tgoop.com/Abumuaz01/1464
Last Update:
#ዙበይር_ደፍጦ_ሚስቱን_በጥፊ_መታት
#የት_አሉ_ሴቶቹ⁉️የት አሉ ወንዶቹስ⁉️
ማነው በአሁን ሰአት ራሱን ያዘጋጀ⁉️ ማነው ቤቱ የቻለው በእውነት⁉️ ማነው ያለፈውስ አልፏል የወደፊት ሂዎቴን አስተካክላለሁ ብሎ የቆረጠ⁉️
ማነው ቤቱን ከማያስፈልጉ እንግዶች የሸበበ⁉️ ማነው ከምር⁉️ኧረ ማነው⁉️
ራሴም ተጠያቂ ነኝ‼️
ዙበይር እና ባለቤቱ
تَزوَجَ الزُبَير بن العوَام - رَضِيَّ اللَّهُ عَنه —امرَأة اشتَرَطَت عَليه أن لا يَمنعَهَا مِن صَلاةِ العِشَاء فِي مَسجِدِ النَّبيُّ - صَلَّى اللَّهُ عَليه وسَلم
ዙበይር ኢብኑልዓዋም ረዲየሏሁ ዐንሁ ከነቢዩﷺ ዐለይሂ መስጊድ የዒሻ ሶላት እንዳከለክላት መስፈርት አርጋበት አጋባት
فَلمَّا أرَادَت أن تَخرُج إلى العِشَاءِ شَقَّ ذَلك عَلى الزُبَير ،
ከዚያም ወደ መስጊድ ልትወጣ ስትል ዙበይር ከበደበት
فَلمَّا رَأت ذَلك قَالت : مَا شِئتُ ، أتُرِيدُ أن تَمنَعنِي ؟!
እሷም የሱን ቅሬታ ስታይ የፈለኩትን መሆን እችላለሁ ልትከልክለኝ ትችላለህ⁉️በፍፁም አለችው
فَلمَّا عَيلَ صَبرُه خَرجت لَيلَة إلى العِشَاءِ فَسبَقَها الزُبَير فَقَعدَ لَهَا عَلى الطَرِيقِ مِن حَيثُ لا تَراه
فَلمَّا مَرَت جَلَسَ خَلفَهَا فَضَّرَبَ بِيَدِه عَلى عَجزِهَا ، فَنَفرَت مِن ذَلك ومَضَتَ
ትእግስቱ ሲፈታተነው ወደዒሻ ወጣችና ዙበይርም በመንገድ ላይ ቀድሟት ሳታየው ደፍጦ ጀርባዋ ላይ በጥፊ ጨብ አርጎ መታት ያኔ እሷም በርግጋ ሄደች
فَلمَّا كَانت الليلَة المُقبِلَة سَمِعَت الأذَان فَلم تَتَحرك
በቀጣዩ ለሊት አዛን እየሰማች ምንም ሳትንቀሳቀስ ቀረች
فقَال لهَا الزُبَير :مَا لَكِ ؟! هَذا الأذَان قَد جَاء !
ዙበይርም ምን ሆንሽ ይሄው አዛን ተባለኮ አላት
فَقَالت :واللَّه ، لَقد فَسَدَ النَّاسُ فِي هَذا الزمَان.
በጌታዬ ይሁንብኝ በእርግጥ በአሁኑ ሰአት ሰዎች ተበላሽተዋል አለች
[ التَمهِيد || ٢٣ / ٤٠٦ ]
ወሏሂ ተገረሚ እህቴ አስተውይበት እውነት አንች ከሚመለከቱሽ ሸሪዓ ከፈቀደለሽ ወንዶች ውጭ ያላስፈላጊ ነገር በሶሻል ሚዲያ አታወሪም⁉️
መቶ በላይ ደንበኛ የሉሺም⁉️አበሉገሌ የአኺራ ወንድሜ ነው ለአሏህ ስል እወደዋለሁ ግን ስለማይፈቀድልኝ በኮንታክቱ ገብቼ አረብሸውም ብለሽ ያስቀመጥሺው የሱና ወንድም ይኖርሻል⁉️ ወዳ ወዲህ ሳትይ ይኖርሻል ወይ⁉️መልሱን ከልብሽ ዱቅ አሏህን ታዛቢ አድርገሽ።
አንተስ ወንድሜ ራስህን እንዴት አየህው⁉️ እውነት እንደ ዙበይር በሚስትህ ላይ ክትትልህ የጠነከረ ነው⁉️
ያናገሩህን የሶሻል ሚዲያ አዳኝ ሴቶችን ለመቋቋምና ለመሸሽ ዝግጁ ሁነሃል⁉️
ሁላችንም ከዚህ በፊት ጠንካራ ካልሆን አሁን ቆርጠን እንነሳ እንወስን።
ጥንቅር በአቡ ሙዓዝ
www.tgoop.com/abumuazhusenedris
BY [የገራዶ ደዕዋ]በአቡ ሙዓዝ/አቡ ሰኒያ]
Share with your friend now:
tgoop.com/Abumuaz01/1464