tgoop.com/AndEmnet/13573
Last Update:
#ቅዱሳን_ያዕቆብ_ወዮሐንስ (ስንክሳር)
➯በዚህችም ቀን ያዕቆብና የሀገረ ፋርስ ኤጲስቆጶስ ዮሐንስ የሐርመዝ ልጅ በሆነ በፋርስ ንጉሥ በሳቦር እጅ በሰማዕትነት አረፉ።
➯አሁን ደግሞ ወደ 4ኛው መቶ ክ/ዘመን ተመልሰን ወደ ምድረ ፋርስ (ኢራን) ወርደን ቅዱሳንን እናዘክር። እነዚህ ቅዱሳንም በሃገረ ፋርስ (ኢራን) በመንግስተ ሳቦር ዘመን የነበሩ አበው ናቸው። ሳቦር ማለት ጸሐይንና እሳትን የሚያመልክና እጅግ ጨካኝ የነበረ ንጉሥ ነው።
➯ቅዱሳኑ ያዕቆብና ዮሐንስ የሐዋርያትን ስም ብቻ ሳይሆን ግብራቸውን ቅድስናቸውንም የያዙ ነበሩ። ዘመኑ ዘመነ ሰማዕታት ባይሆንም ፋርስ ግን በዚህ ዘመንም ለክርስቲያኖች የግፍ ከተማ ነበረች።
➯ከቅዱስ ጊዮርጊስ እስከ ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ ከቅዱስ መርምሕናም እስከ ቅዱስ ኮቶሎስ ሰማዕትነትን የተቀበሉት በዚህችው ሃገር ውስጥ ነው። ቅዱሳን ያዕቆብና ዮሐንስም ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን በልኩ ተምረው መጻሕፍትንም ተረድተው ለክህነት ተመርጠዋል።
➯በኋላም ቤተ ክርስትያን "ይገባቹሃል" ስትል ዻዻሳት አድርጋ ሾመቻቸው:: እነርሱም አላሳፈሯትም። የክርስቶስን መንጋ እያስተማሩ እየናዘዙ ጠበቁላት። ንጉሡ ሳቦር ግን ሕዝቡን ለፀለሐይና ለእሳት ሊያሰግድ ላደረገው ጥረት እንቅፋት ሁነውበታልና ጠላቸው።
➯በወታደሮቹ አስይዞም በፍርድ አደባባይ አቆማቸው። ሕዝቡን በአዋጅ ጠርቶ። አስፈሪ እሳት አስነድዶ "ሕዝቡ ለፀሐይ እንዲሰግድ እዘዙ" ቢላቸው "እንቢ" አሉት።
➯ከነ ልብሳቸው አንስተው ወደ እሳቱ ወረወሯቸው። ቅዱሳኑም በመከራው (በነደደው እሳት) መካከል ሆነው ለሕዝቡ ተናገሩ። "አምላክ አንድ እግዚአብሔር ነውና እንዲህ በሃይማኖታችሁ ጽኑ" አሏቸው። እሳቱም አቃጥሎ ገድሏቸው የክብርን አክሊል ተቀዳጁ።
BY "፩ እምነት" ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ Channel
Share with your friend now:
tgoop.com/AndEmnet/13573