tgoop.com/Abumuaz01/1480
Last Update:
ሁሌ ማዘን ሁሌ ትካዜ!!
በጥምቧ ዘረኝነት ሳቢያ የቡዙ ሰዎች ሂዎች እንደ ጉንዳን እየረገፉ ነው
አሁንም ከበዚህ በፊቱ የባሰ የታፍኖ መወሰድና መገደል ዘመቻው እንደቀጠለ ነው
ወለጋ ነቀምት ላይ ከ 3ቀን በፊት አንድ የሱና ወንድማችን የ 3 ልጆች አባት በኦነጎች ታፍኖ ከህፃን ልጁ ተነጥሎ ተወሰደ!!
የሚገርመው ይሄ ወንድም የዛሬ አመት የተውልድ ሰፈሩ አቤ ደንጎሮ ወረዳ ላይ ታፍኖ ከ 5 ወር በላይ ታስሮ ተለቋል
የዛሬው ግን የመጨረሻ የሂዎት መቀፀፍ መልክት ውስጥ ነው ያስገቡት
የመጀመሪያ ልጁ ከ 11 አመት በላይ በተለያዩ ህመሞች ውስጥ የሚኖር ሲሆን ሳይሰለቹ በትንሹ በ 2 ወር አንድ ጊዜ በአመት 6 ጊዜ ከፍተኛ ህክምና እያደረጉለት ነው የሚኖሩት
ከዚህ አኳያ አድስ አበባ የሚከታተሉለትን ህክምና መድኃኒት ስላለቀበት በቀጠሮው መሰረት ልጁን ይዞ ሂዶ ቸክ አስደርጎ ሲመለስ
ነቀምቴ አልጋ አድሮ ያጣውን መድኃኒት ገዝቶ ወደ አንገር ጉትን በጧት ተሳፍሮ ሲሄድ መንገድ ላይ አስቁመው አማረኛ ተናጋሪዎቹን በመምረጥ ከሌሎች እኛ ያማናቃቸው አማረኛ ተናጋሪዎች ጋር አፍነው ወስደዋቸዋል።
ይባስ ልብ የሚያደማቸው ነገር እነሱ ታፍነው ሲያዙ ህፃኑን ልጅ ሌሎች ሰዎች በእግራቸው ውስጥ በማስገባት ሸሽገው ለመስኪኗ እናቱ አብቅተውታል
የሚገርመው ነገር ልጁ አባቱን ሲያስታውስ በእንባ እየረጬ ሰዎችን ማናገር አለመቻሉ ነው
ያረብ ህዝባችን ከዘረኝነት አውጣልን ለግፈኞችም ቀን አውጣላቸው።
www.tgoop.com/Abumuaz01
www.tgoop.com/Abumuaz01
BY [የገራዶ ደዕዋ]በአቡ ሙዓዝ/አቡ ሰኒያ]
Share with your friend now:
tgoop.com/Abumuaz01/1480