#ዝምታ_ክብር_ያመጣል 💪 #ስራህ_ይናገር 🥰
( ✍️ አቤል ደመላሽ )
ለረጅም ጊዜያት ለሕይወቴ የጠቀመኝ አንድ ነገር ቢኖር በዝምታ ስራ በዝምታ ኑር የሚለው መርሄ ነው ። ለብዙ ሰዎች አንተነትህን ብቻ እየገለጥክ እና እኔ ይህ ነኝ እንዲህ አለኝ በዚህ ወጣሁ በዚህ ገባው የምትል ከሆነ እመነኝ ምንም ያሳካኸው ነገር የለም ማለት ነው...ለዚህ ነው አልሸጥ እንዳለ ዕቃ በሄድክበት የሚያስለፈልፍህ...ሁሌ ዝም በል በዝምታም ስራ አንተ ስላንተ አትናገር...ሁሌም ኑሮህን ብቻ ቀጥል...ዓላማህን ኑር...ሰዎች ጋር ለመታየት አትጣር...እመነኝ ያኔ ነፍስህ ደስተኛ ትሆናለች ። እኛ የምንፈልገው ድል ማድረግን ከሆነ ለምን እወቁልኝ እናበዛለን ። ለብዙ ሰዎች ግር የሚላቸው ነገር የኔ የዝምታ ሕይወት ነው ። ምንም መንገድን ብሄድ በዝምታ እጓዛለሁ...በዚያ ሲገምቱኝ በዚህ ነኝ...ምንም መንገዴ እወቁልኝ የለውም...ስለዚህ የኔ ድል በጊዜው አፍ አውጥቶ ያወራል ። ለዚህ ነው የሚያውቁህ ሰዎች እንዲገምቱህ ዕድል ስጣቸው በሕይወትህ ግን አስደንግጣቸው የሚባለው...ለዓመታት የጠቀመኝ ነገር ሰዎች እርምጃዬን እንጂ ሩጫዬን አለማወቃቸው ነው ። ዛሬም እላለሁ...በዝምታ ስራ...በዝምታ ኑር...ተራ አስተሳሰብ ካላቸው ጋር ወርደህ አትመካከር...እንደ ልጅ ከሚያስቡ የወተት ዘመን ላይ ካሉ ሰዎች ጋር አትወያይ...መልስም አትሰጣጥ...ወርደው ከሚያወርዱ ጋር አትዋል...ስትወድቅ ትተውክ ይሄዳሉና ጌታ ምን ይላል እንጂ ሰው ምን ይለኛል አትበል...ራስህን እና እግዚአብሔር የሚልህን ስማ...እመነኝ ይሄንን ስታደርግ የእግዚአብሔር ሞገስ እና ድል አድራጊ ሕይወት ያንተ ይሆናል ።
#እግዚአብሔር_ይባርካችሁ 🙏🥰
#ጥበብ_እና_ማስተዋል_ይብዛልን

tgoop.com/AbelDemelash1/1622
Create:
Last Update:

BY Abel Demelash - አቤል ደመላሽ
Share with your friend now:
tgoop.com/AbelDemelash1/1622