tgoop.com/AwediMeherit/4262
Last Update:
#ደስ ይበልሽ#
-ቀዳሚት ሔዋንን ሰይጣንን ሸንግሎ ሞት ወደ ዓለም ገባ ፤ ዳግሚት ሔዋን ድንግል #ማርያምን ግን ቅዱስ #ገብርኤል አብሥሯት ሕይወት ተወለደልን።
-ሔዋንን ሰይጣን ሲያታልላት ብዙ መጠየቅ
እየቻለች አመነችው ፤ #እመቤታችንን ግን ቅዱስ #ገብርኤል ሲያበሥራት መረመረችው።
- ሔዋን መልአከ ጽልመትን አምና ነፍሰ ገዳዩ ቃየንን ወለደች ፤ ድንግል #ማርያም ግን ብርሃናዊውን መልአክ አምና ነፍሳችንን የሚያድነውን ወለደች።
- በሔዋን ከጸጋ መጉደልን ዐወቅን ፤ #በእመቤታችን በድንግል #ማርያም ግን በጸጋ መሞላትን ተረዳን።
"ደስ የተሰኘህ ሆነህ ምሥራችን የተናገርህ መልአኩ ቅዱስ #ገብርኤል ሆይ የተሰጠህ ክብር ታላቅ ነው።ወደ እኛ የመጣ (ሰው የሆነን) የጌታን ልደት ነገርኸን ለድንግል #ማርያምም ጸጋን የተመላሽ ሆይ #እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነውና ደስ ይበልሽ ብለህ አበሠርካት" (ውዳሴ #ማርያም ዘረቡዕ)
- ከሔዋን የተረፈውን ኃዘን ልጆቿ ሁሉ ለ5500 ዘመናት ተካፈሉ ፤ #ከእመቤታችን የተረፈውን ደስታ ግን ዓለም ሁሉ ተካፈለ።
-እኛም ከቅዱስ #ገብርኤል ጋር "ጸጋን የተመላሽ ደስተኛዪቱ ሆይ ደስ ይበልሽ"
-ከቅዱስ #ኤፍሬም ጋር "በሚገባ የአምላክ እናት ተብለሻልና ደስ ይበልሽ ፤ የሔዋን መድኃኒት ሆይ ደስ ይበልሽ" እንልሻለን።
#እመቤታችን #ማርያም ሆይ መልአከ ብሥራት አንቺን ደስ እንዳሰኘሽ ፤ በዛሬዪቱ ቀን ያዘንን እኛን ደስ አሰኚን!!!
-አማናዊ በዓለ ሱታፌ ያድርግልን አሜን!!!
#ኢዮብ ክንፈ
#ታኅሣሥ 22/2017 ዓ.ም
BY ዐውደ ምሕረት

Share with your friend now:
tgoop.com/AwediMeherit/4262