ANDEMNET Telegram 13484
#የእመቤታችን_የስደት_ታሪክ_ክፍል_1

#ርዕስ ፦ የእመቤታችን ልደትና ስደት

➯እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደችው በደብረ ሊባኖስ ተራራ ነው:: ድንግል ማርያም በእናቷ በሐና ማሕፀን ከተጸነሰችበት ቀን ጀምሮ የተለያዩ ተአምራትን ታደርግ ነበር። በማሕፀን ሳለች ካደረገቻቸው ተአምራት ሁለቱ የሚከተሉት ናቸው፡፡

➯ - በአንደኛው ዓይኗ ማየት የተሳናት ቤርሳቤህ የተባለች የሐና አክስት ጐረ ቤት ነበረች። እመቤታችንን ቅድስት ድንግል ማርያምን የጸነሰችውን የሐናን አካል በእጅዋ ነክታ /ዳብሳ/ እጅዋን መልሳ ማየት የተሳነውን ዓይኗን በነካችው ጊዜ ቦግ ብሎ በራላት፡፡ ይህ አንደኛው ተአምር ሲሆን።

➯ - ሁለተኛው ደግሞ እንደሚከተለው ነው፡፡ የሐና የአጐቷ ልጅ የሚሆን ሳምናስ የተባለ ሰው ሞተ፡፡ ሐና ለልቅሶ ተጠራች። ሐና ከሞተው ሰው ቤት በገባች ጊዜ ጥላዋ በሞተው ሰው ላይ ወደቀበት። የሞተው ሰውም ሕያው ሆኖ ተነስቶ እንዲህ አለ "«ኦ እሙ ለፀሐየ ጽድቅ ለዘገብረ ሰማየ ወምድረ» ሰማይን እና ምድርን የፈጠረ ጌታን የምትወልድ የቅድስት ድንግል ማርያም እናት የሆንሽ ሐና ሆይ ሰላምታ ይገባሻል፡፡" ለልቅሶ የተሰበሰቡት እስራኤላውያን ይህን ተአምር አይተው በቅንዓት ተቃጠሉ፡፡

➯ኢያቄም እና ሐና የአምላክ እናት ቅድስት ድንግል ማርያምን እንደሚወልዱ ባያምኑም እንኳ አንድ ተአምረኛ ልጅ እንደሚወልዱ ገምተዋል። ቀናተኞች እስራኤላውያን እንዲህ አሉ ከዚህ በፊት ከነገደ ይሁዳ የተወለዱ እነዳዊት እነሰሎሞን በእኛ ላይ ነግሠው አርባ አርባ ዓመት ገዝተውን ነበር። ዛሬም ከኢያቄም እና ከሐና የሚወለደው እኛን ሊገዛ ይችላል። ስለዚህ ተአምረኛውን ልጃቸውን ከመውለዳቸው በፊት ኢያቄምን እና ሐናን እንግደላቸው በማለት መከሩ።

➯የእግዚአብሔር መልአክ ወርዶ ኢያቄምን እና ሐናን ይህንን አገር ለቃችሁ ወደ ደብረ ሊባኖስ ሂዱ አላቸው:: ኢያቄም እና ሐና ወደ ደብረ ሊባኖስ ተሰደዱ፡፡ በስደት ላይ እያሉ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ሊባኖስ ተወለደች። ከወላዶቿ ጋር ሦስት ዓመት ተቀመጠች። ከዚህ በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ተወሰደች። በቤተመቅደስ 12 ዓመት ኖረች። የ15 ዓመት ልጅ ስትሆን ሽማግሌው ዮሴፍ ይጠብቃት ዘንድ ወደ ዮሴፍ ቤት ሄደች። በዮሴፍ ቤት ሳለች የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶን በመንፈስ ቅዱስ ጸነሰችና በቤተ ልሔም ወለደች። ብዙ መከራና ሥቃይንም ተቀበለች፤ የአባቷ ዕጣ ፋንታ ደረሰባት።

➯የእመቤታችን ወላጆች የኢያቄም እና ሐና በማሕፀን ሳለች ሙት ያስነሳችላቸውን ልጃቸውን ለመውለድ ወደ ደብረ ሊባኖስ እንደተሰደዱ ሁሉ ቅድስት ድንግል ማርያምም የሰማይና የምድር ፈጣሪን ኢየሱስ ክርስቶስን ስለወለደች ወደ ግብፅ ተሰደደች

➯ኢያቄምና ሐና ልጃቸው በማሕፀን ተምራትን ስለአደረገች ከቀናተኞች ጐረቤቶቻቸው ዓይን ለመራቅ ነበር የተሰደዱት፡፡

➯እመቤታችን ደግሞ ልጅዋ በሰባሰገል አንደበት የአይሁድ ንጉሥ ስለተባለ ከቀናተኛው ከሄሮድስ ዓይን ለመሠወር ስደተኛ ሆነች። ከዮሴፍ እና ከሰሎሜ ጋር ሀገር ለሀገር ተንከራተተች

➯እንደ ዛሬው የፖለቲካ ስደተኛ በአውሮፕላን፣ በመኪና ወይም በባቡር አይደለም የተሰደደችው። በእሾህ እና ድንጋይ እግሮቿ እየደሙ ቀን በፀሐይ ፊቷ እየተቃጠለ ሌሊት በብርድና በውርጭ ቆዳዋ እየተሰበሰበ በረሃብ እና በጥም ውስጧ እየተጐዳ መራራውን በመከራ ጸዋ እየጠጣች ሦስት ዓመት በመንፈስ ኖራለች።

#ክፍል_ሁለት_ይቀጥላል......

@AndEmnet

tgoop.com/AndEmnet/13484
Create:
Last Update:

BY "፩ እምነት" ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ Channel

Share with your friend now:
tgoop.com/AndEmnet/13484

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

More>> Polls While some crypto traders move toward screaming as a coping mechanism, many mental health experts have argued that “scream therapy” is pseudoscience. Scientific research or no, it obviously feels good. To view your bio, click the Menu icon and select “View channel info.” Done! Now you’re the proud owner of a Telegram channel. The next step is to set up and customize your channel.
from us

Telegram "፩ እምነት" ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ Channel
FROM American