Telegram Web
"...ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ለመርዳት ተጨማሪ ጥረት መደረግ ይኖርበታል" - የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC)

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ እና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በመተባበር በግጭት ለተጎዱ በሺዎች ለሚቆጠሩ ቤተሰቦች የውኃ፣ ምግብ እና መሰረታዊ ቁሳቁሶች አቅርቦት ላይ እየሰሩ እንደሚገኙ ተገልጿል።

በዚህ መሰረትም በቀርቡ በአፋር ክልል ከ16,000 በላይ ለሆኑ ሰዎች የመሰረታዊ የቤት ውስጥ ቁሳቁስ አከፋፍለዋል፡፡

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ለመርዳት ተጨማሪ ጥረት መደረግ ይኖርበታል ብሏል።

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ የአፍሪካ ቀጠና ዳይሬክተር ፓትሪክ ዩሱፍ ፥ “የግጭቱ ውጤት በኢትዮጵያ የሚገኙ የተለያዩ ክልሎች ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ነው፡፡ እኔም የሚደርሰው ጉዳት በጣም አሳስቦኛል፡፡ የተፈናቀሉ ሰዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እየኖሩ ይገኛሉ፡፡ አንዳንዶቹ በጣም በተጨናነቁ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ነው የሚተኙት ሌሎቹ ደግሞ በጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ እየኖሩ ነው” ብለዋል።

#ICRCEthiopia
ባለሃብቱ በሹ ቱሉ አረፉ።

የሲዳማ ክልል ካፈራቸው እውቅ የሀገራችን ባለሃብቶች መካከል በዋነኝነት ሚጠቀሱት ባለሃብቱ በሹ ቱሉ በህመም ምክንያት ማረፋቸው ተሰምቷል።

ባለሃብቱ በሹ ቱሉ በሆቴል ዘርፍ ጨምሮ በሌሎችም የስራ መስኮች ተሰማርተው ለበርካቶች የስራ እድል በማመቻቸት እራሳቸውን እንዲችሉ በማድረግ ሀገራቸውን ያገለገሉ ዜጋ ነበሩ።

በተለያዩ የስራ መስኮች ተሰማርተው ሀገራቸውን ከማገልገላቸው ባለፈ በሲዳማ ክልል ነዋሪዎች ዘንድ እንደ ነፃነት ታጋይም ይወደሳሉ።
#ItsMyDam

ከአሜሪካ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ወገኖች ከተሰባሰበው ገንዘብ ውስጥ ለ3ኛ ግዜ ወደ ኢትዮጵያ 🇪🇹 መላኩን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ አሳወቁ።

አሁን ከአሜሪካ የተላከው $757,294.78 ሲሆን በድምሩ $1,757,304.78 የአሜሪካን ዶላር በኢትዮጵያ የግድቡ የባንክ ሂሳብ ገቢ መደረጉን ገልፀዋል።

ለግድቡ ድጋፍ ማሰባሰቡ ስራ መቀጠሉንም አሳውቀዋል።
#Alert🚨

በሀገራችን በኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በእጅጉ እያሻቀበ ነው።

ዛሬ ምሽት ዘግይቶ በወጣው የጤና ሚኒስቴር እና የአትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት መሰረት በ24 ሰዓት 1,282 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

እነዚህ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች የተለዩት ከተደረገው 9,017 የላብራቶሪ ምርመራ ነው።

በሌላ በኩል በበሽታው ተይዘው የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በየዕለቱ እየጨመረ ሲሆን ባለፉት 24 ሰዓት 14 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

የፅኑ ታማሚዎች ቁጥርም 478 ደርሷል።
* ATTENTION

ከዛሬ ነሃሴ 15/2013 ጀምሮ በሰ/ሸዋ ዞን ሚዳ ወረሞ ወረዳ የሰዓት እላፊ ገደብ ተጥሎ ተግባራዊ መደረግ ጀምሯል።

የሰአት እላፊ ገደቡን የወሰነው የወረዳዉ ፀጥታ ምክር ቤት ነው።

የሚዳ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት አሁን ያለዉ የሃገሪቱ የሰላም ሁኔታ ከወረዳዉ መልክአ ምድር አቀማመጥ ጋር ሲነፃፀር አሳሳቢ ሆኖ በመገኘቱ የወረዳዉ ፀጥታ መዋቅር ዉይይት አካሄዶ ለፀጥታ ስጋት ነዉ በማለት የዉሳኔ አቅጣጫ አስቀምጧል ብሏል።

በዚህ መሰረትም ከዛሬ ነሃሴ 15/2013 ዓ.ም ጀምሮ ፦

1ኛ. መጠጥ ቤቶች ከንጋቱ 12 ሰአት እስከ ምሽቱ 2 ሰአት ድረስ #ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ ተወስኗል።

2ኛ. የግል አሽከርካሪዎች ሞተር ሳይክልን ጨምሮ ከምሽቱ 1 ሰአት በኋላ መንቀሳቀስ እንደማይችሉ ውሳኔ ተላልፏል።

3ኛ. ማንኛዉም የመንግስት ተሸከርካሪ ለስራ የወጡ ካልሆነ በስተቀር ከሁለት ሰአት በኋላ የትም ቦታ ከመንግስት ተቋም ዉጪ መቆም የለባቸውም ፤
- የጤና ባለሙያዎች፣
- የሃይማኖት አባቶች
- ለፀጥታ ስራ ከሚንቀሳቀሱ ሰዎች በስተቀር ከምሽቱ 3 ሰአት በኋላ እንቅስቃሴ የተገደበ ነው።

ህብረተሰቡ ማንኛውም አይነት #የተለየ_ነገር ከተመለከተ ጥቆማ ለመስጠት እነዚህን ስልክ ቁጥሮች ፦
• 096602287 ፣
• 0913146121
• 0901064105 መጠቀም ይችላል።
ካቡል ኤርፖር ት አካባቢ ውጥረት ነግሷል።

#ISIS የአፍጋኒስታን ቅርጫፉ ከአፍጋኒስታን የሚወጡ የአሜሪካ ዜጎች እና ሌሎችም ላይ ጥቃት ሊፈፅም ነው የሚል መረጃ በመገኘቱ በካቡል ኤርፖርት አካባቢ ውጥረት ነግሷል።

ቀደም ብሎ ካቡል ኤርፖርት መግቢያ ባለው የደህንነት ስጋት ከአፍጋኒስታን ሊወጡ ወደካቡል ኤርፖርት የሚሄዱ ሰዎች አዲስ መመሪያ እስኪደርሳቸው ወደኤርፖርት እንይሄዱ መልዕክት ከአሜሪካ ኤምባሲ ደርሷቸዋል፤ ነገር ግን የደህንነት ስጋቱ ምን እንደሆነ አልገለፀም ነበር።

አሁን ላይ አሜሪካ ዜጎቿን ጨምሮ ከአፍጋኒስታን ሚወጡ ሰዎች ወደኤርፖርት የሚገቡበትን አማራጭ መንገዶች እየፈለገች ነው ተብሏል፤ ይህም ከሀገሪቱ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ተሰምቷል።

እኤአ ከነሃሴ 14 ጀምሮ 17 ሺህ ሰዎች የአፍጋኒስታንን ምድር ለቀው የወጡ ሲሆን 2,500 የሚሆኑት አሜሪካውያን ናቸው። አሁን ላይ ወደ 5 ሺህ 800 የአሜሪካ ወታደሮች በካቡል ኤፖርት ጥበቃ እያደረጉ ነው።
ጄሲ ጃክሰን ሆስፒታል ገቡ።

በዓባይ ውኃና በኅዳሴ ግድብ ጉዳይ ኢትዮጵያን በመደገፍ የሚታወቁት እውቁ ጥቁር አሜሪካዊ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ጄሲ ጃክሰንና ባለቤታቸው በኮሮና ቫይረስ ተይዘው ሆስፒታል ናቸው፡፡

የ79 ዓመቱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ጃክሰን ባሳለፍነው ጥር ብዙዎች በተሳተፉበትና ብዙዎች እንዲከተቡ ባሳሰቡበት ይፋዊ ስነ ስርዓት የቫይረሱን ክትባት ወስደው ነበረ፡፡ ሆኖም አሁን በቫይረሱ ተይዘው ከ77 ዓመቷ ባለቤታቸው ዣኩሊዬን ጋር ህክምና ላይ ናቸው፡፡

ጃክሰን ምንም እንኳን የፓርኪንሰን ህመም ተጠቂ ቢሆኑም ጥቁሮች የኮሮና ክትባቶችን እንዲያገኙ ሲቀሰቅሱ እና ሲያስተምሩ ነበር፡፡

የድምጽ አሳጣጥ መብቶችን በተመለከተ የአሜሪካ ኮንግረስ የያዘውን አቋም እንዲተው ለማሳሰብ በያዝነው ወር መባቻ በካፒቶል ሂል ሲደረጉ ከነበሩ ሰልፎች ጋር ተያይዞ ለእስር ተዳርገውም ነበረ፡፡

ከወጣትነት ዕድሜአቸው አንስቶ ከዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጋር ስለ ሲቪል መብቶች በመሟገት የሚታወቁት ጃክሰን በዓባይን ውኃ እና በኅዳሴ ግድብ ጉዳይ ኢትዮጵያን በመደገፍ ይታወቃሉ፡፡

ግብፅ በናይል ውሃ ላይ አለኝ የምትለውን “ታሪካዊ መብት” የቅኝ ግዛት ዘመን መብት እንዲሁም የዐረብ ሊግን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ይታወቃሉ፡፡

የግድቡን ጉዳይ በተመለከተ በግብጽ እና ዐረብ ሊግ ተጽፈው ለተመድ ጸጥታው ም/ቤት የገቡ ደብዳቤዎችን ጉዳይ ጥቁር የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት ኮሚቴ /Congressional Black Caucus እንዲቃወም ከአሁን ቀደም ጥሪ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው፡፡

ከፍ ያለ ተደማጭነት ያላቸው ቄስ (ሪቨረንድ) ጄሲ ጃክሰን ለሁለት (2) ያህል ጊዜ ለአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት ተወዳድረው እንደነበር የህይወት ታሪካቸውን የተመለከቱ ዘገባዎች ይጠቁማሉ፡፡

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ
ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ለተሽከርካሪዎች ዋስትና የሚያስከፍሉት የዓረቦን መጠን ጨመረ።

የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ከወቅታዊ #የዋጋ_ንረት ጋር በተያያዘ የዋስትና ሽፋን ለሚሰጧቸው ንብረቶች የሚያስከፍሉትን የዓረቦን መጠን እየጨመሩ መሆኑን ሪፖርተር አስነብቧል።

ኩባንያዎቹ በተለይ በሞተር ኢንሹራንስ ዘርፍ ለተሽከርካሪዎች የመድን ሽፋን ይጠይቁ የነበረውን የዓረቦን መጠን ከመቼውም ጊዜ በላይ መጨመራቸው ታውቋል ብሏል ጋዜጣው።

ኩባንያዎቹ ለሚሰጡት የመድን ሽፋን ይጠይቁ ከነበረው ዋጋ እስከ እጥፍ ጭማሪ እየጠየቁ መሆኑን የኩባንያዎቹ ደንበኞች እየገለጹም ነው፡፡

ደንበኞቹ የተሽከርካሪ የመድን ሽፋን ሲያሳድሱ በወቅቱ የተሽከርካሪዎች ዋጋ መሠረት ዓመታዊ የዓረቦን ክፍያቸውን እንዲፈጽሙ እየተደረገ ነው፡፡

የኩባንያዎቹ ደንበኞች እንደሚገልጹት ከሆነ ፣ የተሽከርካሪዎቻቸውን የኢንሹራንስ ሽፋን ለማሳደስ ሲቀርቡ ከዚህ ቀደም ሲከፍሉ ከነበረው የዓረቦን ዋጋ በላይ እየተጠየቁ ነው፡፡ ከኩባንያዎቹ የተገኘው መረጃም ፣ ጭማሪ ሳይሆን ወቅቱን ያገናዘበ ማስተካከያ እየተገረገ ነው፡፡

ይህ የተለመደ አሠራር ሲሆን፣ የአሁኑን የሚለየው ከሌላው ጊዜ በተለየ የተሽከርካሪዎች ዓረቦን ዋጋ ጭማሪ ከፍተኛ መሆኑ ነው፡፡ 

አንዳንድ ደንበኞችም አደጋ ደርሶባቸው የጉዳት ካሳ በሚጠይቁበት ወቅት የኢንሹራንስ ሽፋናቸው በወቅታዊው ተሽከርካሪዎች ዋጋ መሠረት ገቢ እንዲያደርጉ መጠየቃቸውንም እያመለከቱ ነው፡፡

የሪፖርተርን ዘገባ ያንብቡ : telegra.ph/Reporter-08-22
ሐጂ የሱፍ አደም አረፉ።

በደሴ ከተማ ከ50 አመት በላይ የአረበኛ እውቀትን ሲያስተምሩ የኖሩት ሐጂ ዩሱፍ አደም ማረፋቸው ተሰምቷል።

ሐጂ ዩሱፍ አደም ለደሴ ህዝበ ሙስሊም የአረብኛ እውቀት አባት ነበሩ።

ወጣቱ የአረብኛ እውቀትን ሲማር ከእሳቸው እውቀት ያልተቋደሰ እንደሌለ ይነገራል።

ለደሴ ከተማ ወጣቶች ትልቅ የእውቀት ባለውለታ ፣ የእድሜ ባለፀጋ ፣ መካሪ እና አቃፊ አባት ነበሩ።

መረጃው ከኡስታዝ አቡበክር አህመድ ነው የተገኘው።
#COVID19

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 785 የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ8 ሰዎች ህይወት ደግሞ ጠፍቷል።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 6,108 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 785 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

በተመሳሳይ በ24 ሰዓታት ውስጥ 8 ዜጎች ህይወታቸው አልፏል።
አሜሪካ ህወሓት /TPLF/ ከአፋር እና አማራ ክልል እንዲወጣ ጥሪ ማቅረቧን ቀጥላለች።

የUSAID ዋና አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር ዛሬ ምሽት በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው ላይ አሜሪካ ህወሓት /TPLF/ ግጭቱን እንዲያረግብና ከአፋር እና አማራ ክልሎች ወጥቶ ለድርድር እንዲቀመጥ ጥሪ ማቅረቧን ትቀጥላለች ብለዋል።

ሳማንታ ፓወር ፥ የህወሓት /TPLF/ ጥቃት ይህንን ግጭት እና የኢትዮጵያን ህዝብ ስቃይ ብቻ ያራዝመዋል ሲሉ ፅፈዋል።

በተጨማሪ USAID በዚህ ሳምንት በአፋር እና አማራ ክልል በግጭት ለተጎዱ ከ136 ሺህ በላይ ሰዎች ምግብ ማድረስ መጀመሩን አሳውቀዋል።

በአፋር እና አማራ ክልል ህወሓት /TPLF/ በፈፀመው ጥቃት በመቶ ሺዎሽ የሚቆጠሩ ሰዎች ከቤታቸው መፈናቀላቸውን ሳማንታ ፓወር በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።
ሙሐመድ አወል ሙሐመድ ሳላህ አረፉ።

በበርካታ የጥበብ ስራዎች የሚታወቁት ድምፀ መረዋው ሙሐመድ አወል ሳላህ በልብ ህመም ማረፋቸው ተሰምቷል።

ትውልዳቸው በደሴ ከተማ አራዳ አካባቢ ሲሆን ከእናታቸው ከወ/ሮ ሰዕዲያ ሰዒድ አህመድ እና ከአባታቸው ሐጅ ሙሐመድ ሳላህ አህመድ በ1958 ነበር የተወለዱት።

ትምህርታቸውን በወ/ሮ ስህን ትምህርት ቤት ከተከታተሉ በኋላ ወደ ውትድርናው አለም በመቀላቀል ሃገራቸውን ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

በወታደር ቤትም በሙዚቀኝነት ሲያገለግሉ ቆይተው ወደሳውዲ ዓረቢያ በማቅናት ለ7 ዓመታት ቆይታ አድርገው ወደ ሃገራቸው በመመለስ የጥበብ ስራቸውን ቀጥለው ነበር።

በኋላም የዓለማዊውን የሙዚቃ አለም በመተው ወደ መንፈሳዊ ህይወት በማዘንበል ህይወታቸው እስካለፈችበት እለት ድረስ ሙሉ በሙሉ የበተለያዩ የኢስላማዊ የኪነጥበብ ስራዎች ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

ሙሐመድ አወል በሙዚቃ ዓለም ከሰሯቸው ስራዎች ባሻገር በእስልምናው ዓለም በርካታ የጥበብ ስራዎችን አበርክተዋል፦
-የለኝ በጎ ሥራ
-ሙሐመድ ተብዬ
-እመስገጃሽ ላይ ታገሺ
-ውዴታ እስከጀነትና ሌሎችም የተካተቱበት ሶስት አልበሞችንና በርካታ ነጠላ ነሺዳዎችን አበርክተዋል።

ሙሐመድ አወል ሳላህ ከሚታወቁበት የጥበብ ሥራ በላቀ መልኩ የበጎ ተግባራት ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ እንዳላቸው የቅርብ ወዳጆቻቸው ይመሰክራሉ።

ባለትዳርና የ6 ልጆች አባት የሆኑት ሙንሺድ ሙሐመድ አወል ሳላህ ለረጅም ግዜ የዘለቀ ልብ ታማሚ የነበሩ ሲሆን በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ህክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው ትላንት ሌሊት ከሌሊቱ 9 ሰዓት አካባቢ ህይወታቸው እንዳለፈች ከቤተሰቦቻቸው ተሰምቷል።

የቀብር ስርዓታቸው ኮልፌ በሚገኘው የሙስሊም መካነ መቃብር ዛሬ ነሐሴ 17 ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ ይፈፀማል።

የመረጃ ባለቤት: ሚንበር ቲቪ
#Djibouti : በጅቡቲ በኩል ወደ ኢትዮጵያ እያቀኑ የሚገኙት የተ.መ.ድ (UN) ምልክት ያለባቸው ተሽከርካሪዎች ንብረትነታቸው የኢትዮጵያ መንግስት ናቸው ሲል በጅቡቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በይፋዊ ትዊተር ገፁ አሳውቋል።

እነዚህ ተሽከርካሪዎች በዳርፉር በ #UNAMID ስር በሰላም ማስከበር ስራ አገልግሎት ላይ ሲውሉ የነበሩ ናቸው።
2025/06/12 08:41:03
Back to Top
HTML Embed Code: