Telegram Web
አንድን ወንጀል ተደጋጋሚ ከሚያደርጉ አስቻዮች (Enablers) አንዱ ከወንጀሉ ጋር የተያያዘው የማህበረሰብ የወል ሰነ ልቦና ነው። አስገድዶ መድፈር በሀገራችን እንደ ወረርሽኝ የተሰፋፋ እና ጉዳቱ በተበዳይ ሳያበቃ ማህበራዊ ሰቀቀን (Social trauma)የሚያሰከተል ቢሆንም የወል ስነ ልቦናችን በፈጠረለት አስቻይ ነባራዊ ሁኔታ መደበኛ የዕለት ዜና ሆኖ ቀጥሏል።

ሌሎች ላይ ዘላቂ ጉዳት የሚያደርስ መስል ጸያፍ ድርጊት በማህበራዊ ውግዘትና በህጋዊ ቅጣት መከላከልና መቀነስ ያልተቻለው ድርጊቱን የሚያበረታታ ማህበራዊ ስነ ልቦና እና የህግ ድክመት በመኖሩ ነው። ከለከፋ ጀምሮ እስከ ጠለፋ የሚደርሰው የትንኮሳና የጥቃት ስንሰለት ብዙ ጊዜ ሰዉር ማህበረስባዊ ድጋፍ አለው። ያሉት ጥቂት ውግዘቶችም ቢሆኑ ጥፋቱ ላይ እንጂ ጥፋቱን ያሰቻለው ከባቢ ላይ አያተኩሩም። ተበዳይን በግል ምርጫዋና አለባበሷ የችግሩ ምንጭ ከማድረግ የሚጀምር የወል ስነ ልቦና ባለበት ተጨባጭ ወንጀሉን ለመቀነስ ህግም ሆነ ማህበራዊ ውግዘት አቅም የላቸውም። መሰል ጥቃት ሴቶች ላይ፥ ህጻናት ላይ፥ ሴት ልጅ ያላቸው ወላጆች ላይ፥ በደልን የሚጠየፉ ዜጎች ላይ የተፈጸመ አካላዊውና ሰነ ልቦናዊ ክፉ ጥቃት ቢሆንም ከተራ ወንጀል ያለፈ ትኩረት ያልተሰጠው የወል ሰነ ልቦናችን ስለሚያሳንሰው ነው።

ለከፋን እንደ እርድና፥ ሴሰኝነትንና ጾታዊ አጥቂነትን እንደ ወንዳወንድነት የሚቆጥር የማህበረስብ ሰሪት እጩ ደፋሪዎች በማምረት ተወዳዳሪ የለውም። ለዛም ነው ራቁቱን ኤርታሌ ውስጥ ሊነከር የሚገባው ወንጀለኛ "የህግ ተቀላቢ" የሆነው።

Ibrahim Abdu
ለህፃን ሄቨን ፍትህ ይገኝ ዘንድ ጫና ለመፍጠር እየተሰበሰበ ያለውን petition እንቀላቀል፣ ሼርም እናድርግ።

https://chng.it/RNMNMvD4
ወዳጄ በእውቀቱ እንደፃፈው... #ሼር አድርጉት!

የሚያሳስበኝ
(በእውቀቱ ስዩም)

ዶስተየቨስኪይ የተባለ የሩስያ ደራሲ ልቦለድ ውስጥ የሚገኝ ኢቫን የተባለ ገጸባህርይ ” ሰውን አውሬ ብሎ መጥራት አራዊትን እንደ መስደብ ይቆጠራል ይላል ፤” ሰው የበጎነት አቅም ያለውን ያህል ፥ በጭካኔ የሚወዳደረው የእንስሳ ዝርያ የለም፤ አንበሳ ሚዳቆን የሚገድለው በልቶ ማደር ስላለበት ነው፤ ሳይቸግረው ያለ አላማ መሰሉን፥ የሚገድል፥ ብጤውን በማሰቀየት የሚደሰት ፍጡር ሰው ብቻ ነው፤

ልጅ ሆኜ በጎችን አሰማራ ነበር፤ ግልገል በግ የሚደፍር ትልቅ በግ አይቼ አላውቅም ፤ ወንዱ በግ ፥ደረሰች በግ ላይ ለመውጣት ራሱ ወቅት ይጠብቃል፤ ለርቢ መድረሷን አሽትቶ ካላረጋገጠ በቀር አይደርስባትም፤

የሰባት አመትዋን ሄቨንን ለመስማት በሚገዘገንን ጭካኔ ደፍሮ የገደላትን ሰውየ “ እንስሳ ፥ወይም አውሬ” ብሎ መጥራት ፍትሀዊ የማይሆነው ለዚህ ነው፤ እንዲህ አይነቱ ቀፋፊ ፍጡር የሚገልጽ ሌላ ቅጽል ተፈጥሮ መዝገበቃላት ውስጥ መካተት አለበት፤

ህግ ካለ ይህ ወንጀለኛ እንደ ምግባሩ ፍዳውን መቀበል ይገባዋል፤ እሱ ብቻ ሳይሆን ወንጀሉን ለመሸፋፈን የሞከሩ እና የዶለቱ ሁሉ ከቅጣቱ ድርሻቸውን ማንሳት አለባቸው፤

አስገድዶ ደፈራ በዋናነት የወሲብ ጉዳይ አይደለም፤ የፈሪዎች እና የግፈኞች “ሀይል “ መግለጫ ነው፤ ከጥቂት ዓመታት በፊት የሰባ ምናምን አመት ሴት የደፈረ ጎረምሳ በአስራት መቀጣቱን የሚገልጽ ዜና ማንበቤ ትዝ ይለኛል ፤ የሰባ አመት ባልቴት እና የሰባት አመት ሴት ሁለቱም ለሩካቤ የሚያሳስብ ነገር የላቸውም፤ ግን ሁለቱም አንድ የሚያደርጋቸው አቅም አልባ መሆናቸው ነው፤ ራሳቸውን ከደፋሪው መከላከል አይችሉም፤ ደፋሪዎች ብዙ ጊዜ ፈሪዎች ናቸው፤ ከሚበልጣቸው ጋራ ወይም ከእኩያቸው ጋራ ጉልበት እንደማይፈታተሹ ያውቁታል፤ በጉልበት የሚያንሳቸውን፤ ሀብት ስልጣን ወይም ወገን የለውም ብለው የሚያስቡትን ከማጥቃት ግን አይመለሱም፤ ብዙ ጊዜ የጥቃት ሰለባዎችን ስናይ ህጻናት፥ የቤት ሰራተኞች፥ እንግዶች፥ የመንገድ ዳር ተዳዳሪዎች ወይም በጦርሜዳ ላይ ያለ ታዳጊ የቀሩ ሴቶች ናቸው፤

ለወላጆች አንድ የጭንቅ ቀን ምክር አለኝ፤ ጨካኝ ፤ጭቦኛና ቀፋፊ ባህርይ ያላቸው ሰዎች
የትም እና መቼም ይኖራሉ፤ሰርሲ ላንስተር እንደተናገረችው Everywhere in the world they hurt little girls ."

ፈታኝ አለም ውስጥ እንደምንኖር አንርሳ፤ ሁሌም በህግ በፈሪሀ እግዚአብሄር እና በባህል በጭምት ፊት ተማምነህ መዘናጋት የለብህም፤የልጆችህ ወታደር መሆን አለብህ ፤ ልጆችሽን እንደ አይንሽ ብሌን ጠብቂ ! ቀላል እንዳልሆነ አውቃለሁ፤ግን ሌላ ምን አማራጭ አለ?

#ሼር አድርጉት
ዛሬ ልደቴ ነው🎂

ይሄን ቻናል ለሌሎች በማስተዋወቅና ሰዎች እንዲገቡ በማድረግ መልካም ልደት ልትሉኝ ትችላላችሁ!

@yismakeworku
እነሆ 18 ካለፈኝ 22 ሞላኝ። እንዳትደምሩት። ጋሼ በሽበቱ እንዳጋጨኝ እኔም በጧት ተነስቼ ጢሜን አየሁት። አንድ ነጭ ጠጉር አበቀልኩ። ነቀልኩት። አንዱን ከነቀልከው፣ ሁለት ሆኖ ይወጣል ብለውኛል። ቶሎ ቶሎ ላርጅማ። "የእናርጅ እናውጋ" ልጅ። ይህን ቃል ስሰማ በሳቅ እፈርሳለሁ። "40 ዓመት ሞላኝ?" አልኩ ራሴን በመስታውት እየተመለከትኩት።
ፎቶ ገጭ 😎
Yismake Worku
Photo
"ፍቅሬን በይስማዕከ መፅሀፎች" (ተገጠመ በህይዎት ዘውዴ)

እኔ እወድሃለሁ

ውብ ነው ንግግርህ እንደ ዴርቶጋዳ፣
ከምትወደው በላይ ሚራዥን ሜሮዳ፣
ከልቤ ወድጄህ ገብቻለሁ እዳ።

እኔ እወድሃለው!
እንደጣና ገዳም የይስማእከ አሳሳል፣
እንደ ሻጊዝ እውቀት የዲወላ ተንኮል።

እኔ እወድሃለሁ !
እንደ ክቡር ድንጋይ የረቀቀ ቅኔ፣
ከቃላት በላይ ነው ያንተ ፍቅር ለ'ኔ።
በልጅነት አቅሜ ያኔ እንዳነበብኩት፣
ባልረዳው እንኳን አይቼ እንዳለፍኩት።

እንደ ሜሎስ መፅሀፍ ትናፍቀኛለህ፣
በፍቅርህ የሳት ሰይፍ ልቤን እየበላህ።
ፍቅርህ ኦጋዴን ነው የበረሀ ሙቀት፣
ትንፋሽህ ይርጋለም የለምለም ምልክት።

ወደ ልቤግባ ከቤቴ ተከርቼም ፣
ወ'ድሃለውና አልቃወምህም።
እንደ ተልሚድ ድርሰት አምዕሮዬን ግዛው፣
በድሬ ተሻግረህ እንገናኝ እዚያው ።

የት ነው አትበለኝ!
ብትፈልግ ፒያሳ ከአቡነ ጴጥሮስ፣
ከሀውልቱ ደርባ አራዳው ጊወርጊስ።
ወይም ደግሞ ጣና ከሀይቁ ዳርቻ፣
እጠብቅሀለሁ ናልኝ አንተ ብቻ።

አንተ እንደተመቼህ!
ከፈለክ መቖለ ወይም ደግሞ አክሱም፣
ከተራራው አናት ብትፈልግ ድል ይብዛም።
ሳልሰስት ዘላለም እጠብቅሀለው፣
ፍቅርህ ለእኔነቴ እንደ ሀገሬ ነው።

አዎ እንደዚያች ሀገር!
በዴርቶጋዳ ላይ እንደተሳለችው፣
በምናብ አይተናት በውነት የጠፋቸው።

እናማ ፍቅሬ ሆይ!
መውደዴን ጨርሼ ዘርዝሬ ባልነግርህ፣
ከዛምራ በላይ ነው እኔ አንተን ስወድህ፣
ግን እንዲህ ሳፈቅርህ ባ'ክህ እንዳትኮራ፣
አይበጅህም እና ግፍን እንዳትሰራ፣

ግፉአዓኖች በዝተው ገፊም ተበራክቶ፣
ልክ እንደ ሀገሬ ብትገፋኝም ከቶ፣
በተስፋ ቃል ኪዳን ሁሌም ወ'ድሃለው፣
ፍቅርህ በልቤ ውስጥ ረቂቅ ተልሚድ ነው።

ተልሚድ ማለት ደግሞ
የረቀቀ ቅኔ የተሰወረ ቃል፣
ትርጉሙን ለማወቅ
ከራስ ተነጥሎ መሄድ ይጠይቃል።
ብቻ እስከማገኝህ ፍቅርህን ተርቤ፣
ደህንነቱን እንጃ የወደደህ ልቤ።



(ሁላሁችንም አመሰግናችኋለሁ።  የዚህ ሸጋ ግጥም ባለቤት "ህይዎት ዘውዴ" ስትሆን የስዕሉ ባለቤት ደግሞ "ማርታ ሳንታ"  ናት።  ህይዎቴ ተነቃቃ። ሁለቱም የልደቴ ስጦታዎች ናቸው። ለመለጠፍ ተቸግሬና ጉረኛ ላለመባል ነው እንጂ ብዙ አነቃቂ ነገሮች ደርሰውኛል። ከሽማግሌ እስከ እነ እማማ፣  ከወይዛዝርት እስከ ወጣት። ሁሉንም አንባቢዎቼን አመሰግናችኋለሁ። እነዚህ ደግሞ በምወደው ግጥምና በምወደው ስዕል ወደ ልጅነቴ መለሱኝ።  'እምቢ አላረጅም' የሚለውን አስታወሳችሁኝ።   እውነት ለመናገር እስካሁን ያሳለፍኩት ጊዜ የብዙ ሰው እድሜ ይመስለኛል። የእኔ ህይዎት Triller ፊልም ይመስላል። እረፍት አልባ ፊልም። አንዱን ገፀ ባህሪ አባብዬ ስሸኘው አንዱ ሽመሉን ልጦ ይመጣል። ህይዎቴ እረፍት አልባ ነበር። እኔ ስተርከው በራሴ ላይ የሚደርሰውንና የሚቀጥለው ደግሞ እንዲህ ሆኖ እንደሚፈፀም በማዎቄ ነው። እንዲህ እንዲህ ያሉ አንባቢዎች አሉኝ። እኔ ምርቃት አልችልም። የጥበቡን መንገድ አብልጦ ይስጣችሁ። አሜን በሉ። የ40 ምናምን ቀን ሽማግሌ ሲመርቃችሁ ሁለት እጆቻችሁን እንደወረቀት ከታች ዘርግታችሁ ዓይኖቻችሁን ወደፈጣሪ አንጋጣችሁ አሜን በሉ)

ይስማዕከ ወርቁ
Channel photo updated
በዚህ የቴሌግራም ገፅ ወይም ከ235 ሺ በላይ ተከታይ ባለው የፌስቡክ ገፅ ማስታወቂያ ማሰራት የምትፈልጉ ቤተሰቦች @AdvertOnPageBot በተሰኘው መድረክ ብታሳውቁኝ የሶሻል ሚዲያ ተቆጣጣሪው ሁሉንም ያሳውቃችኋል።

ማስታወሻ : ከማስታወቂያ የሚገኘው 50% ገቢ ለእርዳታ ድርጅት ይውላል።

መልካም!
ይህ ከታች የምትመለከቱት ፔጅ ድርጅትዎን፣ ምርትዎን እና አገልግሎትዎን የሚያስተዋውቁበት ፔጅ ነውና ይቀላቀሉት!
Facebook:- https://www.facebook.com/bamlakgetaneh2

Telegram:- https://www.tgoop.com/bamlakgetaneh

TikTok:- www.tiktok.com/@bamlakgetanehh
የዘመናችን አትናቴዎስ

ፈጣሪ እድሜና ጤና ይስጥልን!
የአገልግሎት ዘመናቸውን ይባርክልን!

አሜን
Advertisement!

ይህ ከታች የምትመለከቱት ፔጅ ድርጅትዎን፣ ምርትዎን እና አገልግሎትዎን የሚያስተዋውቁበት ፔጅ ነውና ይቀላቀሉት!
Facebook:- https://www.facebook.com/bamlakgetaneh2

Telegram:- https://www.tgoop.com/bamlakgetaneh

TikTok:- www.tiktok.com/@bamlakgetanehh
"መንገድ ብዙዎችን ያገናኛል። ጉንዳኖች ተያይዘው በሚሠሩት መንገድ ታላቅ ወንዝ ይሻገራሉ። ጉንዳኖች ተያይዘው ዓባይን ሲሻገሩ ዓይቻለሁ። እኛም ተያይዘን በምንሠራው መንገድ ወደስልጣኔ እንሸጋገራለን። የኢትዮጵያን እውናዊ አንድነት ከቃል የምናሸጋግረው ህዝቡን በኢኮኖሚና በብዙ ማህበራዊ መስተጋብሮች ስናስተሳስረው ነው። መንገድ የኢትዮጲያ አንድነት ደም ሥር ይሆናል። ..."

ዴርቶጋዳ
ገጽ 196

መንገዳችንን አትዝጉብን። ለማስተላለፍ የተሞከረው ሐሳብ ይህ ነው።
Advertisement

ይህ ከታች የምትመለከቱት ፔጅ ድርጅትዎን፣ ምርትዎን እና አገልግሎትዎን የሚያስተዋውቁበት ፔጅ ነውና ይቀላቀሉት!

Facebook:- https://www.facebook.com/bamlakgetaneh2

Telegram:- https://www.tgoop.com/bamlakgetaneh

TikTok:- www.tiktok.com/@bamlakgetanehh
"እልፍ አእላፍ ቅማል...
የወረሰው ሱሪ - ተናዞልኝ ሞቶ
ይኸው እቀምላለሁ - ያ'ባቴን ድሪቶ።"

ይስማዕከ ወርቁ (ኑዛዜ)
ትልቁ ችግሬ እኔ በራሴ የሆንኩትን ራሴን በትክክል የሚረዳ ማግኘት
አለመቻሌ ነው። ሁሉም ራሱን ሆኖ የሚኖር ሳይሆን ሌላውን አይቶ
የሚያኗኑር በመሆኑ ራሴን ስሆን በተሳሳተ መንገድ የሚረዳኝ ብዙ ነው።

አጥቼ ራሴን ሀኜ ስቀርብ ለማኝ፣ አግንቼ ራሴን ሆኜ ስቀርብ ሌባ አድርጎ የሚረዳ ብዙ ነው። ወደህ ስትቀርብ ተሸናፊ፣ ትተህ ስትርቅ ጠላት የሚያደርገው ብዙ ነው።

በግሌ የሰው አስፈላጊነት ባያስፈልገኝም ሰው የራሴን መሆን ትቶ በስህተት እንዲረዳኝ ግን አልፈልግም። በሰው ዘንድ በብዙ ጥርጣሬ ልታይ ብችልም በመጥፎ ጎኑ መታየት አልፈልግም።

የማልፈልገው መጥፎ ሆኜ መጠርጠርን ሳይሆን እንደጠረጠሩኝ መጥፎ ሆኜ መገኘት ስለማልችል ነው። ብችልማ ችግር የለውም። መጥፎ አድርገውኝ ሲጠረጥሩ የጠረጠሩትን ሆኖ መገኘት ነው።

እኔ የሚደብረኝ ነገር ራሴን ግልፅ አድርጌ አንዲያውቅ ያደረኩት ሰው ተደብቆ ስለኔ የሚፈጥረው ስሜት ነው። ከእኔ የሚፈልገው የእኔን እውነት የሚወክል እውቀት ነው ወይስ በራሱ የስሜት ሸራ የእኔን ምስል መሳል ነው? እኔን ለማወቅ ከኔ የሚጠበቀው ግዴታ ስለእኔ እውነታ መረጃ መስጠት ብቻ ነው።

እኔ እሱ ስለኔ የሚፈጥረው ስሜት መወሰን ስለማልችል ስለኔ የሰጠሁትን መረጃ አለማመኑ አያሳስበኝም።
ቢሆንም ቢሆንም ... 😁
2024/09/30 05:19:24
Back to Top
HTML Embed Code: