው የደማከሴ ስር አፈላልጎ አምጥቶ ፕላስቲክ ቆርጦ በራችን ጋ ተከለ። "ምን ይሰራል አልኩት?"

"ሚስቴን አድኖልኛልና እያመሰገንኩ ላሳድገው..." አለኝ እየሳቀ። እንደ እናት ተንሰፍስፎልኝ፤ እንደ አባት ጠባቂዬ ሆኖ ነበር የኖረው...

ጠዋት ስነሳ ቶሎ ቶሎ ይተነፍሳል። እፍንፍን አድርጎታል። ሀኪም ቤት እንሂድ ብለው "አይ አልሄድም" አለ። "ከደማከሴው ቆርጠሽ ጨምቀሽ ስጪኝ" እሱ ያሽለኛል አለኝ። አደረኩለት ግን ምንም ለውጥ አልነበረም። እኔን ያዳነ ተክል አሳዳጊው ላይ አልሰራም። ተፈጥሮ ለሆነላት አትሆንም እንዴ?

ከሰዓት "ሀኪም ቤት ካልሄድክ እንጣላለን" ብዬ ተቆጣሁት። ቁጣዬን ፈራው? ወይስ ህመሙን ፈራው? "እሺ ጃኬቴን አቀብይኝ" ብሎ ሊነሳ ሲል መነሳት አቃተው። ደግፌ አነሳሁት። ይቺ ደቃቃ ሰውነቴ እንዴት ድጋፍ እንደሆነችው አላውቅም። ሀኪም ቤት ደርሰን ለሀኪሞች ካስረከብኩት በኃላ በጣም ነበር የተሯሯጡት...ያን ያክል እንዳመመው መረዳት ያልቻልኩ ብኩን መሆኔን ተረዳሁ....ወደ 12፡00 ላይ አንዱ ዶክተር ክፍሉ አስገባኝና "አዝናለሁ ያቅማችንን ሁሉ አድርገናል ግን አልቻልንም...የሳንባ ምቹ በጣም ተባብሶ ነበር" አለኝ።
"አልቻልንም ማለት...?" አልኩት ሰውነቴ እየተንቀጠቀጠ

"አርፏል..." አለኝና ዓይኑን ከዓይኔ ላይ አንስቶ አቀረቀረ።...ከዛማ ዓለም ሁሉ ጨለመብኝ። ከዛማ ሁሉ ነገር የሆነው እንደ ሰመመን ነው። ዕንባ ሰው ቢመልስ የኔ ዕንባ እሱን ይመልስ ነበር። እናትና አባቴን አላውቅም። አንድ ዘመድ የምለው የለኝም። እራሴን ሳውቅ ወላጅ አልባ ህፃናት ማሳደጊያ ውስጥ ነው። እሱ ነበር እንደ እናት አባት ወላጅ የሆነልኝ.....ዳግም ወላጅ አልባ ሆንኩ። እያለቀስኩ ቀበርኩት።

ለካ ሞት በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ መምታትም ያውቅበታል። አሁን የለሁም...

Abrham F. Yekedas

@HAKiKA1
2025/07/13 15:49:49
Back to Top
HTML Embed Code: