tgoop.com/DBU11/6507
Last Update:
የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ለአንድ ዓመት እንዲያስተምሩ ሊገደዱ ነው
📌ከ2019 ተመራቂዎች ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል
ትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከመመረቃቸው በፊት ማኅበረሰቡን ለአንድ ዓመት በቅድሚያ እንዲያስተምሩ ወይም እንዲያገለግሉ የሚያደርግ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ ዕቅድ መያዙን አስታወቀ።
ትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ.ም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሃብት ልማት፣ ሥራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ውጤት ዝቅተኛ የሆነበትን መንስዔ በተመለከተ በቀረበ ጥናት ላይ ውይይት ሲደረግ፣ በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ ስለተያዘው እቅድ አብራርተዋል።
''የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ሰርቪስ'' የሚል መጠሪያ የተሰጠው አሠራር ከ2019 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ዕቅድ የተያዘ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ "በአራት ዓመት የሚመረቅ ተማሪ፣ የሦስተኛ ዓመት ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ ወደ አስተማረው ማኅበረሰበብ ተመልሶ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ይሰጥና (ማኅበረሰቡን እንዲያገለግል ይደረግና) እንዲመረቅ ይደረጋል"ሲሉ ተናግረዋል። ይህም ሲሆን የተማሪዎቹ መሠረታዊ ወጪ የሚሸፈን እንደሚሆንም አክለዋል።
ይህ አሰራር ለተማሪዎች ለራሳቸው የተግባር ትምህርት እንደሚሆንና የበለጠ እንዲበስሉ እንደሚያደርጋቸውም ተናግረዋል።
ተማሪዎች የመምህርነትን ሙያ ተላብሰው በዚያው ወደ ሙያው እንዲያመሩ ዕድል በመፍጠር ለጊዜውም ቢሆን በዘርፉ እየቀነሰ የመጣውን ወደ ሙያው የሚገባ የአስተማሪን ቁጥር ለማሳግ እንደሚረዳም ሚንስትሩ አብራርተዋል።
በቅርቡ በመምህራን ላይ በተደረገ ግምገማ ፣ 100,000 የሚደርስ የመምህራን ዕጥረት መኖሩ መታወቁን የተናገሩት ብርሃኑ (ፕሮፌሰር)፣ አሰራሩ በከፍተኛ ደረጃ ያለውን የመምህራን ዕጥረት እንዲቀንስ የበኩልን እንደሚወጣ አስረድተዋል።
Reporter
@DBU11
@DBU11
BY DBU Daily News
Share with your friend now:
tgoop.com/DBU11/6507