Warning: Undefined array key 0 in /var/www/tgoop/function.php on line 65

Warning: Trying to access array offset on value of type null in /var/www/tgoop/function.php on line 65
- Telegram Web
Telegram Web
Forwarded from 💠ኢዮራም ፕሮሞሽን💠
📷 እርግጠኛ ነኝ ፕሮፍይሎን ለመቀየር ፈልገው ፕሮፍይል የሚያደርጉት ጠፍቶ  ተቸግረው ያውቃሉ።

የናንተን ችግር ለመፍታት በአይነቱ ለየት ያለ አዲስ መንፈሳዊ ቻናል ይዘንላችሁ መተናል ከናንተ የሚጠበቀው ከታች ባለው ሊንክ join ማድረግ ብቻ ነው👇👇👇👇👇👇📷

https://www.tgoop.com/addlist/gpX29GzfGs43MWE0
#ዝክረ_ቅዱሳን_ህዳር_1/፩ (ስንክሳር)

እንኳን ለጻድቁ ለኢትዮጵያ ንጉሥ #ለንጉሥ_ነአኩቶ_ለአብ መታሰቢያ፣ እንዲሁም #ለቅዱሳን_መክሲሞስ#ማንፍዮስ#ፊቅጦር እና #ፊልጶስ በሰማዕትነት ላረፉበት ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን።

"በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።"

#ቅዱስ_ነአኩቶ_ለአብ_ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮጽያ)

➯ህዳር አንድ በዚችም ቀን የጻድቁ የኢትዮጵያ ንጉሥ የነአኩቶ ለአብ መታሰቢያው።

➯ሃገራችን ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ ቅድስና ያላቸው ቅዱሳን ባለቤት ናት። በዘመኑ ያለን ወጣቶችም ሆነ ጎልማሶች ከቤተ ክርስቲያንና ከቅድስና ሕይወት ለምን እንደራቅን ስንጠየቅ ከምንደረድራቸው ምክንያቶች አንዱ ሥራችን ነው።

➯ነገር ግን ሥራው በራሱ ኃጢአት እስካልሆነ ድረስ በየትኛውም የሥራ ዘርፍ ቢሆን ቅድስናን ማስጠበቅ እንደሚቻል አበው አሳይተውናል። ቅዱስ ነአኩቶ ለአብም ከእነዚህ ቅዱሳን አንዱ ነው።

➯እርሱ ንጉሥ ነው። ግን ገዳማዊ ሕይወትን በቤተ መንግስቱ ውስጥ ያሳየ ጻድቅ ነው።
➯ሁሉ በእጁ ነው። እርሱ ግን ንጹሕና ድንግል ነው።
➯እርሱ የጦር መሪ ነው። ግን በእጁ ደም አልፈሰሰም።
➯እርሱን "ወደድንህ ሞትንልህ" የሚሉ ብዙ ሰዎች በአካባቢው ነበሩት። ለእርሱ ግን ፍቅር ማለት ክርስቶስ ነበር።
➯የሃገር መሪ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት እንደ መሆኑ እጅግ ባተሌ (busy) ነው። ግን ደግሞ ለክርስትናው ጊዜ ያጣ ሰው አልነበረም።

➯እኛ ቤተ ክርስቲያንን "በሐኪ" ለማለት (ለመሳለም) እንኳ "ጊዜ የለኝም" ስንል እርሱ ግን አብያተ ክርስቲያናትን ይፈለፍል፣ ያንጽ፣ በክህነቱ ያገለግል፣ ማዕጠንት ያጥን፣ ለረጅም ሰዓትም ይጸልይ ነበር።

➯እኛ "ሥራ ውያለሁና ደክሞኛል" ብለን ከስግደት ስንርቅ እርሱ ግን ንጉሥ ሆኖ ሳለ ...ጦር በፊት በኋላ በቀኝና በግራ ተክሎ ይሰግድ ስለ ነበር ደሙ እንደ ውኃ በምድር ላይ ፈሷል። ይህንን ሁሉ ያደረገው ቅዱሱ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት አፄ ነአኩቶ ለአብ ነው።

ለመሆኑ ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ ማን ነው?

➯ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ በዛግዌ ሥርወ መንግስት ከነገሡ 11 ነገሥታት አንዱ ሲሆን ከመጨረሻውም ሁለተኛ ነው። እርሱን በ12ኛው መቶ ክ/ዘመን የወለዱት ቅዱሱ ንጉሥ ሐርቤ (ገብረ ማርያም) እና መርኬዛ ናቸው። ዘመኑ ቅድስና በላስታ ዙሪያ የመላበት በመሆኑ ቅዱስ ሐርቤ ከመመነኑ በፊት ነበር ነአኩቶ ለአብን የወለደው።

➯እናቱ መርኬዛ እርሱን ልትወልድ ምጥ ተይዛ ሳለ ጀሮዋ ቅዳሴን ይሰማ ነበር። ቅዳሴው ሲጀመር የጀመራት ምጥ ድርገት ሲወርዱ (ሥጋ ወደሙ ሲሰጥ) ተፈታላትና ልጇን ተገላገለች። ሕጻኑን አንስታ ስትታቀፈው ዲያቆኑ ማቁረቡን ፈጽሞ "ነአኩቶ" እያለ ሲዞር ሰማችው።

➯እዚያው ላይም "ነአኩቶ ለአብ" (አብን እናመስግነው) ስትል ስም አወጣችለት። ወዲያው ግን አባቱ ቅዱስ ሐርቤ መንግስቱን ለቅዱስ ላሊበላ ሰጥቶ በርሃ በመግባቱ ቅዱሱ ሕጻን ወደ አጐቱ ላሊበላ ቤተ መንግስት ውስጥ ገባ።

➯የቅዱስ ላሊበላ ቤት ደግሞ በቅድስና ያጌጠ ነውና ከርሱና ከሚስቱ (ቅድስት መስቀል ክብራ) ሕጻኑ ነአኩቶ ለአብ ምናኔና ፍቅረ ክርስቶስን ተማረ። በዘመኑ ብዙ ሊቃውንት ስለ ነበሩ ቅዱሳት መጻሕፍትን በደንብ አጠና። ክህነት ተቀብሎ ቤተ ክርስቲያንን ሲያገለግልም እድሜው 30 ደረሰ።

➯በወቅቱ ቅዱስ ላሊበላና ባለቤቱ መስቀል ክብራ ልጃቸው ይትባረክ እያለ ንግሥናቸውን ለቅዱስ ነአኩቶ ለአብ አወረሱ። ቅዱሱ ነአኩቶ ለአብም ምን እንደሚሠራ ሲያስብ አንድ ነገር ተገለጠለት። ቤተ መንግስቱን እንደሚገባ ካደራጀ በኋላ በቤት ውስጥ አንድ ጉድጓድን በቁመቱ ልክ አስቆፈረ።

➯በውስጡም በ4 አቅጣጫ ጦሮችን ተከለባቸው። ድንግል ካህን ነበረና ቀን ቀን ሃገር ሲያስተዳድር ቅዳሴ ሲቀድስ በጾም ይውላል። ሌሊት ደግሞ ወዳስቆፈረው ቦታ ገብቶ ያለማቋረጥ እየጸለየ ይሰግዳል።

➯ወደ ምድር ሲሰግድ በፊቱ ያለው ጦር ይወጋዋል። ቀና ሲል ደግሞ የጀርባው ይቀበለዋል። እንዲህ እያለ የፈጣሪውን ሕማማት ይካፈላል። በተለይ ዐርብ ዐርብ ሲሆን ደሙ፣ እንባውና ላበቱ ተቀላቅሎ ይፈስ ነበር። እርሱ መስቀሉን ተሸክሞ ጌታውን ይከተል ዘንድ መርጧልና።

➯ከተጋድሎው ጐን ለጐን ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ አብያተ ክርስቲያናትንም ያንጽ ነበር። በተለይ በ1211 አካባቢ ያነጻት አሸተን ማርያም ልዩ ናት። እርሷን ካነጸ በኋላ ከቤተ መንግስቱ በደመና ሠረገላ ተጭኖ እየሔደ ያጥናት ይቀድስባትም ነበር።

➯ታዲያ አንድ ቀን አጥኖ ከቤተ መቅደስ ሲወጣ ብዙ ሥውራን ቅዱሳን መቅደሱን ከበው ተመለከተ። እርሱም "ወገኖቼ! ከወዴት መጣችሁ?" ቢላቸው "መዐዛ እጣንህን አሽተን መጣን" ሲሉ መለሱለት። በዚህ ምክንያትም እስከ ዛሬ ድረስ "አሽተን (አሸተን) ማርያም" ስትባል ትኖራለች።

➯ዛሬ ታቦቱ ያለበት ገዳሙም በእርሱ የታነጸ ሲሆን እጅግ ተአምረኛ ቦታ ነው። ቅዱስ ነአኩቶ ለአብ የነገሠ በ30 ዓመቱ ነው። ለ40 ዓመታት በእንዲህ ያለ ቅድስና ኑሮ 70 ዓመት ሞላው። በዚህ ጊዜም ለስም አጠራሩ ጌትነት ይሁንና መድኃኒታችን ክርስቶስ ወደ እርሱ ዘንድ መጣ። ሰላምታንም ሰጠው።

➯"ወዳጄ ነአኩቶ ለአብ! አንተ ስለ እኔ ፍቅር ለ40 ዓመታት መከራን ተቀብለሃልና ሞት አያገኝህም። ክፍልህ ከነ ኤልያስ ጋር ነውና። የሚያከብርህን አከብረዋለሁ። ደጅህን የሳመውን፣ ይህ ቢያቅተው በሩቁ ሆኖ በአድናቆት የተመኘህን፣ መታሰቢያህን ያደረገውን ሁሉ እምርልሃለሁ" አለው።

➯ቀጥሎም "ይሕች ቤት አንተ ስትደማ እንደኖርክባት እርሷም እስከ ምጽዓት ድረስ ለመታሰቢያህ ስትደማ ትኑር" አለው። እነሆ ዛሬም ድረስ ከመቅደሱ ጠበል ይንጠበጠባል። ለዚህም ደግሞ እኛ ኃጥአን ምስክሮች ነን። ሳይገባን የቅዱሱን ደጅ ተመልክተናልና።

➯ቅዱስ ነአኩቶ ለአብም የዚህን ዓለም ተጋድሎውን ፈጽሞ ወደ ብሔረ ሕያዋን መላእክት ወስደውታል። የተሰወረበትን ዕለት ስንክሳር ሕዳር 1 ሲያደርገው አንዳንድ መዛግብት ደግሞ በ3 ነው ይላሉ። በዙፋኑም ላይ የአጐቱ የላሊበላ ልጅ አፄ ይትባረክ ተተክቷል።
#ቅዱሳን_መክሲሞስ_ማንፍዮስ_ፊቅጦር_ፊልጶስ (ስንክሳር)

➯ዳግመኛም በዚህች ቀን ከአፍራቅያ የሆኑ ቅዱሳን መክሲሞስማንፍዮስፊቅጦርናፊልጶስ በከሀዲው ንጉሥ በዳኬዎስ ዘመን በሰማዕትነት አረፉ።

➯በዚህም ከሀዲ ንጉሥ ዘመን ሰባቱ ደቂቅ ሦስት መቶ ሰባ ሁለት ዓመት አንቀላፍተው የነቁ ከእርሱ በሸሹ ጊዜ ነው። እሊህም ቅዱሳን መስተጋድላን ክብር ይግባውና ክርስቶስን ክዶ ክርስቲያኖችን ሲአሠቃይ በአዩት ጊዜ ሃይማኖታቸውን ግልጥ ያደርጉ ዘንድ በአንድ ምክር ተስማምተው በአንድነት ተሰብስበው ወደ ከሀዲው ንጉሥ ቀረቡ እኛ በእግዚአብሔር ልጅ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በግልጥ የምናምን ክርስቲያኖች ነን ለእርሱም እንሰግዳለን እናመልከዋለንም ብለው ጮኹ።

➯ይህ ከሀዲ ዳኬዎስም በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ ከላም ቆዳ በተሠራ ጅራፍ እንዲገርፉአቸው አዘዘ አንድ ጊዜም ሁለት ጊዜም ታላቅ ግርፋትን ገረፏቸው በእሳት በአጋሉትም ከብረት በተሠሩ በትሮች ደበደቧቸው።

➯ከዚህም በኋላ በበርኖስ እላቂ ጨርቅ ከመጻጻና ከጨው ነክረው ቊስላቸውን አሹአቸው የንጉሡንም ትእዛዝ ባልሰሙ ጊዜ ሥቃዩንም ፈርተው ከበጎ ምክራቸው ባልተመለሱ ጊዜ ቁጣን በማብዛት ጽኑዕ ሥቃይን እንዲአሠቃዩአቸው አዘዘ እንዲሁም አደረጉባቸው። ከዚያ የነበሩ ብዙ ሕዝብም ትዕግሥታቸውን በአዩ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምነው በሰማዕትነት ሞቱ በዚያንም ጊዜ ንጉሥ ራሶቻቸውን በሰይፍ እንዲቆርጧቸው አዘዘ እንደዚህም የምስክርነታቸውን ተጋድሎ ፈጽመው የሰማዕትነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ።

➯ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘለዓለሙ አሜን።

@AndEmnet #ስንክሳር ህዳር ፩/1 ቀን
Audio
#ንግስተ_ሰማያት_ወምድር

ንግስተ ሰማያት ወምድር ማርያም ድንግል(×፪)
ተፈጸመ(×፭) ማኅሌተ ጽጌ(×፪)

@AndEmnet መዝሙር
"፩ እምነት" ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ Channel
#የእመቤታችን_የስደት_ታሪክ_ክፍል_5 #ርዕስ ፦ ጉዞ ወደ ምድረ ግብፅ ➯እመቤታችን ዮሴፍ እና ሰሎሜ ወደ ምድረ ግብጽ ሲጓዙ ሦስት ቀን ጫካ ውስጥ ሰነበቱ። በጣም ተራቡ፣ ተጠሙ። በበረሃ በረሀብና በውሃ ጥም እንዳይሞቱ እመቤታችን ጸለየች። ወዲያው የተሠራ ማዕድ የተዘጋጀ ምግብ መጣላቸው በልተው ጠገቡ። ከዚህ በኋላ #ኢንፍሎን ወደተባለ አገር ሄዱና #ርግባዳ ከተባለ ሰው ቤት ተቀመጡ። ብዙ ሰዎች ዕውቀት…
#የእመቤታችን_የስደት_ታሪክ_ክፍል_6

#ርዕስየእመቤታችን ለቅሶ በወንዝ ማዶ

➯እመቤታችን ከዮሴፍ እና ከሰሎሜ ተለይታ ልጅዋን ይዛ ወንዝ ተሻግራ ብቻዋን ተቀመጠች። ከመከራዋ ብዛት የተነሣ በጣም አለቀሰች እንዲህም አለች፡፡ "ሞሳር እና ግብፅ ማደርያዬ ሆነዋል፡፡ ይሁዳን እና ቤተልሔምን የት አገኛቸዋለሁ፡፡ እኔ በተወለድኩበት ሀገር በደብረ ሊባኖስ የሚኖሩ ሰዎች ብፁዓን ናቸው። በኪስባር የሚኖሩ ሰዎች ሰውነቴን አስጨነቋት የንፍታሌም እና የዛብሎን ልጆች ባካችሁ ስለደረሰብኝ መከራ አልቅሱልኝ ተጨንቄአለሁና የገሊላ እና የቁሰጥንጥንያ ልጆች ልታዩኝ አይገባም?፡፡" ዕንባዋን እንደጐርፍ እያፈሰሰች አለቀሰች፡፡ ልቧ በኀዘን ተቃጠለ፡፡ ዮሴፍ ከሩቅ ሆኖ ይመለከታት ነበር፡፡ ሊያረጋጋት በሄደ ጊዜ "በእግዚአብሔር ስም ወደ እኔ አትምጣ" አለችው፡፡ በድንጋይ የተቀጠቀጠችውን እና በጅራፍ የተገረፈችውን ግርፋት ስታስብ መረጋጋት አልሆንላት አላት፡፡ በኀዘን ላይ ኀዘን በለቅሶ ላይ ለቅሶ ጨመረች፡፡

➯ዮሴፍም እጅግ ተበሳጨ ከእመቤታችን ጋር ከሚቀበለው መከራ በላይ የእመቤታችን አለመረጋጋት በብስጭቱ ላይ ብስጭት ጨመረበት በመከራው ላይ ሌላ መከራ ሆነበት፡፡ ትዕግሥቱን ጨረሰና መከራውን በሞት ለመገላገል አሰበ፡፡ ታንቆ ይሞት ዘንድ ገመድ ወስዶ በእንጨት ላይ አሠረና አንገቱን አስገባ። መልአክ ወርዶ ከዮሴፍ አንገት የገባውን ገመድ ቆረጠው፡፡

➯ዮሴፍንም እንዲህ አለው "የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ ለምን ትበሳጫለህ የሰማይ እና የምድር ፈጣሪ ጌታን የታቀፈች እመቤታችን ከዓይኖቿ ዕንባዋን ስታፈስ አታያትምን? ታንቀህ በመሞት ይህን ዓለም እና የወዲያኛውን ዓለም እንዳታጣ ታገሥ" አለው፡፡

➯መልአኩ ዮሴፍን ካረጋጋው በኋላ ወደ እመቤታችን ሄዶ ሰገደላትና ሰላምታ ካቀረበላት በኋላ እንዲህ አላት "የዳዊት ልጅ ማርያም ሆይ ይህን ያህል ኀዘን ለምን ታዝኛለሽ ይህ ሁሉ ድካምሽና ኀዘንሽ ይረሳል፡፡ ዮሴፍ ስለአንቺ እና ስለልጅሽ ቤቱን፣ ንብረቱን፣ ዘመዶቹን ትቶ በበረሃ እየተንከራተተ ነው ለምን አልረጋጋም ትይዋለሽ" ብሎ አረጋጋት፡፡ መልአኩ እመቤታችን ዮሴፍ እና ሰሎሜን አገናኝቷቸው ሄዱ ወደ ኢትዮጵያ ሄዱ፡፡


#ክፍል_ሰባት_ይቀጥላል......

