tgoop.com/Burhantube/199
Last Update:
ከሚስት ጋር በመኗኗር ዙሪያ የረሡል ﷺ ፈለግ
"በመልካምም ተኗኗሩዋቸው" ኒሳእ 119
•┈┈┈┈•✿🌼✿•┈┈┈┈•
❶ በሚስት ፊት ፈገግ ማለት
ረሡል ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
"በወንድምህ ፊት ፈገግ ማለትህ ላንተ ሰደቃ ነው" ቲርሚዚይ ዘግበውታል።
ባለቤትህ ስትሆን ደግሞ አስበሃዋል?
❷ ሚስትን በማጉረስ እሷን ማሞናደል
ረሡል ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
"አንተ አንድንም ነገር ምፅዋት አታደርግም ብትመነዳበት እንጂ፤ ወደ ሚስትህ የምታነሳው ጉርሻ እንኳ ቢሆን"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
➌ ትራፊዋን በመጠጣት ማሞናደል
አዒሻ رضي الله عنها እንዲህ አለች፦
ሀይድ(የወር አበባ) ላይ ሆኜ ሳለ የሚጠጣ ነገርን ጠጥቼ ለረሡል ﷺ አቀብላቸው ነበር፤ ከዚያም አፋቸውን አፌ ባረፈበት ቦታ አድርገው ይጠጡ ነበር"
ሙስሊም ዘግበውታል።
➍ ጭኗ ላይ መደገፍ
ዓኢሻ رضي الله عنها እንዲህ አለች፦
"ረሡል ﷺእኔ ሀይድ(የወር አበባ) ላይ ሆኜ ጭኔ ላይ ይደገፉ ነበር ቁርዐንንም ይቀሩ ነበር " ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
➎ አብሮ በአንድ ዕቃ መታጠብ
አዒሻ ፣ ኡሙ ሰለማ ፣መይሙና እና ኢብኑ ኡመር ባወሩት ሀዲስ
" ነብያችን-ﷺ- እና ባለቤታቸው በአንድ ዕቃ ይታጠቡ ነበር፤ አስቀሪልኝ(ውሃ) ይሏት ነበር እሷም አስቀርልኝ(ውሃ) ትላቸው ነበር"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
➏.....
#ትዳር
@nesiha_ouserya
BY Burhan Tube
Share with your friend now:
tgoop.com/Burhantube/199