tgoop.com/DBU11/6505
Create:
Last Update:
Last Update:
የተማሪዎች ህብረት የተማሪ ህብረት ስራ አስፈፃሚ አባሎችን (የፓርላማ አባል) በየትምህርት ክፍሉ እና ክላሱ እያስመረጠ ነው ነገር ግን በምርጫ ሒደቱ ከተማሪዎች ከፍተኛ ትችት እና ቅሬታ እየቀረበበት ነው። ህብረቱ ትክክል ያልሆነ የምርጫ ሒደት እንቅስቃሴ ማድረግ ለምሳሌ ብዙ ቁጥር ያላቸው የክላስ ተማሪዎች ባልተገኙበት ምርጫ ማድረግ ፤ ከዚህ በፊትም የፓርላማ አባል ያልሆኑ ተማሪዎችን ያልተገባ ሓላፊነት መስጠት ተመልክተናል።
መረጃውን አስቀድሞ ለተማሪዎች ማድረስ ሲኖርበት ህብረቱ በይፋዊ የቴሌግራም ገፁ የፓርላማ ምርጫ እንደሚያካሒድ አለማሳወቁን Daily news ተመልክታለች።
የተማሪ ህብረት የተማሪዎችን መብት በተጋፋ መልኩ እንቅስቃሴዎችን ማድረጉ የተማሪዎችን ችግር መፍታት እንዳይችል ያደርገዋል።
የተማሪዎች አገልግሎት ዲን ፅህፈት ቤት በዛሬው እለት ባወጣው ማስታወቂያ እንደዚህ አይነት ችግሮች እና ቅሬታ ካለ ማንኛውም ተማሪ ሪፓርት ማድረግ እንደሚችል ገልፃል።
ማስታወቂያው ችግሮች እንዳሉ የሚያሳይ ነው።
@ dbu11
@dbu111
BY DBU Daily News

Share with your friend now:
tgoop.com/DBU11/6505