tgoop.com/Campus_love/1944
Last Update:
የሀዘኔ መጨረሻ....
....ክፍል 5....
......በግድ እንድሄድ አደረገች...... እኔም እሺ ብዬ ሄድኩኝ፡፡ ክፍል ውስጥ እያለሁ አንዴ ልቤ ይፈራል አንዴ በጣም ይጨነቃል ፡፡ብቻ መማር አይበለው እንደነገሩ ሆኜ የመለቀቂያ ሰዐታችን ደረሰ፡፡እኔም አቤልን ይዤ እየተጣደፍኩኝ ወደ ቤት ሄድን፡፡ እቤት እንደደረስን የግቢው በር ክፍት ነበር፡፡ቶሎ ብዬ ገባሁኝ ፡፡ማስቴ" እነዚህን የመሰሉ ልጆች ለማን ጥለሽ" እያለች ታለቅሳለች፡፡ ቦርሳዬን መሬት ላይ ጣልኩት እንባዬ ከአይኔ ላይ ድብ ድብ አለ፡፡ ልቤ እንደመትረይስ መታች፡፡ እግሮቼ ተንቀጠቀጡ፡፡ አፌ ተርበደበደ ምን ማድረግ እንደነበረብኝ አላወኩም ነበር፡፡
.......ቶሎ ብዬ ወደ ቤዚ መኝታ ክፍል ሄድኩኝ፡፡ ፊትዋ በነጭ ነጠላ ተሸፍኖ ነበር፡፡ በዛ ሰዐት በድን ሆንኩኝ፡፡ ጎረቤቶቻችን ክፍሉ ውስጥ ነበሩ ከክፍሉ ሊያሶጡኝ ሞከሩ፡፡እኔም " ለምን ታሶጡኛላችሁ ቤዚን ልያት እንጂ " አልኳቸው፡፡እጄን ለቀውኝ ማልቀስ ጀመሩ፡፡ ቤዚ ሞታ ነበር ማልቀስ ጀመርኩኝ፡፡የምር ማመን አልፈለኩኝም ነበር ግን ቤዚ ጠዋት አቤልን አደራ ብላኝ ነበር ይህን ሳስታውስ ተንበርክኬ ማልቀስ ጀመርኩኝ፡፡ ቤዚን ይዣት "ቤዚ እናቴ አልኳት"ግን ምንም መልስ የለም ነበር፡፡ በዛ ሰዐት " አቤት ሰሊ" እንድትለኝ በጣም ፈልጌ ነበር፡፡ ግን እሷ ዝም ነበር ያለችው፡፡ ወድያው አቤል መጣ፡፡"እማ " አላት "ቤዚ አሁንም ዝም አለች፡፡ አቤል ሳያስበው እንባዎቹ ወረድ፡፡ እኔና አቤል ተቃቅፈን ተላቀስን፡፡ ወዲያው ሙሌ መጣ፡፡ ሲያየን በጣም ደነገጠ ፡፡ ማልቀስም ጀመረ"ወይኔ ፍቅሬ ...ወይኔ ምነው ጨከንሽ እኛን ለማን ጥለሽ"እያለ ማልቀሱን ቀጠለ፡፡ ጎረቤቶቻችን ቶሎ አሶጡን፡፡ውጪ ላይ ተንበርክከን ሶስታችንም ተቃቅፈን እየጮህን ማልቀስ ያዝን ፡፡ ሁላችንም በጣም አዝነን ነበር፡፡ብዙ ካለቀስን በሁዋላ ልቤ ላይ ትልቅ ቁስል ያለ ይመስል ተንገበገብኩኝ፡፡የሚገርመው አቤልን ሳየው ቤዚ የነገረችኝ ነገር ትዝ እያለኝ እንባዬ ሳላስበው እንደጉድ ይወርዳል ።ሙሌም አልቻለም የሚገርመው እንደዚህ አይተነው አናውቅም ነበር ። እያየን አንገቱን ደፍቶ ያነባል ያው ቤዚም ከሁለት ቀን በኀላ ተቀበረች የቀብሩ ቀን በጣም ያስጠላ ነበር ማስታወስ እራሱ አልፈልግም እኔ በዛ ሰዐት የእናቴ እቅፍ እፈልገው ነበር ። ትንፋሽ ባይኖራት እንኳን ብታቅፈኝ ብዬ ተመኘው ። ህይወታችን በሙሉ ተቀየረ ቤዚ በጣም ነበር የምትናፍቀን ሙሌም እራሱን ጥሎል ። በዚህ ሁኔታ ቀናት ወራት ተቆጠሩ ።
........ሰኞ ቀን ወደ 4 ሰዐት አካባቢ ፖሊሶች ቤታችን መጥተው ሙሌን ይዘውት ሄዱ እኛም ተከትለናቸው ሄድን ፖሊስ ጣቢያ እንደደረስን ሙሌን የሆነ ክፍል ውስጥ አስገቡት። እኔና አቤልም ወደ መርማሪው ክፍል ገብተን ምን እንደተፈጠረ ጠየቅን ።መርማሪውም" ልጆች ከናንተ ከፍ የሚል ሰው የለም" አለን "አው የለም ለምንድን ነው አባታችንን ያሰራቹት" አልኩት እሱም በረዥሙ ተነፈሰና "አባትችሁ ወንጀል ሰርቷል.... ልጆች አለን" ጉጉት ይሁን ፍርሀት አላውቅም ግን መልሱን ለመስማት በሚፈልግ ስሜት ሆነን ሁለታችንም በእኩል ድምፅ ምን አልነው። ይህን ለኛ መናገር አልፈለገም ግን ግድ ስለሆነበት መሰለኝ "አባታችሁ ባለቤት የሌላቸውን ፎቆች ሲሰራ ተገኝቷል ለዛ ነው "አለን ወድያው ሁሉም ነገር ትዝ አለኝ ። ያ እራት የጋበዘን ቀን የነገረን ነገር ፤ ቤታችን መጥቶ የቤት ካርታውን የወሰደው ሰውዬ ፤ ያ የቤዚና የውሌ ጭቅጭቅ ትዝ እያለኝ ጭንቅላቴን ሊያፈነዳው.........
ክፍል 6 እንዲለቀቅ like ማድረግ አትርሱ
BY Campus love ❤ Stories
Share with your friend now:
tgoop.com/Campus_love/1944