Telegram Web
ለይለተል ቀድርን በመጠባበቅ ላይ ነን፣ እድለኛ የሆነ በየቀኑ ተጠባብቆ ያገኘዋል፣ የተሰላቸና የሰነፈም የአንድ ሺህ ወር ፈድል ያልፈዋል። ካለፈን የማይመለስ እድል ነው፣ እንጠናከር 20 ቀናትን ስንደክምና ደግመን ለመቆም ስንጥር አሳልፈነዋል። አሁን ግን ወደፊት ብቻ ነው መጓዝ ያለብን እድላችንን መለጠቀም መጣር ያስፈልገናል። በዱዓ መጠንከር አለብን፣ የዱንያ ሃጃ አያልቅም በዛ ተጠምደን ስለ ጀነት አንዘናጋ፣ ስለ አኼራችን አላህን አብዝተን አደራ እንበለው፣ ስለ ፍልስጢሞች፣ ስለ የመኖች ሁሉም ቦታ ስለተጨቆኑ ሙስሊሞች አብዝተን ዱዓ እናድርግ። አላህ ለይለተል ቀድርን ከሚወፈቁት ያድርገን!

ረመዷን 21🌙

መድ🪶
@yeruh_weg
اللهم فرِّج همّ المهمومين، ونفِّس كرب المكروبين، وقض الدين عنِ المدينين، واشف مرضانا ومرضى المسلمين.

ረመዷን 22🌙

መድ🪶
@yeruh_weg
اللهم إنا نسألك جنة وما قرَّب إليها من قول وعمل، و نعوذ بك من النار وما قرب إليها من قول وعمل. اللهم أعِّنا على ذكرك وشكرك وحسن عبادتك.

ረመዷን 23🌙

መድ🪶
@yeruh_weg
اللهم اجعل لَّنا من كلِّ همٍ فرجاً، ومن كلِّ ضَيقٍ مخرجاً، ومن كلِّ بلاءٍ عافية.

ረመዷን 24🌙

መድ🪶
@yeruh_weg
اللهمَّ يا سامع الصَّوت ويا سابق الفوت، ويا كاسي العظام لحماً بعد الموت، أعتق رقابنا من النار ورقاب والدينا وجميع المسلمين.

ረመዷን 25🌙

መድ🪶
@yeruh_weg
اللهمَّ إنك عفو تحب العفو فاعف عنا.

ረመዷን 26🌙

መድ 🪶
@yeruh_weg
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ليلة القدر 🌹
الشيخ: بدر المشاري 🍃

https://www.tgoop.com/badr_almhare
♻️ شارك تؤجر ♻️
اللهمّ لا رب لنا سِوَاك فندعوه، ولا مالك لنا غيرك فنرجوه ، من نَطْلُبُ وأنت المَطْلُوب، ومن نسأل وأنت صاحب الكرم والجود.
اللهم اجعلنا ممن دعاك فأجبته، وستهداك فهديته، وستنصرك فنصرته، وتوكل عليك فكفيته، وتاب إليك فقبلته.

ረመዷን 27🌙

መድ 🪶
@yeruh_weg
“‏ رَبَّنَا لَا تُزِغۡ قُلُوبَنَا بَعۡدَ إِذۡ هَدَیۡتَنَا وَهَبۡ لَنَا مِن لَّدُنكَ رَحۡمَةًۚ إِنَّكَ أَنتَ ٱلۡوَهَّابُ.”

ረመዷን 28🌙

መድ🪶
@yeruh_weg
إِنَّهُمْ يَرَوْنَهُ بَعِيدًا¤ وَنَرَاهُ قَرِيبًا.

እነርሱ (ያንን ቀን) ሩቅ አድርገው ያዩታል፡፡
እኛም ቅርብ ኾኖ እናየዋለን፡፡

የምድር ህግ በዚህ አያ ዙሪያ ይሽከረከራል። ጊዜ መቆም አያቅም፣ ሁሌ ገና ሁሌ ሩቅ ይመስለናል እኛ፣ ነገር ግን አንዳሰብነው ሩቅ አልነበረም ሁሉም። ያኔ ስለረመዷን መግባት ስናወራ ገና ስንት ወር ይቀረዋል ብለን ቀን ቆጥረንለት ነበር። ያው ዛሬ ምናልባትም የመጨረሻው የረመዷን ለይላችን ላይ ደርሰናል… የከሰርነውም ከስረን፣ የተጠቀምነውም ተጠቅመንበት በግዳችን ልንሰናበተው ነው። አላህ በበረካው የቀረችንን ተጠቅመንባት የምናልፍ ያድርገን!

ረመዷን 29🌙

መድ🪶
@yeruh_weg
الله اكبر الله اكبر الله اكبر
لا إلاه إلى الله
الله اكبر الله اكبر ولله الحمد

አልሀምዱሊላህ የረመዷንን ወር በፀጋው ላስጨረሰን ጌታ…❤️

ኢድ ሙባረክ
عن ثوبان رضي الله عنه أن رسولُ الله صلى الله عليه وسلم قال:
[ من صام رمضان وستا من شوال فقد صام السنة ] رواه إبن حبان

ከሠውባን(አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) እንደተወራው የአላህ መልእክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:
[ ረመዷንን እና ከሸዋል ስድስት ቀን የፆመ ሰው በእርግጥ አመት ፆመ።]
ኢብን ሒባን ዘግበውታል።


መድ 🪶
@yeruh_weg
ረመዷንን ተሰናብተናል… ሸይጧንም ተፈቷል፣ ሱና መስገድ ቀላላችን እንዳልነበር አሁን ላይ ሸክም እየሆነብን ነው። ኢባዳ ልንሰራ ስንል የሆነ የሚከብደን ነገር አለ፣ ለዛሬ ይቅር የሚል ስሜት አለ፣ ውዱ ኑሮን እዛው መስገጃው ላይ ሆነን ሁለት ረከዓ መስገድ ተራራ መውጣት እየሆነብን ነው። የሸይጧንን ድምፅ ከኛ ሀሳብ የምንለየው፣ ረመዷን ላይ የሰራነውን ስራ አሁን እንዳንደግመው የሚገፋንን ስሜት ስናስተውለው ነው። ኸይርን እጅጉኑ ሲያከብድብን፣ መጥፎን እና ሀራምን ለአይናችን ሲያሳንስብንና ቀላል ሲያደርግልን የሸይጣንን ዊስዋስ ከኛ ሀሳብ እንለየው። በፍፁም አንድ ወር ሙሉ የሰራነው ስራ በአንድ ቀን ለኛ በጣም ከባድ ነገር ሊሆን አይችልም። ሁሌ ራሳችንን ማስታወስ አለብን፣ ከረመዷን በፊት የነበርኩትን እኔ ዳግም ላለመሆን። ሁሉንም ሱና መስገድ ቢከብደን ቢያንስ የሱብሂን ሱና አንተው፣ በቀን ብዙ ጁዝ ለመቅራት ቢከብደን አንድ ገፅ እንቅራ፣ አንድ እንኳን ኸይር በደንብ አጥብቀን ከመያዝ እንሞክር። አላህ ብሎ ቀጣይኛው ረመዷን ላይ ከደረስን፣ አምናና ካቻምና የነበረንን ማንነት ምንም ሳንሻሻል ዳግም መገናኘት የለብንም። ረመዷን በህይወታችን ውስጥ ቢያንስ አንድን ኸይር ትቶ እንዲያልፍ እንፍቀድለት…


መድ🪶
@yeruh_weg
ልጅ እያለን "ወንድሜን እንዳልጠራልህ!"፣ "ወንድሜ በአንድ ቡጢ ይዘርርሃል!" ሲባል በአእምሮአችን ውስጥ የሚፈጠረው የወንድም ተብዬ ግዙፍ ሀያል አስፈሪ ምስል ትዝ አለኝ።

በአንድ ጎን.... እንደተራ አነብንበን ከምናልፈው፣ ሀያሉን ራሱን ከገለፀበት አገላለፅ ጋር አስታያየሁት:-

وَيَسْـَٔلُونَكَ عَنِ ٱلْجِبَالِ فَقُلْ يَنسِفُهَا رَبِّى نَسْفًۭا

ከጋራዎችም ይጠይቁሃል፤ በላቸው «ጌታዬ መበተንን ይበትናቸዋል፡፡
(20 : 105)

.....በእርግጥም ልቦቻችን ያኔ ከነበሩበት ንፅህናና ገርነት ከደነደኑ ቆይተዋል።

@yeruh_weg
ለፈገግታ :)

19 አመቱ ነው

የአሜሪካን የግንኙነት መረቦች በመስበር ብዙ የመንግስት ሚስጥሮችን ሰርቋል በሚል ነበር ለእስር የበቃው። ከብልሃትነቱ የተነሳም "ቀበሮ" የሚል ስያሜ ይሰጠው ነበር።

አባቱ ለብቻቸው የሚኖሩ በእድሜ የገፉ አዛውንት ነበሩ። በጓሮ ውስጥ ድንች መትከል ይፈልጋሉ ነገር ግን በእድሜ ምክኒያት የቁፋሮው ነገር አልሆነላቸውም። ከእለታት አንድ ቀን እስር ላይ ላለው ልጃቸው እንዲህ ያለ መልዕክት ይልካሉ። "ውዱ ልጄ፣ ዛሬ ከጎኔ ሆነህ ጓሮውን በመቆፈርና ድንቾችን በመትከል ብታግዘኝ ተመኘሁ። ሌላ ማንም አጋዥ የለኝም።"

ከልጁ የደረሳቸው ምላሽም እንዲህ የሚል ነበር:- "ውዱ አባቴ፣ እባክህን ያንን ጓሮ በምንም ሁኔታ እንዳትቆፍር! ምክኒያቱም በውስጡ ወሳኝ ነገርን ደብቄበታለሁ። ከእስር በወጣሁ ጊዜም ምን እንደሆነ አሳውቅሃለው።"

....ጥቂት ሰዐታት እንኳን ሳይቆጠሩ የግንኙነት ሃላፊው በወታደሮች ታጅቦ የልጁን ቤት ተቆጣጠረው። ጎሮውንም አንድ ሳይቀር ቆፋፍረው ከመነጠሩት በኋላ ምንም ሳያገኙ ተመለሱ።  ከሰዐታት በኋላ ከልጅ በድጋሚ ሌላ መልዕክት ተላከ:-
"ውዱ አባቴ፣ መሬቱ በደንብ እንደተቆፈረልህ ተስፋ አደርጋለሁ።  ከኔ በኩል ላደርግልህ የምችለው ይሄንን ነው። ሌላ የሚያስፈልግህ ነገር ካለም አሳውቀኝ።"

(በትርጉም የተወሰደ)

@yeruh_weg
🌸 10 أدعية من السنة ليوم عرفة: 🌸

🍃1. أفضل الدعاء:
"لا إله إلا الله وحده لا شريك له، له الملك وله الحمد، وهو على كل شيء قدير".

🍃2. دعاء النبي ﷺ في عرفة:
"اللهم لك الحمد كما نقول، وخيرا مما نقول، اللهم لك صلاتي ونسكي ومحياي ومماتي، لك ربي تراثي، اللهم إني أعوذ بك من عذاب القبر، ووسوسة الصدر، وشتات الأمر، اللهم إني أعوذ بك من شر ما تجيء به الريح".

🍃3. دعاء المغفرة:
"اللهم اغفر لي ذنبي، ووسع لي في داري، وبارك لي في رزقي".

🍃4. الدعاء بالإيمان واليقين:
"اللهم إني أسألك إيمانا لا يرتد، ونعيما لا ينفد، ومرافقة نبيك محمد ﷺ في أعلى جنة الخلد".

🍃5. دعاء الكرب:
"لا إله إلا الله العظيم الحليم، لا إله إلا الله رب العرش العظيم، لا إله إلا الله رب السماوات ورب الأرض ورب العرش الكريم".

🍃6. الدعاء بالعفو والعافية:
"اللهم إني أسألك العفو والعافية في الدنيا والآخرة".

🍃7. دعاء النبي ﷺ المستجاب:
"اللهم أصلح لي ديني الذي هو عصمة أمري، وأصلح لي دنياي التي فيها معاشي، وأصلح لي آخرتي التي فيها معادي، واجعل الحياة زيادة لي في كل خير، واجعل الموت راحة لي من كل شر".

🍃8. الدعاء بالبركة:
"اللهم إني أسألك فعل الخيرات، وترك المنكرات، وحب المساكين، وأن تغفر لي وترحمني".

🍃9. دعاء التضرع:
"اللهم إني ظلمت نفسي ظلما كثيرا، وإنه لا يغفر الذنوب إلا أنت، فاغفر لي مغفرة من عندك، وارحمني، إنك أنت الغفور الرحيم".

🍃10. الدعاء الشامل:
"اللهم رحمتك أرجو فلا تكلني إلى نفسي طرفة عين، وأصلح لي شأني كله، لا إله إلا أنت".

📍نصيحة:يوم عرفة من أفضل أيام الدعاء، فأكثر من الذكر والاستغفار، وادعُ بما في قلبك، فإن الله قريب يجيب دعوة الداعي إذا دعاه.

اللهم تقبل منا ومنكم صالح الأعمال، واغفر لنا في هذا اليوم الكريم.🍀🥀
وَتَزَوَّدُوا۟ فَإِنَّ خَيْرَ ٱلزَّادِ ٱلتَّقْوَىٰ ۚ

ተሰነቁም፤ ከስንቅም ሁሉ በላጩ ጥንቃቄ (አላህን )መፍራት ነው፡፡
(2 :197)

@yeruh_weg
.....ከዛ ደግሞ የማይረባ ሩጫችንን አላህ ከሰባት ሰማያት በላይ ሆኖ በእዝነት የሚመለከተው ይመስለኛል.... አንዱ... ዛሬ በአሊሞች ተመርቆ ምሳሌ እየተደረገ ሳለ ኪታቡ ግን የእሳት እንደሆነ ይናገራል.... የሆነው ደግሞ... አለም ሰቀር ውስጥ መቀመጫ እንዳለው መስክሮነት ሳለ፣ ከጀነቶቹ ብቻ ሳይሆን ከ ቀዳሚዎቹ 70 ሺ ተፅፏል።.... አንዱ ከሰርጉ ምላሽ ሙሉ ቤተሰቡን ቀባሪ ነው.... ሌላው ደግሞ አጀሉን የያዘለትን ታክሲ ነው ከህዝብ ተጣልቶ ተሽቀዳድሞ የያዘው። ብዙው ደግሞ.... ገና ብዙዙዙዙዙ እንደሚኖር ተማምኖ በውርደት ብርድልብሱ ስር.... ስልኩን ተንተርሶ ነው የተኛው። የሆነ ቀን.... እኛ የሆኑ እናት..... 'ብዙዙዙዙዙዙ ኑሩ' ብለው የመረቁን ነገር ግን ስንት ነበር? 20,000 ቀን? 36,500 ቀን? ከሱም ላይ ወደ 9000 የሚጠጋው ቀን የተበላበት?.... እንጃ.... ብቻ... ስንትስ ቢሆን¿...... ወደ ለመድነው እንቅልፋችን....

@yeruh_weg
....ለሩሄ ሰላም ስለሚሰጡት ስለነዛ ተራ ኒዕማዎች አጫውትሻለሁ ደግሞ.... ስክንንን ባለ ምሽት፣ ከመስኮት አጠገብ ተቀምጦ አዛንን እንደማዳመጥ አይነት ስላሉት.... ስንገናኝ...

@yeruh_weg
#ትናንሽ_ልቦችን_ስለማስደሰት

አንድ በጎ አድራጊ እንዲህ ይላል:-

"...መራመድ የተሳናቸው ህፃናት ላሉበት አንድ ድርጅት መንቀሳቀሻ ዊልቸሮችን አበረከትኩ። የድርጅቱ ባለቤትም አብሬው ሄጄ ዊልቸሮቹን በአካል እንድሰጥ አጥብቆ ጠየቀኝ። ተስማምቼም ሄድኩ። በልጆቹ ፊት ላይም ትልቅ ደስታን ተመለከትኩ። ጨራርሰን ለመሄድ እያልኩ ሳለሁም ከህፃናቱ አንዱ እግሬን አጥብቆ ይዞ አይኖቹን ፊቴ ላይ ተክሏቸው አገኘሁት። ጎንበስ ብዬም; 'ሳልሄድ በፊት እንዳደርግልህ የምትፈልገው ሌላ ነገር አለ?' ስል ጠየኩት። እሱም እንዲህ ሲል ሰውነቴን ውርር የሚያደርግ መልስ ሰጠኝ; 'ፊትንህን በደምብ መሸምደድና ማስታወስ እፈልጋለሁ፣ ጀነት ውስጥ ደግሜ ሳይህ እንዳውቅህና አላህ ፊት ደግሜ እንዳመሰግንህ' "


@yeruh_weg
2025/07/03 21:15:42
Back to Top
HTML Embed Code: