tgoop.com/DBU11/6506
Last Update:
የተማሪ ህብረት ምርጫን በተመለከተ የቀረበ ምልከታ ።
የተማሪ ህብረት ምርጫ ላይ ቅሬታ ማቅረብ እና :በእርግጥ አይወክለንም የምትሉትን እጩ በምክንያታዊ ማስረጃ እስከ መጨረሻው በመጋፈጥ : ምርጫው ፍትሀዊ እንዲሆን ማድረግ የምትችሉት እራሳችሁ ተማሪዎች ናችሁ ።
በየትኛው የሀገሪቷ ዩኒቨርሲቲ ያለ ተማሪ ህብረት በስልጣኑ ካድሬነት ከመለማመድ የዘለለ ሚና ባይኖራቸውም ለተማሪው የሚሠሩ አንዳንድ ተመራጮች ይኖራሉና ምርጫችሁን በደንብ መለየት ይገባችኃል ።
የተማሪ ህብረት ሆኖ የሚረጠው አካልም : ስልጣን የሰጠውን ተማሪ ማገልግል እንጂ :እንደ ትልቅ ስልጣን ከተማሪው መገለል አይገባውም ።
በቅርበት የተማሪ ህብረት አደረጃጀት እና ስራዎቹን የሚያውቁ ምንጮቻችን በተዳጋጋሚ የተማሪ ህብረት የጥቅም ሽኩቻዎች የሚታዩበት በመሆኑ ምርጫው ጥንቃቄ ያሻዋል ይላሉ ።
የተማሪ ህብረት ምርጫን ለማከናውን በተሰጠው ቀነ ገደብ እጩን ማሳወቅ እና ቅሬታን ለይቶ ማቅረቡ ሲገባችሁ ዝምታ የመረጣችሁ :የኃላ ተቺዎች በቴሌግራም ጫጫት እና ዛቻ የሚቀየር ተቀይሮም የሚያውቅ ነገር ባለመኖሩ እድላችሁን ተጠቀሙ ።
ለትምህርት እሰከ መጣችሁ ድረስ ከመማር ውጭ ሌላ አላማ ያነገባችሁ ተማሪዎች : ዩኒቨርሲቲው በ2011ዓ.ም የትምህርት ስራውን ሊያስተጓጉሉ በሞከሩ ተማሪዎች ላይ የወሰደውን ዘግናኝ የመጫር ታሪክ እንዳይደግምባችሁ : አላማችሁን ወደ ትምህርት ብታደርጉ ተማራጭ ይሆናል ።
📌ይህ መልክት የተማሪ ህብረት የምርጫ ሂደት እና የቅሬታ የሚመለከት ብቻ መሆኑን እንድታውቁ ይሁን
@DBU11
@DBU11
BY DBU Daily News
Share with your friend now:
tgoop.com/DBU11/6506