@AndEmnet
"፩ እምነት" ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ Channel
#የእመቤታችን_የስደት_ታሪክ_ክፍል_6 #ርዕስ ፦ የእመቤታችን ለቅሶ በወንዝ ማዶ ➯እመቤታችን ከዮሴፍ እና ከሰሎሜ ተለይታ ልጅዋን ይዛ ወንዝ ተሻግራ ብቻዋን ተቀመጠች። ከመከራዋ ብዛት የተነሣ በጣም አለቀሰች እንዲህም አለች፡፡ "ሞሳር እና ግብፅ ማደርያዬ ሆነዋል፡፡ ይሁዳን እና ቤተልሔምን የት አገኛቸዋለሁ፡፡ እኔ በተወለድኩበት ሀገር በደብረ ሊባኖስ የሚኖሩ ሰዎች ብፁዓን ናቸው። በኪስባር የሚኖሩ ሰዎች…
#የእመቤታችን_የስደት_ታሪክ_ክፍል_7

#ርዕስጉዞ ከግብጽ ወደ ኢትዮጵያ

➯እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዮሴፍና ሰሎሜ በደመና ተጭነው ከግብጽ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ #ናግራን ከተባለ ሀገር ደረሱ፡፡ በናገራን ሳሉ ጌታ እንዲህ አለ "ከቀኝ ጐኔ የሚፈሰው ደሜ በብርሃናት አለቃ በዑራኤል እጅ ተቀድቶ በቅድሚያ በዚች በድንግልና ጸንሰሽ በድንግልና እንደወለድሽኝ አምነው የሚያከብሩሽ በእኔም የሚያምኑ ብዙ የተቀደሱ ሰዎች በዚች ሀገር ይወለዳሉ፡፡" ከናግራን ተነስተው ለትግራይ ትይዩ ከሚሆን #ሐማሴን ከሚባለው ሀገር ሲደርሱ በምሥራቅ በኩል ከፍተኛ ተራራ ተመለከቱና ወደ ተራራው ሄዱ፡፡ ጌታም በተራራው ላይ ሳሉ እናቱን እንዲህ አላት "ይቺ ተራራ ምስጋናሽ የሚነገርባት ቦታ ትሆናለች። የተራራውም ስም #ደብረ_ሃሌ_ሉያ ወይም #ደብረ_ዳሞ ይባላል፡፡" ትርጓሜውም የአምላክ ልጅ የመስቀሉ ቦታና የስሙ መገኛ ወይም አደባባይ ማለት ነው።

➯ከዚያም በኋላ ታቦተ ጽዮን ወደምትኖርበት ወደ #አክሱም ደረሱ። ታቦተ ጽዮን ባለችበት ቦታ ሳሉ #ባዚን የተባለው የአትዮጵያ ንጉሥ ታቦተ ጽዮንን ለመሳለም መጣ። የካህናቱ አለቃ #አኪን ለንጉሱ የኢሳይያስን መጽሐፍ አነበበለት፡፡ የተነበበውም የመጽሐፍ ክፍል "«ድንግል በድንግልና ጸንሳ በድንግልና ወንድልጅ ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች»" የሚል ነበር፡፡ ስደተኞቹ ግን ለንጉሡም ሆነ ለካህናቱ ሳይገልጡ የመጽሐፉን ቃል ከሰሙ በኋላ በደመና ተጭነው ወደ #ደብረ_ዐባይ ሄዱ። ጌታም እናቱን እንዲህ አላት "ይቺ ሀገር እንደአክሱም ለስምሽ መጠሪያ ርስት ትሁን በኋላ ዘመን በቀናች ሃይማኖት ጸንተው ሕጌን የሚያስተምሩ አንቺን የሚወዱ ሰዎች ይኖሩበታል" አላት።

➯ከዚያም በኋላ ከደብረ ዐባይ ተነስተው #ሐቅለ_ዋሊ ወደ ሚባለው ገዳም /#ወደ_ዋልድባ/ ሄዱ፡፡ በዋልድባ በረሃም ሳሉ በራባቸው ጊዜ ጌታ በዮሴፍ በትር የአንዱን ዕንጨት ስር ቆፈረ፡፡ 318 ስሮችን አወጣና ለእናቱ "ብይ" ብሎ ሰጣት፡፡ እናቱም "ይህን የሚመር እንጨት አልበላም" አለችው፡፡ ጌታም "በኋላ ዘመን ስምሽን የሚጠሩ አንቺን የሚያከብሩ ብዙ መናንያን ይህን እየበሉ በዚህ ቦታ ይኖራሉ፡፡ ዕንጨቱም የሚጣፍጥ ይሆንላቸዋል" አላት፡፡ ከዚህ በኋላ በደመና ተጭነው ከዋልድባ ወደ #ጣና የባሕር ወደብ ሄዱ። በጣና ደሴትም ደጋግ ሰዎች ተቀብለዋቸው 3 ወር ከ10 ቀን ተቀመጡ፡፡ የኢትዮጵያ ሰዎች በደስታ ተቀብለዋቸዋል እንደ ግብፃውያን አላሰቃዩአቸውም፡፡

➯በጥር አስራ ስምንት /18/ ቀን መልአኩ መጥቶ የሄሮድስን መሞት ነገራቸው ወደ ሀገራቸው ይመለሱ ዘንድ በደመና ከተጫኑ በኋላ ጌታ እናቱን እንዲህ አላት "ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙትን ተራራዎች ሁሉ ለስምሽ መታሰቢያ ይሆኑሽ ዘንድ አሥራት አድርጌ ሰጥቼሻለሁ፡፡" በጐጃም ውስጥ የሚገኙትን ተራራዎችን ሜዳዎችን ኮረብታዎችን ፣ በሸዋ ውስጥም የሚገኙትን ተራራዎችን ሜዳዎችን አሳያት። እመቤታችን ሁሉንም ቦታዎች እየተዘዋወረች እንድታይ ልጅዋን ጠየቀችው፡፡ ልጅዋም የሚመለሱበት ጊዜ እንደደረሰ ነገራት። በብሩህ ደመና ላይ ተቀምጠው በጐንደር ፡ በበጌምድር በወሎ ፡ በሐረርጌና ፡ በአሩሲ ፡ በሲዳሞና በባሌ ፡ በጉራጌ ፡ በከንፓታ ፡ በከፋና  በኤልባቡር ፡ በወለጋና በሌሎቹ ክፍላተ አህጉር እየተዘዋወሩ ተራራዎችን ወንዞችን አስጐበኛት የኢትዮጵያን ምድር ከጐበኙ በኋላ አህጉር እየተዘዋወሩ በደመና ተጭነው ጥር 29 ቀን ምድረ ግብፅ ደረሱ ኢትዮጵያ የገቡት በቅዱስ #ዑራኤል መሪነት ነው። ከግብጽ ወደ ኢትዮጵያ የመግባት ታሪክ በድርሳነ ዑራኤል ላይ በስፋት ተጽፏል።


#ክፍል_ስምንት_ይቀጥላል.....

@AndEmnet
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
"፩ እምነት" ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ Channel
#የእመቤታችን_የስደት_ታሪክ_ክፍል_7 #ርዕስ ፦ ጉዞ ከግብጽ ወደ ኢትዮጵያ ➯እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዮሴፍና ሰሎሜ በደመና ተጭነው ከግብጽ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ #ናግራን ከተባለ ሀገር ደረሱ፡፡ በናገራን ሳሉ ጌታ እንዲህ አለ "ከቀኝ ጐኔ የሚፈሰው ደሜ በብርሃናት አለቃ በዑራኤል እጅ ተቀድቶ በቅድሚያ በዚች በድንግልና ጸንሰሽ በድንግልና እንደወለድሽኝ አምነው የሚያከብሩሽ…
#የእመቤታችን_የስደት_ታሪክ_ክፍል_8 #የመጨረሻ_ክፍል

#ርዕስከግብፅ ወደ ኢየሩሳሌም መመለሳቸው #የመጨረሻ_ክፍል

➯እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዮሴፍ እና ሰሎሜ በስደት የኖሩት ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ነው። ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ከተፈጸመ በኋላ
ኢየሱስ ክርስቶስን ለመግደል ሲጥር የነበረው የገሊላው ንጉስ ሄሮድስ ሞተ። መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ግብፅ ሄደና የሄሮድስን ሞት ለእነዮሴፍ ነገራቸው፡፡ «ሄሮድስም ከሞተ በኋላ እነሆ የጌታ መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሙተዋልና ተነሣ ሕፃኑንና እናቱንም ይዘህ ወደ እስራኤል አገር ሂድ አለው» (ማቴ.2፥19-21)

➯ከዚህ በኋላ ከግብፅ ወደ እስራኤል ሀገር ለመሄድ ተነሡ፡፡ እመቤታችን በግብፅ የቆየችባቸውን ሀገሮች ተራራዎችን፣ ኮረብታዎችን፣ ጫካዎችን እና ሜዳዎችን ባረከቻቸው። ተራራዎችም ጫካዎችም ዕፀዋቱም ለእመቤታችን ሰገዱላት፡፡ በሰላም ወደ ሀገርሽ ግቢ እንደ ማለት ነው፡፡ እመቤታችን እነሱን በመባረክ እነሱም ለእመቤታችን በመስገድ ተሰናበቱ፡፡

➯እነዮሴፍ ከደብረ ‌ቁስቋም ወጥተው #ሞሳር ወደተባለ ሀገር ደረሱ፡፡ ከዚያም #መአልቃ ከሚባል ቦታ ደረሱና በጫካ ውስጥ አደሩ፡፡ ከዚህ በኋላ ከሞሳር ወጥተው በስደት እያሉ ጌታ ውሃ ወደ አፈለቀባት #መጠርያ ወደተባለች ሀገር ደረሱና ጌታ ባፈለቀው ውሃ ታጠቡ፡፡ ውሃይቱም የተባረከችና የተቀደሰች ውሃ ሆነች፡፡

➯ከዚህ በኋላ ወደ እስራኤል ሀገር ሲቀርቡ የሄሮድስ ልጅ አርኬላዎስ በአባቱ በሄሮድስ ፈንታ በይሁዳ እንደ ነገሠ ሰሙ፡፡ ዮሴፍ ይህን ዜና በሰማ ጊዜ እርሱም እንደአባቱ እኛን ለመግደል ፈልጎ ይሆናል ብሎ ፈራ፡፡ መልአኩ መጥቶ በሕልሙ ወደ ሀገርህ ወደገሊላ ግባ አትፍራ አለው፡፡ ዮሴፍ ሕፃኑንና እናቱንም ይዞ ገሊላ ገባ፡፡ ናዝሬት በምትባለው ከተማም ኖሩ። (ማቴ 2፥22-23)


➯የእመቤታችን የስደት ታሪክን የዳሰስንበት በዚው #ተፈጸመ የእመቤታችን በረከትና ረድኤት በሁላችን ይደር አሜን፡፡

                
#አዘጋጅ ፦ ሊቀ ትጉሃን ወንድወሰን ተገኝ የሰዋስዎ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ከፍተኛ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዝሙር

@AndEmnet
#ዝክረ_ቅዱሳን_ህዳር_3/፫ (ስንክሳር)

እንኳን ለቅዱሳን ሰማዕታት #ለአቡነ_መድኃኒነ_እግዚእ ለእረፍታቸው፡ #ለአቡነ_ፍሬ_ካህን ለእረፍታቸው፡ #ለቅዱስ_ኪርያቆስ ለእረፍታቸው፡ #ለአባ_አትናቴዎስና_ለእህቱ_ኢራኢ፡ ለእረፍታቸው እንዲሁም #ለቅዱስ_ዓምደ_ሚካኤል ለእረፍታቸው ዓመታዊ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን።

"በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።"

#አቡነ_መድኃኒነ_እግዚእ

➯መዘንጋታቸው እጅግ ከሚያስቆጭ ኢትዮጵያውያን አባቶች ትልቁን ሥፍራ እኒህ አባት ይወስዳሉ:: የማር ወለላን በሚያስንቅ ጣዕመ ሕይወታቸው ሃገራችንን ያጣፈጡ: ብርሃን ሆነው ብዙ ቅዱሳንን የለኮሱ ታላቅ ጻድቅ ናቸው::

➯አባ መድኃኒነ እግዚእ የተወለዱት በ13ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ትግራይ (አዲግራት) ውስጥ ነው:: ወላጆቻቸውም ቀሲስ ሰንበትና ሒሩተ ማርያም ይባላሉ:: በደግነትም እጅግ የታወቁ እንደ ነበሩ ገድላቸው ይናገራል:: "መድኃኒነ እግዚእ" ማለት "ጌታ መድኃኒታችን ነው" ማለት ነው::

➯ብዙ ጊዜም "ዘደብረ በንኮል - ሙራደ ቃል" እየተባሉ ይጠራሉ:: "ደብረ በንኮል" ማለት ትግራይ ውስጥ የሚገኝና ጻድቁ በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ያነጹት ገዳም ነው:: "ሙራደ ቃል" ደግሞ "የቃል (የምሥጢር) መውረጃ" እንደ ማለት ሲሆን በቦታው ሱባኤ የያዘ ሰው ልክ እንደ ቅዱስ ያሬድ ምሥጢር እንደሚገጥለት የሚጠቁም ስም ነው::

➯ጻድቁ መድኃኒነ እግዚእ በልጅነታቸው ከሊቁ ካህን አባታቸውና ከሌሎችም መምሕራን ተምረው: ምናኔን መርጠው ገዳም ገብተዋል:: በጾም: በጸሎትና በስግደት ተግተው ጸጋ እግዚአብሔር ሲሰጣቸው ወደ ደብረ በንኮል ሒደው ገዳም መሠረቱ::

➯በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ መካከለኛው ዘመን (በተለይ ከ13ኛው እስከ 15ኛው መቶ ክ/ዘመን ድረስ ያለው) የብርሃን ዘመን ይባላል:: ምክንያቱም ዘመኑ
➯ክርስትና ያበበበት::
➯መጻሕፍት የተደረሱበት::
➯ስብከተ ወንጌል የተስፋፋበት::
➯ገዳማዊ ሕይወት የሠመረበት ወቅት በመሆኑ ነው::

ለዚህ ትልቁ አስተዋጽኦ ደግሞ:-

➯አቡነ ተክለ ሃይማኖት::
➯አቡነ ኤዎስጣቴዎስ::
➯አባ ሰላማ ካልዕ::
➯አቡነ ያዕቆብ::
➯ቅዱሱ ንጉሥ ዘርዓ ያዕቆብ::
➯አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ::
➯አቡነ መድኃኒነ እግዚእን የመሰሉ አበው መነሳታቸው ነው::

በተጨማሪም:-

➯12ቱ ንቡራነ ዕድ::
➯7ቱ ከዋክብት::
➯47ቱ ከዋክብት::
➯5ቱ ከዋክብት የሚባሉ አበው አስተዋጽኦም ልዩ ነበር:: ከእነዚህ መካከልም የ7ቱ እና የ47ቱ ከዋክብት አስተማሪ: የአበው 3ቱ ሳሙኤሎች (ዘዋልድባ: ዘጣሬጣና ዘቆየጻ): የሌሎችም እልፍ አእላፍ ቅዱሳን አባት የሆኑት አባ መድኃኒነ እግዚእ የአንበሳውን ድርሻ ይወስዳሉ::

➯ጻድቁ ቅዱሳኑን ሰብስበው: አስተምረው: አመንኩሰው: መርቀው ሰደው: ሃገራችንን እንዲያበሩ በማድረጋቸው እንደ አባ ኢየሱስ ሞዐ እርሳቸውም "ወላዴ አእላፍ ቅዱሳን" ይባላሉ:: ታላቁ ጻድቅና ሰባኬ ወንጌል አባ ዓቢየ እግዚእም (ጐንደር ውስጥ እባብና ጅብ እንዳይጐዳ የገዘቱ አባት ናቸው) የእርሳቸው ደቀ መዝሙር ነበሩ ይባላል::

➯ጻድቁ መድኃኒነ እግዚእ በተትረፈረፈ የቅድስና ሕይወታቸው ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል:: አራዊትን ገዝተዋል: በአንበሳ ጀርባ ላይ እቃ ጭነዋል:: ከረዥም የተጋድሎ ሕይወት በሁዋላም ኅዳር 3 ቀን ዐርፈዋል:: እድሜአቸውም 180 ነው::

➯"መድኃኒነ እግዚእ አቡነ መስተጋድል::
ምንኩስናሁ ምዑዝ ከመ ኮል::
በመንፈሰ ጸጋ ክሉል::" (መጽሐፈ ሰዓታት)

➯"ተአምረ ኃይልከ አባ መድኃኒነ እግዚእ አቡነ::
እም አፈ ዜናዊ ሰማዕነ:: ወበዓይነ ሥጋ ርኢነ::
መንክርኬ አእላፈ ቤትከ ንሕነ::
ባሕቱ በዝ ተአምሪከ ርድአነ::
ለሰይፈ አርዕድ ንጉሥ ዘወሀብኮ ኪዳነ::
ከመ ረድኤቱ ታፍጥን ጊዜ ጸብዕ ኮነ::" (አርኬ)
#አቡነ_ፍሬ_ካህን (ስንክሳር)

➯ዳግመኛም በዚህች ቀን አቡነ ፍሬ ካህን አረፉ።

➯ጻድቁን በመጀመሪያ ከጎጃም ተነሥተው በታዘዘ መልአክ መሪነት ትግራይ ደብረ በንኮል አቡነ መድኃኒነ እግዚእ ገዳም ሄደው መንነው መነኮሱ፡፡ ጻድቁ ስድስት ክንፍ የተሰጣቸው ሲሆኑ በታላቅ መንፈሳዊ ተጋድሎ ይታወቃሉ፡፡ አቡነ ፍሬ ካህን ወንጌልን ሲሰብኩ ሙታንን እያስነሡ በሲኦል ውስጥ ስላለው መከራና ሥቃይ እንዲመሰክሩ ያደርጓቸው ነበር፡፡ ጻድቁ ሐይዳ ገዳም ታቦት ተቀርጾላቸው ገድል የተጻፈላቸው ቢሆንም ሙሉ ገድላቸው ታትሞ ለምእመኑ አልተዳረሰም፡፡ አቡነ ቶማስ ካረፉ በኋላ አቡነ ፍሬ ካህን ገዳማቸውን ተረክበው በጽድቅ መንገድ መነኮሳቱን አስተዳድረዋል፡፡

➯አቡነ ፍሬ ካህን አፈር ከኢየሩሳሌም አምጥተው ዋልድባ ሲደርሱ መነኮሳቱ "ገዳሙን በአህያ አታስረግጥ" ቢሏቸው አህዮቹን ክንፍ አውጥተው እንዲበሩ አድርገዋቸዋል፡፡

➯አባታችን ሽሬ ደብረ ሐይዳ አቡነ ፍሬ ካህን የተባለ ትልቅ ገዳም አላቸው፡፡ ገዳሙ ከአቡነ ቶማስ ዘሐይዳ ገዳም ጋር አንድ ነው፡፡ ወደዚህ ገዳም ውስጥ ሥጋና ቅቤ ተበልቶም ሆነ ተይዞ መውጣት ፈጽሞ አይቻልም፡፡ አልታየሁም ተብሎ በድብቅ ሥጋ ተይዞ ቢገባ ሥጋው ይተላል፡፡ ሥጋና ቅቤ የበላ ሰውም ዕለቱን በድፍረት ወደ ገዳሙ ቢገባ ሆዱ በኃይል ይነፋል በዚህም ይታወቅበታል፡፡ ከብቶችም ቢሆኑ ወደ ገዳሙ አይወጡም፣ ማንም ሳይመልሳቸው ራሳቸው ይመለሳሉ፡፡ የአቡነ ፍሬ ካህን ዕረፍታቸው ኅዳር 3 ነው፡፡
#ቅዱስ_አባት_ኪርያቆስ (ስንክሳር)

➯በዚህች ቀን ከቆሮንቶስ አገር ቅዱስ አባት ኪርያቆስ አረፈ።

➯የዚህም አባት ወላጆቹ ሃይማኖታቸው የቀና የከበሩ ናቸው የቤተክርስቲያንን ትምህርትና የቀናች ሃይማኖትን አስተማሩት ከዚህም በኋላ የቆሮንቶስ አገር ኤጲስቆጶስ ወደ ሆነ ወደ አባ ጴጥሮስ አቀረቡት እርሱም በላዩ ጸልዮ አናጒንስጢስነት ሾመው ለአባ ጴጥሮስም የወንድሙ ልጅ ነው።

➯ከዚህም በኋላ ዘወትር መጻሕፍትን የሚያነብ የቃላቸውንም ትርጓሜ የሚመረምር የቤተ ክርስቲያንንም ሥርዓቷንና ሕጓን የሚያጸና ሆነ በትምህርቱና በእውቀቱም ከብዙዎች ከፍ ከፍ አለ ኤጲስቆጶሱም መጻሕፍት ማንበብን እንዳያቋርጥ ያዝዘው ነበር እርሱም ለሕዝቡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለኤጲስቆጶሱም በቤቱ ያነብለት ነበር። መጻሕፍትንም በሚያነብለት ጊዜ ኤጲስቆጶሱ በእርሱ ደስ ይለው ነበርና።

➯ዕድሜውም ዐሥራ ስምንት ዓመት በሆነ ጊዜ ሚስትን ያጩለት ዘንድ ወላጆቹ ጠየቁት እርሱ ግን ይህን አልወደደም ግን ከገዳማት ወዳንዱ ይሔድ ዘንድ እንዲአሰናብቱት ወላጆቹን ለመናቸው ከዚያም በኋላ አዘውትሮ ወደ ገዳማት የሚሄድና ወደ ወላጆቹ የሚመለስ ሆነ። መመላለሱም ከበዛ ዘንድ የከበረች የምንኲስናን ልብስ ሊለብስ ወዶ ወደ ኢየሩሳሌም ሔደ ከኢየሩሳሌሙ ኤጲስቆጶስ ከአባ ቄርሎስ ጋር ተገናኝቶ ስለ ምንኲስና ኀሳቡን ሁሉ ነገረው። እርሱም በጎ ሥራን ወደሃል አለው ታላቅ አባትም እንደሚሆንና በእርሱም የብዙዎች ነፍሳት ብሩሃን እንደሚሆኑ ትንቢት ተናገረለት።

➯ከዚህም በኋላ የመነኰሳት አባት ወደ ሆነ በፍልስጥዔም ወደ ሚኖር ወደ ክቡር አባ ሮማኖስ ላከው እርሱም በደስታ ተቀብሎ የምንኵስናን ልብስ አለበሰው። የምንኵስናንም ሥርዓት ያስተምረው ዘንድ የሰይጣንንም ተንኮል ያስረዳው ዘንድ በዚያው ገዳም ለሚኖር አንድ አረጋዊ ሰጠው። ከዚህም በኋላ በጾም በጸሎት በስግደት በመትጋት በታላቅ ድካም በቀንና በሌሊት በገድል ተጸምዶ በትዕግሥት በትሕትና በቅንነት ኖረ።

➯እግዚአብሔርም የመፈወስን ሀብት ሰጥቶት ወደርሱ የሚመጡትን በሽተኞች ሁሉ የሚፈውሳቸው ሆነ የትሩፋቱና የቅድስናውም ዜና በሁሉ ቦታ ተሰማ ። የኢየሩሳሌሙ ኤጲስቆጶስ አባ ቄርሎስም የክብር ባለቤት የሆነ መንፈስ ቅዱስን ስለ አቃለለ መቅዶንዮስ መቶ ሃምሳው ኤጲስቆጶሳት አንድነት ወደሚሰበሰቡበት ወደ ቊስጥንጥንያ በሚሔድ ጊዜ ይህን አባት ኪርያቆስን አባ ቄርሎስ ከእርሱ ጋር ወሰደው በላያቸው በአደረ መንፈስ ቅዱስ ስም ተከራክረው ከሀዲ መቅዶንዮስን ረቱት ከምእመናንም ለይተው አሳደዱት።

➯ከዚህም በኋላ በመልካም ሽምግልና እግዚአብሔርን አገልግሎ በሰላም አረፈ። ከዕረፍቱም በኋላ እግዚአብሔር ድንቆች የሆኑ ብዙ ተአምራትን ከሥጋው ገለጠ ከእርሳቸውም አንዱ ከኢየሩሳሌም ገዳማት በአንዱ ሥጋው ይኖራል። ከአረፈበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ዛሬ ሥጋው አልተለወጠም ወደ ኢየሩሳሌም የሚሔዱ ሁሉ ያዩታል እነርሱም በቅርብ ጊዜ እንዳረፈ ያስባሉ እርሱ ግን ያረፈው ለአኖሬዎስና ለአርቃዴዎስ አባታቸው በሆነ በታላቁ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ዘመን ነው።
#አባ_አትናቴዎስና_እኅቱ_ኢራኢ (ስንክሳር)

➯በዚችም ቀን አባ አትናቴዎስና እኅቱ ኢራኢ አረፉ። እሊህንም ቅዱሳን ከሀዲ ንጉሥ መክስምያኖስ ጽኑዕ የሆነ ሥቃይን አሠቃያቸው።

➯በማሠቃየትም በደከመ ጊዜ ዕራቁታቸውን ከጉድጓድ ጨመራቸው በላያቸውም የጒድጓዱን አፍ ዘጋ በውስጧም ነፍሳቸውን አሳለፉ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበሉ።
#ቅዱስ_ዓምደ_ሚካኤል (ስንክሳር)

➯በዚችም ቀን ለኢትዮጵያ ነገሥታት ለዘርዐ ያዕቆብ፣ ለበእደ ማርያም፣ ለእስክንድር የሠራዊት አለቃ የሆነ ቅዱስ ዓምደ ሚካኤል አረፈ።

➯የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም ገላውዴዎስ የእናቱም ስም ኤልሳቤጥ ነው እነርሱም በዚህ ዓለም ገንዘብ ይልቁንም በሃይማኖትና በበጎ ሥራ የበለጸጉ ናቸው። ይህንንም ቅዱስ በቅዱሳን አርባዕቱ እንስሳ በዓል ወለዱት ስሙንም ዓምደ ሚካኤል ብለው ሰየሙት።

➯ከተወለደም አንድ ዓመት ሲሆነው ከቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ከመንበሩ ከርሠ ሐመር ውስጥ ማንም ያየው ሳይኖር እየዳኸ ገብቶ ሦስት ቀን ሰነበተ ወላጆቹም እርሱ እንደሞተ ተጠራጥረው እያለቀሱለት ኖሩ።

➯ከዚህም በኋላ በሦስተኛው ቀን ቄሱ ሊዓጥን ገባ ዕጣንንም ሲፈልግ በከርሠ ሐመሩ ውስጥ ሕፃኑን በሕይወት አገኘው በበታቹም ምንም ምን ጉድፈት አልነበረም። ቄሱም ለወላጆቹ ነገራቸው እነርሱም እጅግ ደስ እያላቸው መጥተው ከዚያ ወሰዱት።

➯ከዚያንም ጊዜ ጀምሮ በጥበብና በዕውቀት አደገ ነገሥታት ገዥ እስከ አደረጉት ድረስ በቤት ውስጥ በሚሠራው ላይ ሁሉ አሠለጠኑት። እርሱም ለድኆች በፍርዱና በምጽዋቱ አባት ሆናቸው በገንዘቡም አብያተ ክርስቲያናትን ሁሉ አደሰ በዘመኑም ሰላም ሆነ በጾሙና በጸሎቱ በምጽዋቱም በቅዱሳንም የጸሎት ርዳታ በወዲያም በወዲህም አገሮችን የሚያጠፉ ጠላቶችንና ዐመፀኞች ጠፉ። ጠላቶችም ሁሉ ለነገሥታቱ ተገዙና ግብርን ገበሩ።

➯የዚህም ቅዱስ ዓምደ ሚካኤል ልቡ በእግዚአብሔር ፍቅር የታሠረ ነው በተጸለየበት ውኃ ሳይጠመቅና ሳይጠጣ አይመገብም ነበር ገንዘቡንም ሁሉ በምጽዋት ጨረሰ።

➯እግዚአብሔርም በጎ ሥራውን በአየ ጊዜ እንዲፈተን ፈቀደለት ዐመፀኞች ሰዎችም በእርሱ ላይ ተነሡ እንዲገድለውም በንጉሥ ዘንድ በሐሰት ነገር ወነጀሉት ንጉሡ ግን እጅግ ስለሚወደው ራራለት በነገራቸውም በዘበዘቡትና በአስጨነቁትም ጊዜ ከጭንቀት የተነሣ ወደ ሩቅ አገር አሥሮ አጋዘው። የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም የሚራዳው ሆነ ሰማያዊ ኅብስት የወይን ጽዋ እያመጣለት ይመግበዋል።

➯ቅዱስ ቁርባንንም መቀበል በሚሻ ጊዜ የክብር ባለቤት የሆነ የክርስቶስን ሥጋውንና ደሙን አምጥቶ ይመግበዋል። ከዚህም በኋላ እሊያ ነገረ ሠሪዎች ይገድሉት ዘንድ ንጉሥ እንዲፈቅድላቸው ተማከሩ በፈቀደላቸውም ጊዜ ወደ ንጉሥ የፍርድ ሸንጎ አምጥተው ገደሉት።

➯በዚያችም ሌሊት እግዚአብሔርን የሚፈራ አንድ መነኵሴ በድኑን ሊያይ ተነሥቶ ሔደ ሥጋውንም ሲያጥኑ ሦስት መላእክትን አገኛቸው። እርሱም እንዳልዋሸ በሕያው እግዚአብሔር ስም እየማለ ይህን ተናገረ። ዳግመኛም የብርሃን ፋና ከሰማይ ሲወርድለት ብዙ ቀን የተመለከቱም አሉ።

➯ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ አዘነ ተጸጸተም በጎ ሥራውንም ሁሉ አሰበ እነዚያንም ሐሰተኞች ረገማቸው በሞትም ቀጣቸው ቅዱስ ዐምደ ሚካኤልም በአባቶቹ መቃብር አክብረው እንዲቀብሩት አዘዘ። እርሱ ቅዱስ እንደሆነ በበጎ ስም አጠራር እንዲጠሩት እንጂ ስሙን በክፉ እንዳይጠሩ አዋጅ አሳወጀ። መታሰቢያውንም አቆመለት ልጆቹንም አከበራቸው እጅግም ወደዳቸው።

➯ከዚህም በኋላ ልብነ ድንግል በነገሠ ጊዜ ከእርሱ ጋር ያለውን የአባቱ የበእደ ማርያምን ቃል ኪዳን ሰምቶ ከዚያ አፍልሰው ወደ አትሮንስ ማርያም እንዲወስዱትና በዚያ በነገሥታት መቃብር እንዲቀብሩት አዘዘ።


➯ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ ሁሉ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።


On imo👇👇👇
https://s.channelcom.tech/1EhjvQ?from=copy_link

On Telegram @AndEmnet

#ስንክሳር ህዳር ፫/3 ቀን
2024/11/12 09:50:38
Back to Top
HTML Embed Code: