Telegram Web
የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ
===============
ደ/ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ለመሐል ሜዳ ካምፓስ የሰው ሃብት ለማሟላት ህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላወጣው የቅጥር ማስታወቂያ ለመወዳደር የተመዘገባችሁ እና ከዚህ በላይ በስማችሁ ፊት ለፊት ስለማሟላታችሁ የተገለፀ ተወዳዳሪዎች ጥር 2 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 በ ደ/ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በመገኘት የሚሰጠውን መመዘኛ ፈተና እንድትወስዱ እናሳስባለን።

@DBU11
@DBU111
👍12
የሬሚዲያል ተማሪዎች

የጥሪ ቀንን በተመለከተ ተማሪዎች ጥያቄያቸው እንዲመለስ እየጠየቁ ይገኛሉ።

ያለ እቅድ በሚኖር ቆይታችንም ተፅዕኖ ፈጥሮብናል፣ጊዜውን ብናውቀው ለቆይታችን እንዘጋጃለን ሲሉ የገለፁት ተማሪዎቹ የዩኒቨርሲቲውን የመጥሪያ ቀን እየተጠባበቁ ይገኛሉ።

ዩኒቨርሲቲውም ለተማሪዎች የሚገባውን የጥሪ እና የትምህርት ማጠናቀቂያ ካሌንደር የማሳወቅ ችግር የጠቅላላው ተማሪ ጥያቄም እንደመሆኑ መጠን ትኩረት ሊሰጥበት ይገባል።



@DBU11
@DBU111
👍64👌4
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታይ ቤተሰቦቻችን እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

🎁መልካም የገና በዓልን በDBUDAILY ስም ተመኘን!

@dbu11
@dbu111
👍68👌4
GAT ለምትፈተኑ ጥር 7 ከጠዋት 2:00ሰአት እንድትገኙ ይሁን

@DBU11
@DBU11
👍16
የተማሪዎች ምግብ ቤት ቡድን ያለፈው ሳምንት ዕሮብ የምግብ ፕሮግራም ቅያሪ ማድረጉን ከላይ በተያያዘው ማስታወቂያ ገልጿል።
በማስታወቂያው ላይ በጠቀሰው ምክንያት ዕረቡ የነበረው የምሳ ፕሮግራም ሐሙስ ሐሙስ የነበረውን ደግሞ ወደ እሮብ ማምጣቱን ነው ያስታወቀው።




@DBU11
@DBU111
👍19
DBU Daily News pinned Deleted message
የምርምር ፕሮጀክቶችን እንዴት መፃፍ ይቻላል በሚል ርዕሰ ጉዳይ ዙሪያ ለካምፓሱ ተመራማሪዎችና መምህራን ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል
=======================================
በደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ በምርምር ዙሪያ ላይ ካሉ መሰረታዊ የምርምር ሂደቶች አንድ ደረጃ ከፍ ያለ በትግበራ ላይ ያተኮረና ወደ ፕሮጀክት የሚቀየር ችግር ፈቺ ምርምሮችን እንዴት መጻፍ ይቻላል እና በተለያዩ ተቋማቶች ከሚቀርቡ የምርምር ፕሮጀክቶች ጋር ተወዳዳሪ ሆነው እንዴት ገንዘብ ማምጣት ይችላሉ በሚሉት ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ለነባርና ጀማሪ ተመራማሪዎች ስልጠና እየተሠጠ ይገኛል፡፡ ስልጠናው ከዛሬ ጥር 5 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 3 ቀናት እንደሚሰጥ ነው የተገለጸው፡፡

@DBU11
@DBU11
👍16
#AD

ክሪስፒ እርጥብ

የምርጦች ምርጥ የተባለለትን አቀራረብ ይዞ በልዩ ቅርፅ እርጥብ ማግኘት ይፈልጋሉ ?

