ቅዱስ ፓትርያርኩ ምን አሉ ?
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ፤ በቅርቡ በቤተክርስቲያኗ ላይ የደረሰው ችግር በቀኖና ቤተክርስቲያን መሰረት በመፈታቱ እጅግ በጣም ትልቅ ደስታ እንደተሰማቸውና ውጭ ሀገር የነበሩት እነ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ የመጡበት ወቅት አይነት ስሜት እንደተሰማቸው ተናግረዋል።
" በዚህ ዓለም ላይ ስንኖር ችግር የሌለበት ጊዜ የለም " ያሉት ቅዱስነታቸው " ችግሩን በእውቀት ፣ በማስተዋል መፍታት ያለ ነገር ነው የኛም ድርሻ ነው ፤ አሁንም ቢሆን የተደረገው ይሄው ነው " ሲሉ ተናግረዋል።
ቅዱስነታቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የትላንቱ ቀን እንደሚመጣ ብዙ መልፋታቸውንና መድከማቸውን አንስተዋል " ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ብዙ ለፍተዋል ፣ብዙ ደክመዋል በተለይ ሰሞኑን እንደው አላረፉም ፤ ሁላችንም እንደዚሁ፤ ወንድሞቻችንም ፣ አባቶችም ሲመላለሱ እንደሰናበቱ አውቃለሁና ይሄንን ታላቁን የቤተክርስቲያን ሚስጥር ወደ ቤቱ መመለሱ በጣም በጣም እጅግ የሚያስደስት ነው " ብለዋል።
" እናተም ደስ ሊላችሁ ይገባል አባቶች (የተመለሱ አባቶችን ማለታቸው ነው) ፤ ወደ ሰላም ስንመለስ አብረን ስንሆን ደስ ሊላችሁ ይገባል ፤ እኛ በእውነቱ የቀኖና ቤተክርስቲያን ስለሆነ ዝም ብለን ስንል ሰነበትን እንጂ ሃዘናችን አልቀረም ፤ እናተን ወንድሞቻችንን በማጣታችን እጅግ ልባችን ሳይቆስል አልቀረም፤ ነገር ግን ቀኖና ቤተክርስቲያን ለመጠበቅ ስለሆነ እኛም ኃላፊነት ስላለብን ነው ይሄን ሁሉ ስናደርግ የሰነበትነው እንጂ ደስ ብሎን አይደለም። ይህንን በማየታችን ደስ ብሎናል ፤ እኔም በጣም ተደስቻለሁ፤ ክብሩ ጠ/ሚኒስትር እናመሰግናለን። " ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።
T.me/yetwahedolijoch

"አራት ፖሊሶች እጆቼን ይዘው በምላጭ ያንገቴን ማህተም በጠሱት"
በሕይወቴ ጥቁር ጠባሳ የጣለብኝ እስር !!
ከታሰርኩባቸው እስሮች ትንሹ የሚባለው ይሄኛው እስር ቢሆንም ከፍተኛ ግፍና ማስጠንቀቂያ ያዘለ እስር ነው ፤ ዝርዝሩን በሰፊው እመለስበታለሁ ። ከመጀመሪያ ጀምሮ ማህተቤን እንድበጥስ ግፊት ቢደረግብኝም ያንን ማደረግ እንደማልችል እና ለእኔ ሞት እንደሆነ ነግሬ አልበጥስም አልኩ !! ከአንድ ቀን ጭቅጭቅ በኋላ አራት ፖሊሶች ብቻዬን በማስጠራት ሳላስበው እጆቼን ከያዙ በኋላ
በምላጭ ያንገቴን ማህተብ በጠሱት እቅም የማጣት ስሜት ተሰማኝ ፤ እንዲደበድብኝ ተሳደብኩ እነሱ ከዱላ በላይ የሆነ ነገር እንዳደረሱብኝ ስለገባቸው ዝም አሉኝ ።
መብላት መጠጣት አቃተኝ በአይኤስ አይኤስ በሰው ሀገር ማህተባችንን አልበጥስም ብለው የተሰው ወንድሞቼ አይነት አቅም እንደሌለኝ ሲሰማኝ ልቤ ክፉኛ ተሰበረ ፤ኡፍፍ ይህ ክፉ ቀን መቼም አረሳወም !!
ይህ እንዲህ እንዳለ ፤ሁሌም ከግፉዓን ጎን የሚቆመው ወንድማችን ጠበቃ ቤተማርያም አለማየሁ በዚህ ፈተና ወቅት ሙያዊ ግዴታው እንዳለ ሆኖ! እንደወትሮ አሁንም ፤ስለ ፍትህ ፤ስለ እውነት በማለት ከእኔ በደለኛ ጎን በመቆም ወንድሜ ቤተ እግዚአብሔር እድሜና ጤና ይስጥህ ፤ አመሰግናለሁ ።
ሁሌም ቢሆን የግፉአን ዓይንና ጆሮ በመሆን የበደለኞችን ድምጽ የምታሰሙ ፤ጋዜጠኞች ፤አክቲቪስቶች ክብር ለእናንተ ይሁን !!
ብቻ ፈተውኛል ለሁላቹም እግዚአብሔር ይስጥልኝ !!
@yetwahedolijoch

«ጾም እስከ ስንት ሰዓት ነው?»
የቅድስቲቱ ቤተክርስቲያን ሥርዓቱ በልኬት እና በምክንያት የታጀበ ነው። ጾምን ስንመለከት አብዛኞቻችን በተለምዶ ሰዓት ሳንጠብቅ (እስከ 3፣ 6፣ 7፣ 9፣ 11 ሰዓታት እያልን) እንጾማለን እንጂ የአዋጅ አጽዋማት የተወሰነ የተገደበ ሰዓት አላቸው።
ፍትሐ ነገሥታችን “ሕማማት እስከ 12 ሰዓት ይጹሟቸው፥ ሌሎቹን አጽዋማት በዓለ ልደት እና ጥምቀት ረቡዕ እና ዐርብ የሚውሉባቸው ካልሆኑ በቀር እስከ 9 ሰዓት ይጹሙ” (ፍት.ነገ አን 15፥565-566) ብሏል።
የአጽዋማትን ዝርዝር ካስቀመጠ በኋላም በዚሁ አንቀጽ ቁጥር 572 ላይ ደግሞ “በእነዚህ በታዘዙት ጾሞች ከቀኑ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ ይጹሙ፣ ... ከዚህ አብልጦ የጾመ ግን ዋጋው ይበዛለታል፣ ከጥሉላት ምግቦች መታቀብ ካልሆነ በቀር እሑድና ቅዳሜ ግን አይጹሙ” ብሎ ወስኗል።
ዐቢይ ጾም ሁዳዴ፣ ጾመ ዐርብዓ ግን ይለያል። “በዐቢይ ጾም መጀመሪያ ሱባኤ ፀሐይ እስኪገባ(እስከ12ሰዓት) ይጹሙ፣ ሌሎቹን ሳምንታት እስከ 11 ሰዓት ይጹሙ፥ በሰሙነ ሕማማት ግን ኮከብ እስኪወጣ ይጹሙ” ብለዋል። (ፍት.ነገ.አን 15፥595)።
ፍትሐ ነገሥት ቁጥር 578 ላይ ደግሞ “(የሰሙነ ሕማማትን) ዓርብንና ቅዳሜን ግን ሁለቱንም በአንድነት ይጹሟቸው፣ የሚችል እስከ ሌሊት ዶሮ ጩኸት ድረስ ምንም ምን አይቅመስባቸው፣ ሁለቱን በአንድነት መጾም የማይቻለው ግን ቅዳሜን ይጹም” ተብሎ ህግ ተሠርቷል።
ከየኔታ በጽሐ የፍትሐ ነገስት መጽሐፍ የተወሰደ።
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
https://www.tgoop.com/yetwahedolijoch

Telegram
የተዋሕዶ ልጆች
<<አንተስ ለእግዚአብሔር ስገድ አለኝ የዚህን መፅሐፍ የትንቢት ቃል አትሰውር ዘመኑ ደርሷልና ፤ እንግዲህስ የበደለውን ይበድሉታል። ያሳደፈውን ያሳድፉታል ጻድቁም ይጽደቅ። ንፁሑም ንፅሑ ይሁን። እነሆ ፈጥኘ እመጣለሁ። ለእያንዳንዱም እንደስራው ከፍየ ብድሩን እከፍለው ዘንድ የምሰጠው ዋጋ ከኔ ጋር ነው (ራዕ ፳፩ ቁ ፰-፲፪ ፤ ኢሳ ፵ ቁ ፲)>>
መልዕክት ካለዎት @TemhrtTewahedoBot
መልዕክት ካለዎት @TemhrtTewahedoBot
❝ እራራለት ❞
❝ ጌታ ሆይ ዘመን ጨልሞ ፍርሃት ሲያይልብን ፈጥነህ የደረስክልን አንተ አይደለህም ወይ ? ፍትህ እየተዛባ ባልቴት መና ስትቀር የጽድቅ ፈራጅ አንተ አይደለህም ወይ ? ለተራበው የዕለት መና ፣ ለተጠማ የአለት ውኃ አንተ አይደለም ወይ ?❞ ❝ ለታመሙ አስታማሚው ፣ ለወደቀው አለው ባዪ ፣ ተስፋ ላጣው ብሥራት ፣ ለተናቀው ክብሩ ፣ ለተራበው ምግቡ አንተ አይልህም ወይ? ❞ ያልተውከው ህዝብ ሲተውህ ፣ የቀረብከው ወገን ሲርቅህ ፣ የወደድከን ስንክድህ እስከመጨረሻው የምትታገሰን ወዳጃችን ነህ ክብር ይድረስህ። ጌታዬ ሆይ እባክህ ገደብ ለሌላው ውድቀታችን አሳልፈህ አትስጠን ። በረከትህ ሙሉ ነውና ስጥ አልከኝ ። ❝ ከአንተ ተቀብሎ የሚሰስት ማንነትን አርቅልኝ ። ❞ ዛሬ አንድ የራበው ሰው ጎበኘው ደስታውን ሳይ ፤ ❝ ባለመስጠት ስንቶችን እንዳስራብኩ አሰብኩ እባክህ ይቅርበለኝ።❞ ዛሬም በበርሃና በስደቱ ፣ በምርኮና መሪር በሆነ አገዛዝ ውስጥ የሚያልፈውን ወገኔን እራራለት ። እርሃብና ጥም ያየለበት ህዝቤን ጎብኝልኝ ። አንተ ተስፋ ነህና ተስፋ ላጣው ወገኔ እራራለት ። ጌታዬ ሆይ እኔ ብደርስ የማላረካ ፣ ብጀምር የማልፈጽም ነኝ ። አንተ ሙሉ መፍትሔ ሙሉ መልስ ነህና ወደ ወገኖቼ እልክሃለሁ ። ለወገኔ መቸገር ኃጢአቴ ምክንያት ነውና እኔንም ባሪያህን ይቅር በለኝ ። ለተቸገረው እራራለት ። ለተራበው እራራለት ። ለተጠማው እራራለት ። ለተጎዳው እራራለት ። ለምኜህ አላፍርምና ክብር ይድረስህ ። የሰው ድንበር ለማይገድበው በረከትህ ምስጋና ይገባል ። በመድኃኒት ስምህ ፣ በማይጎድል በረከትህ ፣ በጽኑዕ መንግሥትህ አምናለሁ ። በማላፍርበት ደግነትህ ለዘለዓለሙ አሜን !
ዲያቆን እስጢፋኖስ ደጀኔ
የካቲት 17 ቀን 2015 ዓ.ም.

Forwarded from በብሂለ አበው ኩኑ ውሉደ ብርሃን
#የስሜት_ቀንበር
#በአንድ_ወቅት_እንዲህ_ሆነ። አንድ ባለ ጸጋ ሰው ብዙ ወርቅ ይዞ ወደ ገዳም በመሄድ በገዳሙ ውስጥ ላሉት መነኮሳት አባቶች እንዲከፋፈልለት ይጠይቃል:: የገዳሙ አበምኔትም ወርቁን ወደ አንድ ወገን እንዲቀመጥ ካደረጉ በኋላ የገዳሙን የጥሪ ደውል ይደውላሉ፡፡ የገዳሙ መነኮሳት ከተሰበሰቡ በኋላም ወደ ወርቁ እያመለከቱ እያንዳንዳቸው ለባለ ጸጋው ሰው ያላቸውን ፍቅር ይገልጡ ዘንድ ድርሻ ድርሻቸውን እንዲያነሱ ይጠይቋቸዋል። በዚህ ጊዜ ደጋግመው ቢወተውቷቸውም መነኮሳቱ ወርቅ ሳይሆን ድንጋይ እንደሚመለከቱ ሆነው በዚያው ቆመው ቀሩ፡፡ የመነኮሳቱ ባሕርይ ያን ባለጸጋ ሰው እጅግ ስላስደነቀው እንደ እነርሱ ይመነኩስ ዘንድ ጠይቆ በዚያው ቀርቷል።
#ውድ_ወንድሜ_ሆይ! ዓለሙና ሥጋችን ስሜታችንን በብዙ ነገር ይማርኩታል። በመሆኑም ቁሳዊና የዓለም የሆኑት ነገሮች በሙሉ ከሆኑት ይልቅ እጅግ የሚያምሩና የሚስቡ ብቻ ሳይሆን መልካም ነገርን የሚያስገኙልን መስለው ይታዩናል፡፡ ይሁን እንጂ ነፍሳችን ከዚህ መሰናክል ከሆነባት ነገር በከፊል ተላቃ በሥጋችን ላይ መሰልጠን ስትጀምር ስሜታችንም አብሮ ነፃ ስለሚሆን ሁለቱም በአንድነት ከዓለማዊው ፍላጎትና አመለካከት ነፃ ስለሚወጡ በነገሮች ላይ አዲስ መንፈሳዊ ግንዛቤዎችን ማዳበር ይጀምራሉ፡፡ ይህ ዓይነቱን ነገር በራስህ ገጠመኝ ታውቀዋለህ። እንበልና ከቤተሰቦችህ ተለይተህ ራቅ ወዳለ ሥፍራ በመሄድ ለረዥም ጊዜ ከቆየህ በኋላ የቤተሰብህ አባላት በሙሉ በታላቅ ፍቅርና ናፍቆት እያቀፉ ይስሙሃል፡፡ በዚህ ጊዜ ላንተ ባላቸው ፍቅር እጅግ ትመሰጣለህ፡፡ ከዚህ ተመስጦ ባሻገር ግን አቅፎ የሚስምህ እናትህ ይሆኑ አባትህ ወይም እህትህ ትሁን ወንድምህ፤ ወንድ ይሁን ሴት የምትለይበት ሁኔታ ብዙም አይታወቅህም።
#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ
@Weldeaman

ሰላም እንዴት አላችሁ ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች🙏 ሰሞኑን በአዳዲስ የንስሃ መዝሙሮች እንገናኛለን። መዝሙሩን ሰምተን ያማረ ፍሬ እንናፈራ የፈጣሪ ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልን አሜን🙏🙏🙏
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ርዕስ:-❤️ለእኔስ ልዩ ነች❤️
ዘማሪ:- ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
❤️🔥❤️🔥❤️🔥
━━━━✦✗✦━━━━
ከተዋሕዶ ልጆች
━━━━✦✗✦━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦⇨ @yetwahedolijoch
⇨ @yetwahedolijoch
ዘማሪ:- ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ
❤️🔥❤️🔥❤️🔥
━━━━✦✗✦━━━━
ከተዋሕዶ ልጆች
━━━━✦✗✦━━━━
⇲⇲⇲⇲ ሼር ያድርጉ!! ⇲⇲⇲⇲
አዘጋጅ፦⇨ @yetwahedolijoch
⇨ @yetwahedolijoch