tgoop.com/yepkil/2345
Last Update:
#ካነበብኩት_ላካፍላችሁ!
አንድ ምሽት በጎልማሶች የትምህርት ክፍለ ግዜ የሳይኮሎጂ መምህሩ ወደ ክላስ ገባና "ዛሬ አንድ Game እንጫወታለን" አለ፡፡ ተማሪዎቹም "ምን አይነት Game?" በማለት በህብረት ጠየቁ፡፡ መምህሩ ቀጥሎ "ፈቃደኛ የሆነ አንድ ሰው?" አለ፡፡ አንድ ፈቃደኛ ሴት "ማርታ እጇን አወጣች፡፡
መምህሩም ማርታን በህይወቷ ትልቅ ቦታ ያላቸውን 30 ሰዎች ስም ጥቁር ሰሌዳው ላይ እንድትፅፍ ጠየቃት፡፡ ማርታም ከቤተሰቦቿ ጀመራ የጎረቤቶቿን፣ የዘመዶቿንና የጓደኞቿን ስም ፃፈች፡፡
መምህሩ በመቀጠል በጣም ጠቃሚ ያልሆኑ 3 ስሞችን እንድትሰርዝ አዘዛት፡፡ እሷም የጎረቤቶቿን ስም ሰረዘች፡፡ አሁንም ሌላ 5ስሞችን እንድትሰርዝ ነገራት፡፡ የሩቅ የምትላቸውን ዘመዶቿን ስም ሰረዘች፡፡ በዚህ መልኩ የአራት ሰዎች ስም ብቻ (የእናቷ፣ የአባቷ፣ የባሏ እና የብቸኛው ልጇ) እስኪቀር ብዙ ስሞችን ሰረዘች፡፡
ሙሉ የክላሱተማሪዎች Gamu ለማርታ ብቻ እንዳልሆነ ተረድተው በተመስጦ ይከታተላሉ፡፡
አሁንም መምሩ ከቀሩት 4 ስሞች 2 እንድትሰርዝ አዘዛት፡፡ ለማርታ በጣም ከባድ ምርጫ ነበር፡፡ እያመነታችና እንዳልተቀበለችው በሚያስታውቅ መልኩ የወላጆቿን ስም ሰረዘች፡፡
መምህሩ በስተመጨረሻ ከቀሩት ሁለት ስሞች 1 እንድትሰርዝ ነገራት፡፡ ማርታ ሙሉ በሙሉ አይምሮዋ ተረበሸ፡፡ በአይኖቿ እያነባች በሚንቀጠቀጡ ጣቶቿ የልጇን ስም ሰረዘች፡፡ መምህሩም ማርታን ወደመቀመጫዋ እንድትመለስ ነገራት፡፡
ከደቂቆች በኀላ መምህሩ "ለምን ባልሽን አስቀረሽ? ቤተሰቦችሽ ላንቺ ብቸኞች ናቸው፤ ልጅሽን አንቺ ነሽ ወደ ህይወት ያመጣሽው፤ ባል ግን ሌላ ማግባት ትችያለሽ፤ ለምን ከእነሱ እሱን አስቀደምሽ?" በማለት ማርታን ጠየቃት፡፡
ሁሉም የማርታን ምላሽ ለመስማት ጓግቷል፡፡ ማርታ በተረጋጋ መንፈስ እንዲሁም በቀስታ እንዲህ ስትል መለሰች፡፡ "አንድ ቀን ቤተሰቦቼ ምናልባት ከእኔ ቀድመው ያልፋሉ፤ ልጄም ሲያድግ ለትምርት፣ ለስራ ወይም በማንኛውም ምክንያት ጥሎኝ ይሄዳል፡፡ ሙሉ ህይወቴን ሁሉን አብሮ የሚጋራኝ ብቸኛ ሰው ቢኖር ባለቤትዬ ነው፡፡"
ሁሉም ተማሪ ከመቀመጫቸው ተነስተው እውነተኛውን የህይወት ገፅታ ስላካፈለቻቸው አጨበጨቡላት፡፡
✍እውነት ነው፡፡ ሁላችንም ቤተሰቦቻችንን ምንም ያህል ብንወዳቸው ጥለናቸው እንሄዳለን፡፡ ለማን ስንል? ለባል ወይም ሚስት፡፡ ልጆቻችንን ምንም ያህል ብንወዳቸው ጥለውን ይሄዳሉ፡፡ ለማን ሲሉ ለሚስታቸው ወይም ለባላቸው ሲሉ፡፡ በስተመጨረሻ አብረው የሚዘልቁት ፈጣሪ ያጣመራቸው ሁለት ነፍሶች ብቻ ናቸው፡፡ ባልና ሚስት!!
ስለዚህ ወዳጄ የህይወት አጋሬ ናት የምትላትን ሴት ከምንም በላይ አክብራት፤ ቅድሚያም ስጣት፡፡ አንቺም እንደዛው እህቴ፡፡
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
[ 📥Comment @Dpapi ]
╔═══✿💌♡💌✿═ ══╗
☞ join & share ☜
☞ @yepkil ☜ @yepkil ☜
╚═══❀💌♡💌❀═ ══╝
BY 💝 የፍቅር_ደብዳቤዎች💝
Share with your friend now:
tgoop.com/yepkil/2345