Telegram Web
ማስታወቂያ

ውድ የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ የ 2017 ዓ/ም ተመራቂ ተማሪዎቻችን የምርቃት ቀንን በተመለከተ እስከ አሁኗ ሰዐት ድረስ ባለን መረጃ መሠረት ቀኑ እሁድ 15/10/17 ዓ/ም እንዳልተቀየረ ለማሳወቅ እንወዳለን ።

አዲስ መረጃ ሲደርሰን የምናሳውቃችሁ ይሆናል

የደ/ብ/ዩ/ተማ/ህ/ጽ/ቤት

https://www.tgoop.com/DBUstudent
https://www.tgoop.com/DBUstudent
የምርቃት ቀናችንን በበጎ ስራ እናሳልፍ !
ስለ መቄዶንያ የአረጋውያን እና የአይምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ምን ያህል ያውቃሉ 🤔 ?

ዛሬ ስለ መቄዶንያ ትንሽ እንበል

-ከ 8,200 በላይ አረጋውያን እና አይምሮ ህሙማንን  በስሩ አቅፎ እንደያዘ
- በመላው ሀገሪቱ በስሩ 45 ቅርንጫፉች እንዳሉት
-2,500 የሚሆኑት ህሙማን በቀን ቢያንስ 3 የአዋቂ ፓምፐርስ እንደሚጠቀሙ
- በቀን ከ 2.5 ሚሊየን ብር በላይ ለመድኃኒት ፣ለምግብ እና ለሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች እንደሚያስፈልገው ....
እንዲሁም ይህ ሁሉ ያለ ምንም የውጪ እና የመንግስት ድጋፍ የሚከወን መሆኑን በመረዳት በቅርቡ በግቢያችን ለዚህ የሀገር ኩራት ለሆነው ማዕከል እርዳታ የሚውሉ የተወሰኑ ተግባራት በቅርብ ቀናት ውስጥ ስለሚከናወኑ እንድትዘጋጁ እየጠየቅን ።  ለጊዜው በአቅማችን የመቄዶንያን እና የሰይፎ ሾው የዩትዩብ ቻናል Subscribe , Like , share እንድታደርጉ እንዲሁም
⋕በ8161 ላይ ok በማለት በቀን 1 ብር እንድትደግፉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን 🙏

Links
የመቄዶንያ 👉  https://youtube.com/@mekedonia?si=kLvP7hGIBAoLEvzm

የሰይፉ ሾው  👉 https://youtube.com/@seifufantahun?si=BJglkVUzR4XY2f3f

ከላይ ባሉ ማስፈንጠሪያዎች ሰብስክራይብ በማድረግ screenshots ከስር ሀሳብ መስጫው ላይ ያጋሩን  🙏

<< ሰው ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነው >>


የደ/ብ/ዩ/ተማ/ህ/ጽ/ቤት

https://www.tgoop.com/DBUstudent
https://www.tgoop.com/DBUstudent
ማስታወቂያ

በነገው ዕለት በቀን 15/10/17 ዓ/ም የምርቃት ፕሮግራም 1:30 መጀመሩን ተከትሎ የቁርስ ሰዐት እስከ 2:00 ሰዐት ስለሆነ በጊዜ ተመግባችሁ ወደ ፕሮግራሙ ገብታችሁ እንድትሳተፋ ለመግለጽ እንወዳለን።

  የደ/ብ/ዩ/ተማ/ህ/ጽ/ቤት

https://www.tgoop.com/DBUstudent
🎓🎉 መልካም የምረቃት ቀን ለሁሉም የ2017 ዓ.ም ተመራቂዎች 🎉🎓
ከደብረ ብርሃን  ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት

ውድ ተመራቂዎች

በቅድሚያ እንኳን ለዚች ለምትናፍቋት እና በጉጉት ስትጠብቋት ለነበረችው ውድ ቀን በሰላም አደረሳችሁ።

ዛሬ የደስታ እና ድል አንድ ቀናችሁ ነው። ከብዙ እንቅልፍ አልባ ሌሊቶችና  ዓመታት እንዲሁም ከሌሎች ብዙ አስቸጋሪ የህይወት ውጣ ውረድ በኋላ በመጨረሻም ከዛሬው እለት ደርሳችኋልና እንኳን ደስ አላችሁ።

እናንተ ማለት ለበተሰቦቻችሁ ብርሃን፣ ላሳደጋችሁ እና ላኖራችሁ ማህበረሰብ ተስፋ እንዲሁም ለሃገራችሁ የወደፊት ተረካቢ ናችሁ፤ ይህንንም ደግሞ እስከዛረዋ እለት ድረስ በዘለቀው ጥረታችሁ አረጋግጣችኋልናልና ከልብ እናመሰግናለን።

📚 ከመጀመሪያው ወደ ግቢ ከገባችሁበት እለት እስከ መጨረሻዋ እለት ድረስ ያሉት እያንዳዷ እርምጃ በሁላችሁም ህይወት ውስጥ መቼም የማይፋቅ ትውስታ፣ ጓደኝነት እና ቤተሰባዊነትን ጥለው አልፈዋል።

ሁሉም መጨረሻ ለሌላ አዲስ መዕራፍ መጀመሪያ ነውና ይህም ምርቃት ለሌላ አዲስ ተለዕኮ መጀመሪያ ነው ከዚህ ግቢም ወጥታችሁ ቤተሰባችሁንና ሃገራችሁን የምትጠቅሙና ስራ ፈጣሪዎች ሆናችሁ ለሌሎች የምትተርፉ ጥሩና መልካም ዜጋ እንድትሆኑ መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን።



በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ፤እንኳንቭተመርቃችሁ!!!
እንኳን ደስ አለሽ ተማሪ ፈቲሃ አሕመድ

ከኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል 4.00 ነጥብ በማምጣት የዩኒቨርስቲውን 🏆 ዋንጫ ወስዳዋለች ።
የሴቶች ዋንጫም ወስዳዋለች በድጋሚ እንኳን ደስ አለሽ በርቺልን

የደ/ብ/ዩ/ተማ/ህ/ጽ/ቤት

https://www.tgoop.com/DBUstudent
https://www.tgoop.com/DBUstudent
ማስታወቂያ 

ለሁሉም በዩኒቨርስቲው ውስጥ ለሚገኙ ተማሪዎቻችን ከነገ ማለትም ረቡዕ ቀን 18/10/17 ዓ.ም  6:00 ሰዐት በኋላ  ግቢው ውሰጥ አገልግሎት ስለማታገኙ አስፈላጊ ነገሮችን በተቻለ ፍጥነት እንድትጨርሱ ለማሳወቅ እንወዳለን።

የደ/ብ/ዩ/ተማ/ህ/ጽ/ቤት

https://www.tgoop.com/DBUstudent
2025/07/12 14:05:09
Back to Top
HTML Embed Code: