Telegram Web
ይህ ከላይ የምትመለከቱት "self editing table" ለተከበረው የረመዷን ወር አስመልክቶ ጊዜን በአግባቡ ለመጠቀም የተዘጋጀ ሲሆን ተጨማሪ መከናወን ያለባቸው ተግባራት ካሉ በግላችሁ ማካተት ትችላላችሁ🥰🤍

በአሏህ ፍቃድ የምትጠቀሙበት ይሆናል

♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⎙ㅤ     ⌲            
ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ
   
@ArkemMy
     
                    
📿𝐑𝐚𝐦𝐚𝐝𝐚𝐧......😊8

ረመዳን 8🌙

የሰደቃ ወር

ۖ وَأَحْسِن كَمَا أَحْسَنَ اللَّهُ إِلَيْكَ ۖ وَلَا تَبْغِ الْفَسَادَ فِي الْأَرْضِ ۖ إِنَّ اللَّهَ لَا يُحِبُّ الْمُفْسِدِينَ

«አላህም በሰጠህ ሀብት የመጨረሻይቱን አገር ፈልግ፡፡ ከቅርቢቱም ዓለም ፋንታህን አትርሳ፡፡ አላህም ወደ አንተ መልካምን እንዳደረገልህ (ለሰዎች) መልካምን አድርግ፡፡ በምድርም ውስጥ ማጥፋትን አትፈልግ፡፡ አላህ አጥፊዎችን አይወድምና»


ሰደቃ ደረትን ያሰፋል…… ለቀልብ እረፍት ይሠጣል

(ረሱል ሰዐወ)  ስለ ስስታምና ለጋሽ ሰው ምሳሌ ሲያስቀምጡ፡-

ምሳሌያቸው ከብረት የሆነ ጡሩር ደረታቸው ላይ እስከ አንገታቸው ድረስ
እንደለበሱ ሁለት ሰዎች ነው፡፡ ለጋሹ ሰውዬ በለገሰ ቁጥር ትሰፋለታለች፡፡
ቆዳውም እስኪሸፈን ድረስ ታለብሰዋለች፡፡
ስስታም ሰው ደግሞ አንድን ነገር ለመስጠት ባሰበ ቁጥር እሱ ማስፋት ቢፈልግም እንኳ እያንዳንዷ ቀለበት ቦታዋን ጥብቅ እንቅ አድርጋ ትይዛለች፣ አትሰፋም፡፡› ብለዋል፡፡

ሰደቃ የአላህን ሱብሃነሁ ወተዓላ ቁጣ ታበርዳለች፡፡ የአላህ መልእክተኛ
ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም “በሚስጢር የምትሰጥ ሰደቃ የልዕልና ባለቤት የሆነውን የአላህን ቁጣ ታበርዳለች፡፡” ብለዋል፡፡

“ውሃ እሳትን እንደሚያጠፋው ሁሉ ሶደቃም ወንጀልን /ሐጢኣትን/
ታጠፋለች፡፡”

“በየቀኑ ባሮች በሚያነጉበት ቀን ሁለት መላእክት ይወርዳሉ፡፡ አንደኛው ‹አላህ
ሆይ ለሚለግስ ሰው ተካለት፡፡› ይላል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ‹አላህ ሆይ! የሚሰስትን ሰው አጥፋበት፡፡› ይላል፡፡”

ሰደቃ የሚሰጥ ሰው ሀብትና ገንዘቡ ይባረክለታል፡፡

የአላህ መልእክተኛ ሰዐወ “ሰደቃ ከሀብት አንዳችም ነገር አይቀንስም፡፡” ብለዋል ፡፡

♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⎙ㅤ     ⌲            
ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ
   
@ArkemMy
     
                    
📿𝐑𝐚𝐦𝐚𝐝𝐚𝐧......😊
ያለፈው ረመዷን በአንድ ሱፍራ አብረውን ያፈጠሩ፣ ዛሬ ከመሬት በታች የሚገኙ ብዙ ወዳጆቻችን አሉ። ዛሬ ይሆን ነገ እያለን በመጠባበቅ ላይ ሳለን፣ ስንቶች አንዲት ቀን ተቀድመው ተሸኙ። እኛም የአላህ ፍቃድ ሆኖ ዛሬ እኛ እዚህ ላይ ተገኝተናል። ፈሊላሂል ሀምድ🤍 ይህ ብዙዎች ሲመኙት የነበረው እድል ዛሬ እኛ እጅ ላይ ወድቋልና ሳንጠቀምበት የማናልፍ አንሁን። አላህ የምንጠቀምበትም ያድርገን🖤

♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⎙ㅤ     ⌲            
ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ
   
@ArkemMy
@Quran_KG

Best Quran Channel
1.Abdul Rahman Sudais
2.Maher Al Muaiqly
3.Muhammad Ayyub
4.Nasser Al Qatami
5.Idres Abkar
6.Nabil Al Rifai
7.Al Ausy
8.Al Zain Muhammad Ahmad
9.Fares Abbad
10.Ahmad Shalabi
11.Halifa Al Tonaeijy
12.Ahmad Al Ajmiy
13.Abdulloh Matrood
14.Zuhair Hafez
15.Ali Al Huzaify
16.Abdulloh Juhaniy
17.Salah Bukhatir
18.Mhammad Jibril
19.Saud Al Shuraim
20.Yaser Al Dossary
21.Halid Al Jaliyl
22.Ahmad Al Nufais
23.Ahmad Al Misbahi
24.Halil Hussary
25.Hani Al Rifai
26.Abdulbasid Abdussomad
27.Al Minshawi
28.Abdulbasid Qobilov
29.Mishary Rashid Al Afasy
30.Abubakir Shatry
31.Abdul Rashid Ali Sufi
32.Mahmud Al Banna
33.Muhammad Abdul Karem
34.Adel Rayan
35.Muhammad Toblavi
36.Abdullah Ali Jaber
37.Aziz Alili
38.Yasen Al Jazairy
39.Emad Al Mansary
40.Saad Al Ghamidi
41.Bandar Balilah
42.Rashid Al Arkani
43.Raad Al Kurdi
44.Muhammad Anvar
45.Al Luhaidan
46.Ibrahim Al Akhdar
47.Wadee Al-Yamani
48.Abdullah Al Mudhaffar
49.Ayman Rushdi Suwayd
50.Abdullah Kamal
51.Abdulaziz Zahrani
52.Hasanxon Abdulmajid
53.Tawfeq As Sayegh
54.Abdulhady Kanakery
55.Ghassan Al Shorbajy
56.Mustafa Ismail
57.Abdullah Basfar
58.Yusuf ibn Nuh
59.Jazza Al Swailah
60.Fahad Al Kandary
61.Musa Bilal
62.Mahmod Al Rifai
63.Ibrahim Al Asirry
64.Salah Al Budair
65.Muhammad Al Sharef
66.Abdulmuhsin Al Qasim
67.Mustafa Al Azzawi
68.Abdul Razzaq Dulaimi
69.Yusuf Ahmad
70.Muhammad Hasan
71.Jamaan Al Osaimi
72.Moftah Al Saltany
73.Anas Al Emady
74.Salah Al Sahud
75.Ali Yakupov
76.Zaki Dagistany
77.Abdullah Halif
78.Ahmad Al Lahdan
79.Abdusattar Sammak
80.Yahya Hawwa
81.Mahmud Abdulwahhab
82.Ibrahim Al Jarmi
83.Salah Al Hashim
84.Shirzad Taher
85.Yaser Al Kushary
86.Muhammad Riza
87.Umar Al Qozobry
88.Ahmad Al Haddod
89.Ahmad Naina
90.Adel Al Kalbany
91.Amr Al Kazmy
92.Abdulmuhsin Al Harty
93.Abdulbary Al Sabuuty
94.Hatam Al Wair
95.Mahir Shahashiro
96.Murad Ali
97.Sayyid Sadaqat Ali
98.Mustafa Lahuni
99.Salah Yasen
100.Ahmad Al Hawashi
101.Muhammad Al Muhaysin
102.Anas Al Mayman
103.Ibrahim Al Kashidan
104.Yusuf Al Shuya
105.Ahmad Al Tarabulsy
106.Haled Al Qahtany
107.Haled Al Abdulkafi
108.Hamid Sinan
109.Fuad Al Khamry
110.Ahmad Diban
111.Bara ibn Basfar
112.Ibrahim Al Dossary
113.Hasan Salih
114.Ibrahim Al Jebren
115.Muhammad Hady Toure
116.Muhammad Loiq
117.Saber Abdul Hakam
118.Muhammad Al Alim
119.Rahmatulloh Obidov
120.Akram Al Aqimy
121.Abdul Wadood Hanif
122.Rashid Darwish
123.Nuriddin Obidxon
124.Waled Al Naehi
125.Hisham Abdulbariy
126.Abdullah Ghayilan
127.Karim Mansury
128.Shahriyar Parhezkar
129.Abdul Aziz bin Ahmad
130.Badr Ali
131.Muhammad Saleh
132.Abdullah Shakir
133.Ahmad Al Abid
134.Haled Muhannah
135.Mehmet Amin
136.Yaser Sallama
137.Hazza Al Balushi
138.Ahmad Saber
139.Muhammad Sidque
140.Ilhan Tuk
141.Muhiddin Al Kurdi
142.Abdullah Hayat
143.Abdullah
144.Muhammad Sad Ibrohim
145.Muhammad Al Abdullah
146.Hatlan bin Hatlan Ali
147.Umar Al Saba
148.Eid Hasan abu Aachra
149.Fatih Seferagic
150.Salman Al Utaybiy
151.Hamid Shakir
152.Ahmad Muhammad Amr
153.Mahmud Abdul Hakam
154.Hasan Al Aziz
155.Kamal Al Marwash
156.Adel Muslim
157.Peshawa Kurdi
158.Haramain
159.Seyed Ramadan
160.Al Fateh Al Zubair
161.Islam Sobhi
162.Ayun Al Kushiy
163.Doniyor Fayz
164.Abdul Rauf Ridvan
165.Karem Haririy
166.Nemaha Al Hasan
167.Salah Bauthman
168.Fateh Colak
169.Ahmad Halil Shahin
170.Anas Al Jalhum
171.Maria Ulfah
172.Abdullal Al Kandary
173.Ali Hajjaj Al Souissi
174.Tareq Abdulgani Daawob
175.Saad Al Khateb
176.AbdulRahman Al Majed
177.Abdulmohsin Al Obaikhan
178.Muhammad Said Rojeh
179.Muhammad Ali
180.Ahmad Zahraniy
181.Abdulhalim Husayn Idres
182.Ahmad Rizo Qori
183.Usama Muhammad Abu Zaid
184.Ahmad Said Hashim
185.Abdul Mujib bin Kiron
186.Mustafa Gharibi
187.Mazzen Al Shehri
188.Abdulrahman Al Shahat
189.Mufti Menk
190.Shayx Alijon Qori
191.Obaida Muafaq
192.Murad Sabatiy
193.Ahmad Nasr
194.Ibrahim Al Zaim
195.Taha Muhammad
196.Hamzah Al Faar
197.Muhammad Ghazzali
198.Muhammad Umar Janany
199.Salah Al Kurashy
200.Xayrulla Hamidov
201.Ibrahim Al Maghriby
202.Hasan Al Daghreyriy
203.Ahmad Al Roziqiy
204.Ahmad Al Swailem
205.Sheikh Okasha Kameny
206.Malick Diaw

