Telegram Web
#ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ!

ሴቱን ሁላ ሪጃል ያደረገው ሑቡ!

የኡሑድ አምበሳ ተብላ የምትሞካሸው ኑሰይባ ቢንት ከእብ ወይም በቅፅል ስሟ ኡሙ አማራህ እስልምናን በማለዳ ከተቀበሉ የአንሷር ሴቶች ውስጥ አንዷ ናት። ሰዎች አል አቀባህ ላይ ከነቢ ጋር ቃል ሲጋቡ አብራ ቃሏን ለውዱ ሰው ሰጥታለች። ወቅቱ አዳዲስ አማኞች በቁረይሽ ይንገላቱ የነበረበት ነው። በዚህ መንገድ ላይ ብዙዎች የገፈቱን ፅዋ ወደው ተግተዋል። ለሐጅ ከመዲና ወደ መካ ይመጡ የነበሩ ሰዎች የቁረይሾቹን እይታ ሽሽት ሚና አቅራቢያ ካለ ተራራማ ስፍራ ነበር እስልምናን የሚቀበሉት። ኡሙ አማራህም በዚሁ መልክ ነው ወደ ሰይዳችን ማሳ ጎራ ያለችው።

ጀግና ነች። ከሒጅራ በኋላ በተካሄዱ አብዛኞቹ ውጊያዎች ላይ ከነቢ ጎን ሆና ጠላትን ተፋልማለች። ኡሑድ ቢባል ሁደይቢያ፣ ኸይበር አልቀራት ሁነይን የማማህ ቢነሳ በቃ ሰይፏን ያልመዘዘችበት የጦር ሜዳ የለም። በኡሑድ ዘመቻ እድሜዋ አርባ ሶስት ነበር። ባልና ሁለት ወንድ ልጆቿም በዚህ ዘመቻ ላይ ተሳትፈዋል። የጠማውን ልታጠጣ፣ የደከመውን ልታቀና ኮዳዋን ውኃ ሞልታ ተነሳች። በኡሑድ ጅምሩ ላይ ሙስሊሞች ድል እዬቀናቸው ነበር። በቅፅበት ግን ሁኔታዎች ተቀዬሩና ጠላት የአሸናፊነቱን ማማ ይቆናጠጥ ጀመር። ይሄኔ ነቢን ለመግደል አሰፍስፎ የነበረ የጠላት ወታደር እንደ ማዕበል እያጓራ ይጠጋቸው ያዘ። ዓይን በሚርገበገብበት ፍጥነት ክንፍ አውጥታ ነቢ አጠገብ ደረሰች። ከየትኛውም አቅጣጫ ማንም እንዳይቀርባቸው አድርጋ ጠበቀቻቸው። በቁርጥራጭ ጨርቆች የተጠቀጠቀ መቀነት ታጥቃ ነበር። ቁስለኞችን ታክማለች። እሷ ራሷም ወደ አስራ ሁለት ቦታ ተወጋግታለች። አንደኛው ግን እጅግ ጎድቷታል። ኡሙ ሰዓድ ረ.ዓ በኡሙ አማራህ ትከሻ ላይ ከባድ ቁስለት ተመልክታ ምን ሆና እንደሆነ ስትጠይቃት የኡሑድ እለት ያጋጠማት መሆኑን አውግታታለች።

ኡሑድ አስጨናቂ ዘመቻ ነበር። ሰዎች በድንጋጤና በግራ መጋባት ሲሸሹ ኢብን ቁመይህ ወደነሱ ሲገሰግስ ኡሙ አማራህ አዬችው። "መሐመድ የታል? ብቻ አንድ ሰው ያለበትን ይንገረኝ። ዛሬ በህይወት ከተረፈ እኔ ሞቻለሁ!" እያለ ይጮሃል። እሷ፣ ሙስዓብ ኢብኑ ኡመይርና ሌሎችም አስቆሙት። እሱ ነው ትከሻዋ ላይ በሃይል የወጋት። በእርግጥ እሷም አላስተረፈችውም። ግን ደራርቦ የነበረው የጦር ልብስ አስመለጠው። ሌላ ሰው ሊያጠቃት ፈረሱን እየጋለበ ሲጠጋት በጋሻዋ ሰይፉን መከተችው። መለስ ሲልም ፈረሱን ከኋላው አጥቅታ እግሩን በጦር ደለቀችው። ፈረሱም ጋላቢውም ወደቁ። ወዲያው ነቢ ልጇን ተጣሩ። በቅፅበት ደረሰና ጅምሩን አብረው ጨረሱት። ልጇ አብደሏህ ቢን ዘይድም ግራ እጁ ቆስሎ ደሙን እያዘራ ነበር። ነቢ በፋሻ እንድታስርለት ነገሯት። ከመቀነቷ ፋሻ አውጥታ ቁስሉን ካሰረችለት በኋላ "ልጄ ተመልሰህ ሄደህ እነዛን ጣዖት አምላኪያን ተዋጋ!" አለችው። ነቢ ይሄን እያዩ ነበር። "ኡሙ አማራህ ሆይ የአንቺ አይነት ወኔ ያለው ማን አለ!?" አሉ በመደነቅ። ለሷና ለቤተሰቧም ደጋግመው ዱዓ አደረጉላቸው። አንድ ጠላት ከኡሙ አማራህ ፊት ሲመጣ ነቢ ከጎኗ ቆመው ነበር። "ይህ ሰው ነው ልጅሽን ያቆሰለው።" አሏት። ዘላ እግሩ ላይ ብታቀምሰው ተዘረረ። ራመድ ብለው ወደ መጨረሻው ሸኙት። ነቢ ፈገግ ብለው "ኡሙ አማራህ ለልጇ ተበቀለች!" አሉ።

ለዓመት ያክል ህክምና ቢደረግላትም ቁስሉ ሊድንላት አልቻለም። በዚህ መሃል ነቢ ወደ ሐምረዑል አሰድ ለመጓዝ ተነሱ። እሷም አብራ ለመሄድ ተዘጋጅታ ነበር። ሆኖም በደንብ ያልዳነው ቁስሏ አገዳት። ነቢ ከዚህ ዘመቻ ተመልሰው ሊዘይሯት ወደ ቤቷ እንዳቀኑ ለውጧን ሲያዩ ደስ አላቸው። "በኡሑድ የተጎዳነው እነሱ በፈረስ እኛ በእግራችን ስለነበርን ነው። ሁለታችንም እግረኛ ሆነን ብንፋለም ውጊያው ፍትሃዊ ይሆን ነበር።" እያለች ትቆጫለች። ነቢ ጌታቸውን ሲለምኑላቸው ኡሙ አማራህ "ያነብዬላህ በጀነት ካንቱ ጋር እንድሆን ዱዓ አድርጉልኝ።" ብላቸው ነበር። ቃሏን ተቀብለው የሙራዷን ሞሉላት። ጌታቸውን "እነዚህን ሰዎች የጀነት ጓዶቼ አድርግልኝ።" አሉት። "ከዛች እለት በኋላ በህይወቴ በገጠሙኝ ፈተናዎች በአንዳቸውም አልተረበሽኩም።" ትላለች። በዬዘመቻው ስትፋለም ኖራ በሃምሳ ሁለት ዓመቷም የማማህ ላይ በወኔ ተሰለፈች። እንደ አራስ ነብር በጀግንነት ስትፋለም ያያት የገፋ እድሜዋን አያምንም። በዚህ ዘመቻ እጆቿን አጣች። ገላዋ በድጋሚ ተበሳሳ።ያላትን ሁሉ ለነቢ ስትሰጥ ኖራ አለፈች። ነገ ቃል በተገባላት ጀነት ቁስሏ በሚስክ ታሸጎ፣ ሰምበሯ ኑር አፍልቆ፣ ከወደደችው ጋር ትገኛለች ቢኢዝኒላሂል ከሪም።

#ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ
አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!💚💚💚
                              💚💛❤️
                                 💚💛❤️
                                       💚💛❤️
❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ   
      ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ              ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ
💚💛❤️
💚💛❤️
   💚💛❤️
       💚💛❤️
🙏ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡💚💛❤️
🙏እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ🙏
                   👇
                  👇
               👇👇
:¨·.·¨: ❀   ቻናላችንን ▶️🀄️🀄️ሉን!
·. Telegram 👇Join ያድርጉ
@yeresulnfkrmeglecha
@yeresulnfkrmeglecha
┄┄┉┉✽‌»‌‌🌹🌹»‌‌✽‌┉┉┄┄
                              💚💛❤️
                                 💚💛❤️
                                       💚💛❤️
❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ   
      ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ              ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ
💚💛❤️
💚💛❤️
   💚💛❤️
       💚💛❤️
🙏ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡💚💛❤️
🙏እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ🙏
                   👇
                  👇
               👇👇
:¨·.·¨: ❀   ቻናላችንን ▶️🀄️🀄️ሉን!
·. Telegram 👇Join ያድርጉ
@yeresulnfkrmeglecha
@yeresulnfkrmeglecha
┄┄┉┉✽‌»‌‌🌹🌹»‌‌✽‌┉┉┄┄
#ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ!

አሕለል በይቶች እናንተን ጠራናችሁ ቢያቅተን!

የሰይድ ዓልይ የክፉ ቀን ምሽግ፣ የእመት ፋጢማ ምትክ፣ የሰይድ አባስ እናት፣ የኢማም ሑሰይን ደጀን ፋጢማ ቢንት ሁዛም አል ኪላቢያ (ኡሙል በኒን)
የዘር ሃረጓ ከበኑ ኪላብ ይመዘዛል። የተገኘችበት ጎሳ ሐሺሚዮች ዘንድ እጅግ የተከበረ፣ በብልሃታቸውና በጦረኝነታቸው የታወቁ አባላት ያሉት ነው። የነቢ ወለላ፣ የጀነት ሴቶች አለቃ እመት ፋጢማ ረ.ዓ ካለፈች ከዓመታት በኋላ ኢማም ዓልይ ትዳር እንደሚፈልጉ ለወንድማቸው ሰይድ ዓቂል ኢብን አቡጧሊብ ሹክ አሏቸው። ሰይድ ዓቂል የትዳር አጋር መረጣ ይሳካላቸዋል። ወዲው ፋጢማ ቢንት ሁዛምን ጠቆሙና ጋብቻው ተፈፀመ።

ከጋብቻው ቀደም ብሎ ሰይድ ዓልይ ረ.ዓ በእለተ አሹራ ከኢማም ሑሰይን ረ.ዓ ጎን ተሰልፎ የሚሰዋ ወንድ ልጅ እንደሚያገኙ ተተንብዮላቸዋል። ሰይድ ዓልይም ከዛች እለት አንስቶ ያንን ወንድ ልጅ ሲጠባበቁ ቆይተዋል። ያ ወንድ ልጅ ሰይድ አባስ ነበሩ። ከሰርጉ በኋላ ሰይደት ፋጢማ (ኡሙል በኒን) ወደ ሰይድ ዓልይ ረ.ዓ ቤት መጣች። በዛ ቤት ውስጥ ትኖር የነበረችው ሴት ታላቋ ፋጢማ ቢንት ረሱሉላህ መሆኗን ፈፅሞ አልዘነጋችም። እግሯ ቤቱን እንደረገጠ የእመት ፋጢማ ልጆች ባሪያ ለመሆን ለራሷ ቃል ገባች። ባለቤቷን ሰይድ ዓልይንም ፋጢማ ብለው በሥሟ እንዳይጠሯት ጠዬቀች። አንድም ለቢንት ረሱሉላህ ክብር ሁለትም የሰይዳህ ፋጢማህ ልጆች እናታቸውን እያስታወሱ እንዳያዝኑና መጥፎ ትዝታ እንዳይቀሰቀስባቸው በመስጋት። ይህንን ያስተዋሉት የሰይደት ፋጢማ ቢንት ረሱሉሏህ ልጆች እጅግ አከበሯት። አላቋት። ከእናታቸው በኋላ እናት አድርገው ያዟት። አላህ የሰይዳ ፋጢማን ማህፀን ባርኮታል። በዚህ ጋብቻ ለሰይድ ዓልይ አራት ወንድ ልጆችን አሳቅፋለች። አባስ፣ አብደሏህ፣ ጃዕፈር እና ኡስማንን። ለዚህም ነው ኡሙል በኒን የሚል ስያሜ የተሰጣት። የወንድ ልጆች እናት። ልጆቹ ጀግንነትን፣ ለጌታ መዋደቅን፣ አሽረፈል ኸልቅን ከሁሉ አብልጦ መውደድን፣ ለወንድም ራስን አሳልፎ መስጠትን ከአባታቸው ከዓልይ ሲከርሩ አደጉ። እሷም ታንፃቸው የነበረው የወንድማቸው የኢማም ሑሰይን ባሪያ እንዲሆኑ ነበር። እነሱም ይሄው ሰርፇቸው ኖሮ ኢማም ሑሰይንን ወንድማችን ብለው አያውቁም። ይልቁኑ እንደ እናታቸው መሻት ሁሌም ከእግራቸው ሥር ነበሩ። ከርበላ ላይ አቧራው በጨሰበት፣ ሰይፍ ባፏጨበት፣ ፈረሶች በጭንቅ ባጓሩበት፣ የአሕለል በይት ደም በተንዠቀዠቀበት በዛ በጭንቅ ወቅትም ሁሉም ልጆቿ ከኢማም ሑሰይን ጎን ተሰውተዋል። የነቢን ቤተሰብ እንጠብቅ ብለው፣ እናታችንን እንታዘዝ ብለው፣ ለወንድም ጌታችን ጋሻ እንሁን ብለው ወድቀዋል።

ፋጢማ ቢንት ሑዛም ልጆቿን በሸሂድነት ካጣች በኋላ ሰዎች ኡሙል በኒን ብለው እንዳይጠሯት ተማፀነች። ኡሙል በኒን የባለቤቷ የአብራክ ክፋይ፣ የረሱሉሏህ ደምና ስጋ፤ የሰይደት ፋጢማ ስስት ለሆኑት ለኢማም ሑሰይን ያላት ፍቅር እጅግ የላቀ ነበር። ልክ እንደዛች የዘመዶቿ መገደል እዬተነገራት የረሱሉሏህን ደህንነት ትጠይቅ እንደነበረችው ሴት የአራት ልጆቿን የሞት ዜና ስትሰማ "ስለ ሑሰይን ንገሩኝ" ነበር ያለችው። መስዋዕት መሆናቸው ሲነገራትም ሃዘኗ መሪር ሆነ። "ምነው የደም ባንቧዎቼ በተበጠሱ፤ ምናለ አለኝ የምለው ሁሉ ለሱ ሲባል ፊዳ በሆነ!" እያለች ደረቷን ደቃች። በመዲና ያሉ ሴቶችን በቤቷ ሰብስባ እንባ ተራጨች። ታላቅ ገጣሚ ነበረች። የኢማም ሑሰይንን ጉዳት አሁንም አሁንም በእንባ በሚረጥቡ እጆቿ ከተበች። ሁሌም እነዛ ውብ ፍጥረታት ወዳረፉበት በቂዕ የመቃብር ስፍራ ጎራ እያለች የሃዘን ፅሁፎቿን ታነበንብም ነበር። ታድያ የሰማት ሁሉ አብሯት እንባውን ያረግፋል። እነዚህን የሃዘን መነባንቦቿን ታሪክ በደማቁ መዝግቧቸዋል። በዓረብኛ ቋንቋ ከተሠሩ የጥበብ ሥራዎች ላቅ ያለውን ደረጃም ተቆናጥጠዋል። ከከርበላው ክስተት በኋላ ኡሙል በኒን መዳከም ጀመረች። ሃዘን ውስጥ ውስጧን እዬበላት ነበር። በመጨረሻም በስልሳ አራተኛው ዓመተ ሒጅራ በጀማዱሳኒ ይህችን ዓለም ተሰናብታ ከወደደቻቸው ጋር በመዲና ጀነቱል በቂዕ አረፈች። እንኳን የግንዱ የቅርንጫፉ ፍቅር ያንገበግባል!

ሶሉ ዓለል ሐቢብ!
አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!💚💚💚                              💚💛❤️
                                 💚💛❤️
                                       💚💛❤️
❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ   
      ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ              ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ
💚💛❤️
💚💛❤️
   💚💛❤️
       💚💛❤️
🙏ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡💚💛❤️
🙏እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ🙏
                   👇
                  👇
               👇👇
:¨·.·¨: ❀   ቻናላችንን ▶️🀄️🀄️ሉን!
·. Telegram 👇Join ያድርጉ
@yeresulnfkrmeglecha
@yeresulnfkrmeglecha
┄┄┉┉✽‌»‌‌🌹🌹»‌‌✽‌┉┉┄┄
#ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ!

ወለላው ነቢ፣ ዘይኔው ነብዬ፣ የከውሰር ባላባት፣ የሐውዱ አሳላፊ፣ እንኳን ውልደቱን ፅንሰቱን ታሪክ የከተበው፣ አይደለም ዛቱ የፀጉሩ ዘለላ የተሰነደው፣ የሚያምረው አሕመድ፣ ታማኙ መሐመድ፣ ትልቁ ሰው፣ ጥንፍፉ ሙስጦፋ፣ ጌታው ጦሓ ያለው፣ አብሬትዬ "ሐመለት ኡሙሁ ፊ ሸሕሪ ረጀቢ!" እንዳሉት በዚህ ወር ነው የተፀነሱት። በይተል መቅዲስ አቅንተው፣ በማዕናው መወጣጫ መቃመል መሕሙድ የደረሱትም በዚሁ በረጀብ ነው። የረጀብ ባሕር ጥልቅ ቢሆንባቸው ዋናተኞቹ ጠቅለል አድርገው "ረጀብ ሸሕሩን አጀብ!" አሉ።

ረጀብ የዘለቀ ጊዜ "ጥንፍፍ የጥንፍፍ ልጅ በአባቱም በእናቱ!" ያስባለው አስደናቂ ሰርግ ተደገሰ። እሜቴ አሚና እጅግ ለተከበሩና ለታፈሩት የጌታው አብዱልሙጦሊብ ልጅ ሰይድ ዐብደላህ ተዳሩ። ጀሊሉ በቁድራው የሰይደት አሚናን ጅስም አጠናና የዓለሙን ኑር ጣደበት። ረጀብ አንድ ባለበት የጁምዓ ለይል በጦሐራው ማ‘ጠን ላይ ዘራቸው። ኸበሩ ሰማይ ቀበሌ ድረስ ኖጋ። ኢብሊስ በረገገ። የኢንስ ባልንጀሮቹ ተራወጡ። ዐርሽ ኩርሲዩ በደስታ ዋለለ። ጀነት ተዘዬነች። ተሸለመች። ጀሃነም በረደች። ቀዘቀዘች። ሰማይ ምድሩ፣ ሸርቅ ጘርቡ አበራ። ጀሚዑል ካኢናት ተደሳ። ለኢማሚል ዓለሚን፣ ኒዛሙል ሙርሰሊን ጅማሮ አደገደገ። መለኮቹ እርስ በርስ አወጉ። የሚመጣውን ሰው በዝና ያውቁታል። ይህቺን ቀን ለዘመናት ሲጠባበቋት ኖረዋል። አዋቂ የተባለ አወካ። አይ^ሁድ "መምጫው ከ’ኔ ቀዬ ነው!" ብሎ ዓረብ ላይ ፎከረ።

ደጋጎቹ "የረጀብን ወር የመጀመርያ ለሊት በዒባዳ ያነጋ ሰው ልቦች በሚሞቱበት ጊዜ የሱ ልብ አትሞትም፤ አላህም ኸይሩን፣ ራሕመቱን፣ ኒዕማውን ያፈስበታል። ያንቧቧለታል።" ብለው አባሸሩን። መቀማመጣችንን መዝግቦ ያንቧቧልና። ሸኾቻችን ሃጃቸውን ወደዚህ ወር ያስጠጋሉ። በተለይ አብሬትዬ የጠበቀ ሀጃ ሲገጥማቸው "ቆይ ረጀብ ይምጣ" ብለው በጉዳዩ ላይ ይዝቱበት ነበር ይባላል። ረጀብ መጥቶ የማይወጣ ሀጃ፣ የማይሞላ ሙራድ፣ የማይፈታ ትብታብ፣ የማይማር ወንጀል የለም።

ጌታችን በከላሙ ከወራቶች አራቱ የተከበሩ መሆናቸውን ተናግሯል። ውዱ ነብይም "ረጀብ የአላህ፣ ሻእባን የኔ፣ ረመዷን ደግሞ የዑመቴ ወራት ናቸው።" ብለዋል። አብሬትዬ ታድያ የረጀብ ወር በኢስላም ከተመረጡት አራት ወራት አንዱ መሆኑን አስተውለው፣ የካኢናቱ ሁሉ አለቃ፣ የእዝነቱ ነብይ የተፀነሱበት መሆኑን ተረድተው ለሰይዳችን ዊላዳ መደሰቻ ይሆን ዘንድ ከወቅቱ ሁላ እሱን መረጡት። ኢማም ሙሳ ካዚም እንደተናገሩት ደግሞ "ረጀብ ጀነት ውስጥ ያለ ከወተት የነፃ፣ ከማር የጣፈጠ ወንዝ ስም ነው። በዚህ ወር ነፍሳቸው ከወንጀል የፆመችላቸው፣ በበጎ ሥራ የተጠመደችላቸው ሰዎች መልካምን የተመነዱ ናቸው።" ይላሉ።
ትላልቆቹ "ረጀቡ ያማረ ሻእባኑ ያምራል። ሻእባኑ ያማረ ረመዷኑ ያምራል።" ብለዋልና ሁሉንም ያሳምርልን።
"ረጀብ ዘር የምንዘራበት፣ ሻእባን ማሳችንን የምናጠጣበት፣ ረመዷን የምንሰበስብበት ነው።" እንዳሉትም ደግሞ ከስባችንን አላህ ያብዛው። ዘራችን የሚያፈራ፣ ፍሬውንም የምንበላ ድርገን። እንግዲህ እታለም ወቅቱ የገበያ ነውና የእስቲግፋር መቀነትሽን ታጥቀሽ አትርፊ፣ አንተም ወንድሜዋ የሶለዋት መውዜርህን አንሳና አልመህ ተኩስ!

ሶሉ ዓለል ሐቢብ!
አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!💚💚💚                              💚💛❤️
                                 💚💛❤️
                                       💚💛❤️
❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ   
      ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ              ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ
💚💛❤️
💚💛❤️
   💚💛❤️
       💚💛❤️
🙏ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡💚💛❤️
🙏እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ🙏
                   👇
                  👇
               👇👇
:¨·.·¨: ❀   ቻናላችንን ▶️🀄️🀄️ሉን!
·. Telegram 👇Join ያድርጉ
@yeresulnfkrmeglecha
@yeresulnfkrmeglecha
┄┄┉┉✽‌»‌‌🌹🌹»‌‌✽‌┉┉┄┄
                              💚💛❤️
                                 💚💛❤️
                                       💚💛❤️
❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ   
      ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ              ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ
💚💛❤️
💚💛❤️
   💚💛❤️
       💚💛❤️
🙏ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡💚💛❤️
🙏እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ🙏
                   👇
                  👇
               👇👇
:¨·.·¨: ❀   ቻናላችንን ▶️🀄️🀄️ሉን!
·. Telegram 👇Join ያድርጉ
@yeresulnfkrmeglecha
@yeresulnfkrmeglecha
┄┄┉┉✽‌»‌‌🌹🌹»‌‌✽‌┉┉┄┄
i ሁዳዊው እንግዳ…ከሩቁ ስለ ውዱ ሰው እዝነት ቸርነታቸው፣ወዳጅም ተወዳጅ ስለመሆናቸው፣ታማኝ ፍትሓዊ እንደሆኑ፣ ሰው ሳይጠየፉ ኹሉን በፍቅር እንደሚያስጠጉ፣በዓለም ታሪክ ያልታየ ዳግም የማይታይ ውብ ስብዕናን የታደሉ የሰው አበባ መሆናቸውን ሲነገር ሰምቷል። ኑር ያካበባቸው በሸሻ መልከኛ፣ በአስተሳብ፣ በቁመናም ሆነ በግርማ ሞገስ ሑለመናቸው አሏህ በቁድራው ሙሉ አድርጎ የፈጠራቸው በሻሻ ተፈቃሪ ሰው መሆናቸው ተረድቷል።

የሰማው ዝና እንዲሁ ሰምተው፣ ተገርመውበት የሚታለፍ ዓይነት አልነበረም። ሩሕ ድረስ ዘልቆ የፍቅር ጎጆ የሚሰራ፣የቀልብን አፀድ ተቆጣጥሮ ምርኮኛ የሚያደርግ እንጂ። "አምጣልኝ፣ ዓይኑን ልየው…" እያለ ዓቅል’ና ልብን የሚያሸፍት። ዘወትር ወደ’ሱ እያሸፈተ እረፍት የሚነሳ ውትወታ’ና ፈላጊነትን የሚሞላ ነው።

ሰውዬው በሰይድ አቡበክር ዘመን ወደ መዲና ከተማ ገባ። ሲዲቅን አግኝቶ… «አንቱ አባበክር ሆይ ስለ ረሱለሏህ በጥቂት ቃላት ንገሩኝ?» በማለት ጠየቃቸው። ለሰይድ አቡበክር ግን የተፈቃሪያቸውን ምግባር እንዲህ ነበር ብሎ በቀላሉ ለመንገር የማይሰላ ነበር። «አንተዬ ነገሩ የጠና ነው። እስቲ በል ሰይድ ዑመር ጋር ዘልቀህ ጠይቃቸው» ብለውት ሸሹ።ነገሩ ለሰይድ ዑመር የከበደ ሆኗል።እሳቸውም «ባይሆን የዒልሙ ሐገር መዝለቂያ ደጃፍ ወደሆኑት ሰይድ ዓሊ ጋር ደርሰህ ጠይቅ!» ብለው ጠቆሙት።

ያደመጠው ኸበር በልቡ የለኮሰውን የትርታ ነዲድ ለማርገብ የጓጓው እንግዳ…« አንቱ አሊ ሆይ ስለ ረሱለሏህ በጥቂት ቃላት ንገሩኝ?» እያለ መጠይቁን አቀረበ። ሰይድ ዓሊም በነገሩ ተገርመው እንደ ብልህነታቸው…ለጥያቂው ጥያቄን አስከተሉ። «አንተ ሰው እስቲ ቀድመህ በዚህች ዓለመ ዱንያ ያለውን ፀጋ በጠቅላላ በጥቂት ቃላት ግለፅልኝ?» አሉት። ነገሩ ቢቆጠር፣ ቢዘረዘር የማይደረስ፣የማይቋጭ ለመንገር የማይቻል እንደሆነ የገባው ሰውዬም…«በዚህ ግዙፍና ሰፊ ዓለም ያለው ኒዕማማ ምኑ ተቆጥሮ፣በምን ቃል ይገለፃል? ይሄም ለወግም አይመችም አንቱዬ» ብሎ ምላሹን ሰጣቸው።

ሰይድ አሊም ይኼኔ ቁርዓናዊ ገለፃቸውን አቀበሉ… «አንተዬ አሏህ በቁርዓኑ …«ቁል መታዑ ዲንያ ቀሊል» ሲል ምን ያህል ትንሽ መሆኗን ያወራላትን ዱንያ አንተ አሁን በቃላት ለመግለፅ ከብዶሃል። ታዲያ አሏህ በቁርዓኑ…«ኢነከ ለዓላ ኹሉቂን ዓዚም…» ሲል ልቅናቸውን የመሰከረላቸውን ሰይዲ ረሱለሏህን በትንሽ ቃላት ልገልፅልህ ትጠይቀኛለህ?» አሉት። ይኼኔ ነበር የሰውዬው የልብ ትርታ የረጋው። ወዲያውም አለ…«አሽሓዱ አን ላኢላሃ ኢለሏህ፣ ወአሽሓዱ አነ ሙሐመደን ረሱሉሏህ»!💜

አሏሁመሰሊ ወሰሊም
አላ ሰይዲና ሙሐመድ!💜                              💚💛❤️
                                 💚💛❤️
                                       💚💛❤️
❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ   
      ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ              ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ
💚💛❤️
💚💛❤️
   💚💛❤️
       💚💛❤️
🙏ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡💚💛❤️
🙏እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ🙏
                   👇
                  👇
               👇👇
:¨·.·¨: ❀   ቻናላችንን ▶️🀄️🀄️ሉን!
·. Telegram 👇Join ያድርጉ
@yeresulnfkrmeglecha
@yeresulnfkrmeglecha
┄┄┉┉✽‌»‌‌🌹🌹»‌‌✽‌┉┉┄┄
በኡሁድ ጦርነት መስዋዕት የሆኑ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ ባልደረቦች በተነሱ ቁጥር በቀዳሚነት ከሚነሱት መካከል ሙስዓብ ኢብኑ ኡመይር ዋነኛው ነው። የሙስዓብ ህይወት በመስዋዕትነት የተከበበ ነበር። እያንዳንዱን የህይወት እንቅስቃሴውን ብንመለከት በእያንዳንዱ እርከን አንድ ነገር መስዋዕት ሳያደርግ አያልፍም! ለእስልምና ሲል ሀብቱንና ድሎቱን ሰውቷል። ሰሀቦች መዲና ከመሄዳቸው በፊት እንደ አምባሳደር የተላከው ቆንጅዬው ሙስዓብ ነበር ረዲየላሁ አንህ! 💛

የኡሁድ ጦርነት እንደሚታወቀው ለሙዕሚኖች ከባድ እና ፈተና የበዛበት ዘመቻ ነበር። ድል ለሙስሊሞች ይሆን የነበረውን ቀስተኞቹ ቦታቸውን በመልቀቃቸው ምክንያት ድል ለሙሽሪኮች ሆነ! በሰአቱ ሙስሊም ያልነበረው ኻሊድ ኢብን ወሊድ እና ወታደሮቹ ሙስሊሞችን ከጎን አጠቁ። ሰራዊቶቹም የአላህን መልዕክተኛ ﷺ ለማጥቃት ወደሳቸው መጋለብ ጀመሩ! ሰሀቦች ረሱለላህን ለመከላከል ወደሳቸው ሮጡ!

