BURHANTUBE Telegram 208
ያለንበትን ጊዜ የገንዘብ ዘካህ ኒሷብ (የግዴታው መነሻ መጠን) በተመለከተ ጥያቄዎች በርክተዋል፤ ይህን ከማስፈራችን በፊት ሁለት ቁም ነገሮችን ማስተዋል ያስፈልጋል፦

#አንደኛው፦ ይህ የሚመሰረትበት የወርቅ እና የብር ዋጋ ቋሚ ባለመሆኑ በየአመቱ የዘካው ግዴታ በደረሰበት ጊዜ (በረመዳንም ይሁን በሌላ ወር) የሚኖረው እለታዊ ዋጋ ላይ መመርኮዝ ተገቢ ነው። አንድ ጊዜ ተሰልቶ የተነገረ የገንዘብ ኒሷብ ለሁል ጊዜ አይሰራም።
በዚህ መሰረት ሰሞኑን በነሲሓ ቲቪ የተላለፈው ፕሮግራም ከአመት በፊት የተቀረፀ በመሆኑ ያኔ የተገለፀው የገንዘብ ኒሷብ ለዘንድሮ እንደማይሆን ልብ ይሏል።

#ሁለተኛው፦ ስሌቱን ስንሰራ የምንመረኮዘው በጌጣጌጥ መሸጫ ዋጋ ላይ ሳይሆን ማዕድኑ ከተጣራ በኋላ ሳይቀረፅ በፊት ባለው ቱባ ዋጋ ላይ ነው። ዘካህ የሚደነገገው በጌጣጌጥ ላይ ብቻ ሳይሆን በተጣራው ጥሬ ማዕድን ላይም በመሆኑ የዋጋ ልዩነቱን ማስተዋል ያሻል። ይህን ለማወቅ በየአገሩ ያለውን ዋጋ በየቀኑ፣ ብሎም በየሰዓቱ በሚያቀርቡ አስተማማኝ ድረ ገፆች (websites) መታገዝ ይቻላል።

በመሆኑም ሰሞኑን #ረመዳን_1442 ዓ.ሂ በአገራችን ያለው የጥሬ ብር ማዕድን አማካይ ዋጋ በግራም ወደ 35 ብር የተጠጋ ነው። ኒሷቡን ለማወቅ ይህን በ595 (የ200 ዲርሀም ክብደት በግራም) እናበዛዋለን፦

35 x 595 = 20,825

👉 የዘንድሮው ረመዳን ኒሷብ ወደ ሀያ ሺህ አካባቢ ነው ማለት ነው።

ስለዚህ ከዚህ ሳይቀንስ የጨረቃ አመት ያስቆጠረ ገንዘብ ያለው ሰው አንድ አርባኛውን (2.5%) ወጪ ያደርጋል።

ረመዳን 20/ 1442
___________

ስለ ወረቀት ገንዘብ የዘካህ ህግ አጭር ማብራሪያ ከፈለጉ የስረኛውን ያንብቡ።
====
በዘመናችን የዋጋ ተመንነትን ተክቶ የሚገኘው የገንዘብ ኖትን አነሳስና ታሪካዊ ሂደት፣ እንዲሁም በአሁኑ ወቅት ሊሰጠው የሚችለውን ሸሪዓዊ ብይን የተመለከቱ በርካታ ጥናቶች ተደርገዋል።
ባጭሩ የገንዘብ ኖት አነሳሱ ላይ ለወርቅ ወይም ለብር ባለቤትነትና ለእዳ ማረጋገጫ ሰነድ (ሪሲት) ሆኖ ሲዘዋወር ቆይቷል፤ ሆኖም ይህ ተጭባጭ ተቀይሯል።
የዛሬው የኢኮኖሚው ዓለም ነባራዊ ሂደት በግልፅ እንደሚያሳየው የወረቀት ገንዘቡን በሚወክለው የወርቅ ወይም የብር መጠን በባንክ የመቀየር መብት በመሻሩና ያለ ተቀማጭ የወርቅ ሽፋን መታተም በመጀመሩ በኖቶቹ እና በወርቁ ወይም በብሩ መካከል የነበረው ህጋዊ ትስስር ቀርቷል። በዚህም መሰረት የእያንዳንዱ አገር ገንዘብ (currency) የግዢ አቅም ከአገሩ የኢኮኖሚ ሀይል ጋር የተዛመደ ሆኗል።
ይህም ማለት የገንዘብ ኖት የሰዎች ዋነኛ መገበያያና የዋጋ ተመን መሆኑ በተዘዋዋሪ ከወርቅና ከብር ጋር ቢያመሳስለውም ከሁለቱ ጋር ያለው የእዳ ትስስር ቀርቶ ራሱን የቻለ የዋጋ ተመን ሆኗል።

ስለሆነም «ኒሷብ» የደረሰ የገንዘብ መጠን ኖሮት አመት ያሳለፈ ሙስሊም ከገንዘቡ 1/40ኛውን (2.5%) ለዘካህ መክፈሉ የግድ ይሆናል።

ታዲያ ዘካ ግዴታ የሚሆንበት አነስተኛ የገንዘብ መጠን (ኒሷብ) የሚገደብበት መሠረት የወርቅ ኒሷብ ዋጋ ወይስ የብር? የሚለውን ጥያቄ አስመልክቶ ውዝግብ ቢነሳም ብዙሀኑ የዘመናችን ሊቃውንት የመረጡት ሚዛን ደፊ አቋም በወቅቱ ከሁለቱ የኒሷብ ዋጋዎች አነስተኛ በሆነው ላይ እንደሚሆን ነው። ከላይ እንዳሳለፍነው የወረቀት ገንዘብ ራሱን የቻለ የዋጋ ተመን መሆኑ ከሁለቱ ኒሳቦች በአንዱ ላይ ብቻ ሳንወሰን ልክ አብዛኛዎቹ ቀደምት ሊቃውንት የንግድ ዘካህን አስመልክቶ እንደፈረዱት በየትኛውም በኩል አንደኛው የኒሷብ መሰረት ላይ መድረሱን ብቻ ከግምት እንድናስገባ ያደርገናል። ይህ ብዙ ሰዎች ዘንድ ወጪ የሚሆንውን የዘካህ መጠን ስለሚያበዛው ለዘካህ ተቀባዮች ይበልጥ ጠቃሚ ይሆናል።

ለምሳሌ፦
ዘካህ በሚወጣበት ወቅት የአንድ ግራም ወርቅ ዋጋ 2000 የኢት. ብር #ቢሆን ይህንን በ85 ስናበዛው የወርቅ ኒሷብን ዋጋ ይሰጠናል፦
2000 x 85 = 170,000 ብር ይሆናል፤

የብር (ሲልቨር) ዋጋ ደግሞ በግራም 30 ብር #ቢሆን ይህንን በ595 ስናበዛው የኒሷቡን ዋጋ ይሠጠናል፦
30 x 595 = 17,850 ይሆናል፤

ይህ ውጤት ከወርቁ የኒሷብ ዋጋ ያንሳል። በመሆኑም የገንዘብ ኖት ዘካህ በብር ዋጋ ላይ የተመሠረተ ይሆናል ማለት ነው።

የወርቁ ወይም የብሩ ጊዜያዊ ዋጋ በተቀየረ ቁጥር የኒሷቡም ዋጋ አብሮ መቀየሩ እንዳይረሳ።

በአሁኑ ጊዜ ያለው ተመን የሚያሳየንም የብር ኒሷብ ዋጋ ከወርቅ ኒሷብ ዋጋ እጅግ እንደሚያንስ ስለሆነ ቢያንስ 595 ግራም ጥሬ ብር የሚገዛ የገንዘብ መጠን ያለው ባለሀብት 1/40ኛውን (2.5%) ወጪ ማድረግ ይጠበቅበታል።

https://www.tgoop.com/ustazilyas

tgoop.com/Burhantube/208
Create:
Last Update:

BY Burhan Tube

Share with your friend now:
tgoop.com/Burhantube/208

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Hui said the messages, which included urging the disruption of airport operations, were attempts to incite followers to make use of poisonous, corrosive or flammable substances to vandalize police vehicles, and also called on others to make weapons to harm police. But a Telegram statement also said: "Any requests related to political censorship or limiting human rights such as the rights to free speech or assembly are not and will not be considered." Step-by-step tutorial on desktop: The Channel name and bio must be no more than 255 characters long You can invite up to 200 people from your contacts to join your channel as the next step. Select the users you want to add and click “Invite.” You can skip this step altogether.
from us

Telegram Burhan Tube
FROM American