tgoop.com/Campus_love/1945
Last Update:
....የሀዘኔ መጨረሻ.....
ክፍል 6
........ሊያፈነዳው ደረሰ፡፡ ወድያው እራሴን ሳትኩኝ ፡፡ አፋፍሰውኝ ስታፍ አስገቡኝ ስነቃ አቤል እጄን ይዞኝ ያለቅሳል። መርማሪው ቆሞ እጁን አፉ ላይ ደቅኖ በግርምት ያየናል፡፡ ሌሎችም ሁለት ፖሊሶች ነበሩ፡፡ መንቃቴን ሲያዩ "አይዞሽ ተረጋጊ ተረጋጊ" አሉኝ። አቤል እያለቀሰ "ሰሊ አንቺም እንደነሱ አትተይኝ እባክሽ" አለኝ ::እነሱን ያለው ቤዚን እና ሙሌን ነው እያለቀስኩኝ አይኖቹን በስስት እየተመለከትኩኝ "እንዴት ወንድሜ እንዴት እንደዚ አደርጋለው" አልኩት:: እቅፍ አደረገኝና "እህቴ በጣም እወድሻለው "አለኝ እቅፍ አድርጌ እኔም አልኩት ...
ትንሽ ከተረጋጋሁኝ በኀላ ወደ ቤት ሄድን ፡፡ ማስቴ በጣም ጨንቋት ነበር ቤቱን ለማን ጥዬ እሄዳለው ብላ ነው እንጂ መምጣት ፈልጋ ነበር፡፡ ልክ እንደደረስን "ሰሊ ምንድን ነው" አለችኝ ሁሉንም ነገር ነገርኳት እጇን አፏ ላይ አድርጋ በግርምት እኔን ማየት ጀመረች ፡፡ እኔም "በቃ አሁን ትንሽ ልረፍ "ብያት ወደ ክፍሌ ሄድኩኝ፡፡
ክፍሌ ገብቼ አልጋዬ ላይ ጋደም ልል ስል አቤል "ሰሊ" አለኝ::እኔም የሚነግረኝን ለመስማት ውስጥ ባለ ስሜት "ወዬ" አልኩት:: በስስትና በፍርሀት ያየኝ ጀመረ ፡፡ምን ሆንክብኝ አልኩት ፡፡እሱ ግን ዝም ብሎ እያየኝ ነበር ፡፡እጁን ጉትት አድርጌ እቅፍ አድርጌው ፀጉሩን እያሻሸሁኝ" አይዞህ ወንድሜ እኔ አለሁልህ ምንም እንድትሆን መቼም ቢሆን አልፈቅድም" አልኩት:: ሁለታችንም ተቃቅፈን ትንሽ ተኛን፡፡ስንነሳ ማስቴ ምግብ ሰራርታ ነበር እሱን በላልተን ወደ ሙሌ ጋር ሄድን:: ግን መግባት አትችሉም ተባልን መርማሪው በጣም ስላሳዘንነው ከሙያ ስነምግባሩ ውጪ ሆኖ ሙሌን አሳየን ፡፡ሁለታችንም ሙሌን ስናየው በጣም ደስ አለን ሙሌም እያለቀሰ "ልጆቼ ይቅር በሉኝ "አለን ፡፡"አባ ሁሉን ነገር ካንተ መስማት እፈልንለው" አልኩት:: እሱም ሁሉንም ነገር ነገረን ይቅር በሉኝ አለን "እያለቀስኩኝ አባታችን ነህ እኮ እንዴት ይቅርታ አናረግልህ አንተ ፈልገህ አይደለም እንደዚህ የሆነው ሁሉም በእግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ነው ከልባችን ይቅር ብለንሀል" አልኩት::እኔንም አቤልንም እቅፍ አደረገን:: ገና የአባቴን እቅፍ ሳልጠግበው መርማሪው"በቃ ሰዐት አልቋል" ብሎ ሙሌን ይዞት ሄደ ፡፡እኛም ወደቤት ተመለስን ከሁለት ቀን በኀላ ሙሌ ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡ ዳኛውም የ13 ዐመት ፅኑ እስራት ፈረደበት፡፡
......አቤል "አባቴን አትውሰድብኝ እባካችሁ" እያለ ያለቅሳል እኔ ምንም ማድረግ አልቻልኩም:: አቤል እንደዛ ሆኖ ሳየው የቤዚ ቃል በአእምሮዬ ላይ ድቅን ይሉብኝ ነበር፡፡ተቀምጬ አይኔን እንኳን ለማርገብገብ ሳልደፍር አለቀስኩኝ ፡፡ፖሊሶቹም ሙሌን ወሰድት ፡፡ማስቴ አቤልን ያዘችው ፡፡ሙሌ "አይዟቹ ልጆቼ" ሲል ይሰማኛል ነገር ግን አንገቴን ለማዞር እንኳን አቅሙ አልነበረኝም ነበር፡፡ ሁሉም ከሄድ በኀላ ማስቴ በሉ ወደቤት እንሂድ አለችን አቤል እያለቀሰ አባቴን ጥዬው አልሄድም አላት:: እሷም በሀዘን ተውጣ ማልቀስ ጀመረች፡፡ ድንገት ሳይታሰብ ከተቀመጥኩበት ተነስቼ እንባዬን እየጠራረኩኝ "በቃ እንሂድ አልኳቸው" አቤል "አልሄድም አለኝ" ተኮሰታትሬ "አይ እንግዲ" ብዬ እጅን እየጎተትኩኝ ከፖሊስ ጣቢያ ወጣን፡፡ እኔ የአቤልን እጅ ይዤ በፍጥነት እየተራመድኩኝ ነው ማስቴ ከኀላችን እየሮጠች ትከተለናለች፡፡ አቤልም ማስቴም "ሰሊ ሰሊ ...."ብለው ይጠሩኛል እኔ ግን ዝም ብዬ መንገዴን ቀጥያለው በድንገት.............
ክፍል 7እንዲቀጥል like ማድረግ አትርሱ
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
BY Campus love ❤ Stories
Share with your friend now:
tgoop.com/Campus_love/1945