በዛ መሃል ሙስዓብ የሙሽሪኮች ትኩረት በጣም ከሚያፈቅራቸው ነብይ ላይ እንዲዞር መላ ዘየደ! እሳቸው ካሉበት ራቅ ብሎ በመሄድ ባንዲራውን ይዞ ጮክ ባለ ድምፅ ተክቢራ ማለት ጀመረ! እቅዱም ተሳካለት! ብዙ ፈረሰኞች ሙስዓብ ወዳለበት ስፍራ ዞሩ!

ነገር ግን! ሙስዓብ አሁን ተራው የሱ እንደሆነ አውቋል። ወደሱ ዞረው እንደሚያጠቁት ገብቶታል! በዛ ቅጽበት መወሰን እና ለራሱ መመለስ ያለበት ጥያቄ ነበር። "ማንን ነው አስበልጬ የምወደው?" ... እራሴን ወይስ የአላህን መልዕክተኛ ﷺ?" 🥺

ይህን ጊዜ ሙስዓብ ወደ ጠላቶቹ መጋለብ ጀመረ! ምን እንደሚፈጠር ያውቃል! ምን ውስጥ እየገባ እንዳለም ተረድቷል። ሰባ የሚሆኑ ሰዎች እሱን ሊያጠቁ እንደተዘጋጁ አውቋል! ሙስዓብ የሙስሊሞችን ባንዲራ አጥብቆ ያዘ! ከፍ አድርጎ እያውለበለም ወደነሱ ጋለበ! በዚህም ወቅት በጣም ጨካኙ ሙሽሪክ አብደላህ ኢብን ቀሚኣ ባንዲራው ከፍ ብሎ መውለብለቡን ሲመለከት በያዘው ሰይፍ ቀኝ እጁን ቆረጠው! ሙስዓብ ባንዲራውን ወደ ግራ እጁ አስተላልፎ ተክቢራውን ቀጠለበት! ግራ እጁንም ቆረጠው። መጨረሻ ላይ መያዝ የሚችለው በደረቱ ስለነበር በደረቱ የሙዕሚኖችን ባንዲራ ታቀፈው!

አንድ አካሉ በተቆረጠ ቁጥር እና ሙስሊሞች "መልዕክተኛው ሞ*ተዋል" የሚለውን የሀሰት ወሬ እያስተጋቡ መረበሻቸውን ሲመለከት በደከመ አንደበቱ: "ወማ ሙሐመዱን ኢላ ረሱል ቀድ ኸለት ሚን ቀብሊሂ ሩሱል!" የሚለውን ይደጋግም ነበር ይላሉ። ቆንጂዬው ሙስዓብ ተሰዋ! 70 የጎራዴና ጦር ቁስሎች ሰውነቱ ላይ አርፏል ይላሉ!

መልሱ እሱ ነበር! ...ማንን አስበልጬ እወዳለሁ ለሚለው ጥያቄው መልሱ ይህ ነበር! 💛

ሙስዓብ ሲሞት ከከፈን ውጪ ምንም አላገኘንም ይላሉ ሰሀቦች! ከፈኑም ሙሉ ሰውነቱን መሸፈን አልቻለም። "ጭንቅላቱ ሲሸፈን እግሩ ይገለጥ ነበር፤ እግሩ ሲሸፈን ደግሞ ጭንቅላቱ ይገለጥ ነበር።" ይላሉ! ያ ረብ!

ሸፊዒ ﷺ ከጦርነቱ በኃላ ሙስዓብ ጋር ሲደርሱ ስቅስቅ ብለው አለቀሱና እንዲህ አሉ! "ያ ሙስዓብ! ወላሂ በመካ ተመልክቼሃለው! በጌጥ እንዳንተ የተዋበ አልነበረም፤ በገፅታም ያማረ እንዳንተ ማን አለ?! ዛሬ ግን አንተን የምንሸፍንበት ሀብት ከቤትህ አጣን። ሁሉንም ለእስልምና አውለኸዋል። አዎ! አንተ አሁን ጭንቅላትህ በመናኛ ሸማ ተሸፍኗል። 'ፊል ጀነቱ ሂየ ሊቃእ: የምንገናኘው ጀነት ነው!' : አል ፊርዶውሱል አዕላ: የላዕለኛው ፊርዶውስ ውስጥ።" በማለት ተሰናበቱት! 😭

ሙስዓብ እጅግ በጣም ለሚያፈቅራቸው መልዕክተኛ ﷺ ሲል እጁ ተቆራረጠ! ለቁጥር የሚታክቱ ቁስሎችም አረፉበት! ይህ ሁሉ የሆነው ለኛ ነብይ ﷺ ነው! ለአለሙ ሹም! ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያ ረሱለላህ ﷺ!

አላሁመ ሰሊ አላ ሰይዲና ሙሐመድ ﷺ                              💚💛❤️
                                 💚💛❤️
                                       💚💛❤️
❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ   
      ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ              ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ
💚💛❤️
💚💛❤️
   💚💛❤️
       💚💛❤️
🙏ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡💚💛❤️
🙏እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ🙏
                   👇
                  👇
               👇👇
:¨·.·¨: ❀   ቻናላችንን ▶️🀄️🀄️ሉን!
·. Telegram 👇Join ያድርጉ
@yeresulnfkrmeglecha
@yeresulnfkrmeglecha
┄┄┉┉✽‌»‌‌🌹🌹»‌‌✽‌┉┉┄┄
#ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ!

ምንጩን ከዋናው ሰው እጅ የተጎነጩት ያስታውቃሉ። ልዩ ምልክት አላቸው። ሸኽ መሐመድ አልሐቢብ ሌሊቱን ሳይተኙ የሚያሳልፉ ባካኝ ነበሩ። ድቅድቁን ሌሊት ተከናንበው ከሃያ ሽህ ጊዜ በላይ ደጋግመው የጌታቸውን ሥም እያነሱ፣ "አላህ አላህ" ሲሉ ያነጋሉ። እድሜያቸው ዘጠናን ተሻግሮ፣ ጉልበታቸው ዝሎ፣ አካላቸው ደክሞም ይሄን ከማድረግ አላረፉም። አንድ ምሽት ታድያ እንደለመዱት "አላህ አላህ" እያሉ እየተወዘወዙ ሳለ ሌባ ቤታቸው ገብቶ ወደ ክፍላቸው ያመራል። እድል ቀንቶኝ ገንዘብ ወይ ጌጣጌጥ ባገኝ ብሎ መሳቢያዎቹን እየከፈተ ይበረብራል። ሸኹ መኖራቸውንም ልብ አላለም። የሌባውን መንጎዳጎድ የሰሙት ሸኽ ቀስ ብለው ጠሩትና የፈለገውን እንዲወስድ ብቻ መጽሐፎቻቸውን እንዲተውላቸው ጠዬቁት። ከዛም ባለቤታቸውን ሻይ አስፈልተው ሰጡት። እህልም አልቀመሰ ይሆናል ብለው ምግብ እንዲዘጋጅለት አደረጉ። በምቾትና በነፃነት ተመገበ። እንዳይጨነቅ አባሸሩት። ሲሳይ ስለሚለግሰው የሰማይና የምድር ባለቤት ነገሩት። ሁሉን ይቅር ስለሚለው አዛኙ ጌታ አወጉት። ለሁሉም ክፍት ስለሆኑት የንስኃ በሮች አጫወቱት። በማይታመነው የሸኹ ደግነት የተማረከው ሌባ የሚናገረው አጥቷል። ያፈነውን ግርምት በዓይኖቹ በኩል ለቀቀው። እንባ ያፈልቅ ጀመር። በዛቹ ቅፅበትም ወደ ጌታው ተመለሰ። አጋጣሚው ህይወቱን ቀዬረ። የአዛኙ ጌታና የአዛኙ ነቢ ሰዎች ማማራቸው!

አንድ እናክል!

ድፍን ሃገር ያወቀው ሌባ ነው። ታድያ የተለመደውን የሌብነት ተግባሩን ሊፈፅም አንድ ደጅ ይረግጣል። ዙሪያ ገባውን ቃኝቶ ማንም አለመኖሩን ሲያረጋግጥ ወደ ውስጥ ዘለቀ። ግን በለስ አልቀናውም። ቤቱ ውስጥ የጠበቀው ንብረት ቀርቶ ቁራሽ ዳቦም ያለ አይመስልም። ቢሆንም አንዴ ገብቷልና ኦናውን ቤት ተስፋ ባለመቁረጥ ማሰስ ጀመረ። ወዲያ ወዲህ እየተራወጠ አንዱን ሲያነሳ ሌላውን ሲጥል በቤቱ አንድ ጥግ መስገጃቸው ላይ ከተቀመጡት የቤቱ ባለቤት ጋር ተገጣጠመ። አንዳች ነገር ሳያገኝ ባዶ እጁን እየወጣ ነበር። ግርማቸው ለዓይን የሚሞላው ሰው "ባዶ እጅህን ከምትወጣ አንዴ በነቢዩ ላይ ሶለዋት አውርድና አስር ምንዳ ይዘህ ውጣ!" አሉት። የገጠመው ፈፅሞ ያልገመተው ነገር ነበር። ከፍንጅ የተያዘን ሌባ ሁሉም ተረባርቦ ግደለው ስቀለው በሚልበት ሃገር ባዶ እጅህን ከምትወጣ እንዲህ ያለ መልካም ሥራ ሠርተህ ምንዳ አግኝ የሚል ሰው መገኘቱ እጅግ አስገረመው። በድርጊታቸው የተማረከው ሌባ በሃፍረት አንገቱን ደፍቶ አጠገባቸው ተቀመጠ።

ሰውዬው ታላቁ ዓሊም ማሊክ ኢብኑ ዲናር ነበሩ። ሲረጋጋ ምክር ጠዬቃቸው። አንዴ ልቡን አግኝተውታልና ለምርኮኛቸው የሩህ ቀለብ ይሰፍሩለት ጀመር። በዚህ መካከል የሶላት ወቅት በመድረሱ አብረው ወደ መስጊድ ሊሄዱ ከቤት ሲወጡ ኢማሙን አጅበው ወደ መስጊድ ለመሄድ የተዘጋጁት ጎረቤቶቻቸው ዓይናቸው ባዬው ጉድ ተደናጡ። ማሊክ ኢብኑ ዲናር የሃገሩ ታላቅ ዓሊም መሆናቸውን ያውቃሉና በትዝብት "እውቁ ዓሊም ከእውቁ ሌባ ጋር!" ብለው አጉረመረሙ። ኢማሙም እንዲህ ሲሉ መለሱላቸው። "ሊሰርቀን መጥቶ ሰረቅነው።" እድለኛው ሌባ የኋላ ኋላ ኢማሙን ስር ስር እየተከተለ ታላቅ ደረሳቸው ለመሆን በቃ። በሌላ ወግ ደግሞ ውኃ በእቃ አምጥተው "በባዶ ከምትመለስ ውዱዕ አድርገህ ሁለት ረከዓ ሶላት ስገድ!" እንዳሉትና ሶላቱ ጥሞት እሳቸው የሚሆኑትን እዬሆነ ሶስት የእንግድነት ቀናት እዛው እንዳሳለፈ፣ ኢማሙን ተሰናብቶ ወደ አካባቢው ሲመለስም "ልሰርቅ ሄጄ ራሴ ተዘርፌ መጣሁ!" እያለ ያወራ እንደነበር ተነግሯል።

የጌትዬው ወዳጆች፣ የወለላው ኮቴ ተከታዮች!

#ሶሉ ዓለል ሐቢብ!
አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመዲን ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!💚💚💚                              💚💛❤️
                                 💚💛❤️
                                       💚💛❤️
❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ   
      ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ              ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ
💚💛❤️
💚💛❤️
   💚💛❤️
       💚💛❤️
🙏ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡💚💛❤️
🙏እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ🙏
                   👇
                  👇
               👇👇
:¨·.·¨: ❀   ቻናላችንን ▶️🀄️🀄️ሉን!
·. Telegram 👇Join ያድርጉ
@yeresulnfkrmeglecha
@yeresulnfkrmeglecha
┄┄┉┉✽‌»‌‌🌹🌹»‌‌✽‌┉┉┄┄
ከ30 አመታት በፊት መዲና ከተማ ላይ ነፍሰ ጡር ባለቤቱን ትቶ ለ*ጂ-ሀድ ወደ ቡካራ እና ሰመርቀንድ የሄደው ፈሩኽ ከ30 አመታት በኋላ በውድቅት ሌሊት ወደ ቀድሞ ከተማው መዲና ተመልሶ ገባ።

በጨረቃማው ሌሊት መዲና ከተማ ገብቶ ወደ ቀድሞ ቤቱ አቀና። ፈሩኽ ቤቱን አልተሳሳተም ነበር ቀጥታ ከነ ቀድሞ ይዘቱ ቤቱን አገኘው። የግቢው በር ትንሽ ገርበብ ተደርጎ ተመለከተ'ና በደስታ ሳያንኳኳ እንዲሁ ከፍቶ ገባ። ደጃፍ ላይ ቆሞ ግቢውን ሲመለከት ድንገት ከቤቱ አንድ ጎረምሳ ብቅ አለ።

ጎረምሳው ግቢው ውስጥ ሰይፉን ያነገበ ሰው ያለ ፈቃዱ ገብቶ ሲመለከት ለግብግብ እራሱን አዘጋጀ። ሁኔታውን በቅርበት ስታጤን የነበረችውን ባለቤቱን ግቢ ወደ ውስጥ አላት።

ባዶ እግሩን ከቤቱ ወጥቶ ፈሩኽን፦‹‹ጨለማን ተገን አድርገኽ እና ሰይፍህን ታጥቀህ ግቢዬ ምን ትሰራለህ?›› ብሎ ያዘው።
ሀለቱም ተያያዙ፤ ጨኸታቸው ሲያይል ጎረቤት ከየቤቱ መውጣት ጀመረ። የተሰበሰበው ሰውም ለጎረቤታቸው አግዘው ፈሩኽን በህብረት ያዙት።

የቤቱ ባለቤት ጎረምሳውም፦‹‹ወላሂ ለህግ ሳላቀርብህ አለቅህም አንተ የአላህ ጠላት!›› እያለ ይዝት ጀመር ሌባ መስሎት።

ፈሩኽም፦‹‹እኔ የአላህ ጠላት አይደለሁም። የገዛ ቤቴን ክፍት ሁኖ ሳገኘው ነው የገባሁት›› እያለ ይለፍፍ ጀመር። ግና ማንም ከቆብ አልቆጠረውም።

ወደ ህዝቡ ዞሮም፦‹‹ሰዎች ስሙኝ እንጂ! ይኼ ቤት የገዛ ቤቴ ነው። በንፁህ ገንዘቤ ነው የገዛሁትም። ሰዎች እኔ እኮ ፈሩኽ ነኝ፤ ከ30 አመት በፊት ለጂሃድ የወጣ ጎረቤታችሁን አንዳችሁም አታስታውሱትም ማለት ነው?›› ብሎ ጮኸ።

ይህን ሲል አንዲት አሮጊት መስኮቷን ከፈተች። ግቢው በህዝብ ተሞልቷል፤ ልጇ ከአንድ ታጣቂ ጋር ተፋጧል። አሮጊቷ ሰይፍ ታጣቂውን በትኩረት ስትመለከት ከ30 አመት በፊት አስፈቅዷት ለጂሃድ የወጣው ተናፋቂው ባለቤቷ ሁኖ አገኘችው።

ልሳኗ ተሳሰረ፣ አንደበቷ ተቆላለፈ፦‹‹ተዉት...! ልጄ ልቀቀው! የያዝከው እኮ አባትህ ነው።›› ብላ ጮኸች። አሮጊቷ ወጥታ ባሏን አቀፈችው፦‹‹ይሄ ምትታገለው እኮ ያኔ ያረገዝኩት ልጅህ ነው! የአብራክህ ክፋይ›› አለችው።

ፈሩኽ አይኖቹ በእንባ ተሞሉ፤ ያለየውን ልጁን እያሸተተው መሳም ጀመረ። ጎረምሳውም የአባቱ አንገት ውስጥ ገብቶ እዬዬ እያለ ይስመው ያሸተው ያዘ። አሮጊቷ ይኑር ይሙት መረጃው የሌላት ባሏ ድንገት ሲመጣ ደስታው እራሷን ችላ መቆም ተሳናት፤ ወደ ቤት ይዛውም ገባች።

ፈሩኽ የቆየበትን ምክንያት፣ በቆይታው የገጠሙትን ገጠመኞች ሁሉ ሲተርክላት አሮጊቷ ግን ልቧ ሌላ ጭንቅ ውስጥ ተጠምዶ ነበር'ና በወጉም አላደመጠችውም።

ተናፋቂ ባሏን በማግኘቷ የተሰማትን የደስታ ጣዕም አጣጥማ ሳትጨርስ ባሏ በአደራ መልኩ እሷ ዘንድ ያስቀመጠውን 30,000 ዲናር በማጥፋቷ ትካዜ ውስጥ ገባች። 30,000 ዲናር በአሁኑ ዘመን ሲመነዘር 60 ሚልየን ብር ይገመታል።

‹‹በአደራ እኔ ዘንድ ያስቀመጠውን ገንዘብ ቢጠይቀኝ ምላሼ ምን ይሆን? ያን ሁሉ ገንዘብ አንድን ልጅ ለማሳደግ አወጣሁት ብል ማንስ ያምነኛል? ልጄ እንደሁ ለራሱ ሳይሆን ችግረኛን ሲረዳ ነው ገንዘቡን የጨረሰው›› እያለች በውስጧ መብከንከን ጀመረች።

በዚህ ሀሳብ እየቆዘመች ሳለ ነበር ፈሩኽ፦‹‹ከሄድኩበት ስመለስ ይህን 4 ሺህ ዲናር ይዤ ነው የተመለስኩት፤ እናም አንቺ ጋር ካለው ዲናር ጋ አንድ ላይ አስቀምጪው›› ብሎ ከሀሳቧ ያባነናት።

ፈሩኽ ንግግሩን ቀጠለ፦‹‹በህይወት እስከቆየን ድረስ በዚህ ገንዘብ ለመኗኗሪያ ቤት እና አንድ ማሳ'ም እንገዛበታለን›› አላት።

ምላሽ አልሰጠችውም፤ ዝም አለች።

‹‹ገንዘቡን አምጪው እስቲ›› ብሎ ከ30 አመት በፊት ያስቀመጠውን ገንዘብ ጠየቃት።

‹‹በሚገባው ቦታ አስቀምጨልኻለሁ፤ ከትንሽ ቀናት በኋላ እሰጥኻለሁ...›› እያለችውም ንግግራቸውን የሱብሂ አዛን አቋረጠባቸው።

የዉዱ ውሀ ይዞ ልጁ ወደ ሚገኝበት ክፍል እየሄደ፦‹‹ልጄን ቀስቅሱት፤ መስጂድ አብረን እንሄዳለን›› አለ። ግና ልጁ ወደ መስጅድ ቀድሞት ሂዶ ኑሯል።

ፈሩኽ መዲና ከሚገኘው ከነቢዩ ሰዐወ መስጂድ ከግብቶ ሰገደ። ሰላቱ እንደተጠናቀቀም ወደ ቤቱ ሊሄድ ዞር ሲል ከኋላው የሰገደው ህዝብ ከሰላት በኋላ የሚሰጠውን ትምህርት ለማዳመጥ ተስተካክሎ ተቀምጧል፤ መውጫ መፈናፈኛ አልነበረም።

ፈሩኽ መውጫ ሲያጣ በቦታው ተቀመጠ፤ ህዝቡ ትምህርት የሚሰጠውን ሸይክ በጉጉት እየጠበቀ ሳለ አንድ ፎጣ የለበሰ ሰው ህዝቡ ፊት ወጥቶ ቁጭ አለ።

ሸይኩ የሚናገረውን እያንዳንዷን ንግግር ህዝቡ በማስታወሻ ይይዝም ጀመር። የሸይኩን ትምህርት ለመከታተል በኢስላሙ ዐለም ትልቅ ድርሻ የሚሰጣቸው እነ ኢማም ማሊክ እነ አቡ ሀኒፋ እነ ሱፍያን አሰውሪ እነ ያህያ ብኑ ሰዒድ እና ሌሎች ምሁራን በእንብርክካቸው ተቀምጠዋል።

ፈሩክ የሸይኹ ንግግር ማርኮት፤ የህዝቡ ጉጉት ገርሞት የሸይኩን ማንነት ለማጣራት ቢሞክርም የቦታው ርቀት እና የመስጅዱ ፅልመት ግን አልፈቀደለትም ነበር።

በዚህ ሁኔታ ሸይኩ ትምህርቱን አጠናቆ ከቦታው ብድግ ሲል ህዝቡ ከቦት እና አጅቦት ከመስጅድ ተከትሎ ወጣ። ፈሩክ ሸይኩን ሊዘይር ቢሞክርም ግፍያው አላስጠጋውም ነበር።

ድንገት ወደጎኑ ዞር ብሎ ከጎኑ ያለውን ሰው፦‹‹ኧረ እንደው በጌታህ! ይህ ሸይክ ማን ነው?›› ብሎ ጠየቀው።

ሰውዬውም፦‹‹የመዲና ሰው አይደለህም ነው?›› ብሎ በአግራሞት ፈሩክን ተመለከተው።
ፈሩክም፦‹‹እንዴታ! የመዲና ሰው ነኝ እንጂ!›› ሲል መለሰ።
ሰውዬውም፦‹‹እንግዲ የመዲና ሰው ሁኖ ሸይካችንን ማያውቅ የለም›› አለው።
ፈሩክም፦‹‹የመዲና ሰው ብሆንም ለ30 አመታት ከመዲና ራቅ ወዳለ ስፍራ ነበርኩ፤ ገና ማታ መምጣቴ ነው›› አለው።

ሰውዬውም፦‹‹በል እንግዲህ ትንሽ ቁጭ በል ስለ ሸይኩ ላውጋህ›› ብሎ አስቀመጠው።

ሰውዬው ንግግሩን ቀጥሏል፦‹‹ይህ ሸይክ ምንም እንኳ በእድሜው ልጅ እግር ቢሆንም የመዲና ከተማ ፈቂህ ነው። የእርሱን ትምህርት ለመከታተል እልፍ አእላፋት ይሰለፋሉ።

ደግሞም እንዴት ያለ ቸር እና ለጋስ ልጅ መሰለህ! ለዚህች አለም ደንታ የሌለው፤ ጭንቀቱ ሁላ አኺራ የሆነ ሰው ነው።›› ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ ፈሩኽ በጉጉት ንግግሩን አቋረጠው።

‹‹ስሙን እኮ አልነገርከኝም›› ሲል ፈሩኽ ጠየቀ።
ሰውዬውም፦‹‹ስሙ ረቢዓ አሰላሳዩ ይባላል›› አለው።
ፈሩኽ ግራ በመጋባት፦‹‹ረቢዓ አሰላሳዩ?›› ሲል ዳግም ጠየቀ።

ሰውዬውም፦‹‹አዎን! አሰላሳዩ ብለው ስም ያወጡለት የመዲና ዑለማኦች ናቸው፤ ብዙ ግዜ አሻሚ የሆኑ ሀይማኖታዊ ጉዳዮች ሲገጥሙ ዑለማኦች ወደሱ ያመጡታል፤ እሱም መፍትሄውን ከሸሪዓው አጣጥሞ ያበጃል። ለዝያ ነው አሰላሳዩ ያሉት›› አለው።

ፈሩኽ በዚህ ሸይክ በጣሙን ተደምሟል፦‹‹እስቲ እንደው ጎሳውን ንገረኝ፤ ዘሩ ከየት ይመዘዛል?›› ሲል ጠየቀ።

ሰውዬውም፦‹‹ረቢዓ የፈሩኽ ልጅ ይባላል፤ አባቱ ከ30 አመታት በፊት ነው መዲናን ለቆ ለጂ*ሀ"ድ የሄደው። ይህን ሸይክ ያሳደገችው እናቱ ናት ›› ብሎ ሲናገር ፈሩኽ እንባው ከአይኖቹ መፍሰስ ጀመሩ።

ይህ ገናና ዐሊም የሱ ልጅ መሆኑን ሲሰማ ፈሩኽ ዳግም በእቅፉ ሊያስገባው ሩጫ ወደ ቤት ጀመረ። ቤት ሲደርስም የፈሩኽ ሚስት ባሏ አይኖቹ በእንባ ተሞልተው ስትመለከት፦‹‹ምን ገጠመህ›› አለችው።

‹‹ደስታ ነው፣ ሀሴት ነው ሚያስለቅሰኝ፤ ልጄን በዕውቀት ማማ ላይ ተከብሮ ሳይ ደስታውን አልቻልኩም›› አላት።
ሴትዮዋ ብልህ ነበረች'ና አጋጣሚውን ለመጠቀም፦‹‹ከዚህ ደስታ እና እኔ ዘንድ ካስቀመጥከው ገንዘብ አንዱን ምረጥ ብትባልስ?›› አለችው።

‹‹እንዴታ! ይህን ደስታዬን ምድር ላይ ካለው ገንዘብ ሁላስ ቢሆን እንዴት አወዳድራለሁ›› ሲል ፈሩኽ መለሰላት።

‹‹እንግዲህ ይህን ለመሰለ ልጅ ገንዘቡን አውጥቼ አውዬዋለሁ፤ እሱም ገንዘቡን በሙሉ በአላህ መንገድ ላይ አውሎታል›› አለችው                              💚💛❤️
                                 💚💛❤️
                                       💚💛❤️
❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ   
      ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ              ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ
💚💛❤️
💚💛❤️
   💚💛❤️
       💚💛❤️
🙏ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡💚💛❤️
🙏እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ🙏
                   👇
                  👇
               👇👇
:¨·.·¨: ❀   ቻናላችንን ▶️🀄️🀄️ሉን!
·. Telegram 👇Join ያድርጉ
@yeresulnfkrmeglecha
@yeresulnfkrmeglecha
┄┄┉┉✽‌»‌‌🌹🌹»‌‌✽‌┉┉┄┄
#ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ!

ለሕዳቸው በነቢ ሚስክ ገላ ከታጠነላቸው አምስት እድለኛ ሰዎች ውስጥ አንዱ ነው። ሐረጉ በመዲና አቅራቢያ ከሚገኝ ሙዘይናህ የተባለ ጎሳ ይመዘዛል። ገና ልጅ ሳለ ነው አባቱን በሞት ያጣው። አባቱ ሲሞት አንዳች የተወለት ነገር አልነበረምና ከሚስኪን እናቱ ጋር ድህነት ደቆሳቸው። ሳይደግስ አይጣላም እንዲሉ የናጠጠ፣ እጅግ የተከበረ አጎት ነበረው። አጎቱ ልጅም ወራሽም አልነበረውም። ወደደው። እንደ ልጁ አድርጎ ያዘው። እሱም የርሱ ቢጤ ሃብታም እስኪሆን ድረስም በምቾትና በቅንጦት አሳደገው። አማርጦ ለብሶ፣ ያማረውን በልቶ፣ ተንደላቆ ኖረ። አሁን ጎርምሷል። ወለላው ነቢ በሒጅራ መዲና እስኪደርሱ ድረስ መካ ውስጥ እየሆነ ስለነበረው ነገር ምንም መረጃ አልነበረውም። ደጉ ሰው መዲና መግባታቸውን ከሰማ አንስቶ ግን በውስጡ የኢስላም ፍላጎት ያድር ጀመር። ከአካባቢው ወጣ እያለ ከመካ ወደ መዲና የሚጓዙ ሶሐቦችን ስለ ነቢ፣ ስለ ኢስላም ይጠይቃል። የቻሉትን ይነግሩታል። ቀልቡ ተከፈተ። ገና ነቢን ሳያይም እስልምናን ተቀበለ። ከሰው ተደብቆ ለጌታው ሲሰግድ ከረመ። አሁንም ግን አልረካም። ሶሐቦቹን ወዳገኘበት መንገድ ደጋግሞ እየወጣ አስተምሩኝ ይላቸዋል። እነሱን ቁረይሾች ከኋላ እያሳደዷቸው ነው። ብዙ ኪሎሜትሮች አብሯቸው እየኳተነ ይማራል። በዚህ መልኩ አጎቴ ከዛሬ ነገ ይሰልማል በሚል ተስፋ ጥቂት ዓመታትን አሳለፈ። ወይ የዓይኑን ረሐብ ነቢን አላዬ፣ ወይ አጎቱ አልሰለመ ትዕግሰቱ ተሟጠጠ። ሶሐቦቹም እዛው መዲና መጥቶ ነቢን እንዲያገኝ መክረውት ነበርና አንድ ቀን ቆረጠ። አጎቱን "ትሰልማለህ ብዬ በተስፋ ጠበቅኩህ። ግን አልሆነም። ስለዚህ ወይ ስለም አለዚያ እኔ መስለሜን ይፋ እንዳደርግ ፍቀድልኝ።" አለው። አጎቱ የሚይዝ የሚጨብጠውን አጣ። እሳት የሚተፉ ዓይኖቹን በልጥጦ "እስልምናን የምትቀበል ከሆነ ቁራጭ ልብስ ሳይቀር የሰጠሁህን በሙሉ እነጥቅሃለሁ።" አለው። የኖረበት ድሎት አላሳሳውም። ፈርጠም ብሎ "እንግዲያውስ ያሻህን አድርግ። እኔ ከዚህ ወዲያ ሃሰተኛ አምላክ ማምለኬን ትቻለሁ። እስልምናንም ተቀብያለሁ። ሁሉን ነገር መውሰድ ትችላለህ።" አለ። አጎት እንደፎከረው አደረገ። ዛቻውን ተገበረ። ቤሳ ሳያስቀር ባዶ እጁን ወደ እናቱ ላከው። ይህ ሰው ጀግናው የነቢ ወዳጅ ሰይድ አብደሏህ ዙልቢጃደይን ረ.ዓ ነው።

አሁንም አርፎ መቀመጥ አልሆነለትም። የነቢ ፍቅርና ናፍቆት እንቅልፍ ቢነሳው ወደ ነቢ ጉዞ ጀመረ። ይሄን ያወቀችው እናት በፍጥነት ወደ ጎሳዋ ሰዎች ሄዳ ነገረቻቸው። ልጇን እንዲመልሱላትም ጠየቀቻቸው። ሲመልሱት ሃለቱን ታውቃለችና "እሱ እጅግ ጨዋና ዓይናፋር ነው። ልብሱን ካወለቃችሁበት ወዴትም አያመልጥም።" ብላ ሚስጥር ሹክ አለቻቸው። እንደተባሉት እርቃኑን አስቀሩት። በመውደድ ተይዟልና አንድ ክፍል ብቻውን ተቀምጦ እህልና ውሃ እርም አለ። እናት ይሄን ስታይ አንጀቷ ተማታ። "ልጄ ሙሐመድ ጋር ካልደረሰ እህል ባፉ ላያዞር ምሏል። ይሞትብኛል ብዬ ሰግቻለሁና በቃ ልብሱን መልሱለት።" አለቻቸው። አሻፈረን አሉ። ጆንያ የመሰለ መከናነቢያዋን ሁለት ቦታ ቆርጣ ሰጠችውና እንዲሄድ ፈቀደችለት። የመውደዱ ዘማች ያችን እራፊ ጨርቅ አገልድሞ መዲና በምሽት ደረሰና በነቢ መስጅድ አረፍ አለ። ነቢ ለፈጅር ሶላት መጥተው ሲያዩት ማን እንደሆነ ጠየቁት። "አብዱልዑዝዛ እባላለሁ። ያንቱ ውዴታ ያሰደደኝ፣ ካንቱ ጋር መኖር የምሻ ምርኮኛ ነኝ።" ብሎ ስላሳለፈው፣ እሳቸውን መርጦ ስለተወው ነገር ሁሉ ነገራቸው። ዓይኖቻቸው በእንባ ተሞልተው "ያለህን ሁሉ ትተህ መጣህን? የጀነት ልብስም ምግብም ላንተ ይሁን፤ ከዚህ በኋላ ሥምህ አብዱላህ፣ ቅፅል መጠሪያህ ዙልቢጃደይን ነው፤ ከቤታችን አጠገብም ትኖራለህ።" አሉት። ከርሳቸው ለአፍታም መነጠል አይፈልግም። ቁርዓን ያስቀሩታል። ከእርሳቸው ከተለዬ በኋላ ደግሞ መስጅዳቸው በር ላይ ተቀምጦ የተማረውን ጮክ ብሎ ሲቀራ፣ ሲዘክር፣ ሲሰግድ ይውላል። አንድ ጊዜ ሰይድ ዑመር "ያረሱለላህ ይሄ ገጠሬ እዩልኝ ስሙልኝ ይመስል ቁርዓን ሲቀራ እየጮኸ ሌሎችን ሲረብሽ አልሰሙትምን?" አላቸው። ደጉ ነብይም "ዑመር ተወው እርሱ አላህንና መልዕክተኛውን ብሎ የተሰደደ ነው። ጌታቸውን አልቅሰው ከሚለምኑት ልበ ንፁሆችም ስለሆነ እንጂ ለታይታ አይደለም።" አሉት። ሰይድ ዙልቢጃደይን ማግባት የከጀለ ጊዜ መጀመሪያ ሰይድ አቡበክርን ቀጥሎ ሰይድ ዑመርን ሽምግልና ልኮ ነበር። ሆኖም ልጅት አልፈቀደችም። ዘይኔ ዜናውን ሲሰሙ አብሸር አሉትና ኒካሑን አሰሩለት።

መጨረሻው ደረሰ። ወሩ ልክ እንደ አሁኑ ረጀብ ነበር። ዘጠነኛው ዓመተ ሒጅራ። ነቢ ወደ ተቡክ ዘመቻ ሲነሱ አብደላህም አብሮ ተጉዞ ረሱልን "ያረሱለሏህ አላህ ሸሒድነትን እንዲያድለኝ ዱዓ አድርጉልኝ!" አላቸው። የግራር ዛፍ ልጥ እንዲያመጣ ነገሩትና ክንዱ ላይ አስረው "አላህ ሆይ ደሙን ለካሃዲያን እርም አድርገው!" አሉ። ይሄኔ በመከፋት ስሜት "አይ እንደሱ አልፈልግም!" አለ። በሻሻው ነቢ ፈገግ ብለው "አብሽር ጅሃድ ስትወጣ በትኩሳትም ሞትክ፣ መጓጓዣህ ገልብጦህም ሞትክ ያው ሸሒድ ነህ።" አሉት። ደስ አለው። ተቡክ ደርሰው ጠላትን ለሃያ ምሽቶች ጠበቁ። እሱ እዛው ታሞ በትኩሳት ሞተ። እሱ ብቻ ነው በዛ ዘመቻ ላይ የሞተው። ሰይዱና ቢላል ቢን ሐሪስ ረ.ዓ አብደላህ ሲቀበር አይቷል። ምሽት ነበር። ሰይድ ቢላል ኢብኑ ረባሕ ማሾ ይዟል። ነቢ ቀብሩ ውስጥ ገብተው "ወንድማችሁን በክብር አምጡት።" አሉና ጀናዛውን ራሳቸው አስተኝተው ቀብሩን በርብራብ ዘጉት። ከዚያም "አላህ ሆይ እኔ ተደስቼበታለሁ። አንተም ተደሰትበት።" ብለው ዱዓ አደረጉ። ረሱሉ በሞቱ በጣም አዝነው ነበር። ሃዘናቸውን ያዩት ባልደረቦቻቸው "ያረሱለሏህ በሞቱ በጣም አዝነዋል።" ሲሏቸው "አዎን እሱ አላህንና መልዕክተኛውን እጅግ ይወድ ነበር!" አሉ። ነቢ ለአብደላህ ዙልቢጃደይን ያሳዩትን ፍቅርና ክብር ሲያዩ ሰይድ አብዱላህ ኢብን መስዑድ "በአላህ ይሁንብኝ ምንም እንኳን እኔ ከሱ ቀድሜ እስልምናን የተቀበልኩ ብሆንም በሱ ቦታ በሆንኩ ብዬ ተመኘሁ።" አሉ። ሰይዱና አቡበክርም "ምናለ እዚህ ቀብር ውስጥ ያለሁት እኔ በሆንኩ!" ብለዋል። መገን ነቢ፣ መገን ፍቅር፣ መገን ወዳጆቻቸው!

ሶሉ ዓለል ሐቢብ!
አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!💚💚💚                              💚💛❤️
                                 💚💛❤️
                                       💚💛❤️
❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ   
      ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ              ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ
💚💛❤️
💚💛❤️
   💚💛❤️
       💚💛❤️
🙏ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡💚💛❤️
🙏እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ🙏
                   👇
                  👇
               👇👇
:¨·.·¨: ❀   ቻናላችንን ▶️🀄️🀄️ሉን!
·. Telegram 👇Join ያድርጉ
@yeresulnfkrmeglecha
@yeresulnfkrmeglecha
┄┄┉┉✽‌»‌‌🌹🌹»‌‌✽‌┉┉┄┄
#ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ!

ጭምቱ መኮንን የሙላው እርጋታ!

እጅግ ትሁት፣ ጨዋና ሰው አክባሪ ነበሩ። በማንም ላይ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አያውቁም። ለማንም ክፉ አይወጣቸውም። በሻሻ ፊታቸው ሁልጊዜ ፈገግታ አያጣም። በጣም መልካም፣ እዝነት የተሞላባቸውና የሁሉ አርአያ መሆናቸውን ከጌታቸው ቀጥሎ ወዳጆቻቸው ሁሉ በአንድ ድምፅ መስክረዋል። ቀድሞ ይጠሏቸው የነበሩትና የኋላ ኋላ ደግነታቸውን አይተው በፍቅር የወደቁት ባለቤታቸው እሜቴ ሰፊያ ቢንት ሁየይ "ከነብዩ የበለጠ መልካም ስነ ምግባር ያለው ሰው አይቼ አላውቅም።" ብለው ለትልቁ ሰው ፍቅራቸውን ገልፀዋል።
አብደላህ ኢብኑ መስዑድ "እርሳቸውን ባዬሁ ጊዜ ፊታቸው ላይ የአላህን ፍራቻና ትህትና አያለሁ።" ብለው የልባቸውን አውግተውናል። ኡሙ ሰለማ ደግሞ "እርሳቸው ከሁሉም ሰዎች የበለጠ ትሁት እና ለጋስ ነበሩ።" ብለው አከሉልን። ዓልይ ኢብኑ አቢ ጣሊብን "ሰይዳችን በጣም ለጋስ፣ ደፋር፣ እውነተኛና ከሁሉም ሰዎች የበለጠ ታማኝ ነበሩ።" ሲሉ ሰማናቸው። አቡ ሁረይራ በተራቸው "ከነብዩ የበለጠ ቆንጆ እና መልካም ባህሪ ያለው ሰው አይቼ አላውቅም።" ሲሉ የአዘሉን ሲር ሹክክ አሉን።

የሰው ቀልብ ያሳሳቸዋል!

አንድ ቀን አንድ ሰው እርሳቸው ዘንድ መጣና ንግግር ጀመረ። ተብታባ ነው። ቃል ከአንደበቱ ማውጣት ምጥ የሚሆንበት ዓይነት ። አብረዋቸው የነበሩ ሰዎች ተቁነጠነጡ። ይሄኔ ሰውየው በጣም አፈረ። ተጨነቀ። የኔ ነቢ ግን ምንም አልተናገሩም። አላቋረጡትም። ዝም ብለው በትዕግስት አዳመጡት። ሰውዬው ንግግሩን እንደምንም ሲጨርስ በረጋ መንፈስና በአክብሮት መለሱለት። በጣም ተደሰተ። በመልካም አያያዛቸውም ተገረመ።

ሰው አይለዩም። አይመርጡም። ሀብታም ይሁን ድሃ፣ ትልቅ ይሁን ትንሽ፣ ነፃ ይሁን ባሪያ፣ ለሁሉም እኩል ትኩረት ይሰጣሉ። አንድ ጊዜ ታድያ በመዲና እንዲህ ሆነ። ከባልደረቦቻቸው ጋር ተቀምጠው ሳለ አንዲት አሮጊት መጣችና አንድ ነገር ልትጠይቃቸው ፈለገች። ሴትዮዋ በጣም ዝቅተኛ ኑሮ የምትኖር እንደነበረች ይታወቅ ነበር። ባልደረቦቻቸው ሴትዮዋን ትንሽ አቅልለው ሲያዩ ነቢ ወዲያው ከተቀመጡበት ተነስተው በሙሉ አክብሮት አናገሯት። ጥያቄዋን አዳምጠውም የሚችሉትን ሁሉ እንደሚያደርጉላት አበሰሯት። ስትመለስ በደስታ ተሞልታ ነበር።

ከማንም ጋር ቃል ቢጋቡ ቃላቸውን ይጠብቃሉ። ጊዜው ቢረዝም አይረሱ፤ ለመሙላት ቢከብደቸው አያፈርሱ። ከሒጅራ በፊት መካ ሳሉ ከአንድ ሰው ጋር አንድ ነገር ለመግዛት ተስማምተው ነበር። ነገር ግን በወቅቱ ገንዘቡ አልነበራቸውም። ስለዚህ ለሰውዬው በቻሉ ጊዜ እንደሚመልሱለት ቃል ገቡለት። ቀናት አለፉ። ከመካ ወደ መዲና ተሰደዱ። ይህ ሆኖም እንኳ ያንን ቃል አልረሱትም። በተባለው ቀን ወደ መካ መልእክተኛ ልከው ሀቁን ሞሉ።

እንኳን ለሰው ለዛፍ ለውኃው ይቆረቆሩ ነበር። ዛፍ መቁረጥን ይከለክላሉ። እንዲያውም አንድን ዛፍ ያለ በቂ ምክንያት የቆረጠ ሰው በአላህ ዘንድ ተጠያቂ እንደሚሆን ይናገሩ ነበር። ውኃ እንዳይባክን ያስተምራሉ። አንድ ጊዜ ከባልደረቦቻቸው ጋር በአንድ ቦታ ሲያልፉ አንደኛው ውኃ እያባከነ ሲታጠብ አዩትና እንዲህ አሉት፦ "ወንዝ ዳር ሆነህ እንኳ ብትታጠብ ውኃ አታባክን።" ለአካባቢና ለተፈጥሮ ጠበቃ መሆን ዘመን አመጣሽ ፋሽን ሳይሆን ከሁሉን ቻዩና ዘመን ተሻጋሪው ነብይ ያየነው ነው። አንቱን ያገኘ ምን አጣ ያ ነብዬሏህ!?

ሶሉ ዓለል ሐቢብ!
አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!💚💚💚                              💚💛❤️
                                 💚💛❤️
                                       💚💛❤️
❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ   
      ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ              ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ
💚💛❤️
💚💛❤️
   💚💛❤️
       💚💛❤️
🙏ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡💚💛❤️
🙏እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ🙏
                   👇
                  👇
               👇👇
:¨·.·¨: ❀   ቻናላችንን ▶️🀄️🀄️ሉን!
·. Telegram 👇Join ያድርጉ
@yeresulnfkrmeglecha
@yeresulnfkrmeglecha
┄┄┉┉✽‌»‌‌🌹🌹»‌‌✽‌┉┉┄┄
የላይ ገንዳው ዘማች!

አሰላሙዓለይከ ያሷሒበል ኢስራዕ ወል ሚዕራጅ!

የአርሹ ባለቤት መረጣቸው። ሙሐመድ ብሎ ሾማቸው። ወደርሱ ጉዞ ጠራቸው። የላይ ገንዳን ግርዶ ገላለጠላቸው። የልቅናን ሸማ አለበሳቸው። ማንም ያልደረሰበት አደረሳቸው። ሥማቸውን ከሥሙ አድርጎ አሳያቸው። አይገርምህም ወይ የአላህ መለገስ መካ ተወልዶ አርሽ ላይ መንገስ?! በአርሹ ድንኳን ተሞሸሩበት። ጅብሪል የፈራውን የአርሽ የኩርሲይ ባሕር እንዳሻቸው ዋኙበት። የሲድረል ሙንተሐውን፣ የረፍረፉን፣ የመቃመል መሕሙዱን ጢሻ እየጣሱ አለፉት። የመዲናው አንዋር የሰማዩን ቀበሌ አበራው። ሰባ ሺውን ግርዶ በእጁ ገለጠው። ከኋላ መጥቶ ሁሉን በለጠው። ለተኳለ ለተዘዬነው ሙሽራ መለክ አሸርጦ አገልድሞ አደገደገ። ሚዜ ሊሆን ተሰበሰበ። በአርሽ የአዘል ሽቶ ተርከፈከፈ። ብኹር ተነሰነሰ። የቁድራ ጢስ ተጓፈጠ። የኑር ቄጤማ ተጎዘጎዘ። የነቢ ደስታ ታወጀ። ለዛም ነው ብዙ ሙሒቦች በዚህ ሌሊት መውሊድ የሚያወጡት። ኑሕ ቢወደድ፣ አደም ቢነሳ፣ ኢብራሒም ኸሊል ቢባል፣ ኢሳ ቢወሳ ያለ ነቢ በአርሽ የሰገደ አንድም የለም። አዎን ጌትዬ ለነቢ የሰጠውን ለማንም አልሰጠም። ለ‘ርሳቸው ያሳዬውንም ለማንም አልገለጠም። ከስጦታዎቹም ሁሉ በላጩ ሲዲቁ ሰይድ አቡበክር ረ.ዓ ሲቀሩ ሰዎች አይደለም በእውን በህልም እንኳን መከሰቱን ለማመን የተቸገሩበት፣ የመካ ጣኦታውያን የተሳለቁበት፣ በተከበረው ረጀብ ከመካ እስከ አቅሷ ከዚያም ወደ ሰማዬ ሰማያት ቡራቅ ጋልበው ያደረጉትና ተኝተው የነበረበት ፍራሽ ሞቅታው እንኳን ሳይበርድ የተመለሱበት ከስሌት በላይ የሆነው የኢስራዕና የሚዕራጅ ጉዞ ነው። ዓመል ሁዝን ነበር የሀዘን አመት። ነብዬ ሁለቱን ታላላቅ ምርኩዞቻቸውን እናታችንን ኸዲጃን ረ.ዓ እና አጎታቸውን አቡ ጧሊብን ያጡበት። ግና ሳይደግስ የማይጣላው ጌታ ሃዘናቸውን መርሻ፣ ላጡት መካሻ፣ ውድቀት እንዳይሰማቸው የበለጠ ከፍ ማድረጊያ ሰጣቸው።

የሆነው እንዲህ ነበር።
ከወደ ሒጃዝ ምድር፣ በመካ ዙሪያ አንድ ክቡር ሰው ጋደም ብለዋል። የፈጅር ወገግታ ከመቅደዱ ጥቂት ደቂቃዎች ቀደም ብሎ የዚህ ሰው በር ተንኳኳ። የመላዕክቱ ሁሉ አለቃ ሰይድ ጂብሪል በር ላይ ቆሟል። "ዛሬ የአላህ እንግዳ ነህና ተከተለኝ" አለ። ነቃ አሉና ውዱን ልብሳቸውን ተላብሰው ወደ መስጂደል ሐረም ሜዳ ወጡ። እኚህ ክቡር የአላህ ነብይ ይህንን ወዳጃቸውን ተከትለውት ወደ ውጪ ሲወጡ ሰይድ ሚካኢል የጀነቱን በቅሎ ቡራቅን በልጓሙ ይዞ ተመለከቱት። ተደነቁ። ወደ እርሱ ቀረቡ። ቡራቅ ነብዬን ያዬ ጊዜ በብዙ ሐያእ አድርጎ ተንበረከከ። ሱጁድም ኢክራም አደረገ። ጊዜ አላባከነም ሰይዱና ጂብሪል ተሳፈረው፣ ከዚያም ሰይዳችን ሙሐመድ (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ተፈናጠጡ፣ ሰይዱና ሚካኢል ተከተለና ጉዞ ጀመሩ። ወደተቀደሰችው ምድር፣ ወደተከበረው መስጂድ፣ ወደ መስጂደል አቅሷ አቀኑ። እዚያ ሰፊ ሜዳ ላይ መለክ የተባለ ሁሉ፣ ነብይ እና አርሳል በሙሉ፣ የጀነት ሁር በጠቅላላው ሰልፍ አሳምረው ቆመዋል። አውሊያው ሳዳቱ በሩሕ ሐድሯል። ከፊሉ በጀሰድም ተጥዷል ብለው በሰነድ ነግረውናል ሸይኾቻችን። እዚያ ሲደርሱ እኚያን በሩሕ የቀደሙ ነብይ ከሁሉም ኸልቅ ጋር አስተዋወቃቸው። ከአባታቸው አደም ጋር አዘያይሮ፣ ከወንድማቸው ኢስማዒል ጋር አስተቃቀፋቸው፣ ከመሪያቸው ከነቢ ኢብራሒም ጋር አቀማመጣቸው። ይህ ሁሉ በቅፅበት ተከወነ። ከዚያም አንቢያእ በሞላ በየደረጃው ተሰለፈ። መላኢካው እነርሱን ከበበ። ሰይዱና ጂብሪል የድንገቴ "ያ ሙሐመድ" ሲል ተጣራ። ሰይዱል ዉጁድም "ለበይክ" አሉ። "ወደዚህ ምኩራብ ቅረብ፣ ተቀደም፣ አሰግድ" አላቸው። ለሶላተል ኢብራሂምያ ጥሪ ተደረገ። በዚያ ዘመን ገና የነብያችን ሶላት አልተደነገገምና ሁለት ረከዓ ተሰገደ።

ነብያቱ ከሶላቱ መጠናቀቅ በኋላ ወደየመቃማታቸው ተመለሱ። ወዲያውኑ ጉዞ ቀጠለ። ወደ ሰማይ። የአንደኛው ሰማይ ተንኳኳ። በሰይዳችን ስም ተከፍቶ ዘለቁ። በየሰማዩ ነብያትን ዳግም አገኙ። ሰይዱና ኢብራሂም በይተል መእሙርን ደገፍ ብለው ሲያገኟቸው "ለሕዝቦችህ ሰላምታዬን አድርስልኝ" አሏቸው። እኛም "ወዓለይከ ሰላም ያኸሊለላህ" ብለናል። የሰማዩ ጉብኝት አልቆ ከከውኑ ክልል አለፉ። የፍጥረት መባቂያ ደረሱ። እዚያ ላይ ሰይዱና ጂብሪል ነብያችንን ከኑሩ ባህር ገፍተር አድርገው "በል ሂድ እኔ ቦታዬ እዚህ ነው" አሉ። ነብዬ ተደናገራቸው። የሰማዩን መንገድ አዋቂው፣ ጋባዡ እና አስጎብኚው በቃኝ ማለቱ አስፈራቸው። ከዛማ አንድም ፍጥረት ያልደፈረውን ሰይዳችን ደፈሩት። አለፉት። ተሻገሩት። የኑር ስብስቡ በሌላ ኑር ተዘፈቁ። ከመብረቅ ቅፅበት በፈጠነ፣ ጊዜ እና ቦታ፣ ቁጥር እና ስፍራ፣ አቅጣጫ እና እንዴታ በሌለው ዓለም ተሰየሙ። ራሳቸውን የዓርሽ ምንጣፍ ላይ አገኙት። አቆራርጠው ያለፉት ያ ሁላ ግርዶ ድንገት ትውስ ቢላቸው ተደናገጡ። "ፊ ሐድረቲ ሹሁዲ ረህማን" ተሰይመው መሆኑን ሲያውቁ ድፍት አሉ። ዒባዳ ለጠቁ። ጌታቸውን በማወደስ ዋለሉ። "አትህያቱ" እያሉ ተደገደጉ። የጌታቸውንም ሰላምታ ተሸለሙ። የወዳጆቹ ወግ ደራ። ደጉ ሰው በደስታውም በሃዘኑም እኛን ካላነሳሱ አይሆንላቸውም። "አሰላሙዓለይከ አዩሃ ነቢዩ!" የተባሉ ጊዜ ዓለሙን በሚያስረሳ የደስታ ማማ ላይ ሆነው አልረሱንም። "አሰላሙዓለይና ወዓላ ኢባዲላሂ ሷሊሒን!" ብለው በዛ ሐድራ ወሊዮቹ ጋር ጣዱን። በዚያ እነ ሰይድ ጂብሪል ሁሉን በሚረሱበት ዓለም ኡመታቸውን አስታወሱ። ሁሉን ዋ ለነፍሴ ዋ ለራሴ በሚያስብለው የጭንቅ ጊዜም ኡመቲ ኡመቲ ነው የሚሉት።

ኢስራዕ ተአምር ነው። ጌትዬው ተዓምርነቱን ሲገልፅ "ያ ባሪያውን ከተከበረው መስጊድ ወደዚያ ዙሪያውን ወደባረክነው ወደ ሩቁ መስጊድ በሌሊት ያስኬደው ጌታ ጥራት ይገባው!" ይልና "ከተዓምራቶቻችን ልናሳዬው!" ይላል። ጉዞውን እንዳጠናቀቁ አቡ ጀሕል ስለ ተዓምሩ ሰማና ሰዎች ሰብስቦ አሳቀባቸው። ሌሎቹም አምኖ መቀበል ከበዳቸው። አቅሷን የሚያውቁ ሰዎች ሊፈትኗቸው ስለ አካባቢው ጠይቀዋቸው ማስታወስ ባይችሉም አላህ አቅርቦ አሳይቷቸው አስረድተዋቸው ትክክል መሆናቸውን መስክረዋል። እንደዚሁም ሌላ በጉዟቸው ያጋጠማቸውንና አስረጂ ይሆንልኛል ያሉትን ተናግረው ሰዎቹ ሲያጣሩ ሃቅ ሆኖ አግኝተውታል። ግና ሲደፈንብህ ማስረጃም መረጃም አያስረዳህምና አልተቀበሉም። አስረዳን የምንለው ለዚህ ነው። ኢስነይንና ኢስራዕ ገጠመ። ምን ይሁን ትላለህ ከዚህ የበለጠ! እንባ አበሹ ጌታ፣ ለሀዘናቸው መፅናኛ የላከው ጌታ፣ ከሃም ጘም መውጫ ይላክልን። ሲሩ ባልታወቀው የኻሉቅና መኽሉቁ ግንኙነት ይሁንበት!

ለነቢ ደስታማ ለይሉን እንቆማለን። ቀኑን እንፆማለን። እንኳን አደረሳችሁ!
አሏሁመሶሊ ዓላ ሙሐመዴ የጅብሪል ወዳጅ የአላህ ባለሟል ሰይዲ ጀማሉል ጀማል!💚💚💚                              💚💛❤️
                                 💚💛❤️
                                       💚💛❤️
❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ   
      ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ              ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ
💚💛❤️
💚💛❤️
   💚💛❤️
       💚💛❤️
🙏ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡💚💛❤️
🙏እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ🙏
                   👇
                  👇
               👇👇
:¨·.·¨: ❀   ቻናላችንን ▶️🀄️🀄️ሉን!
·. Telegram 👇Join ያድርጉ
@yeresulnfkrmeglecha
@yeresulnfkrmeglecha
┄┄┉┉✽‌»‌‌🌹🌹»‌‌✽‌┉┉┄┄
                              💚💛❤️
                                 💚💛❤️
                                       💚💛❤️
❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ   
      ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ              ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ
💚💛❤️
💚💛❤️
   💚💛❤️
       💚💛❤️
🙏ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡💚💛❤️
🙏እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ🙏
                   👇
                  👇
               👇👇
:¨·.·¨: ❀   ቻናላችንን ▶️🀄️🀄️ሉን!
·. Telegram 👇Join ያድርጉ
@yeresulnfkrmeglecha
@yeresulnfkrmeglecha
┄┄┉┉✽‌»‌‌🌹🌹»‌‌✽‌┉┉┄┄
#ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ!

ሲወዳቸው ልክም የለው። ቢያዝኑ ራሱ ያባብላቸዋል። ብቸኝነት ቢሰማቸው በመለክ ያጅባቸዋል። ቢናፍቁ፣ "ትቶኝ ይሆን?" ብለው ቢሰጉ ቁርዓን ያወርድላቸዋል። ቀልባቸው ቢሰበር ለመጠገን ከውኑን ያገላብጠዋል። ፀሐይ እንዳይነካቸው ደመና እንደ ጃንጥላ ይዘረጋላቸዋል። ባልደረቦቻቸው ውኃ ቢጠማቸው ከተባረከ ጣታቸው ውኃ ያፈልቅላቸዋል። ለጨለመበት ማብሪያ ገላ ምግባራቸውን አብርቶላቸዋል። ሰው አላምን ቢላቸው በቃሉ ሙግት ይገጥምላቸዋል። አለፍ ካለም ጨረቃ ይገምስላቸዋል። በድንጋይ በዛፉ፣ በአዕዋፍ በእንሰሳው ያስመሰክርላቸዋል። ሁሉን ለርሳቸው ገርቶታል። በያ’ገሩ ያለው ሁላ ደግሞ "የኔ ነሁ!" ይላቸዋል። ኧረ እንኳን ሠው ቀናትም ወራትም ይፎካከራሉ። ይሄው ሻዕባን ነቢም ሶለዋቱም የኔ ናቸው እያለ ይፎክራል። ለኛም ደጉ ወር ከለይሉ ጋር ገጠመልን።

ውልውል እንዳለው ሰማይ ለተመልካች ሁሉ ውብ፣ ከነውርም የፀዱ አድርጎ ዘይኖ ነው የኸለቃቸው። የኔ ነቢ የሙሐባቸው ጥላ ሥፍራ፣ ጎሳ፣ ቀለም፣ እድሜ ሳይመርጥ በሁሉም የሰው ዘር ቀልብ ላይ ማረፉን ተመልክቼ ስገረም ወዲያው وَرَفَعْنَا لَكَ ذِكْرَك ብሎ የነገራቸው ቃል አዘል ብስራት ትውስ ይለኛል። መወሳታቸው ከፍ እንዲል አድርጓል። ነቢ የዓለም ቋንቋችን፣ አዛናችን፣ ኹጥባችን፣ ዱዓ ኢስቲጃባችን፣ መሰብሰቢያ ቂብላችን ናቸው። የውበታቸው ወጋገን የፈነጠቀለት፣ የስብዕናቸው ጮራ የወጣለት ሁሉ በየአንደበቱ በየልሳኑ ያወዳድሳቸዋል። በወሎ መቸስ ሰይድ ጫሌ "ሳልጠነሰስ በናቴ ማ’ጠን ፊት ጀምሬያለሁ መድሑን ማጠንጠን!" እንዳሉት ሳር ቅጠሉ፣ ሜዳ ገደሉ፣ ተራራ ዛፉ ሴት ወንዱ ሁሉ ነቢ ነቢ ነው ድልቂያው!

ከአካባቢዬና ከለመድኩት አለፍ ሻገር እያልኩኝ የማዬት ልምድ አለኝ። አርጎባ በሐድራ መሃል የነቢ ስም ሲጠራ በደስታ ወደ ሰማይ ይተኮሳል። ጎንደር፣ ዳንግላ፣ ሞጣና ባሕርዳር ጠምደው ሲያርሱ ውለው የሚያድሩ የሐድራ ገበሬዎች ተቆጥረው አያልቁም። አንድ ሰሞን "አወየው ነቢ!" የሚል ልብ ብርብር የሚያደርግ የአፋርኛ መድሕ ሰምቼ ያለርሱ ምንም አላዳምጥም ነበር። በሐረሪ ዚክርና መድሖችም ተለክፌ አውቃለሁ። አንድ ጊዜ ወደ ሶማልኛ ተሻግሬ በሶማልኛ ቋንቋ የተሠሩ የነቢ መወድሶችን መስማት አዘውትሬ ነበር። ሴት አይል ወንድ፣ አዛውንት አይል ወጣት ደስ የሚሉ አወዳሾች አሏቸው። ሰሞኑን ደግሞ "ወለላ ወለላ" የሚል ትግርኛ መንዙማ ያዋልለኝ ይዟል። ሩሕ ከተገናኘ ቋንቋን አለመረዳት ሙሐባን ከማጣጣም አያግድም። በኦሮምኛው፣ በጉራጊኛው ነቢ ያልተወደሱበት ምን አለ?
ከሐበሻ ወጣ ብለን እዚህ ጎረቤት ሱዳን ብናርፍ ከነቢ ዳውድ ዓ.ሰ ድምፅ ተጨልፎ የተሰጠ በሚመስለው ድምፃቸው ከልብ በመነጨ ፍቅር ልጅ አዋቂው ነቢ ነቢ ሲል እናገኛለን። ኤርትራና የመንማ ዋነኛ ዓሺቆች ናቸው። ሞሪታንያ ቢባል ሲሼልስ፣ ታንዛኒያ ቢኬድ ማሊ የነቢ ሑብ ያማለለውና ለፍቅራቸው የሚቀኘው እልፍ ነው። ወደ ሞሮኮና አልጄሪያ የተቃናችሁ እንደሆነ በሶለዋትና በዚክር የተገነቡ የሙሒብ አገራት ናቸው ትላላችሁ። መለስ ብለን ወደ ምዕራቡ ብናቀና የምናገኛት ሴኔጋል የሳፊዎቹ ሱፊዮች የመድሕ ጠረን ያውደናል።

ከአፍሪካ ሻገር ብለን የነቢን ስም ሲሰሙ እጃቸውን ደረታቸው ላይ የሚያሳርፉት ቱርኮች ጋር ብንሐድር ለነቢ ያላቸው ፍቅር ለጉድ ሆኖ እናየዋለን። ፋርስም ሻምም ብንዘልቅ የምናገኘው ያንኑ ነው። ማሌዥያማ ኸልቁ ሁሉ በሙሐባ የተሞላ ነው። ጭራሽ ቺቺንያ ነቢ የሚልቁት በመሪ ደረጃ ነው። ሕንድና ፓኪስታኖችን ያዬ ሌላው መች ነቢን ይወዳል ይላል። አንዳንድ ጊዜ በተለያዩ ክፍላተ ዓለማት የተካሄዱና በየጊዜው የሚደረጉ የመውሊድ አከባበሮችን አያለሁ። ሠው ሁሉ አፉን በፈታበት፣ በገራለት ፍቅሩን ሲገልፅላቸው ሳይ ደስ ይለኛል። ብቻ ነቢ ታድለዋል። "አንተን ለኔ፣ ከውኑን ላንተ" ብሏቸው መኽሉቁ ሁላ ያደገድግላቸዋል። ሁሉ "የኔ" ይላቸዋል። ቀልቡን ይሰዳል፣ እጁን ይዘረጋል። እንኳንም ተኸለቁ፣ እንኳንም የርሳቸው ተከታይ ሆንን፣ እንኳንም በተውፊቁ ሙሐባቸውን ረዘቀን፣ እንኳንም አደግዳጊ አደረገን! መደድ መደድ ያረሱለሏህ!

#ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ!
አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!💚💚💚
                              💚💛❤️
                                 💚💛❤️
                                       💚💛❤️
❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ   
      ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ              ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ
💚💛❤️
💚💛❤️
   💚💛❤️
       💚💛❤️
🙏ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡💚💛❤️
🙏እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ🙏
                   👇
                  👇
               👇👇
:¨·.·¨: ❀   ቻናላችንን ▶️🀄️🀄️ሉን!
·. Telegram 👇Join ያድርጉ
@yeresulnfkrmeglecha
@yeresulnfkrmeglecha
┄┄┉┉✽‌»‌‌🌹🌹»‌‌✽‌┉┉┄┄
                              💚💛❤️
                                 💚💛❤️
                                       💚💛❤️
❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ   
      ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ              ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ
💚💛❤️
💚💛❤️
   💚💛❤️
       💚💛❤️
🙏ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡💚💛❤️
🙏እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ🙏
                   👇
                  👇
               👇👇
:¨·.·¨: ❀   ቻናላችንን ▶️🀄️🀄️ሉን!
·. Telegram 👇Join ያድርጉ
@yeresulnfkrmeglecha
@yeresulnfkrmeglecha
┄┄┉┉✽‌»‌‌🌹🌹»‌‌✽‌┉┉┄┄
ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ!

ዑስማንን የሐያዕ ዝናር ያስታጠቀው!

ነቢ "እያንዳንዱ ነብይ በጀነት ልዩ ባልደረባ ይኖረዋል። የኔ የጀነት ልዩ ባልደረባ እሱ ነው!" ብለዋቸዋል። የተወለዱት በመካ ከሀብታም እና እጅግ ከተከበረ ቤተሰብ ነው። ወለላው ነቢ ወደ ኢስላም ጥሪ ሲያደርጉ በሰይድ አቡበክር ረ.ዓ ግብዣ እስልምናን ከተቀበሉት የመጀመሪያዎቹ ሰዎች አንዱ ሲሆኑ ለዲኑ ያላቸውን ሁሉ ሰጥተዋል። የተዋጣላቸው ነጋዴ እንዲሁም ሀብታም ነበሩ። ሀብታቸውን ግን ሙስሊሞችን ለመርዳት እንጂ ለግል ጥቅማቸው ሲያውሉ አልታዩም። ከባድ ድርቅ ቢገጥም ከሻም የመጣን እህል በሙሉ ገዝተው በነፃ ለሙስሊሞች አከፋፈሉ። ሙስሊሞች በመዲና በነበሩበት ጊዜ የመጠጥ ውኃ እጥረት ቢከሰት የሩማ የተባለውን የውኃ ጉድጓድ ገዝተው የአረዳውን ጥም ቆረጡ። የመዲና መስጂድ በሙስሊሞች ቁጥር መጨመር ምክንያት እየጠበበ ሲመጣ በገንዘባቸው መስጂዱ እንዲሰፋ አደረጉ። የሙስሊሙን የጦር ሰራዊት በገንዘብ እና ቁሳቁስ ሲደግፉ ኖሩ።

ከወለላው ነቢ በቀጥታ ተጎንጭተዋል። መጀመሪያ ከሰይደት ሩቀያ ረ.ዓ ጋር እሷ ከሞተች በኋላ ደግሞ ከሰይደት ኡሙ ኩልሱም ረ.ዓ ጋር ተጋብተው የሰይዳችንን ሁለት ሴት ልጆች የማግባት እድል አግኝተዋል። በዚህም ምክንያት "ዙ ኑረይን" የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸዋል። "የሁለት ብርሃኖች ባለቤት!" ደጉ ሰው ያለፉ ጊዜም ከሰይድ አቡበክርና ሰይድ ዑመር ቀጥሎ ሶስተኛ ምትክ ሆነው ለአስራ ሁለት ዓመታት አገር አስተዳድረዋል። በርሳቸው የኸሊፋነት ዘመን የእስልምና ግዛት ይበልጥ ሰፍቷል። በምስራቅ እስከ አሁኗ ኢራን እና አፍጋኒስታን፣ በምዕራብ ደግሞ እስከ ሰሜን አፍሪካ ድረስ ዘልቋል። ይህ መስፋፋት የእስልምናን መልዕክት በበርካታ አካባቢዎች ለማድረስ ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል። ታድያ ከግዛቶች መስፋፋት የተነሳ ቁርአን በተለያዩ ቦታዎች በተለያየ መልኩ ይነበብ ነበር። ይህ ልዩነት ወደፊት አለመግባባት እንዳያስከትል የሰጉት ኸሊፋው የነቢ የቅርብ ባልደረቦች የነበሩትን ሰይድ ዘይድ ኢብኑ ሳቢትን ረ.ዓ ጨምሮ ሌሎች ታላላቅ ሰሃቦችን በማሳተፍ ሰይዳችን በህይወት እያሉ የተጻፉትን የቁርአን ክፍሎች በጥንቃቄ በመሰብሰብና በማረጋገጥ አንድ ወጥ የሆነ የቁርአን ቅጂ እንዲዘጋጅ አድርገዋል። ይኸውም "የዑስማን ሙስሐፍ" በመባል የሚታወቀውና ዛሬ ድረስ የምንጠቀምበት ቅጂ ነው። የቁርአን ቀላጤ ናቸው። ቁርአንን በቃላቸው ከሸመደዱ ጥቂት ባልደረቦች መካከልም አንዱ ነበሩ። እስትንፋሳቸው እስኪቋረጥ ድረስ ቁርአንን አዘውትረው በማንበብ አሳልፈዋል።

ይህ ታላቅ ሰው ሥማቸው ብዙም የማይነሳው፣ እጅግ ለስላሳ፣ ዓይናፋር እና ጨዋ የነበሩት፣ በሐያእ እና በልከኝነታቸው የሚታወቁት ሰይድ ዑስማን ኢብኑ ዓፋን ረ.ዓ ናቸው። ነቢ ስለ እርሳቸው ሲናገሩ "መላኢኮች እንኳን ዑስማንን ያፍራሉ።" ብለዋል። ዑስማን ረ.ዓ በኸሊፋነታቸው ዘመን ውስጣዊ ተቃውሞዎችና ግጭቶች ገጥመዋቸዋል። እሳቸው ግን በእነዚያ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሳይቀር ፀንተዋል። በመጨረሻም በሙስሊሞች መካከል ከፍተኛ ሀዘን እና ቁጣን የቀሰቀሰ ነገር ተከሰተ። እየተባባሰ የመጣውን ተቃውሞ ተከትሎ ሰይድ ዑስማን በቤታቸው ውስጥ ቁርአን እያነበቡ ሳለ በሰዎች እጅ ተገደሉ። ሲያነቡት የነበረው አንቀጽ "በእርሱ ባመናችሁት ቢጤ ቢያምኑ በእርግጥ ተመሩ። ቢዞሩም እነርሱ በጭቅጭቅ ውስጥ ብቻ ናቸው። እነርሱንም አላህ ይበቃሃል፤ እርሱ ሰሚው ዐዋቂው ነው!" የሚል ነበር። ጌታቸውን እንደወደዱ፣ ነቢን እንዳፈቀሩ፣ ለቁርአን እንደተንሰፈሰፉ ኖረው ደማቸው እዛው ባልተለዩት ገጽ ላይ "አላህ ይበቃሃል" የሚለውን ለይቶ ፈስሶ አለፉ።

ሶሉ ዓለል ሐቢብ!
አላሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!💚💚💚                              💚💛❤️
                                 💚💛❤️
                                       💚💛❤️
❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ   
      ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ              ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ
💚💛❤️
💚💛❤️
   💚💛❤️
       💚💛❤️
🙏ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡💚💛❤️
🙏እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ🙏
                   👇
                  👇
               👇👇
:¨·.·¨: ❀   ቻናላችንን ▶️🀄️🀄️ሉን!
·. Telegram 👇Join ያድርጉ
@yeresulnfkrmeglecha
@yeresulnfkrmeglecha
┄┄┉┉✽‌»‌‌🌹🌹»‌‌✽‌┉┉┄┄
#ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ!

የአላህ ካዝና ቁልፉ!

ሸዕባን የሰይዳችን ወር ነው። ዱዓቸው ተሰምቶ ጨረቃ ከሁለት የተገመሰላቸው በሸዕባን ነው። መዲና ላይ ቂብላ እንዲቀዬር ፈልገው ቂብላው እርሳቸው እንደሚፈልጉት የሆነው በዚሁ ወር ነው። ለዑመታቸው ሸፋዐ የመሆናቸው ብስራት የደረሳቸውና ረመዷንን የተሰጡትም በዚሁ ወቅት ነው። ከምንም በላይ "አሏህና መላኢካዎቹ በነብዩ ላይ ሶለዋት ያወርዳሉና እናንተም አውርዱ!" የሚል መልዕክት ያለው የቁርአን አንቀፅ የወረደውም በዚሁ ጊዜ ነው። በሸዕባን ከሁሉም ሥራ በላይ የሚወደደው ሶለዋት ማብዛት ነው። ምንም ሥራ ብንሠራ ሥራችን እንጥልጥል ነው። እርግጠኛ የሚኮንበት ነገር የለም። ወይ ማትረፍ ነው፣ አልያም ዋናውን መያዝ ነው፣ ኪሳራም አይጠፋም። ሐቢበሏህን ማውሳት ሲቀር። የሶለዋትን ምርጥ ዘርማ የትም እንዴትም ብንዘራው ዝናብ አይፈልግ፣ ፀሀይ አይፈራ ያብባል፣ ፍሬ ይሰጣል፣ በሶለዋት ታጅበው ያነሱት እጅ ባዶውን አይመለስም!!

ኒስፉሳ? ኒስፉማ ዒዳቸው ነው። ለዛውም "ምን ቢሞኙ ኸሚስን አይተኙ!" የተባለላት የሶለዋት መንቧቢያዋ ለይለቱል ጁምዓ ጋር ገጥሞ! "ምን ይሁን ትላለህ ከዚህ የበለጠ!?" ያሉት’ኮ እንዲህ ያለ ሰርግና ምላሽ አንድ ላይ ተደግሶላቸው ነው። ታድያ እንዲህ ያለ እጣ ገጥሞን ሶለዋቱን ማጋጋም እንጂ ሌላ ምን ትካር አለን? አዎ ማደግደግ ይበጃል መርቅኖ ለነቢ! እንግዲህ ለይሉን የጉርጁን አሳላፊውን፣ የደጁን ሚፍታሑን ፋቲሑን ነቢ ዘይኔን ይዘን በጌትዬው ቀዬ እንንጎራደዳለን። ያ ሐናን…ያመናን እንለዋለን። ሰቢትና ዓለል ኢማን፣ ሰሊምና ነጂና ሚነል በላዕ እያልን እንለምነዋለን። በሐጃ መሙያዋ፣ በፈረጃ ማግኛዋ፣ በበጀት ማፅደቂያዋ፣ በዑምር መቀጠያዋ፣ ለይለቱል በራእ ላይ ተገኝተንማ አንተኛም። ለተከበረችው፣ እጅግ ከፍ ያለ ደረጃ ላላት፣ ዱዓ የበለጠ ተቀባይነት ከሚያገኝባቸው አምስት ሌሊቶች ዋናዋ ለሆነችው ለይል አድርሶንማ አናንቀላፋም። ሰውታችን አርሽ አደባባይ እንዲሰማ፣ በላዑ ተብሪድ፣ አገሩ አማን፣ የታመመው ዓፍያ እንዲሆን፣ ዑዝረኛው  ከዑዝሩ፣ የጨነቀው ከሐም ጘምሙ እንዲላቀቅ፣ የደከመው እንዲጀደድ፣ ያጣው እንዲያገኝ፣ የከፋው እንዲስቅ፣ የራቀው ኸይር እንዲቀርብ፣ አልሆን ያለው እንዲገራ፣ ጧዓ እንዲጣፍጥ፣ ቀልባችን ጦሀራ፣ ሙሐባችን በሐቂቃ፣ ሥራችን በኢኽላስ እንዲሆን በላይ ገንዳው ግርዶ እንጎናበሳለን። የሚዘንበውን ራሕመት ለይሉን ቆመን፣ ቀኑን ፆመን እንቀበለዋለን።

በሶስት ያሲን እማይበጀን ይታገድ፣ ሪዝቃችን ሰፋ እድሜያችን ገፋ ይበል፣ አዋጁም ፍራጁም ለ‘ኛ ይሁን፣ የሻ የሻውን ያግኝ፣ የኛ የተባለን ሁላ ከሸር አሽራር በሲትሩ ጥላ በሒፍዙ አጥር ጥብቅ ክልክል ያድርግልን ነቢ መጀን!! አዎ ዛሬማ እጣችን ይገለጥ እያሉ ያሲኑን ተባረኩን፣ ኢኽላሱን፣ ፈለቁን፣ ናስ እና ፋቲሐውን በዬሱራው በዬፈኑ መግለጥ ነው። ዓይሻችን እንደ ሚስክ ያውድ እያሉ ሶላዋትና ዱዓውን እንደ ወሎ ጭስ ማጓፈጥ ነው።

#ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ!
አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!💚💚💚                              💚💛❤️
                                 💚💛❤️
                                       💚💛❤️
❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ   
      ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ              ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ
💚💛❤️
💚💛❤️
   💚💛❤️
       💚💛❤️
🙏ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡💚💛❤️
🙏እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ🙏
                   👇
                  👇
               👇👇
:¨·.·¨: ❀   ቻናላችንን ▶️🀄️🀄️ሉን!
·. Telegram 👇Join ያድርጉ
@yeresulnfkrmeglecha
@yeresulnfkrmeglecha
┄┄┉┉✽‌»‌‌🌹🌹»‌‌✽‌┉┉┄┄
#ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ!

አልሐምዱሊላሂ ምን ልግስናው ያምር ሽቶ የኸለቀን ከፋጡማ ዘር!

የሙስጦፈል ሙኽታር ልጅ፣ ከጫፍ እስከ ስር የጠራች ሙሉ እመቤት፣ የንጉሶች እናት ዘህረቱል አንዋር፣ ሰሚዑን በሲር ባጢን ዟሂሯን በቁርአን የዘየነው፣ ዘርፏን የጠበቀው፣ ዝርያዋ ሁላ ለዓዛበናር እርም የተባለው፣ አይበጆን ለነስሏ ፊዳ ያደረገው፣ በሃሳብ በትካዜ እንዳትሸበር ሩኋ በአዘል የተባሸረው ሰይደት ፋጢማህ ቢንት ረሱሉሏህ!

ለአንድዬ መጎናበሻ ልዩ ስፍራ ነበራት። በጎጆዋ ሚሕራብ ለይሉን ከጌታዋ ጋር ስታወጋ፣ ለሱ ስትዋደቅ ታሳልፋለች። ሌሊቱ እንደሷ ያለ ሰጋጅ አይቶ አያውቅም። ትዳር ከያዘችም በኋላ አባቷ ረሱሉሏህ የፈጅር ሶላት ሲደርስ በሯን ደገፍ ብለው ይቆሙና "የሙሐመድ ቤተሰቦች ሶላት!" ብለው ባማረ ጥሪ ይጣራሉ። አንድ ቀን ረሱሉሏህ ወደ እመቤት ፋጡማ ቤት ገቡ። ሰይድ ዓልይ ተኝተዋል። "እኔ፣ አንቺ ወደ ሐሰንና ሑሰይን እየጠቆሙ እነዚህ ሁለቱ እና ወደ ዓሊይ እያመላከቱ ይህ ጀግና በቂያማ እለት መገኛችን አንድ ቀዬ ነው!" አሏት።
ሲሳሱላት ለጉድ ነው። ሰርክ ትናፍቃቸዋለች። ቤታቸው የሄደች እንደሆን ቁጭ እንዳሉ አይቀበሏትም። ገና ሲያይዋት ብድግ ይላሉ። በእጆቻቸው ይይዟታል። ግንባሯን ይስሟታል። አጠገባቸው በክብር ያስቀምጧታል። እሷም እሳቸው ወደ ቤቷ ሲመጡ ልክ እንደዚሁ ነው የምታደርገው። ለጉዞ ሲወጡ ጠረኗ አብራቸው እንዲከርም ብለው ከሰው መጨረሻ ነው የሚሰናበቷት። ሲመለሱ ደግሞ ቀልባቸው የሚረጋው፣ ናፋቂ ዓይናቸው የሚያርፈው ቀድመው እሷን ሲያዩ ነበር። እንዴት ያለች ልጅ፣ እንዴት ያሉ አባት!

በሐያት ሳሉ ደስታቸው እረፍቷ፣ ጭንቀታቸው ሸክሟ ነበር። ማለፋቸውማ ምን ቀረኝ አስብሎ ገዝግዞ አስከትሏታል። ጀሀነምን የምትገልፀውና وإن منكم إلا واردها (ከእናንተ ማንም የለም ወደሷ የወረደ ቢሆን እንጂ) የምትለው አንቀፅ የወረደች ጊዜ ሰይዳችን የኡመቱ ነገር አሳስቧቸው ሃሳብ ላይ ወደቁ። በጣም ያለቅሱም ጀመር። ሶሐቦች ቢጠይቋቸውም ምንም አላሉም። ከዛም ሰይደት ፋጢማ ረ.ዓ መጥታ ጠየቀቻቸው። "አባቴ ምንድን ነው ያስለቀሰህ?" አለች።  እሳቸውም "ያ ፋጢማ እኔን ያስለቀሰኝማ ይሄ አንቀፅ ነው።" ብለው ነገሯት። እሷም አለቀሰች። ጊዜ ሳታባክን በቀጥታ ወደ ሰይድ አቡበክር ረ.ዓ በመሄድ የሆነውን ተናግራ እንዲህ አለቻቸው። "አንቱ የሙሃጂሮች ዋና ሆይ ነገ የውመል ቂያማ ከነብያችን ኡመት ሽማግሌዎቹ ጀሀነም እንዳይገቡ ፊዳ መሆን ይችላሉ ወይ?" ብላ ጠየቀቻቸው። እሳቸውም "አዎን እችላለሁ አብሽሪ።" አሏት። በመቀጠልም ወደ ሰይድ ዓልይ በመሄድ "አንተ ደግሞ ከሰይዳችን ኡመት ለወጣቱ ክፍል ፊዳ ልትሆንና ከጀሀነም ልታድነው ዝግጁ ነህ ወይ?" አለች። "አዎ መርሃባ እችላለሁ።" አሏት። በዚህ አላቆመችም። ወደ ሰይድ ሐሰንና ሑሰይን በመሄድ "እናንተስ ከሰይዳችን ኡመት ህፃናትና ልጆች ጀሀነም እንዳይገቡ መስዋዕት ለመሆን ዝግጁ ናችሁ?" አለቻቸው። "አዎን እናታችን ዝግጁ ነን።" አሉ። እሷ ደግሞ በተራዋ "እኔ ደግሞ ለሴቶች ራሴን ፊዳ አደርጋለሁ።" ብላ የሁሉንም ሴት ኃላፊነት ተሸከመች።

የዚህን ጊዜ ሰይድ ጂብሪል ዓ.ሰ ወደ ሰይዳችን ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም በመምጣት እንዲህ አላቸው። "አሏህ ሰላም ይልሀል፤ ለፋጢማም መልዕክት ንገራት ‘አትዘኚ እኔ በአንተ ኡመት እሷ የሚያስደስታትን ነው የምሠራው!"😍
የአባቷን ጭንቀት ስለተሸከመች ነው "ኡሙ አቢሃ" የሚል ስያሜ የተሰጣት። የአባቷ እናት! መገን!

ሶሉ ዓለል ሐቢብ!
አሏሁመሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም!💚💚💚
                              💚💛❤️
                                 💚💛❤️
                                       💚💛❤️
❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ   
      ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ              ﷺ❤️ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ ﷺ
💚💛❤️
💚💛❤️
   💚💛❤️
       💚💛❤️
🙏ተመሳሳይ ሃሳብ ያላቸው መልክቶች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሳቹ ቻናላችንን
Join እንዲያደርጉ እንጠይቃለን፡፡ሼር በማድረግ ለሎሎች እንዲደርሱ
ያግዙን፡፡💚💛❤️
🙏እባክወ ለሚወዱት ሸር ያድርጉ🙏
                   👇
                  👇
               👇👇
:¨·.·¨: ❀   ቻናላችንን ▶️🀄️🀄️ሉን!
·. Telegram 👇Join ያድርጉ
@yeresulnfkrmeglecha
@yeresulnfkrmeglecha
┄┄┉┉✽‌»‌‌🌹🌹»‌‌✽‌┉┉┄┄
2025/02/21 05:20:27
Back to Top
HTML Embed Code: