tgoop.com/Campus_love/1939
Last Update:
አዲስ የጎሀው
እንሆ ጀመረ 👇👇👇
....የሀዘኔ መጨረሻ....
....ክፍል 1 .....
☺️☺️😍😍☺️☺️
.....ሰላም እባላለሁ ታሪኬን ላካፍላችሁ ያኔ 17 አመቴ ነበር የ10ኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩኝ :: የምኖረው ከእናት አባቴ እንዲሁም ከወንድሜ ጋር ነበር፡፡ አባቴ የኮንስትራክሽን ባለሙያ ነበር፡፡ እናቴ የህክምና መስጫ ተቋም ውስጥ ዳይሬክተር ነበረች፡፡ ያው ዶክተር ማለት ነው፡፡ እሁድ እሁድ ከእንቅልፌ የምነሳው 4 ሰዐት ነበር ፡፡ በ1እሁድ ቀን ግን የተነሳሁት 2 ሰዐት ነበር፡፡ ምክንያቱም አቤል ቤተ ክርስቲያን እንሂድ ስላለኝ፡፡
......አቤል የ 7 አወት ታናሽ ወንድሜ ነው፡፡ አቤልን በጣም እወደዋለው፡እናም መኝታ ክፍሌ ገብቶ "ሰሊ ሰሊ ተነሺ" አለኝ አይኔን እያሻሸሁኝ "በጌታ ተወኝ" አልኩት፡፡"ተነሺ ቤተ ክርስቲያን እንሂድ በናትሽ" አለኝ፡ ትንሽ ከተግደረደርኩኝ በኀላ "እሺ" አልኩት፡፡ ደስ ብሎት ከአልጋዬ ሊወርድ ሲል "ግን" ብዬ እጁን ያዝኩት ፡፡ዞር ብሎ "ምን" አለኝ እየተቅለሰለስኩኝ "ያው የሳምንት ብር ተሰቶሀላ"አልኩት"፡፡እናትና አባታችን የሳምንት ብለው እሁድ ጠዋት ከእንቅልፋችን ስንነሳ ብር ይሰጡናል፡፡ አቤልም ድምፁን ቀነስ አድርጎ "አው"አለኝ፡፡ "እሺ የተሰጠህን ብር ግማሹን ትሰጠኛለህ"አልኩት "አልሰጥሽም" ሲለኝ ተመልሼ ተኛው::
...ትንሽ ከቆየ በኀላ ባዘነ ድምፅ "እሺ "አለኝ፡፡ ከዛ ተነስቼ ተጣጥቤ ሄድን፡፡ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ሲያልቅ ትንሽ ቁጭ አልን፡፡ በድንገት የሆነ ልጅ መጣና እጄን ያዘኝ፡፡ዞር ብዬ በግርምት "አቤት" አልኩት ከዛ "ይቅርታ ከሰው ጋር ተመሳስለሽብኝ ነው" አለኝ፡፡ እኔም"እሺ ምንም ችግር የለውም "ብዬ ዞር አልኩኝ፡፡ ድጋሚ መጥና...........
ክፍል 2 እንዲለቀቅ like . Share ❤️በማረግ ተባበሩን....
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
••●◉Join us share
❣
┄┄┉┉✽̶»̶̥🌺✿🌺»̶̥✽̶┉┉┄┄
BY Campus love ❤ Stories
Share with your friend now:
tgoop.com/Campus_love/1939