1.Shayx Muhammad Sodiq Muhammad Yusuf (UZB)
2.Afzal Rafiqov (UZB)
3.Elmer Kulliyev (RU)
4.Muallimi soni
  . . . . . . . . . . . . . . . . . . .
    - - @Quran_KG - -
አፍቃሪ በማፍቀሩ ምክነያት የሚያገኘው የማፍቀር ደረጃ እንዲሁ ጥቅም  እንደሚያፈቅሩት ሰው አይነት እንደሚለያይ ያውቁ ኖራልን?

ለምሳሌ፦

๏ [አንድን ሴት የሚያፈቅሩ አንድ ሺህ ወንዶች ቢኖሩ ያቺን ሴት በማፍቀር የሚጠቀሙት እርሷም እርሱን አፍቅራው የምታገባው ነው]…

[የአሏህን መልዕክተኛ የሚያፈቅሩ አንድ ሚሊየን ሰዎች ቢኖሩ ግን ደረጃን እንዲሁ ጥቅሙን አልፎም የእርሳቸውን ውዴታ የሚያገኙት ሁሉም ናቸው]

ዐለይሂ ሶለዋቱሏሂ ወሰላሙሁ

♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⎙ㅤ     ⌲            
ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ
   
@ArkemMy
     
                   
#ኢስቲግፋር (From My Note Book1)

(መዚዳ ተማም)

አንዳንዴ ቲኒኒሽ ናቸው ብለን የሰራናቸው እና ኢስቲግፋር ማድረግ የረሳንላቸው ወንጀሎቻች Anxiety, Depression መንስሄ ሊሆኑ ይችላሉ በኢስቲግፋር ብናፀዳቸው ጭንቀታችን ከነሰንኮፉ ይነቀል ይሆናል።

