Telegram Web
ታላቅ የኪነ- ጥበብ ምሽት ለኪነጥበብ አፍቃራያን

ሆሄ ተስፋ የኪነ-ጥበብ ቡድን በዚህ አመት ሁለተኛ ተወዳጅ የኪነ- ጥበብ ስራዎችን ሊያቀርብላችሁ ዝግጅቱን ጨርሶ በቀን 18/05/17 ዓ.ም በእለተ እሁድ ከቀኑ 8፡30 ጀምሮ በዕለቱ ግጥሞች፣ ወግ፣ በሙዚቃ፣ ውዝዋዜ የመፅሐፍ ጥቆማ እንዲሁም ሌሎች አዝናኝና አስተማሪ ፕሮግራሞች በዕለቱ ይቀርባሉ፡፡
ሁላችሁም ተጋብዛችኋል”

“ሆሄ ተስፋ የኪነ-ጥበብ ቡድን”

@DBU1
@DBU111
👍10👌1
ማስታወቂያ
========
ቀን 16/05/2017

ለመ/ሜዳ ካምፓስ በተለያዩ የሥራ መደቦች ላይ ተወዳድራችሁ ከ70% የጽሑፍ ፈተና ወስዳችሁ 35 እና በላይ ውጤት ያመጣችሁ ቃለ መጠይቅ በ17/05/2017 ስለሚሰጥ በዋናው ግቢ ጧት 2:30 በብቃትና ሰው ሀብት አስተዳደር ቢሮ እንድትገኙ እናሳውቃለን፡፡


@dbu11
👍10
የመውጫ ፈተና እንደመድረሱም
Gemini
Copilot

ብዙዎቻችሁ ታውቋቸዋላችሁ የሚል ግምት ይኖረኛል። AI bot ናቸው።
ልዩነታቸው Copilot Creative bot ሲሆን ነገሮችን በራሱ አስቦ(ፈጥሮ) ሊመልስ ይችላል።

Gemini ደግሞ Analysis Bot በመሆኑ ነገሮችን ከያሉበት ቀራርሞ መልስ ያዘጋጃል።

ሁለቱም የየራሳቸው ድክመት አላቸው።

የፈተናው ጊዜ እንደመቅረቡም አሁን ጥያቄዎችን መዘጋጀት ይበልጥ ውጤታማ የሚያደርግ ይመስለኛል።




ሌላው እንደግል የምጠቁማችሁ ነገር ቢኖር ሞዴል ፈተና ላይ እና የዚህን ዓመት ፈተና እንደየዲፓርትመንታችሁ ከየትኛው ግቢ እንደሚወጣ በማጣራት ይበልጡን የዚያን የሞዴል ጥያቄዎች ብትሰሩ ይመረጣል።

መልካም የጥናት ጊዜ
@DBU11
@DBU111
👍24
Notice

የፕሮግራም መተላለፍ !!

ሆሄ ተስፋ የኪነ-ጥበብ ቡድን በዚህ አመት ሁለተኛ ተወዳጅ የኪነ- ጥበብ ስራዎችን ሊያቀርብላችሁ ዝግጅቱን ጨርሶ ፕሮግራሞች ያቀርባል ተብሎ ታስቦ የነበረ ቢሆንም በግቢው ውስጥ ባጋጠመ የመብራት አለመኖር ምክንያት ፕሮግራሙ ለነገ 10 ሰዓት መተላለፉን ስናሳውቅ ከታላቅ ይቅርታ ጋር ነው፡፡

“ሆሄ ተስፋ የኪነ-ጥበብ ቡድን”

@DBU1
@DBU111
👍10
እንኳን ደስ አላችሁ
============
ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በወንዶች ቴኳንዶ ወርቅ አገኘ
=================================
ዛሬ ከሰአት በኋላ ከ80 ኩሎ በታች በተካሄደ የፍጻሜ የወንዶች ቴኳንዶ ውድድር ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ወርቅ አገኘ። በመጀመሪያ ማጣሪያ በፎርፌ ለፍጻሜ የደረሰው ፋሲል የሽዋስ ከሰአት በኋላ የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ታጋጣሚውን ተማም ሰኢድን በሁለት ዙር አሸንፎ ለደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያውን ወርቅ አምጥቷል። በትላንትናው እለትም በሴቶች ሀናን አብዲኑር የብር ሜዳሊያ ለቡድኗ ማምጣቷ የሚታወስ ነው።

@DBU11
@DBU11
👍36👌3
ዝግጅታችንን ጨርሰናል

ጥራትና ውበት ያላቸውን ባይንደሮች ሁሉንም ባማከለ ዋጋ ከ250 ብር ጀምሮ ከሽክረት ህትመትና ማስታወቂያ

በግልና በቡድን ማዘዝ ይችላሉ

ለበለጠ መረጃ
Telegram: @SHIKRET007
Phone: 0940219376

@DBU11
@DBU111
👍26👌5🤬1
የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ እግር ኳስ ቡድን የጋምቤላ አቻውን 1ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈ
==========================
ዛሬ 3ኛ ቀኑን በያዘው የኢትዮጽያ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች የስፓርት ፌስቲቫል በአቃቂ አድቬንቲስት ትም/ቤት ሜዳ የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያውን ያደረገው የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ እግር ኳስ ቡድን የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲን በናትናኤል አስራት ብቸኛ ግብ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፎ 3 ነጥብ ይዞ መውጣት ችሏል።

ናትናኤል ተቀይሮ ገብቶ ግብ ማስቆጠር የቻለ የተከላካይ መስመር ተጫዋች ነው። ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በነገው እለትም በተመሳሳይ ሰአት ወሎ ዩኒቨርሲቲን ካቻ መጫወቻ ሜዳ ላይ የሚገጥም ይሆናል።

@DBU11
@DBU11
👍31👎1
ማስታወቂያ:
ለደብረብርሃን ዩንቨርስቲ ተማሪዎች በሙሉ

የ True Culture University Essay ውድድርን ይቀላቀሉ እና በፓን አፍሪካኒዝም ላይ ያለዎትን ግንዛቤ ያካፍሉ! የማሸነፍ እና የእውቅና እድል ለማግኘት እስከ አርብ ጥር 23 ድረስ ድርሰትዎን ያቅርቡ። እንዳያመልጥዎ - ለመሳተፍ ዝርዝሮችን እና መስፈርቶችን ይመልከቱ!
ፅሁፋን በ [email protected]  ይላኩ

@dbu11
@dbu111
👍19👎1
NOTICE

ለሁሉም የግቢያችን ተማሪዎች በሙሉ ከትላንትናው እለት ጀምሮ መብራት መጥፋቱ ይታወቃል በመሆኑም የሲስተም ችግር ስለሆነ እስኪስተካክል ድረስ በትእግስት እንድጠብቁ ለማሳሰብ እንወዳለን።

የደ/ብ/ዩ/ተ/ህ ጠቅላላ አገልግሎት ዘርፍ

@dbu11
@dbu111
🤔6🤬6👍4👎4
በትላንትናው ዕለት የሆሄ ተስፋ የኪነ ጥበብ ቡድን የዓመቱ ሁለተኛ መድረኩን በደማቅ ሁኔታ አቅርቦ ዋለ።

የግቢያችን ብቸኛው የኪነጥበብ ቡድን ሆሄ ተስፋ የሁለተኛ መርሀ ግብሩን ለ18/05/2017 አሰናድቶ መጨረሱን አስታውቆ ለ19/05/2017 ማራዘሙ የሚታወስ ሲሆን በቀጠሮው መሰረት በትላንትናው ዕለትም እንደተለመደው ግጥም፥ ሙዚቃ፥ ተውኔት እና ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ የነበረው የውዝዋዜ ቡድን በአዲስ መልክ ስራ ጀምሮ የምጀመሪያ የመድረክ ስራውን አሳይቷል።

@dbu11
@dbu111
👍24👎1
2025/07/12 20:41:05
Back to Top
HTML Embed Code: