tgoop.com/Capitalethiopia/12081
Create:
Last Update:
Last Update:
#CapitalNews ከሁለት ዓመታት በፊት በባንኮች ላይ ተጥሎ የነበረዉ የብድር ጣሪያ በመጪው በመስከረም ሊነሳ እንደሆነ ተገለፀ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከመጠን በላይ በሆነ የብድር ስርጭት ምክንያት የተከሰተዉን ከፍተኛ የዋጋ ግሽበትን ለመቋቋም በሚል ከነሐሴ 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ባንኮች በሚሰጡት የብድር ጣሪያ ላይ ገደብ ጥሏል።
ከሁለት ዓመት በፊት ወደ ስራ የገባው የብድር ጣሪያ ባንኮች አመታዊ የብድር እድገታቸው ከቀደመው የብድር ክምችት መጠን በ14 በመቶ ብቻ እንዲያድግ የሚያደርግ የነበረ ሲሆን ባለፈው ወር መጨረሻ እድገቱ ወደ 18 በመቶ እንዲሆን በማዕከላዊ ባንኩ ተወስኖ ነበር።
ሆኖም ካፒታል ከተቋሙ ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ባንኮች የሚሰጡት የብድር መጠን ላይ ተጥሎ የቆየው ጣሪያ በቀጣይ መስከረም ይነሳል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን በዚህም በቀጣይ በዘርፉ ሊኖር የሚችል እድገት የተሻለ እንደሚሆን ከአሁኑ ተስፋ ተጥሎበታል።
አይኤምኤፍ በተራዘመ የብድር አቅርቦት ስር ባደረገው የቅርብ ጊዜ ግምገማ፣ የገንዘብ እና የፋይናንስ ሁኔታዎች ጥብቅ ሆነው የቆዩ ቢሆንም የአዲሱ የገንዘብ ፖሊሲ ማዕቀፍ ውጤታማነት አሁንም ደካማ ነዉ ሲል ገልጿል።
BY Capitalethiopia
![](https://photo2.tgoop.com/u/cdn4.cdn-telegram.org/file/UJy6kVyQV6dRssb-h2FOP-0_f1e7cOM2NL6nWhd5mwZLwIdrYhJUqVnHylSLl72i7shIyQ74-GIVh0hQZ312U00iiJ8NW33iAd_GwD0sVrY3YFrNEUa6CQRGiqWMEreWbLuCbzfifIhP1GRqSTdHdEV0-0WpiC85M834ADgNrE6bwJChCpZh3nVqN6BiUSVX1dTwxOjntQDKZzRemOqJFp0Xq1ni01NK6rLAG3QKf1P12r8wOqpARm3DjYxMPa1DsY3TKN7bw22gOuCZQGe9ppHJPPYWZqUYwSC99Q-SSOWSXniEdbVX984KIDb2bCc7CGZPZnUm63JmHRyYaLsw-g.jpg)
Share with your friend now:
tgoop.com/Capitalethiopia/12081