يَوْمَ يَبْعَثُهُمُ اللَّهُ جَمِيعًا فَيُنَبِّئُهُم بِمَا عَمِلُوا ۚ أَحْصَاهُ اللَّهُ وَنَسُوهُ ۚ وَاللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ شَهِيدٌ}

"አላህ ሁላቸውንም በሚቀስቃሳቸው ቀን (ይቀጣቸዋል)፡፡ የሠሩትንም ሁሉ ይነግራቸዋል፡፡ የረሱት ሲኾኑ አላህ ዐውቆታል፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ዐዋቂ ነው፡፡"

በኖርናቸው አመታት ልንረሳቸው እምንችላቸውን ቲናንሽ ወንጀሎቻችን ምን ያህል እንደሚሆኑ አስቧቸው እስኪ😔 አል-ረሂም ይቅር በለን እንዲሁ🤲

ትላልቅ አፅያቶች ናቸው ተብለው የተነገሩንን አፅያቶች እስካልተዳፈርን ኢስቲግፋር በማድረግ እንዳልታዘዝን ኢባዳ እንዳልሆነ እረስተነው ይሆናል ግን ደግሞ ያለፈውንም መጪውም ወንጀሎቹ ሁሉ የተማረላቸው የኛ ነቢ(ሰዐወ) በየቀኑ ንጋት ላይ 100ጊዜ ከጌታቸው ምህረትን ይጠይቁ ነበር፡፡

ከአቡ ሙሳ አል‐አሽዓሪይ እንደተዘገበው የአላህ መልክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል: ‐ «ምን ጊዜም ንጋት ላይ በጠዋት መቶ ጊዜ ኢስቲግፋር ሳላደርግ ቀርቼ አላውቅም።»


ይብዛ ወይም ይነስ እንጂ ሁላችንም ሀጃዎች አሉብን ያስጨነቀን ጉዳይ ወይም ይደርስብናል ብለን የፈራነው አደጋ አለን መውጫችን ኢስቲግፋር ነው ከትናንተ ፀፀት እና ከነገ ስጋት ተላቀን ዛሬን እንድንኖር ያደርገናል፡፡ የትናንት ስህተትን ያፀዳል ነገን ከስጋት ያላቅቃል ሪዝቅን ያሰፋል በነገራችን ላይ ኢስቲግፋር ሪዝቅን እንደሚያመጣ ተነግሯል(I think this part motivates us more)

« አራት ነገራት ሪዝቅን ያመጣል። የለሊት ስግደት፣ በለሊቱ መጨረሻ ላይ ምሕረት (ኢስቲግፋር) ማብዛት፣ ምጽዋት በመስጠት ላይ መጽናት፣ የጥዋትና የምሸት ዚክር ማድረግ።»
[ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንላቸው።]

ሪዝቅ ብዙ አይነት አለው ሀብት አልያም መልካም ሚስት/ባል ልጆች ወይም ጤና መወደድ ኢማን የውስጥ እርጋታ ብላ ብላ ዌል እንግዲ ድህነትን እማይፀየፍ በሀብት መባረክ እማይፈልግ የለም በመልካም ሚስት/ባል መባረክ እማይፈልግም እንደዚያው የያኖቹ ማረፍያ በሆኑ ልጆች መባረ ጤና መወደደ ሌሎችንም እንደዛው፡፡


ክልክል የሆኑ መስመሮችን ስትጥስ ውስጥህ ይረበሻል ኣ? ልብህ በሂወት ስላለ ነው መጣስህን ተለማምደህ ልብህ በድን እስኪሆንና Normal እስኪመስል አትጠብቅ ደጋግመህ ብታጠፋ ደጋጎመህ ተመለስ እንደዛ አይነት ልብ ይኑርህ ከነፍስያህና ከሸይጣን ታገል ተናነቃቸው ፈፅሞ ግን አትውደቅላቸው መታገልህ በራሱ ክፍያ አለው አላህ እነዚያ የታገሉትን እመራቸዋለው ብሎን የለ፡፡

وَالَّذِينَ جَاهَدُوا فِينَا لَنَهْدِيَنَّهُمْ سُبُلَنَا ۚ وَإِنَّ اللَّهَ لَمَعَ الْمُحْسِنِينَ