🖊ስፔሻል እርጥብ (በእንቁላል ፣ ሠላጣ፣ አትክልትና ፣ካቻፕ)
🖊ኖርማል እርጥብ (በካቻፕ)
🖊ሻይ እንዲሁም ቡና እጅግ በሚማርክ መልኩ እናዘጋጃለን ።

📌በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲ ግቢ ድረስ እርጥብ ለምትፈልጉ ደንበኞቻችን Free delivery አዘጋጅተናል።

👉እንዳትሸወዱ  በእርጥብ ቤታችን መተው ከተመገቡ በኋላ የሚሰጥ የfree card ዕድል አዘጋጅተናል፤ ዕድለኞች የተሰጣቸው Business card ላይ free የሚል ፅሁፍ ካገኙ ነፃ እርጥብ ከክሪስፒ ይኖራቸዋል።😄

የት ነው???🤔

ከዩኒቨርሲው ፊት ለፊት ከመስኪ ቡና እና ከአልሚ ምግብ ቤት መሃከል ላይ እንገኛለን።
ወይም
0901633037
0931512004 ይደውሉ።

@dbu11
@dbu111
👍19👌4
ጥምቀት [ደብረብርሃን]

የ2017 ዓም የጥምቀት በዓል በደብረብርሃን ከተማ ያሉ ሁሉም አድባራት በአንድ ቦታ እንደሚያከብሩ የሰሜን ሸዋ ሃገረስብከት ስራ አስኪያጅ መጋቢሃዲስ ነቅዓጥበብ አባቡ ገልፀዋል።

ከዚህ ቀደም በ2013 ዓም የሃገረስብከቱ ሊቀጳጳስ አቡነ ቀለሜንጦስ በዓሉ በአንድነት እንዲከበር ገልፀው የነበረ ቢሆንም በዓሉ ሲከበርበት የነበረው ዘርዓያዕቆን አደባባይ ለአድባራቱ ምዕመናን በበቂ ሁኔታ ስለማያስተናግድ ላለፉት ሁለት ዓመታት በዚህ መልኩ ሳይከበር ቆይቷል።

በመሆኑም ቤተክህነቱ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመነጋገር በቋሚነት ለጥምቀት በዓል ማክበሪያ በቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን አካባቢ 100ሺ ካሬ ሜትር ቦታ በመሰጠቱ የዘንድሮው የጥምቀት በዓል በከተማይቱ ያሉ አድባራት በአንድነት በመሆን የጥምቀት በዓልን ያከብራሉ።

@DBU11
@dbu111
👍28
ጥምቀት [ደብረብርሃን]

የ2017 ዓም የጥምቀት በዓል በደብረብርሃን ከተማ ያሉ ሁሉም አድባራት በአንድ ቦታ እንደሚያከብሩ የሰሜን ሸዋ ሃገረስብከት ስራ አስኪያጅ መጋቢሃዲስ ነቅዓጥበብ አባቡ ገልፀዋል።

ከዚህ ቀደም በ2013 ዓም የሃገረስብከቱ ሊቀጳጳስ አቡነ ቀለሜንጦስ በዓሉ በአንድነት እንዲከበር ገልፀው የነበረ ቢሆንም በዓሉ ሲከበርበት የነበረው ዘርዓያዕቆን አደባባይ ለአድባራቱ ምዕመናን በበቂ ሁኔታ ስለማያስተናግድ ላለፉት ሁለት ዓመታት በዚህ መልኩ ሳይከበር ቆይቷል።

በመሆኑም ቤተክህነቱ ከከተማ አስተዳደሩ ጋር በመነጋገር በቋሚነት ለጥምቀት በዓል ማክበሪያ በቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያን አካባቢ 100ሺ ካሬ ሜትር ቦታ በመሰጠቱ የዘንድሮው የጥምቀት በዓል በከተማይቱ ያሉ አድባራት በአንድነት በመሆን የጥምቀት በዓልን ያከብራሉ።

@DBU11
@dbu111
👍46
2025/07/10 15:33:51
Back to Top
HTML Embed Code: