tgoop.com/Andkelem/39
Create:
Last Update:
Last Update:
ገብረ ሕይወት
አቡነ ንብሎ ለገብረ ሕይወት፥
እስመ አምጽአ ለነ ትንባሌሁ ሥርየት።
ወንወድሶ በቃለ ማኅሌት፥
እንዘ ንብል ሃሌ ሉያ፥
ሰብአ ግብፅ ወኢትዮጵያ።
ስምዖን ፣ አቅሌስያ በእግዚአብሔር ፊት ፃድቃን፥
ወለዱልን ፀሐይ ብሩህ እም ብሩሃን፥
ግብፅ ብቻ አልበራ ፣ ባሕቢት አል ሐጋራ፥
ናኘ በኢትዮጵያ የትሩፋቱ ጮራ።
ዝቋላ በገድሉ ፣ ምድረ ከብድ በዐፅሙ፥
በተአምራቱም ኃይል ዝጊቲ ገዳሙ፥
በነፍስ ፣ በሥጋ ዳኑ የታመሙ፥
ወውስተ ኩሉ ምድር ወጽአ ነገሮሙ።
እንደ መቶ ሃያው አናብስት አናምርት፥
ከእግረ መቅደስህ አደግሁ ባንተ ትምህርት፥
ዛሬም እልሃለሁ "አቡየ ፣ አቡየ"
"ነዓ አድኅንነኒ ፣ ርድአኒ" ብየ።
ርእሰ ባሕታዊ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፥
በትጉኃን ክቡር ፣ በመላእክት ውዱስ፥
በማለድከው ምልጃ ተዘቅዝቀህ ባሕር፥
በኪዳንህ ያመንሁ እኔን አምላክ ይማር።
✍️ከሣቴ ብርሃን
🎼ዘማሪት ሕይወት ወልዴ
_____
http://www.tgoop.com/Andkelem
http://www.tgoop.com/Andkelem
BY አንድ ቀለም ከከሡ ጋር

Share with your friend now:
tgoop.com/Andkelem/39