እነዚያም በእኛ መንገድ የታገሉ መንገዳችንን በእርግጥ እንመራቸዋለን፡፡ አላህም በእርግጥ ከበጎ ሠሪዎች ጋር ነው፡፡ (ዐንከቡት 69)

ትግል ሜዳ ላይ ብቻ አይደለም ከወንጀሎቻችን ለመላቀቅ ከነብስያና ከሰይጣን ጋር ምናደርገው ትግልም ጂዐድ ነው፡፡

ትላልቅ ወንጀሎችን ስላልተዳፈርን ብቻ ከኢስቲግፋር መራቅ አንርቅም ኢባዳዎቻችን በራሱ ኢስቲግፋር ያስፈልጋቸዋል በእውነቱ ስንቶቻችን ነን ሀቃቸውን ጠብቀን ምንተገብራቸው?፡፡

አስተግፊሩላህ ለዘነጋናቸው ቲናንሽ ወንጀሎቻችን ላጓደልናቸው ኢባዳዎች ላስተባበልናቸው ፀጋዎች...፡፡

በስተመጨረሻም
አላህ ኢስቲግፋር ካገራልህ ሊምርህ ፈልጎ ይሆናል፡፡

ኢስቲግፋር ለማዘውተር ልቦና ከሰጠህ ምህረቱን ሊያወርድልህ መፈለጉን ማወቅ አለብህ
(ዓሊ ቢአጣ―ዐሰ)

@ArkemMy
🕋የጁሙዐ ቀን ሱናዎች🕌

1-ነቢዩ(صلى الله عليه وسلم)ላይ ሶለዋት ማውረድን ማብዛት

2- 📖 ሱረቱ–ከህፍን መቅራት

3-🚿 ሸዋር መውሰድ

4-⬜️ካለው ሻል ያለውን ልብስ መልበስ

5-🦷ሚስዋክ መጠቀም(ጥርስን መፋቅ)

6-🌹 ሽቶ መቀባት

7-🌅 ወደ መስጂድ አበክሮ መሄድ

8- ወደ መስጅድ በግር መሄድ

9-📿 ከጁሙዐ ሶላት ቡሃላ 4 ረከዓ(2+2) መስገድ

10- ዱዓ ተቀባይነት ያላትን ሰዓት መጠባበቅ


ቤተሰብ እስኪ ሼር እያደረጋችሁ ቻናላችንን እናሳድገው አብረን

ሼር https://www.tgoop.com/ArkemMy
ከትውስታ ቀደም ካሉ ስራዋች

በተስፋ ቃልህ አፅናናኝ
            
                 ቀኔ ሲጨልም ፣ አልታይ ሲለኝ
                 የችግሬ ቋጦች፣ በተራ ሲወግሩኝ
                 ተስፋ በታጠነው ፣ በቃልህ አፅናናኝ
                 *                      *                      *
                 መኖር ባይሆንልኝ፣ ተስፋዬ ጨልሞ
                  ሂወት ብታስጠላኝ ፣ "ኢማኔም" ታሞ
                  ድንገት ናልኝና ፣ በተስፋ ክበበኝ
                  መድሀኒት በሆነው፣ በቃልህ አክመኝ
                  *                        *                      *
                  ህመም ሲወዳጀኝ ፣ ትቶኝ ላይሄድ ምሎ
                  መኖርያው ሲያረገኝ፣ መሰረቱን ጥሎ
                  ከሰይጧን አብሮ ፣ ተስፋዬን ሲቀማኝ
                  ተስፋ በታወደው፣ በቃልህ አፅናናኝ
                   *                     *                      *
                   ኢነ መአል ዑስሪ ፣ዩስራ
                   ይ'ን አንቀፅ አሰማኝ፣ ከቃሎችህ ተራ
                   ተስፋ ያለብሰኛል ሲያርዘኝ መከራ
                            (መዚዳ ተማም  )
                    
                                       
                   T.me/ArkemMy 👈 join
🕋የጁሙዐ ቀን ሱናዎች🕌

1-ነቢዩ(صلى الله عليه وسلم)ላይ ሶለዋት ማውረድን ማብዛት

2- 📖 ሱረቱ–ከህፍን መቅራት

3-🚿 ሸዋር መውሰድ

4-⬜️ካለው ሻል ያለውን ልብስ መልበስ

5-🦷ሚስዋክ መጠቀም(ጥርስን መፋቅ)

6-🌹 ሽቶ መቀባት

7-🌅 ወደ መስጂድ አበክሮ መሄድ

8- ወደ መስጅድ በግር መሄድ

9-📿 ከጁሙዐ ሶላት ቡሃላ 4 ረከዓ(2+2) መስገድ

10- ዱዓ ተቀባይነት ያላትን ሰዓት መጠባበቅ


https://www.tgoop.com/ArkemMy
**የደቂቃ ማስተዋልን ወስደህ ተመለስ**

የደቂቃ ፍፁም ፀፀትህ፤ የቅፅበት እውነተኛ መመለስህ ላንተ እኮ በቂህ ነበር፤ የጌታህ ምህረት እጅጉን ቅርብ ነውና። አንተ ግን ተዘናጋህ!!

ለዘመናት በዝንጋቴዎችህ ውስጥ ሸይጣን የማይፈርስ የሚመስል ቤቱን እለት በእለት በወታደሮቹ እየገነባ ከጌታህ በጠንካራ መሰል ግንብ ሊያርቅህ ይለፋል። እያንዳንዱ ዝንጋቴህ፣ ስህተትህና ውድቀትህ በዙሪያህ ለሚገነባው አጥር ጡቦች ናቸው።

ይህ የዘመናት ግንብ ግን የጌታህን ምህረት በከጀሉ እውነተኛ የፀፀት እምባዎች ይወድማል፤ ወደ ኃያሉ አምላክህ መመለስን ፍፁም ቁርጠኛ በሆኑ የደቂቃ ጥሪዎች እንዳልነበር ይሆናል፤ የማይፈርስ የመሰለው ከልካይ ቤትም ፈርሶ ዳግመኛ በጌታህ ፍቅር ታብባለህ። ምንም ቢገዝፍ የሸይጣንና ወታደሮቹ ግንብ ፈራሽ ነውና!

ኢብኑ አል ቀይም አል ጀውዚያህ እንዲህ ሲል ተቀኝቶ ነበር።

‏بنى ما بنى حتى إذا ظن
إن ما بناه وطيد راسخ الأسس محكم
أتى العفو من كل القواعد ما بنى
فخر عليه سقفه المتهدم
ولو أن ألفا من بناة جنوده
بنوا كل يوم ألف بيت ورمموا
لهدت بيوت الكل توبة مخلص
على ما جناه وصح منه التندم
ከቃላት በላይ የሆነ ህዝብ፤ ከገለፃ በእጅጉ የላቀ ውድ ምእመን!

ገዛ ያቀፈችው ግን ምን አይነት ህዝቦችን ነው? መኖርም መሞትም በናንተ ተዋበ።

በማያቋርጥ እሳት ውስጥ ሆነው የዛሬውን ጨለማ ነገ የሚያበሩ አዲስ ብርሃኖችን በመጠለያ ካምፓች ውስጥ መውለዱን ቀጥለዋል፤ ቁርኣንን በልባቸው ያኖሩ ህፃናት ሁፋዞችን በመጠለያ ካምፕ አስመርቃለች።

ጌታዬ ሆይ የመኖርም የመሞትም ምሳሌ አድርገሃቸዋልና በመንገዱ ላይ ትእግስትን ለግሳቸው፤ በትግሉም ላይ እግሮቻቸውን አፅና፤ በጠላቶቻችንም ላይ ድልን ለግሳቸው።
Arqem[አርቀም]
Voice message
🕋የጁሙዐ ቀን ሱናዎች🕌

1-ነቢዩ(صلى الله عليه وسلم)ላይ ሶለዋት ማውረድን ማብዛት

2- 📖 ሱረቱ–ከህፍን መቅራት

3-🚿 ሸዋር መውሰድ

4-⬜️ካለው ሻል ያለውን ልብስ መልበስ

5-🦷ሚስዋክ መጠቀም(ጥርስን መፋቅ)

6-🌹 ሽቶ መቀባት

7-🌅 ወደ መስጂድ አበክሮ መሄድ

8- ወደ መስጅድ በግር መሄድ

9-📿 ከጁሙዐ ሶላት ቡሃላ 4 ረከዓ(2+2) መስገድ

10- ዱዓ ተቀባይነት ያላትን ሰዓት መጠባበቅ


https://www.tgoop.com/ArkemMy
Sekeken Final_
<unknown>
ሰቀቀን (ግጥም)

የፉአድ ሙና አዲስ ግጥም 🙌
2025/03/09 01:43:37
Back to Top
HTML Embed Code: