አል ኢማም ጦበራኒይ፥ ዓብዱሏህ ኢብኑ ዓባስን (ረዲየሏሁ ዓንሁ) ዋቢ አድርገው እንዳስተላለፉት የአሏህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
"ጀነት፥ ለረመዷን ሲባል ከዓመት ዓመት በእጅጉ ተውባ ትጌጣለች። የረመዷን የመጀመሪያው ሌሊት ሲሆን ከዓርሽ ስር "ሙሲራ" የተሰኘች ነፋስ ትነፍሳለች፤ የጀነት ዛፍ ቅጠሎችን ታወዛውዛቸውና ተሰምቶ የማይታወቅ ጥዑም ድምፅ ይስተጋባል።
ጀነትም ትላለች፥ "ጌታዬ ሆይ! የዚህ ወር ባተሌዎችን የኛ ነዋሪዎች አድርግ።"
የጀነት "ሑረል ዒኖችም" (ውብ አይናማዎች) እንዲህ ይላሉ፦ "ጌታችን ሆይ! የረመዷን ጎበዛዝቶችን ለኛ ባሎች አድርግልን"
___
ወዳጆቼ፦ ይህ ወር፣ ዑለሞቻችን እንዳሉት "እንደተቀሩት ወሮች አይደለም።" አንዲትም ደቂቃ ያለ አግባብ ላትባክብን ዘንድ በተውበት፣ ቁርአን በመቅራት፣ በዒባዳ ልንሞላት ግድ ይለናል።
ዕድለኛ ማለት፦ ረመዷንን ያገኘ ብቻ ሳይሆን አግኝቶ የተጠቀመበት ብቻ ነው።
አል ሓፊዝ ኢብኑል ጀውዚይ (አት’ተብሲራ) በሰኙት ኪታባቸው እንዲህ ብለዋል፦
لو قِيلَ لِأَهلِ القُبُورِ تَمَنَّوا لَتَمَنَّوا يَومًا مِن رَمَضَانَ، وَمَا ذَاكَ إِلَّا لِعَظِيمِ شَهرِ رَمَضَانَ وَعَظِيمِ بَرَكَاتِهِ.
"በቀብር ውስጥ ላሉት ሰዎች "ተመኙ" ቢባሉ፦
የሚመኙት ከረመዷን አንድ ቀን ማግኘትን ነው።
ምክኒያቱ ደግሞ ረመዷን ያዘለው ትሩፋት የላቀና ያቀፈው በረከቱ አያሌ በመሆኑ ነው"
___
አዛኙ ጌታችን አሏህ፦ የወሩ ተጠቃሚዎች ያድርገን!
ኡስታዝ ሰዒድ አሕመድ

አንድ ጊዜ ሶስት ሰዎች ወደ ኢማም ሐሰነል በስሪ መጡ። ሁሉም የየራሳቸውን ችግር እና ህዝባቸው ላይ ስላጋጠማቸው መከራ ሊያማክሯቸው ነበር።
አንድኛው "ኢማም ሆይ፦ ድህነት አስቸገረን!" አላቸው
ሁለተኛውም "ኢማም ሆይ፦ በድርቅ ተመታን!" አለ
ሶስተኛውም ቀጠለ "ኢማም ሆይ፦ ዘራችን አልበረክት አለን"
የሁሉንም ሸክዋ በየተራ ካደመጡ በኋላ ኢማም ሐሰን አልበስሪ ረሒመሁሏህ አንድ መፍትሄ አስቀመጡ። ለእያንዳንዳቸው
"አስተግፊሩሏህ በሉ" ብለው ወደ አላህ መመለስን እና ምሕረት መለመንን አደራ አስይዘው ወደመጡበት ሰደዷቸው።
ሰዎቹ ሄዱ። ከተማሪዎቻቸው መካከል አንዱ ለሶስቱም ሰዎች አንድ ዓይነት ምላሽ የመስጠታቸውን ሚስጥር ጠየቀ። እሳቸውም
"ቁርኣንን ብትመለከት አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ስለ ኑሕ ዓለይሂ ሰላም ሲናገር እንዲህ ይላል፦
فَقُلْتُ اسْتَغْفِرُوا رَبَّكُمْ إِنَّهُ كَانَ غَفَّارًا
«አልኳቸውም፡- ጌታችሁን ምሕረትን ለምኑት፡፡ እርሱ በጣም መሐሪ ነውና፡፡
يُرْسِلِ السَّمَاءَ عَلَيْكُم مِّدْرَارًا
«በእናንተ ላይ ዝናምን ተከታታይ አድርጎ ይልካል፡፡
وَيُمْدِدْكُم بِأَمْوَالٍ وَبَنِينَ وَيَجْعَل لَّكُمْ جَنَّاتٍ وَيَجْعَل لَّكُمْ أَنْهَارًا
«በገንዘቦችና በልጆችም ይለግሰላችኋል፡፡ ለእናንተም አትክልቶችን ያደርግላችኋል፡፡ ለእናንተም ወንዞችን ያደርግላችኋል፡፡»

«ሸይጧን ትናንት በኃጢኣት ቢያሳስተኝም ዛሬ ግን በተውበት እና በኢስቲግፋር ወገቡን እሰብረዋለሁ።» ሱፍያን አስ‐ሰውሪይ
በቀን አንድ ሺህ ጊዜ ብታምፁም ኢስቲግፋር አድርጉ! ሲሉ ደጋጎች ይመክራሉ
አቡዳዉድ ከኢብኑ ዑመር [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንዲህ ማለታቸውን ዘግበዋል: ‐ «አንድ አንዴ በተቀመጥንበት የአላህ መልክተኛ [ﷺ] መቶ ጊዜ እንዲህ ሲሉ እንቆጥር ነበር:
[ረብ‐ቢግፊር ሊ ወቱብ ዐለይ‐የ ኢን‐ነከ አንተት‐ተው‐ዋቡር‐ረሒም]
(ጌታዬ ሆይ! ማረኝ። ፀፀት አድርግልኝ። አንተ በጣም ፀፀትን ተቀባይ እና አዛኙ ነህ!)
#ኢስቲግፋር
ለሰሐባው ሑዘይፋ (ረዐ) አንድ ሰው እንዲህ አላቸው፦ ሙናፊቅ እሆን ብዬ ስጋት ይገባኛል።
እሳቸውም መለሱለት፦ «ከሰዎች ስትገለል ትሰግዳለህ? ወንጀል በፈጸምክ ጊዜ አላህን ምህረታ ትለምናለህ? (ኢስቲግፋር ታደርጋለህ?)
"አዎን" ሲል መለሰ
ሑዘይፋም (ረዐ) እንዲህ አሉት፦ ሂድ አላህ ከሙናፊቆች አላደረገህም።
ታላቁ ታብዕይ ሐሰን አል በስሪ ጓደኛቸው ሞቶ ከቀበሩት በኋላ ቀብሩ አፋፍ ላይ ቆሙ፤ ከዚያም ከጎናቸው ወደ ቆመ አንድ ሰው ዞሩና እንዲህ አሉት ...
ሐሰን አል በስሪ ፡- "ይህ ሟች ወደ ዱኒያ ቢመለስ ምን የሚያደርግ ይመስልሀል ?" ብለው ጠየቁት
ሰውየው፡- "ኢስቲግፋር ያደርግ ነበር፤ ይሰግድም ነበር፤ መልካም ነገሮችንም ሁሉ ይጨምር ነበር" አላቸው
ሐሰን አል በስሪ ፡- ለእርሱ አምልጦታል፤ ለአንተም እንዳያመልጥህ.....
የኢስቲግፋሮች አለቃ የተባለው ዱዓ
«اللهم أنت ربي لا إله إلا أنت، خلقتني وأنا عبدك، وأنا على عهدك ما استطعت. أعوذ بك من شر ما صنعت. أبوء لك بنعمتك علي وأبوء بذنبي فاغفر لي ذنوبي. فإنه لا يغفر الذنوب إلا أنت»
«አላሁም‐መ አንተ ረብ‐ቢ ላ ኢላሀ ኢል‐ላ አንተ። ኸለቅተኒ ወአነ ዐብዱከ ወአነ ዐላ ዐህዲከ ወወዕዲከ መስተጦዕቱ። ከሰራሁት ነገር ክፋት ባንተ እጠበቃለሁ። አቡኡ ቢኒዕመቲከ ዐለይ‐የ። ወአቡኡ ቢዘንቢ። ፈግፊር ሊ ዙኑቢ። ፈኢን‐ነሁ ላ የግፊሩዝ‐ዙኑበ ኢል‐ላ አንተ።»
:
ትርጉም: ‐ አላህ ሆይ አንተ ጌታዬ ነህ። ከአንተ በስተቀር ሌላ አምላክ የለም። ፈጥረኸኛል። እኔም ያንተ ባርያ ነኝ። እኔ በቻልኩት መጠን ላንተ በገባሁት ቃልኪዳን እና በገባህልኝ ቃል በመተማመን ላይ ፅኑ ነኝ።
በእኔ ላይ የዋልከውን ፀጋ እለፈልፋለሁ። ኃጢኣቴንም እለፈልፋለሁ። ጌታዬ ሆይ ኃጢኣቴን ማረኝ። ከአንተ በስተቀር ኃጢኣትን የሚምር የለምና።
:
በሐዲስ እንደተጠቀሰው: ‐ «ይህንን ኢስቲግፋር በውስጡ ያለውን መልእክት ከማመን ጋር በጧት ብሎት ከማምሸቱ በፊት ከሞተ የጀነት ሰው ይሆናል። በሌሊት ይህንን ብሎ ከመንጋቱ በፊት ከሞተም የጀነት ሰው ይሆናል።»
ቡኻሪ፣ ቲርሚዚ እና ነሳኢ ዘግበውታል።

ሳቅ ጨዋታን እንጂ አንዴም አልተቆጡ፣
ሁሉን አልሰስት ነበረ ሲሰጡ፣
ድህነት አይፈሩ ለነገ እንኳ ቢያጡ፣
ንጉስ ቢሆኑ’ንኳ አርሽ አልተቀመጡ፣
ኹሉን ለመኻደም ነበር ሲሯሯጡ።
ሰዉ ቤት አንዳ’ልገቡም ፍቃድ ሳይጠይቁ፣
አደበኛ ናቸው ባ’ደብ የደመቁ፣
ሐይባቸዉ ያሰፈራል ሲታዪ ተሩቁ፣
በኑር ተኳኩለው በኑር የደመቁ፣
ስንቶች አይተው ብቻ በፍቅርሁ ወደቁ ።
ተጉተናዎ ላይ ኑር ዳምኖ ሲያጎርፈዉ፣
በርቁ ተወርውሮ አርዋህ የሚኸጥፈው፣
ያ’ይኖችሁ ጀማላ በነظራ ሚገርፈዉ፣
የ ቅንድብሁን ማማር ቀለም አልወሰፈው፣
ላንድ’ዜ ለራቀሁ ሸውቅሁ ሚጋረፈው።
ይኼ ያንቱ ምስኪን ቢርቅ ታ’ንቱ ሐድራ፣
ኒፋቅ ሞልቶት ስራው የበዛው ኪሳራ፣
እንዲህ እንዳይጠፋ ኻቲማውን ፈራ፣
መላ ኣለ በስምሁ ለዱንያም ላ’ኺራ።
መድሓኒቴ ብሎ አሽከር ተጣራ።
ያንቱ ስም ነው መላ በሑለቱም ሐገር፣
ስምሁ ጋር ከዋለ አሽከር አይቸገር፣
በስሙ ይሆናል ነገሩ ሁሉ ገር፣
ያንቱን ስም የያዘ ማሕሸር አይሸበር፣
ባንቱ ሸፋዓ ነው የሚገኘው መክበር።
ቁጣው ሲስገመገም ጉዱ ሲፈነዳ፣
አደራ የዚያን ቀን በማሕሸሩ ሜዳ፣
ኹሉም ነፍሴን ብሎ ያመኑት ሲከዳ፣
እናት ልጇን ስትሸሽ ዘመድ ሲሆን ባዳ፣
አደራ ሰይዲ አርጉኝ አንቱ ዘንዳ።
ሰይዲ ያ ረሱለሏህ!❤️
ሁሉን አልሰስት ነበረ ሲሰጡ፣
ድህነት አይፈሩ ለነገ እንኳ ቢያጡ፣
ንጉስ ቢሆኑ’ንኳ አርሽ አልተቀመጡ፣
ኹሉን ለመኻደም ነበር ሲሯሯጡ።
ሰዉ ቤት አንዳ’ልገቡም ፍቃድ ሳይጠይቁ፣
አደበኛ ናቸው ባ’ደብ የደመቁ፣
ሐይባቸዉ ያሰፈራል ሲታዪ ተሩቁ፣
በኑር ተኳኩለው በኑር የደመቁ፣
ስንቶች አይተው ብቻ በፍቅርሁ ወደቁ ።
ተጉተናዎ ላይ ኑር ዳምኖ ሲያጎርፈዉ፣
በርቁ ተወርውሮ አርዋህ የሚኸጥፈው፣
ያ’ይኖችሁ ጀማላ በነظራ ሚገርፈዉ፣
የ ቅንድብሁን ማማር ቀለም አልወሰፈው፣
ላንድ’ዜ ለራቀሁ ሸውቅሁ ሚጋረፈው።
ይኼ ያንቱ ምስኪን ቢርቅ ታ’ንቱ ሐድራ፣
ኒፋቅ ሞልቶት ስራው የበዛው ኪሳራ፣
እንዲህ እንዳይጠፋ ኻቲማውን ፈራ፣
መላ ኣለ በስምሁ ለዱንያም ላ’ኺራ።
መድሓኒቴ ብሎ አሽከር ተጣራ።
ያንቱ ስም ነው መላ በሑለቱም ሐገር፣
ስምሁ ጋር ከዋለ አሽከር አይቸገር፣
በስሙ ይሆናል ነገሩ ሁሉ ገር፣
ያንቱን ስም የያዘ ማሕሸር አይሸበር፣
ባንቱ ሸፋዓ ነው የሚገኘው መክበር።
ቁጣው ሲስገመገም ጉዱ ሲፈነዳ፣
አደራ የዚያን ቀን በማሕሸሩ ሜዳ፣
ኹሉም ነፍሴን ብሎ ያመኑት ሲከዳ፣
እናት ልጇን ስትሸሽ ዘመድ ሲሆን ባዳ፣
አደራ ሰይዲ አርጉኝ አንቱ ዘንዳ።
ሰይዲ ያ ረሱለሏህ!❤️
ከወንጀሎች ሁሉ የከፋው ወደ አላህ በነፍስ (እኔነትን ይዞ) መግባት ነው ይላሉ ታላላቆቹ።
"አልሐምዱሊላህ" በማለቴ ለሰላሳ ዓመታት በሙሉ አላህን ምሕረት ስለምነው ኖሬያለሁ አሉ አንድ የአላህ ደግ ባርያ። ነፍሴን አይቼ "አልሐምዱሊላህ" አልኩኝ... ይኸው ጸጸቱ እስከዛሬ ያነደኛል። ጌታዬንም እንዲያዝንልኝ እማጸነዋለሁ። ሲሉ ያደመጡ ሰዎች በግርምት "እንዴት?" ብለው ጠየቋቸው።
"አንድ ቀን በግዳድ ውስጥ እሳት አደጋ ተከሰተ። ሰደዱም ተቀጣጥሎ ቤቶችችና ድንኳኖችን አወደመ። ሰዎች እሳቱን ለማጥፋት እየተመሙ ይሯሯጣሉ። እናም አንድ ሰው መንገድ ላይ አግኝቶኝ "አብሽር! ያንተ ሱቅ ተርፏል" አለኝ። አልሐምዱሊላህ አልኩ። ያን ጊዜ ነፍሴን ብቻ ተመለከትኩ...ወንድሞቼንም ረሳሁ...ይኸው ለሰላሳ ዓመታት "አልሐምዱሊላህ" ላልኩበት ኢስቲግፋር እያደረኩ አለሁ" አሏቸው።
ምንም ዓይነት ስራ ስንሰራ፣ ማንኛውንም ነገር ስንጀምር "ቢስሚላህ" እንላለን። በአላህ ስም ያልተጀመረ በረካ አይኖረውም፣ አይገራምም። በነፍሱ የገባ ከሰረ። አላህ የቁርኣኑን ሱራዎች በስሙ ሲጀምር ለአደም ልጆች መልእክቱን እያስተላለፈ ነው። ሁሉን ነገር በአላህ እንጂ በራሳችሁ አትግቡ፣ በእኔ እንጂ በእናንተ የሚሆን ነገር የለም እያለ ነው።
እኔ ያልክ ጊዜ ትጠፋለህ፣ ኪሳራህ ብዙ ነው። ኢማመል ኪሳኢ አንድ ገጠመኝ አላቸው
ሃሩን አልረሺድን ኢማም ሆኜ እያሰገድኩ ነበር...እናም ቁርኣን አቀራሬ ለራሴ ማረከኝና ነፍሴን አሞገስኳት...እኔ'ነትን ባሰብኩበት ጊዜ ህፃን ልጅ እንኳን የማይሳሳተውን ቃል ተሳሳትኩ..."የርጂዑውን" የሚለውን "የርጂዒይን" ብዬ ቀራሁ። ሃሩን እንኳን ሊያርመኝ አፍሮ ሰላቱን ካጠናቀቅን በኋላ ነው የጠየቀኝ ይላሉ።
በማንኛውም ጉዳይ ዱንያዊም ሆነ ዲናዊ፣ ወደ አላህ ስትጣራም ሆነ ወደ'ሱ ስትጓዝ፣ በምታደርገው እና በምትተወው እያንዳንዱ ነገር ላይ ነፍስህን ይዘህ እንዳትመጣ አደራ ይሉናል

#ዚክር
ረሱልﷺ ተጠየቁ፡ የትኛው ፆም ነው በላጭ?
"በብዛት አላህ የተወሳበት (ዚክር የተደረገበት) ፆም ነው" በማለት መለሱ
#ላኢላሃኢለሏህ
ተህሊል በ ሱፊ መሻይኾች ዘንድ ላ ኢላሀ ኢለላህ ከ ሁሉ ነገር በፊት አጥብቀዉ የሚዘክሩት እና ለ ተከታዮቻቸዉ አደራ የሚሉት ዚክር ነዉ።
ሸይኻችን እንደነገሩን በ ገዉስ አል አእዘም ሸይኽ አብዱል ቃዲር ጄላን ጊዜ ከ ቀን አዉራዳቸዉ መካከል ተህሊል ወይም (ላ ኢላሀ ኢለላህ) 140,000 ጊዜ እንደሚዘከር እንደነበር ይታወቃል። የ ሲልሲለቱል ቃድሪያ ጠሪቃ የ አዉራድ ኪታብ ዉስጥም ተጠቅሶ ይገኛል።
ነገር ግን ወደ ሀገራችን የ ሱፊ መሻይኾች ስንመጣ ለተከታዮቻቸዉ አዉራዱ እንዳይከብዳቸዉ በማሰብ እዉቁ የ አገራችን አዉሊያ በህረል ኡሉም ሚስኩል ሀበሻ ሸይኸ ሰይድ ጀማሉል አኒይ ረዲ አላሁ አንሁም። የቀኑን 140,000 ተህሊል ወደ 70,000 ቀንሰዉት ነበር። ከዛም ቡሀላ ሸይኽ ሰይድ አህመድ አዳኒይ ረዲ አላሁ አንሁም 70,000 ተህሊል በየቀኑ መዘከር ለ ዘመኑ ሰዉ ይቸግረዋል ብለዉ በማሰብ ወደ 24,000 እንዲሁም እሱም ለከበደዉ 12,000 ተህሊል በየቀኑ እንዲዘክር የቀን አዉራድ ይሰጡት ነበር።
ላ ኢላሀ ኢለላህ ምትለዋን ዚክር አብዝተን በዘከርናት ቁጥር ወደ ቀልባችን እየገባች ትመጣለች። ከ ዚክር ሁሉ በላጭ ላ ኢላሀ ኢለላህ ነዉና እቺን ዚክር እናብዛ።
قال رسول الله صلى الله عليه وسلم “أَفْضَلُ الذِّكْرِ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ،

ቁርኣን ከመቅራት ቀጥሎ በምላስ ከሚፈጸሙ አምልኮዎች ሁሉ ዚክርን፣ አላህን ማውሳትን እና ዱዓ ማድረግን የሚበልጥ ነገር የለም።
አላህ ሱወ እንዲህ ብሏል
"አስታውሱኝም፤ አስታውሳችኋለሁና" (በቀራህ 152)
"(እነርሱም) እነዚያ ቆመው፣ ተቀምጠውም፣ በጎኖቻቸው ተጋድመውም አላህን የሚያወሱ..." (ኣሊ ዒምራን 191)
"ጌታህንም በምስጢር ተዋድቀህና ፈርተህ ከጩኸት በታችም በኾነ ቃል በጧትም በማታም አውሳው። ከዘንጊዎችም አትኹን።" (አል-አዕራፍ 205)
የማንም ጥላ በሌለበት ቀን አላህ በጥላው ስር ከሚያስጠልላቸው ሰባት ዓይነት ሰዎች መካከልም "ለብቻው ተገልሎ ባለበት ሁኔታ አላህን በማውሳት ዐይኑ እንባ ያፈሰሰች ሰው" እንደሚገኝበት በሐዲስ ተነግሯል።
በሌላ ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ ሰለሏሁ ዓለይሂ ወኣሊሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል
"ከስራዎቻችሁ ሁሉ በላጩ፣ በንጉሣችሁ (ጌታችሁ) ዘንድ ምርጡና ደረጃችሁን ከፍ የሚያደርገው፣ ወርቅና ብር ከመለገስ በላይ በላጭ የሆነው፣ እንዲሁም ጠላቶቻችሁ ጋር ተገናኝታችሁ አንገቶቻቸውን ከምትመቱና አንገቶቻችሁን ከሚመቱ በላይ በላጭ የሆነውን ልንገራችሁን?" አሉ። ሰሃቦችም አዎን ይንገሩን አሏቸው። እርሳቸውም "የልዕልና ባለቤት የሆነውን አላህን ማውሳት ነው።" አሉ
© ኢሕያእ ዑሉሚዲን

ኢብኑ ነሕዊይ ይናገራሉ رحمه الله
አንድ ቀን ኢብኑ ዓጣኢ'ላሂ‐ሰከንደሪ መጅሊስ ላይ ተገኘሁ ፣ የዛኔ የዘመኑ ታላቅ ሸይኽ ነበሩ
በአድናቆት ሆኜ ዕውቀትና ሊቅነታቸውን እየተመለከትኩ ለራሴ ይህን አልኩ
"እንደው የትኛው መቃም* ላይ ይሆኑ ይሆን?"
ወደኔ ተመለከቱና " ወንጀል ሰርተው ምህረትን ከሚለምኑት" አሉ
በነገሩ በጣም ተገርሜ ከግርማ ሞገሳቸው የተነሳ ጭጭ አልኩ ! ከዛም ሰላምታ አቅርቤ ሄድኩኝ
በዛው ለሊት በህልሜ ነብዩን ﷺ ከፍ ያለ ስፍራ ላይ ሆነው በዙሪያቸው የተከበሩ ሰሓቦች ተሰብስበው አየሁ
ነብዩም ﷺ
« የታለ ታጁዲን ኢብኑ ዓጣኢ'ላህ አሉ »
"አቤት አለሁ ያ ረሱለላህ ﷺ" አሉ
ነብዩም ﷺ
«ተናገር አላህ ንግግርህን ይወዳል »አሉ
ከእንቅልፌ ባነንኩ ፣ ባየሁት ነገርም በጣም ተደነቅሁ !
ወደ ሰይዲ ኢብኑ ዓጣኢ'ላህ ዘንድ ስመጣ
በህልሜ ነብዩ ﷺ ፊት ሲናገሩ የሰማሁትን ሲናገሩ አገኘኋቸው !
ለራሴም በውስጤ
"በአላህ እምላለሁ ይህ ነው መቃሙ" አልኩ።
ኢብኑ ዓጣኢ'ላህ ወደኔ ተመለከቱና
"አንተ ላይ`ኮ የተደበቀው የላቀው ነበር" አሉኝ።
መደድድድድድድድ ያ አህለል‐ኡንሲ ቢላሂ
* መቃም مقام = የመንፈሳዊ ከፍታ የልህቀት ደረጃ
✍tof nas yusuf ❤️

በሸኽ ሺብሊ እንደተተረከው፦ አንድ ጎረቤታቸው ከሞተ በኋላ በህልም ያዩታል ፣ ከዚያም ለጎረቤታቸው "አላህ ምን አደረገህ?" በማለት ጠየቁት
እርሱም እንዲህ ሲል መለሰ - “ሼኽ ሆይ! በመቃብር ውስጥ በጣም አስፈሪ ነገሮችን ተመለከትኩ በዚህም ሰቀቀን ውስጥ ገባሁ መልአክቱ ሙንከርና ነኪር ስመለከት ደሞ የምናገረውም ጠፋብኝ ፣ ለራሴም ‘ዋ.. ጥፋቴ አከተምልኝ አልኩ’ "በዱንያ ላይ ሙስሊም ነበርኩ የሞትኩትም በእስልምና ነበር ,
ከዚያም ሁለቱ መላእክት ጥያቄዎቻቸውን በከፍተኛ ድምፅ ጥያቄዎቻቸው እንድመልስ ጠየቁኝ." በድንገት አንድ መልከ–መልካም እና ጥሩ መዓዛ ያለው ሰው ብቅ አለ ፤
የሁለቱን መላእክት ጥያቄዎች በተሻለ መንገድ መልስ ለመስጠት በእኔ እና በሁለቱ መላእክት መካከል እራሱን ሰየመ, ከዚያም አላህ ይዘንልህና “አንተ ማን ነህ? አልኩት"
እርሱም፦ እንዲህ ሲል መለሰ - “እኔ [ሶለዋት] አላሁመ ሶሊ 'ዓላ ሰይዲና ሙሐመድ ወ'ኣላ ኣሊ ሰይዲና ሙሐመድ' ነኝ ..የትም ብትሆን በፈለከው ጊዜ አንተን ለመርዳት እና ለማዳን ሃላፊነት ተሰጥቶኛል” አለ።
📚—كتاب الصلوات مفتح حل المشكلات، علي قزويني، ص : 96.
©

የመለያው ቀን
እያንዳንዱ ስልጣኔ ከማበቡና የልቅና ማማ ላይ ከመድረሱ በፊት ወሳኝ ታሪካዊ ክስተት ያሳልፋል፡፡ ለሙስሊሞች ይህ ወሳኝ ክስተት ረመዳን 17 2ኛ ዓ.ሂ የተካሄደውና በቁርአን ስሙ የተጠቀሰው ታላቁ የበድር ጦርነት ነው፣ አላህ ይህን ዕለት የውመል ፉርቃን(የመለያው ቀን) ብሎ ጠርቶታል፣ እውነትና ውሸት የተለዩበት የየራሳቸውን ጎራ ይዘው ፊት ለፊት የተያዩበት ዕለት ነው፡፡
‹‹...በዚያም እውነትና ውሸት በተለየበት ቀን፣ ሁለቱ ጭፍሮች በተገናኙበት(በበድር) ቀን…››አል አንፋል 41
የአላህ መልእክተኛ ሰ.ዐ.ወ የቁረይሾችን የንግድ ቅፍለት ለመቆጣጠር ከተወሰኑ ሰሃቦች ጋር ሆነው ከመዲና ወጡ፤ የቅፍለቱ መሪ የነበረው አቡ ሱፍያን ይህ ወሬ ሲደርሰው ወደ መካ መልእክተኛ ላከ፡፡ ቁረይሾችም 1300 የጦር ሰራዊት፣700 ግመሎችና በቁጥር የበዙ ፈረሶችን ይዘው ተንቀሳቀሱ፡፡ የሙእሚኖች ብዛት ከ313-319 ሲሆን 70 ግመል እና 2 ፈረስ ብቻ ነበር የያዙት፡፡ ነቢ ሰ.ዐ.ወ የባልደረቦቻቸውን ሃሳብ መስማት ፈለጉና ውጊያ እናድርግ ወይስ እንመለስ ብለው አማከሯችው፤ ምክንያቱም አወጣጣቸው ቅፍለቱን ለመማረክ እንጂ ለጦርነት አልነበረም፡፡ በመጀመሪያ አቡበክር ተነሱና ጥሩ ንግግር አደረጉ፤ ዑመርም በመቀጠል ተናገሩ፤ ከዚያም ሚቅዳድ ኢብን ዐምር ተነሳና፡-
‹‹የአላህ መልእክተኛ ሆይ፡ አላህ ያመላከተዎትን ተግባር ይፈፅሙ እኛ ከጎንዎ ነን፤ በአላህ እምላለሁ እስራኤሎች ለሙሳ ‹አንተና አምላክህ ሂዱና ተዋጉ፤ እኛ አዚህ ተቀምጠን እንጠብቃችኋለን› እንዳሉት እኛ አንልዎትም፡፡ ይልቁንም እርሶና አምላክዎ ሄዳችሁ ተዋጉ፤ እኛም ከናንተ ጋር እንዋጋለን፡፡ በእውነት በላከዎ ጌታ እምላለሁ ወዳሻዎ ቦታ ብትወስዱንም እስከመጨረሻው እንከተሎታለን፡፡›› አለ፤ ነቢ ሰ.ዐ.ወ በንግግሩ ተደስተው ጥሩ ብለሀል አሉትና ዱዓእ አደረጉለት፡፡ ሁሉም ሰሀቦች እንደ ሚቅዳድ ታዛዥ እንደሆኑ ያውቃሉ፤ ነገር ግን አሁንም ደግመው ሀሳባቸውን ጠየቋቸው፤ ‹‹እናንተ ሰዎች ሆይ፡ አስተያየታችሁን ስጡኝ›› አሉ፡፡ አንሳሮችን ማለታቸው ነው፤ ምክንያቱም አንሳሮች ከነቢ ሰ.ዐ.ወ ጋር የዐቀባን ስምምነት በተዋዋሉ ጊዜ መዲና መጥቶ የሚያጠቃቸውን ጠላት እንጂ ከመዲና ውጪ ወጥተው እንዲዋጉ አያስገድዳቸውም፡፡
ሰዐድ ኢብን ሙዓዝ ‹‹የአላህ መልእክተኛ ሆይ፡ የኛን አስተያየት ነው የፈለጉት? ›› ብሎ ጠየቃቸው እሳቸውም አዎ አሉት፡፡ እሱም አንሳሮችን ወክሎ እንዲህ ተናገረ፡-
‹‹ በእርሶ አምነን እውነት ብለን ተቀብለንዎታል፤ ያመጡት መልዕክት እውነት ስለመሆኑም መስክረናል፤ እርስዎን ለመታዘዝ ቃልኪዳን ገብተናል፤ የአላህ መል/እክተኛ ሆይ፡ የሚፈልጉትን ይፈፅሙ በእውነት በላክዎ አምላክ እምላለሁ ይህን ባህር ሰንጥቀን እንድናልፍ ቢያዙን እንኳ እናልፈዋለን፤ ከመካከላችን አንድም ሰው ወደኋላ አይቀርም ነገ ከጠለት ጋር ብንፋለም የምንጠላ አይደለንም በጦርነት ላይ ታጋሾችና ፅኑዎች ነን፤ ከኛ የሚደሰቱበትን ነገር አላህ ያሳይዎ ይሆናል በአላህ በረከት የታየዎትን ይፈፅሙ፡››
ነቢ ሰ.ዐ.ወ በሰዕድ ንግግር ተደሰቱ፤ ወኔያቸውም ይበልጥ ተነሳሳ፤ “ተጓዙ አይዟችሁ አላህ ከሁለት በጎ ነገሮች አንዱን እንደሚገጥመኝ ቃል ገብቶልኛል፤ በአላህ እምላለሁ ሰዎች (ጣኦታውያን) ሲረፈረፉ ይታየኛል” አሉ፡፡
የዛን ቀን ምሽት አላህ ሱ.ወ ዝናብ አወረደ ከሀድያንን ያዳክመች፣ ለሙእሚኖች ጥንካሬ የጨመረች ዝናብ አዘነበ፡፡ “ ከርሱ የሆነን ሰላም ሊለግሳችሁ በእንቅልፍ በሸፈናችሁ ጊዜ፣ እንዲሁም በርሱ ሊያፀዳችሁ፣ የሰይጣንንም ጉትጎታ ሊያስወግድላችሁ፣ ለልቦቻችሁም ጥንካሬን ሊያጎናፅፍና እግሮቻችሁንም (ውጊያ ላይ) ሊያፀና ከሰማይ ውሃን ባወረደ ጊዜ (የሆነውን አስታውሱ) አል አንፏል 11
ጣኦታውያን ሲገለፁና ሁለቱ ሀይሎች ሲተያዩ የአላህ መልዕክተኛ ሰ.ዐ.ወ እንዲህ ብለው አላህን ለመኑ፡-
“አላህ ሆይ ቁረይሾች ከነ ትዕቢትና ኩራታቸው አንተን ለመቀናቀን እና መልእክትህን ለማስተባበል እነሆ ታድመዋል፤ አላህ ሆይ ቃል የገባህልኝን ድል ስጠኝ፤ አላህ ሆይ ሽንፈትን አከናንባቸው›› የሰራዊታቸውን ረድፍ አስተካክለው ከጨረሱ በኋላም አምላካቸውን አጥብቀው ከመማፀን አልተቆጠቡም፤ “አላህ ሆይ ቃልህን እንድትሞላ እማፀንሀለው›› እያሉ ይለምኑት ነበር፤ ጋቢያቸው ከትከሻቸው እስኪወድቅ ድረስ ዱአቸው በረታ፤ አላህም ለመላእክቱ እንዲህ የሚል መልዕክት አስተላለፈ፡-
“እኔ ከናንተ ጋር ነኝ እማኞችን አጠናክሩ፤ በነዚያ በካዱት ሰዎች ልቦች ውስጥ ፍርሀትን እለቃለሁ….›› አልአንፋል 12 ለመልዕክተኛውም እንዲህ ሲል አበሰራቸው፡
“ተከታትለው በሚወርዱ ሺህ መላዕክት እገዛ አልክላችኋለሁ”
“አዎን ብትታገሱና ብትጠነቀቁ ከዚህም ፍጥነታቸው (ጠላቶቻችሁ) ቢመጡባችሁ፡ ጌታችሁ ምልክት ባላቸው አምስት ሺህ መላእክት ይረዳችኋል›› አሊ ዒምራን 125፡፡ መላእክት በወረዱ ጊዜ ነቢ ሰ.ዐ.ወ ይህንን የቁርአን አንቀፅ አነበቡ
“ስብስበቸው ድል ይምመታል፡ ጀርባዎቻቸውንም ይዞራሉ” አልቀመር 45፡፡
በእጃቸው እፍኝ አፈር ቆነጠሩና ወደ ቁረይሾች አቅጣጫ በመዞር “ፊቶቻችሁ ይበላሹ” እያሉ በተኑት፤ አሸዋው በእያንዳንዱ ጣኦታዊ አይንና አፍንጫ ውስጥ ገባ፡፡
ጦርነቱ በጣኦታውያን ከባድ ሽንፈት፡ በሙስሊሞች አንፀባራቂ ድል ተደመደመ፡፡ ከሙስሞች 14 ሰማዕታት ሲኖር ከጣኦታውያን 70 ሰዎች ተገድ' ለው 70ዎቹ ተማረኩ፤ ከሙታንም ሆነ ከምርኮኞች አብዛኛዎቹ መሪዎችና በላባቶች ነበሩ፡፡

በሰይዲና ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ዘመን በተውበቱ ላይ ቋሚ ያልነበረ፣ ሁሌም እየቶበተ ተመልሶ እዚያው የሚነከር የኔ ቢጤ ነበር። ሃያ አመት በዚህ ሁኔታ ቆይቷል። እኔስ ብሆን ስንት ዓመቴ በዚህ መልኩ ስኖር?!…
:
አላህ ሰይዲና ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ላይ ራእዩን አወረደ። "እገሌ ለሚባለው ባርያዬ ንገረው። እኔ ተቆጥቼበታለሁ!" አላቸው።…
ሰይዲና ሙሳ መልእክቱን አደረሱ። ሰውየውም እጅግ አዘነ። ደነገጠ። እንዲህ እያለ ወደ ሜዳ ወጣ: ‐
«ኢላሂ! እዝነትህ አልቆ ነው?! ወይስ ኃጢኣቴ ጎድቶህ?! የይቅርታ ካዝናህ ነጠፈ?! ወይስ በባሮችህ ላይ ሰሰትክ?! የቱ ወንጀል ነው ከይቅርታህ የሚገዝፈው?!…
ቸርነት ቀዳሚ ጠባይህ ነው።…
መናጢነት፣ ኃጢኣት የመጤው "እኔ" ተከሳች ጠባይ ነው።…
ታዲያ የኔ ጠባይ ካንተ ጠባይ ሊያይል ይችላል?!…
ባሮችህን ከረሕመትህ ከጋረድክ ማንን ይከጅላሉ?!…
አንተ ካባረርካቸው ወደ ማን ይሸሻሉ?!…
ኢላሂ! እዝነትህ ካለቀና ቅጣትህን መቅመሴ የግድ ከሆነ የባሮችህን ኃጢኣት በሙሉ እኔ ላይ አድርግ። በነፍሴ በዥቻቸዋለሁ!… »
:
አዛኙ አላህ እንዲህ አለ: ‐ «ሙሳ ሆይ! ሰውየው ዘንድ ሂድና እንዲህ በለው: ‐ «ኃጢኣትህ ሰማይና ምድርን ቢሞላ እንኳን እምርሃለሁ። በሙሉ ኃያልነቴ፣ በሰፊው ይቅርታዬ፣ በማይነጥፍ እዝነቴ እና በማያልቀው ምህረቴ እስካወቅከኝ ድረስ ምሬሃለሁ!»
:
ታሪኩን ኢማም አል‐ገዛሊይ "ሙካሺፈቱል‐ቁሉብ" ላይ አውርተውታል።
✍ tewfik bahiru
https://www.tgoop.com/fiqshafiyamh
[…አሏሁምመ ኢነከል ዐፉው፣ ቱሒቡል ዓፉው ፈዓፉ አንና…ያ ራሒም!❤️…]

ዘካተል ፊጥር ለአዲስ አበባና ለአካባቢዋ ለአንድ ሰው 200 ብር ነው። ወደ ክፍለሀገርሮች ስሌቱ ከዚህ የተለየ ሊሆን ስለሚችል በአካባቢው ያሉ ዐሊሞችን አማክሩ።
ሠራተኛንና ዘበኛን ጨምሮ በምታስተዳድሯቸው ቤተሰቦች ልክ ተሰልቶ ዛሬና ነገ በፍጥነት ማውጣት ለተቀባዮች ለዒድ ዝግጅት የበለጠ ጠቃሚ ይሆናል።
https://www.tgoop.com/hassentaju

#ተፋዑል
#የኸሚስ_መጃሊስ
#ድልን_መጠባበቅ_አምልኮ_ነው
አንድ ዓሊም እንዲህ ይላሉ፦
[ ሰዎች የፈለገ የጸሐይ ብርሐን ቢያስፈልጋቸው ጸሐይ መጥለቋ አይቀርም። በመጥለቋ ምክንያትም የሚያለቅስ ኾነ የሚያዝን የለም ምክንያቱም ነገ ተመልሳ እንደምትወጣ ስለምናውቅ፤ ይህ "መተማመን" ይባላል። የጸሐይን ዳግም መውጣት አምናችሁ፥ በተከታዩን የአላህን ቃል «ከችግር ጋር ምቾት አልለ።» አልኢንሺራሕ፤06 በሚለው አልተማመናችሁም? አላህ ከችግር በኋላ እርሱ በፈለገው ነገር ይገላግልሃል። በተከታዩ የአላህ ቃልስ አልተማመንም?! « አላህ ፈቃዱን አድራሽ ነው።» ጠላቅ፤03 ]
ሰዎች የወደፊታቸውን የመመለከት ዕድል ቢኖራቸው ዛሬያቸው ምንም ይኹን ያመሰግኑታል ይወዱታል። አላህ ለነገ ከመስራትና ከመልፋት ጋር በውስጣችን ለነገ ከመጨነቅና ሐሳብ ውስጥ ከመግባት እንድንቆጠብ ግን አዝዞናል። "ሪዝቅ" በሰፊው ትርጉሙ ከሰማይ የሚመጣ ነገር ነው። ሰማይ ማለት የዱዓ፣ የራሕመት፣ የበረካ ቂብላ (መቅጣጫ) ነው። ትዳር፣ ልጅ፣ ገንዘብ፣ ጤንነት ከብዙ የሪዝቅ ዓይነቶች መካከል ናቸው። ብቸኛ ግን አይደሉም የኢማንን ሪዝቅ ሳንሰጥ የሐብት ሪዝቅ ቢሰጠን ጎዶሎ ነው። ስንጠይቅ የተሟላ ሪዝቅ መጠየቅ ደግ ነገር ነው። ሰዎች የሚያማርሩትና ወደ አላስፈላጊ ትዕግስት ማጣት የሚገቡት የተሰጣቸውን ሪዝቅና የሚያስፈልጋቸውን ሪዝቅ ባለመረዳታቸው ነው። ስንት ጸጋ በእጃችን እያለ ወደ ማማረር እና አለማመሰገን የሚያስገባን ሸይጧን ነው። እርሱ (ሸይጧን) ወደዚህች ዐለም የመጣበት ዋነኛ ዐላማ ሰዎችን እንዳያመሰግኑ ማድረግ ነው። ካላመንከኝ የአዕራፍ አንቀጽን አንብብ። ከሰይጣን ጉትጎታ (ወስዋስ) በላይ ደግሞ የሰዎች ጉትጎታ (ወስወሳ) አደጋ ነው። የለንበት ደረጃ ምንም ይኹን እናመስግን፣ ችግር ላይ ብንወድቅ ራሱ ከዚህ ችግር አላህ እንጂ ማንም እንደማየወጣን እንመን። የሰው አንመለከት፣ በአንደበታችን በድርጊታችን የሰው ልብ ላይ ወስዋስ የሚፈጥር ነገር ላለማድረግ እንጣር።
ሰዎች የዚህን የተውሒድ እሳቤ ባለመረዳታቸው ሳቢያ ለነፍሳቸው ክፋት ይጋለጣሉ። በመጨረሻም የሰይጣንና የሰዎች ጉትጎታ (ወስወሳ) መረብ ውስጥ ይገቡና የሚኖሩት በርሱ ክበብ ውስጥ ይኾናል።
ወደ ተጨባጩ ስንወስደው ምንም ያላጣና ፏ ብሎ የሚሰራን ወጣት ምን ነካው ሳይባል ተነስቶ ይሰደዳል። ተረጋግተው በፍቅር በሚኖሩ ጥንዶች መካከል የረባ በማይባል ቀውስ ፍች ይፈጸማል፣ ተረጋግቶ የሚነግደው ነጋዴ ባልረባ የስነምግባር ቀውስ ሕይወቱ ይናጋል። ሌሎች በርካታ ችግሮች መምጫቸውን ብናጤን ባልተገባ መንገድ ለማደግ ከመከጀል፣ ያለንን ባለማወቅና ባለማመስገን፣ የገጠሙንን ችግሮች ወቅታቸውን ጠብቀው እንዲወገዱ ዕድል ባለመስጠት የሚመጡ የችኮላ ውጤቶች ሆነውም እናገኛቸዋለን።
ችግር ውስጥ ነህ? አላገባህም? ባለዕዳ ነህ? ድኽነት አስቸገረህ? ወደ መፍትሔ እንጂ ራስህንም ኾነ ሕዝብን የሚጎዳ ተግባር ውስጥ አታስገባ፤ ታግሶ ይህን ነገር ከአላህ መጠባበቅ በራሱ አምልኮ ነውና። በተጨማሪ ራሳችንን በአምልኮ በዚክር እንዲሁም ካላስፈላጊ ሰይጣናዊ ሐሳብ ለማራቅ ኢማን ላይ መሰንበት ጥሩ መውጫ መንገድ ነው።
አላህ ያስረዳና ♥
እርሱ ይፈርጀና ♥

[…አንተ የኔ አሏህ 1…]
ፍቅርህ ብርሓናማ ነው! በ’ኛ አድማስ ላይ የተጋረደው ድቅድቅ ፅልምት ባሻገር ኃያል፣አሸናፊው፣እና ንጉሱ የሆንከው አሏሃችን ያንተ ህያው ብርኃን አለ።ወደ’ኛ የሚወነጨፈው ፍቅርህ በሩሓችን ላይ ደማቅ መንፈሳዊ ሕያው ብርሓንን ያኖራል። የኑር ብራቅህን ወደ ባዶው እኛነታችን ሰንዝረህ እንድናስብህ አደልከን። መድረስ ወዳንተው ነው፣ ማድረስም ያንተ ነው።አላህዬ☺️
እኛም…አሰብንህና ደግሞ…ካንተ ውጪ ላለ ለሁሉም ነገር ምንም ግድ አጣን
የወደቅንበትን፣የባዘንንበትን የስቃይ አረንቋ ዘንግተን ፍካት በልባችን ተሞላ።አንተን በማሰብ ውስጥ ተጠመድን። እኛማ በምን አቅማችን…! አንተው አሰብኸን ኣሳሰብኸንም፣ እንድናስብህ ኣደረግኸን። ልታድነን ስትፈልግ።ከዚያ በኃላ…አንተ ፈቅደህ፣በኛ ላይ እንዲሆን የሻኸው ሁሉ እንዲጣፍጠን ሆነ። በሁሉም መከራ ውስጥ ጥበብህ…ፍቅር ውዴታህ አዛኝነትህ ይታየን ጀመር።እናም ያኔ ስለ ሁሉም ነገር ግድ የለንም። ግድ የሚሰጠን "አሏህ…አሏህ" ማለት ሆነ!
الله…!💚

« በአንድ በጎ ባርያ ላይ የሚሰፍን የአሏህ ውዴታ በቃላት ሊገለጽ የማይችል ስሜት አለው።
እጅግ በጣም ቀዝቃዛ እና ብርድ በሆነ ሌሊት ሞቅ እንዳለ ብርድ ልብስ ልብህን ያካብባል። ወይም የመለኮታዊ ብርሃን ብልጭታ ነውና ወዳንተ ዘልቆ፣ በደም ስርህ ውስጥ ይጓዛል..…ይቆጣጠርሃል።…ከዚያም ስሙን በምላስህ ማዘወተር፣ጣፋጭ ሱስ ይሆንብሃል! »
«በየ ኹሉም የኑሮ ሒደት ውስጥ…በየ ሰዓቱ የምትደጋግመው…ጣፋጭ ስም የርሱ ስም ይሆናል። የስሙ ጥፍጥና የሚሰጥህ ጥልቅ የመደድ መንፈስ የፍቅር ምናኔ ውስጥ ያስገባሃል።ስሙ ቀልብህ ለይ ኢማንን፣ ሩሕ ዘንድ ሰኪናን፣ ጀሰድህ ላይ ደግሞ የኑር ጀማላን ፈገግታን ውበትን…ሞልቶ ያሸበርቅልሃል!»
ስሙን ብቻ መጥራት ህያው ኑር ያለብሳል…
الله🩵

ለነቢ ረሱለሏህ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) በሚኖር ውዴታ’ና ቅርበት የሚገኙ እድያዎች፣በቁጥር ከማይዘለቁ፣ሕይወትን ከሚለውጡ ተዓምራዊ በረከቶች አንዱ…
«ነቢ ረሱለሏህን ወዶ የቀረበ ኹሉ፣የላቀ ክበር’ና ራሕመትን መቋደሱ ነው።»ከሰው ዘር የሶሓቦቹ ማሳያ ነው። ጨለምተኛ ነበር ብርሃኃን ሞሉት። ለክብረቱ ምሳሌ ሰይዲና ቢላልን ያነሷል።ነቢ በመውደዱ ከውርደት ወጣ።በክብር ዙፋን ተደላደለ። ነቢን አገኘ’ና ተውሒድን፣ ኑርን፣ ጀነትን ተጎናፀፈ። ገድሉን ታሪክ ለፊት ገፁ፣አድምቆ ሚዘክረው ሰው ሆነ።
ሀሳቡ ከሰው ልጅ ውጪ ሲታይ ልብ ገዥ ነው።የቴምር ጉቶ ተላምዷቸው በልሳን ከማውራት ጀነት እስከመሰጠት።ለፍቅር ታሪክ ሕያው ማሳያ ሆኖ መወሳት አገኘ።
"ያዕፈር"? የሚባለው መጓጓዣ አሕያቸው የአብሮነት ታሪክ ስለነበረው በዘገባዎች፣ የእስልምና ጉዞ ታሪክ ተካፋይ ሆኖ በክብር እየተወሳ ይኖራል።አፍቃሪዋ ግመላቸው ቀስዋ ስለ ነቢ ረሱለሏህ ፍቅር ተምሳሌታዊ ምስክር በመሆን፣ከልዩ ክብርና ስስት ጋር ስሟ ይወሳል።ከክፍለ ዘመናት በኋላ ሳይቋረጥ እንደ ሁሉም አፍቃሪ ፍቅሯ በክብር ይተረካል።
የተገለገሉበትት ቁስ፣የተጓዙበት መንገድ፣ ያረፉበት ዋሻ፣ የለበሱት፣የኖሩበት ሌላም ሌላው ግዑዝ እቃ እንኳን…በዑመቱ ልብ ውስጥ ቅዱስ ቅርሶች ሆነው ለመከበር ያበቃቸው፣ በነቢ ረሱለሏህ ዙርያ መገኘታቸው፣ከነቢ መቅረባቸው፣በሳቸው መነካታቸው ነው። ምናልናት የ አንድ ጊዜ የመዳፋቸው ዳበሳን በመታደላቸው!
አሏህም ይኸው እድያ በሁሉም ዘመን የማይቋረጥ እንዲሆን፣ወደ’ሳቸው ፍቅር መጠጊያ ትልቁን የቅርበት ገመድ የሆነውን ሰላዋትን ለዑመታቸው ከመስጠቱ። በረካው ማ’ድ የተደረገ የፍቅር፣የራሕመት ግብዣ ጥሪ ነው!
አላሁመሰሊ ወሰሊም ወባሪክ ኣላ ሰይዲና ሙሐመድ!💜

አባት ያህል ዋርካ ለሐገሩ ለቤቱ ሲለፋ የኖረው፣
ዛሬ ግን…በመጦሪያው ዘመን የማጣት ቅጣቱ በርትቶ ሰበረው።
እናት ያህል ዓለም ለልጇ ስትኳትን
የዕድሜ ጀንበር ሸሽቷት ዛሬ ወድቃ ብትቀር፣
ማን ይሁን ሚደርሰው ለ’ኛ ከ’ኛው በቀር።
Bejai Nerash Naiker
Link : https://web.facebook.com/vijai.naiker/posts/9169807963096730?comment_id=1143840440691572&cft[0]=AZXyZ_yn3OqnS187vrxUKgj8JO8Y_iFne-d-raRvTKkAQCEKd4EYz2vs3_ClLMLe12R-NZ6xurk-zwvkFOMdCu4_q2kxRgFEl3Pv9WwSXoL8dSZR0LqfBmxQRu0Y0UtBmcLuNPymhIHjkeqm1DqmxGGQsPQSpbrkJ9XxiOMvP6Qtntn__=R]-R

Facebook
Bejai Nerash Naiker
48ኛው Missiin 100k ለ Daniel Moti ነው። በድምጽ 50% በባለሙያ ዳኛ 50% የታየ ነው። እንኳን ደሥ አለህ። ዳኞች፣ተወዳዳሪዎች ፣ደጋፊዎች ምሥጋና ይግባችሁ።
ውድድር!
49ኛው mission 100k ተከፍቷል ተወዳደሩ። ውድድሩ እዚህ ነው ። daniel moti የሠራውን ግራፊክሥ በመጠቀም አራት...