Telegram Web
ዛሬ ረቡዕ ማታ ከምሽቱ 2:16 ላይ እጅግ አስገራሚው በተፈጥሮ ሁሉ ላይ የተቀመጠው "የወርቃማው ቁጥር " ይቀርባል። እነ ሞናሊዛን ያሳመረው አጃኢብ የሚያሰኝ ከሰማይ እስከ ምድር የተዘረጋው፤ በሰውነታችን ኹሉ ላይ የሚታየው "ወርቃማው ክፍልፋይ" ተተንትኖ በDr Rodas Tadese YouTube ይቀርባልና አደራ እንዳያመልጦት።
Dr Rodas Tadese 888
ኀሙስ ከምሽቱ 2:22 ላይ ሙሴ 10ሩን ቃላት የተጻፈበትን ጽላት የተቀበለበት፤ እግዚአብሔር በታላቅ ግርማ የተገለጸበት የሲናን ተራራ የወጣሁትን አስደናቂ ጉዞ በDr Rodas Tadese YouTube ላይ አቀርብላችኋለሁ። የጥበብ የብርሃን ልጆች በሰዓቱ ይህን አስደሳች መርሐ ግብር ተከታተሉ።
Watch "ሙሴ 10ሩን ቃላት የተቀበለበት የሲና ተራራ፤ አስደናቂው የእግዚአብሔር ተራራ" on YouTube
https://youtu.be/12bpEabYsyg
Watch "አስደናቂው የሰውነታችን ምስጢር ቁጥር ሲከፈት" on YouTube
https://youtu.be/BEtpkUjw3oA
Watch "የድንጋዩን ጽሑፍ አሳዩኝ ተገርሜያለሁ" on YouTube
https://youtu.be/iprleOFSXDM
Watch "የሰባቱ ድብቅ ኮድ በፊታችን፣ በጣታችን፣ ፊደላችን ላይ" on YouTube
https://youtu.be/fMXFeaqiUr4
Watch "26ቱ ኮዶች ተከፈቱ አእምሮን ያበራል" on YouTube
https://youtu.be/6vTHZsYSIA8
[24ኛው መጽሐፌ "ማዛሮት" ታኅሣሥ 19/ 2014 ዓ.ም. ከወጣ ዛሬ 1 ዓመት ሞላው። መጽሐፉን ያነበቡ ኹሉ ተራቀው በማየቴ ተመስገን እላለሁ።]

💥 ሰማያዊ ምስጢራትን የያዘው "ማዛሮት" የተባለው ብዙዎች ሲጠባበቁት የነበረው 24ኛ መጽሐፌ በ376 ገጾች ተዘጋጅቶ ለአንባብያን የቀረበ ነው።

💥 ይህ መጽሐፍ በ 4 ታላላቅ ምዕራፎች የተከፈለና 170 ርዕሶችን የያዘ ሲሆን፦ ከእነዚህ ውስጥ ጥቂቶቹ፦
✍️ ፀሐይ የያዘችውን 35 መንፈሳዊ ምስጢራትን በዝርዝር ይዟል
✍️ የዮሐንስ ራእይን 7ቱን ማሕተም ለሚያጠኑ ሊቃውንት እስከ 2100 ዓ.ም. ድረስ የሚከሰቱ የ100 ዓመታት የደም ጨረቃ ግርዶሽ (Super Blood Moon) መቼ እንደሚከሰቱ

✍️ 46 ቱ ሕብራተ ከዋክብት የያዙት ረቂቅ ሙሉ መንፈሳዊ ሰማያዊ ምስጢር
✍️ ፀሐይ የምትዞራቸው የ12ቱ የዞዲያክ መገብተ አውራኅ ከዋክብት ምስጢርና ምሳሌ
✍️ ፕላኔቶች የያዙት ረቂቅ ምስጢርና ምሳሌ

✍️ የኢትዮጵያ ፊደላት ከፕላኔት ጋር ያላቸው ድንቅ ትስስር
✍️ ሰብአ ሰገልን ስለመራው የቤተልሔም ኮከብ ምስጢር
✍️ የጨረቃ መንፈሳዊ ምሳሌ

✍️ በመሉ ጨረቃ ጊዜ በሰዎች፣ በአራዊት የሚከሰተው የጠባይ መለዋወጥ መነሾው
✍️ ጨረቃ በምታስነሣው ማዕበል ስለሚከሰተው ቀጣይ ጎርፍ
✍️ የሴቶች የወር አበባ ዑደትና የጨረቃ ዑደት ያለው ትስስር

✍️ 12ቱ ነፋሳት፣ ደመናት፣ መባርቅት፣ ነጎድጓድ፣ ዝናብ፣ በረዶ የያዙት ምሳሌዎች
✍️ የኢትዮጵያ ሊቃውንት ያመሰጠሩት በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሱት ሰማያት አካላት በሙሉ ትርጓሜ ተካቶበታል።

✍️ ያለንበት ዘመን የዕውቀት፣ የጥበብ፣ የማስተዋል ጊዜ ነውና ይህን መጽሐፍ አንብበው ከፍተኛ ሥጋዊና መንፈሳዊ ዕውቀትን ይሸምቱ። የገና ስጦታ አድርገው ለሚወዱት ሁሉ ይስጡ።
✍️ መጽሐፉን በሁሉም የመጻሕፍት መደብርና በሚያዞሩት በ200 ብር ያገኙታል። ወይም ብርሃን መጻሕፍት አከፋፋይ 0913422447 ደውለው ያገኙታል።
✍️ በውጭ ሀገራት ለምትፈልጉ በአማዞን ላይ
https://www.amazon.com/dp/0578260875/ref=cm_sw_r_apan_glt_i_ZP0XDRH8DPNN29PB1R7X

ይዘዙ።
Watch "የገና አባት እና የገና ዛፍ" on YouTube
https://youtu.be/tf__1Nf0NoQ
Watch "ሰብአ ሰገልን የመራው የቤተልሔም ኮከብ ምን ነበር? ሳይንቲስቶች ምን አሉ?" on YouTube
https://youtu.be/8sABOhqvjJA
Watch "ፊደሉ እንዳይጎድል፤ የገና ጀንበር አለበት፤ 182 ቀመር ነው" on YouTube
https://youtu.be/xkzm5AcWCc8
👉 የሕትመት ዋጋ በመጨመሩ የጥበብ የብርሃን ልጆች አንባብያን በመጻሕፍት መሸጫ ዐጥተውት በጠየቁት መሠረት 25ኛ መጽሐፌ 888 ለሦስተኛ ጊዜ ታትሞ ለአንባብያን ቀርቧል።
👉 መጽሐፉ በኹሉም የመጻሕፍት መሸጫዎች ይገኛል ወይም 0913422447 (ብርሃን) ብለው ይደውሉ።
👉 በውጪ ሀገር የምትኖሩ በቀላሉ በአማዞን ላይ ማግኘት ይቻላል። ሊንኩም https://www.amazon.com/dp/B0BGZ14FBD/ref=cm_sw_em_r_mt_dp_X81QK1M112XS84KPYFSY
👉 አማዞን ሲታዘዝ እያተሙ ስለሚልኩ Out of stock ቢልም ችግር የለም ካዘዙ እነርሱ አትመው በአድራሻዎት ይልካሉ።
💥 የመጽሐፉ መሸጫ 350 ብር ብቻ ነው። መጽሐፉ በ27 ምዕራፍ የተከፈለ ሲኾን በኢትዮጵያ የፊደል ቀመር ውስጥ የሚገኙ:-
👉 የፊደላት ጂኦሜትሪ፣ ድምፅ፣ ቁጥር
👉 በመቅረዙ ውስጥ የተቀመጠው የ7 የብርሃን ቀመር
👉የ አ ቡ ጊ ዳ ሙሉ ቀመር
👉 በመጽሐፈ ሔኖክ የሚገኘው የስመ አምላክ ቀመር
👉 በገነት ውስጥ የነበሩ የዕፀ ሕይወት እና ዕፀ ጥበብ ቀመር
👉 በግእዝ ፊደላት ያለው የ3.14 የፓይ ቀመር
👉 የ DNA እና RNA ቀመር
👉 የፔሪዮዲክ ሠንጠረዥ የንጥረ ነገራት ቀመር
👉 የፕሩቶንና የኤሌክትሮን ቀመር
👉 የልብ እና የአእምሮ ዐይኖች መክፈቻ የግእዝ ቀመር
👉 በ182 የግእዝ ፊደላት የተቀመረው የኢኪውኖክስ (Equinox) ቀመር
👉 በፊደላችን የሚገኝ የሥርዐተ ፀሐይ ቀመር
👉 ከአድማስ እስከ ናጌብ የምድር ልኬት ቀመር
👉 በፊደላችን የተገለጸ የጨረቃና የምድር ራዲየስ ልኬት
👉 በግእዝ ፊደላችን የተገለጸ በሜትር ፐር ሰከንድ የሚቀመር የድምፅ ፍጥነት
👉 በፊደላችን የተገለጸ በሚክሮሜትር የሚቀመር የቀይ የደም ሴል፣ በደም ቧንቧ ውስጥ ያለው ቀመር
👉 በግእዝ ፊደላት ውስጥ የሚገለጸው ቀመረ ምጽአትና የርኅወተ ሰማይ (የሰማይ ደጃፍ) Portals መክፈቻ ቀመር እና ሌሎች ብዙ ድንቅ ምስጢራት ተካተውበታል።
💥 በተጨማሪም በውጪ ሀገራት በአማዞን ላይ ያሉ ሌሎች መጻሕፍት ሊንክ ከፈለጋችሁ
👉 የፊሳሎጎስ መጽሐፍ ሊንክ
https://www.amazon.com/Book-Phisalgos-Amharic-Rodas-Abebe/dp/1638779805/ref=sr_1_4?dchild=1&qid=1626212320&refinements=p_27%3ARodas+Abebe&s=books&sr=1-4&text=Rodas+Abebe
👉 የማዛሮት መጽሐፍ ሊንክ
https://www.amazon.com/dp/0578260875/ref=cm_sw_r_apan_glt_i_ZP0XDRH8DPNN29PB1R7X
👉 የቴሌግራም ቻናሌ
https://www.tgoop.com/Rodas9
👉 የሕትመት ዋጋ ከዕለት ወደ ዕለት በከፍተኛ ኹኔታ እየጨመረ በመኼዱ ወደ ፊት መጻሕፍት ላይገኙ ስለሚችሉ ፈጥነው በእጅዎ ያስገቡ።
👉 የ 888 መጽሐፉ መታሰቢያነቱ
💥 ዘመናቸውን በጠብ ሳይኾን በጥበብ ለፈጸሙ፡፡ ቀለባቸውን ሳይኾን ቀልባቸውን ላስቀደሙ፡፡
ለጠበቡ ሳይኾን ለተጠበቡ፡፡
ለቀናተኞች ሳይኾን ለቅኖች፡፡
ለምን ተወለዱብን ሳይኾን እንኳን ተወለዱልን ለተባሉ፡፡
ሰውን በአንደበታቸው ላዋረዱ ሳይኾን የሰውን ክብር ለተረዱ እና ሰውን ለረዱ፡፡
ለተሳዳቢዎች የጨለማ ልጆች ሳይኾን፤ ለሚመርቁ የብርሃን ልጆች ኹሉ ይኹንልኝ።
👉 መጽሐፉ በእጃችሁ የገባ መጽሐፉን ይዛችሁ ፎቷችሁን በአስተያየት መስጫው ላይ ብታስቀምጡ የበለጠ ደስ ይለኛል።
2025/07/13 22:51:12
Back to Top
HTML Embed Code: