Telegram Web
#እንኳን #ለቅድስት #ሥላሴ #በዓል #አደረሳችሁ
አብርሃም ይስሐቅን ለመሰዋት ወደተራራ ወስዶት ነበር። እግዚአብሔር ግን በይስሐቅ ፈንታ በግን በዕፀ ሳቤቅ አወረደለት። ያ በግ ከሦስቱ አካላት የአንዱ የወልድ ምሳሌ ነው። ለጊዜው ይስሐቅ ከሞት የዳነው በዚያ በግዕ ቤዛነት ነው። የሰው ልጅ ሁሉ ከሞት የዳነበት ሕያው በግዕ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ዕፀ ሳቤቅ የድንግል ማርያም ምሳሌ ነው። ክርስቶስ ለእኛ ቤዛ ሆኖ በመስቀል ተሰቅሎ አዳነን።

"አብርሃም ወሰዶ ለይስሐቅ ወልዱ ከመ ይሡዖ።
አውረደ ሎቱ ቤዛሁ በግዐ"።

በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ።
.          መስቀል ለምን እንሳለማለን

መስቀል ስንሳለም ምዕመኑ ይፍቱኝ ይባርኩኝ ብለን በፍጹም ትህትና በእምነት ሆኖ ወደ ካህኑ እንቀርባለን ካህኑም በመስቀሉ የላይኛው ክፍልና በታችኛው ክፍል ግንባራችንና አፋችንን አሳልመው ይባርኩናል።
ግንባሩን ማስነካታቸው በአዕምሮ የተሰራውን ከንፈሩን ማስነካታቸው በመናገር የተሰራውን ኃጥያት እግዚአብሔር ይተውላችሁ ማለታቸው ነው።ቀዳሲያኑ ለቅዳሴ መምህሩ ለማስተማር ዘማሪው ለመዘመር ሲነሱ በማዕረግ ከፍ ካሉት ካህን መስቀል የሚሳለሙት።
ኃጢያት በሶስት መንገድ ይሰራል
፩. በገቢር (በመስራት)
፪.በነቢር (በመናገር)
፫.በኅልዩ (በማሰብ)
ታዲያ በገቢር በመስራት የተፈጸመውን ኃጢአት ለማስተሰረይ ጊዜ ሰጥቶ ወደ ንስሐ አባት ቀርቦ በኑዛዜ ቀኖና መቀበልና ቀኖናውን መፈፀም ይገባል። ለዚህ ነው አሁን አሁን በከተሜው ዘንድ እምብዛም ባይታይም ወንጌሉ የገባቸው ክርስቲያኖች ካህን ባዩ ቁጥር መስቀል ለመሳለም የሚጓጉት። ለሌሎች እንዲደርስ ሼር ማድረጋችሁን አትዘንጉ
እያወቅን በድፍረት ሳናውቅ በስሕተት የሰራነውን ኃጢአት ይቅር ይበለን ።
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
በዓለ ደብረ ቁስቋም
እንኳን አደረሰን

ደብረ ቁስቋም በደቡብ ግብፅ የሚገኝ ተራራ ነው፡፡ ደብረ ቁስቋም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲሁም ቅዱስ ዮሴፍንና ቅድስት ሰሎሜን ይዛ ከስደት ሲመለሱ ያረፉበት ቦታ ነው፡፡

ይህም በቅዱስ ወንጌል እንደተጻፈ ሄሮድስ ክርስቶስን ለመግደል በፈለገ ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ለአረጋዊው ዮሴፍ በሕልሙ ‹‹ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ›› ባለው መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ (ማቴ. ፪፥፲፫-፲፭)

የክርስቶስ ስደቱ ቀድሞ በነቢዩ ኢሳይያስ ‹‹. . . እነሆ፥ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተቀምጦ ወደ ግብፅ ይመጣል፡፡ የግብፅም ጣዖታት በፊቱ ይዋረዳሉ›› ተብሎ በተነገረው መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ ነቢዩ ፈጣን ደመና ያለው ጌታችን በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ጀርባ ላይ ሆኖ ወደ ግብፅ መውረዱን ለመግለጽ ነው፡፡ (ኢሳ. ፲፱፥፩) በስደቱም ጣዖታተ ግብፅ እየተሰባበሩ ሲወድቁ፤ በእነርሱም አድረው ሰውን ሲያስቱ የነበሩ አጋንንትም ሲሸሹ ታይተዋል፡፡

ደግሞም ጌታችን ዳግማዊ አዳም ነውና በምክረ ከይሲ (ዲያብሎስ) ምክንያት ተሰዶ የነበረው ቀዳማዊ አዳምን ለመካስ ተሰደደ፤ በዚህም አጋንንትን ከሰው ልቦና አውጥቶ አሳደደ፡፡

እመቤታችንም ልጇን ይዛ ከስደት ስትመለስ ያረፈችበትን ተራራ ደብረ ቁስቋምን ባረከችው ቀደሰችውም፤ ይህ ተራራ የተቀደሰ ተራራ ስለመሆኑ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ታኦፊሎጎስ በድርሳነ ማርያም እንዲህ አለ፤ ‹‹ይህም ከሀገሮቹ ሁሉ ተራሮች የሚበልጥ (የተለየ) ከፍ ያለ ተራራ ነው፡፡ በውስጡ ቅዱስ አግዚአብሔር ያድራል፡፡ ይህንን ተራራ የእግዚአብሔር ልጅ ወዶታል፤ አክብሮታልምና፤ ከዓለም ሀገሮች ሁሉ ከተቀደሰች እናቱ ጋር አድሮባታልና፡፡ ከመላእክት ቤት ያድር ዘንድ አልወደደም፤ ቢታንያንም አልመረጠም፡፡
ከተራራው ላይ ባለች ገዳም ቤት ውስጥ አደረ እንጂ፤ ነቢዩ ዳዊት፤ የጽዮንን ተራራ ወደደ፤ በአርያምም መቅደሱን ሠራ እንዳለ፡፡››
‹‹አንተ ተራራ ሆይ የእግዚአብሔር ማደሪያ በሆንህ ጊዜ በኪሩቤልና በሱራፌል መካከል ፍጹም ደስታ ተደረገ፡፡ የመላእክት ሠራዊት ቅዱስ የሆነ ፈጣሪያቸውንና ጌታቸውን ይታዘዙ (ያገለግሉ) ነበር፡፡

አንተ ተራራ ሆይ ያደረብህ ጌታችን ስለሆነ ከተራሮች ሁሉ ከደብረ ሲናም ይልቅ ከፍ ከፍ አልህ፤ ጌታችን በደብረ ሲና ባረፈ ጊዜ ፍጹም ደስታ፣ ታላቅ ብርሃንም በሆነ ጊዜ መቅረብና መመልከት ከሙሴ በቀር የቻለ የለም፡፡

እርሱም ቢሆን ፊቱን ማየት አልቻለም፡፡ ሥጋ ለባሽ ሁሉ እርሱን ዐይቶ በሕይወት መኖር የሚቻለው የለምና፡፡ እኛ ግን አየን፤ ከዚህ ማደሩንም ተረዳን፤ ዳግመኛም ንጽሕት በሆነች በማርያም ዘንድ አየነው፡፡ ቅድስት ከሆነች ከእመቤታችን ማርያም ዘንድ በቤተልሔም ስለ እኛ በተዋሐደው ሥጋ በጨለማና በሞት ጥላ ሥር ያለን እኛን ከቸርነቱና ሰውን ከመውደዱ የተነሣ መጥቶ አዳነን፤ ከዓለም ሁሉ ይልቅ ጣዖትን በማምለክ ሲበድሉም ወደ ግብፅ  ሀገር ወርዶ በእነርሱ ላይ የመለኮትነት ብርሃኑን በማብራት ታላቅ የሆነ ክብሩን ገለጠ››፡፡ (ድርሳነ ማርያም)
ኅዳር ፮ ቀንን የሚነበበው የመጽሐፈ ስንክሳር ክፍል ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛም በኋላ ዘመን ሐዋርያትን በደብረ ቁስቋም ሰብስቦ፤ ታቦትንና ቤተ ክርስቲያኑን አክብሮ የቊርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙን እንደ ሰጣቸው፤ እኛንም ለዚህ ክብር የበቃን እንሆን ዘንድ የእግዚአብሔር አምላክ ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልን፤ አሜን፡፡

ምንጭ፤ ድርሳነ ማርያም መጽሐፍ ትርጉም
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
ኅዳር ጽዮን
"ጽዮን" ማለት "ጸወን አምባ፣ መጠጊያ" ማለት ነው:: ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም፣ ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል፡፡

ኅዳር ፳፩ ቀን በታቦተ ጽዮን የተፈጸሙ ታላላቅ ተአምራት የሚታሰቡበት ቀን ነው፡፡ በዚህ ቀን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የታቦተ ጽዮንን ተአምራት እግዚአብሔር ቃል ቅድስት ድንግል ማርያምን ታቦቱ አድርጎ ከፈጸማቸው ታላላቅ የድኅነት ሥራዎች ጋር በማነጻጸር እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በነገረ ድኅነት ውስጥ ያላትን ድርሻ በስፋት ታስተምራለች፡፡

ነቢዩ ሙሴ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጸልዮና ጹሞ ዐሥርቱ ቃላት የተጻፈበትን ጽላት ከእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑን ታቦት ‹ታቦተ ጽዮንን› እንደተቀበለ መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጻል፡፡

ታቦተ ጽዮን ከማይነቅዝ እንጨት የተቀረጸችበት ምክንያት የእመቤታችን ድንግል ማርያምን ንጽሕና ለማመልከት ነው፡፡ በውስጥም በውጪም በጥሩ ወርቅ የተለበጠች መሆኗ ደግሞ የእመቤታችን ድንግል ማርያም ቅድስናዋንና በሁለት ወገን ድንግል የመሆኗ ምሳሌ ነው፡፡

ንጉሥ ዳዊት የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ከአቢዳራ ቤት ወደ ጽዮን ከተማ ባስመጣበት ወቅት በታቦቷ ፊት በሙሉ ኃይሉ በደስታ እየዘለለ ለእግዚአብሔር በዝማሬ ምስጋና አቅርቧል፡፡ ‹‹ለንጉሥ ዳዊትም “እግዚአብሔር የአቢዳራ ቤት የነበረውን ሁሉ ስለ እግዚአብሔር ታቦት ባረከ” ብለው ነገሩት፡፡

ዳዊትም ሄዶ የእግዚአብሔርን ታቦት ከአቢዳራ ቤት ወደ ራሱ ከተማ በደስታ አመጣት፡፡ ከእርሱም ጋር የእግዚአብሔርን ታቦት የተሸከሙ ሰባት መሰንቆ የሚመቱ መዘምራን ነበሩ፤ በሬዎችንና በጎችን ይሠዉ ነበር፡፡ ዳዊትም በእግዚአብሔር ፊት በገና ይደረድር ነበር›› እንዲል፤ ነቢዩ ዳዊት በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት የተቀኘው ለሰው ልጆች ሁሉ የመዳናችን ምክንያት የሆነችውን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሲያመስገን ነው፡፡ (፪ሳሙ.፮፥፲፪-፲፬)

ታቦተ ጽዮን እስራኤል የዮርዳኖስን ባሕር ለመሻገር በተቸገሩ ጊዜ ነቢዩ ኢያሱ እግዚአብሔር አምላክ በነገረው መሠረት ካህናቱ የቃል ኪዳኑን ታቦት ይዘው በሕዝቡ ፊት ወደ ዮርዳኖስ እንዲሄዱ ነገራቸው፤ እነርሱም እንደታዘዙት አደረጉ፤ ታቦቱን የተሸከሙት የካህናቱ እግሮች በውኃው ዳር ሲጠልቁ ከላይ የሚወርደው ውኃ ቆመ፤ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙ ካህናት በዮርዳኖስ መካከል በደረቅ መሬት ጸንተው ቆመው ነበር፤ ሕዝቡም ሁሉ ዮርዳኖስን ፈጽመው እስኪሻገሩ ድረስ እስራኤል ሁሉ በደረቅ መሬት ተሻገሩ፡፡ (ኢያ. ፫፥፩-፲፯)

እስራኤላውያን በመካከላቸው የቃል ኪዳኑ ታቦት በያዙ ቁጥር በጦርነታቸው ሁል ጊዜ ያሸንፉ ነበሩ፡፡ ነገር ግን ልዑል እግዚአብሔር ሕዝበ እስራኤል ስለበደሉት እንዲሁም የኤሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ በደላቸውና ክፋታቸው ስለበዛ ታቦተ ጽዮን ተማርካ ወደ ፍልስጥኤም ሄደች፡፡ በዚያ በአሕዛብ ምድርም ልዩ ልዩ ተአምራትን እያደረገች ፍልስጥኤማውያንን ስለአስጨነቀቻቸው የፍልስጥኤማውያን አለቆች የቃልኪዳኑን ታቦት ልዩ ልዩ ገጸ በረከቶችን አስይዘው ወደመጣችበት በሠረገላ አድርገው በክብር ሸኝተዋታል፡፡ (፩ኛ.ሳሙ. ፭፥፩-፲፭)
ሀገራችን ኢትዮጵያም በንግሥተ ሳባ አማካኝነት ለታቦተ ጽዮን መቀመጫ እንድትሆን የእግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኗል፡፡ ይህም እንዲህ ነበር፤ ንግሥተ ሳባ የንጉሥ ሰሎሞንን ጥበብ ለማድነቅ ምድረ እስራኤል ድረስ መጓዟን ተከትሎ ከንጉሡ ቀዳማዊ ምኒልክን ፀነሰች፡፡

ቀዳማዊ ምኒልክ ከአደገ በኋላ አባቱን ሊጠይቅ ሂዶ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለስ አብረውት አንድ ሺህ ሁለት መቶ እስራኤላውያን የበኩር ልጆች፣ ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት በአዛርያስ የሚመሩ ሌዋውያን ካህናትም አብረውት ለጉዞ ተነሡ፡፡ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትንና ሌሎች በርካታ ቁሳቁሶችን ይዘውም ነበር።

ነገር ግን ታቦተ ጽዮንን አዛርያስና ካህናቱ ተማክረው ቀዳማዊ ምኒልክ እንኳን ሳይሰማ በምሥጢር ይዘዋት ሊመጡ ተስማሙ፡፡ ዕቅዳቸውን ለማሳካት በታቦተ ጽዮን አምሳያ ሌላ ታቦት አዘጋጅተው ለመሄድ በሚነሡበት ዕለት ሌሊትም ወደ ቤተ መቅደስ ይዘውት ሄዱ፡፡

ከቤተ መቅደስ ሲደርሱም የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበርና የቤተ መቅደሱ በር ተከፍቶ እና ውስጡም በብርሃን ተሞልቶ ታቦተ ጽዮንም ከመንበሯ በመነሣት ከፍ ብላ አገኟት። በዚህም የአምላክን ፈቃድ ተረድተውና እግዚአብሔርን እያመሰገኑ በፍጥነት ይዘዋት ወጡ፡፡ በአምሳያዋ የሠሩትንም ቅርፅ በመንበሩ ላይ አስቀምጠው ሄዱ።

የንጉሡ ወታደሮች በፍጥነት ቢጓዙም ቀዳማዊ ምኒልክ እና አዛርያስ ታቦተ ጽዮንን ይዘው ሲጓዙ እጅግ ፍጣን ስለበር ሊደርሱባቸው አልቻሉም። መጽሐፈ ክብረ ነገሥት ይህንን ሲጠቅስ ‹‹ከመሬት አንድ ክንድ ያህል ከፍ ብለው ይሄዱ ነበር›› በማለት ይገልጸዋል። ባሕረ ኤርትራን ከተሻገሩና ግብፅ ከደረሱ በኋላ ዕረፍትን ባደረጉ ጊዜ አዛርያስ ለቀዳማዊ ምኒልክ ታቦተ ጽዮንን ይዘዋት እንደመጡ ነገረው፡፡

አያይዞም ‹‹አንተም ብትሻ ታቦቷንም ወደ ሀገሯ ልመልሳት ብትል አትችልም፤ አባትህ ሰሎሞንም ሊወስዳት ቢመጣ አይሆንለትም›› አለው። ከቦታ ቦታ ይዣት እንቀሳቀሳለው ቢልም ያለ ፈቃዷ ምንም እንደማያደርግና ሁሉ ነገር በአምላክ መልካም ፈቃድ እንደሚፈጸም ነገረው። ቀዳማዊው ምኒልክም ይህን ሲሰማ ተደሰተ፤ ሕዝቡና ሠራዊቱ በሙሉ ልዑል እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ ከግብፅ ምድር ወጥተው እስከ ኢትዮጵያ በታላቅ እልልታና ሆታ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ መጡ።

ኅዳር ፳፩ ቀን አክሱም በደረሱ ጊዜም እናቱ ንግሥተ ሳባ ተቀበለችው፤ ደስታና እልልታውን ተመልክታ ያገኙት ነገር እንዳለ ብትጠይቀው ታቦተ ጽዮንን እንዳመጧት ነገራት፡፡ የእርሷም ደስታ እጥፍ ድርብ ሆነ። ታቦቷንም በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን አስቀመጡአት፡፡

ከዚያም ዘመን ጀምሮ በየዓመቱ ኅዳር ፳፩ ቀን ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም በታቦተ ጽዮን የተፈጸሙ ታላላቅ ተአምራትን በማሰብ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ታከብራለች፡፡
         ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
ምንጭ፤
ክብረ ነገሥት ተርጓሚ ሥርግው ገላው (1994 ዓ.ም)
መዝገበ ታሪክ ቊጥር 1 (መምህር ኅሩይ ኤርምያስ)
#ትውፊት_ማለት_ምን_ማለት_ነው?
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 እንደ ቤተ ክርስቲያናችን አስተምሮ ቤተ ክርስቲያናችን የምትመራበት 3 ህግጋቶች አሏት። እነርሱም ፦
                        👉(1) ፦ ዶግማ
                        👉(2) ፦ ቀኖና
                        👉(3) ፦ ትውፊት ናቸው።

🔵👉 እግዚአብሔር ቢፈቅድ ዛሬ ክፍል (3) ትውፊት ማለት ምን እንደሆነ በአጭሩ እንመለከታለን።

           🔴👉
#ትውፊት_ማለት_ምን_ማለት_ነው?

🔴👉 ትውፊት ማለት አወፈየ ከሚለው የግእዝ ግሥ የመጣ ሲሆን ውርስ፣ ቅብብል ተብሎ ይተረጎማል፡፡ ትውፊት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ትምህርቶቿን ጠንቅቃ ከያዘችበት እና ልጆቿንም ከምትመራባቸው ሦስቱ የመሠረተ እምነት ምንጮች ውስጥ አንደኛው ነው፡፡

🔷👉 የቤተ ክርስቲያን መሠረተ እምነት ተብለው የሚጠቀሱት፡- ዶግማ፣ ቀኖና እና ትውፊት ሲሆኑ እነዚህ መሠረቶች ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሳትለወጥና ሳትበረዝ እንደ ደመቀች ከትውልድ ወደ ትውልድ እንድትተላለፍ አድርገዋታል፡፡ ለቤት መቆም ብቻ ሳይሆን ቤቱ ዕድሜ እንዲኖረውም የሚያደርገው የመሠረቱ ጥንካሬ ነው፡፡

🔷👉 በዚህም መሠረት ትውፊት አንድ ሰው ከእርሱ በፊት ከነበረው ማኅበረሰብ የሚቀበለውና የሚወርሰው እምነት፣ ባህል፣ የአኗኗር ዘይቤ፣ …ወዘተ ሲሆን ሒደቱም በዚህ ሳያበቃ እርሱም በተራው ለተተኪው የሚያስተላልፈው ነው፡፡

🔴👉 ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ ስለ ትውፊት እንዲህ በማለት ማብራሪያ ይሰጣሉ፡-“ትውፊት በቃል ወይም በጽሑፍ ወይም በተግባር እንቅስቃሴ ከአንዱ ወደ ሌላው የሚተላለፍ ታሪክ፣ ትምህርት፣ ባህል፣ ወግና ሥርዓት ነው፡፡ ትውፊት በተጨባጭ በትክክል የተፈጸመ እንጂ ተረት አይደለም፡፡ ከሕገ ልቡና ወደ ሕገ ኦሪት፣ ከሕገ ኦሪት ወደ ሕገ ወንጌል፣ በቅብብሎሽ የመጣ የተወረሰና ለተከታዩ ትውልድ የተላለፈ ነው፡፡

🔵👉 ትውፊት ልማደ ሀገርን ሕገ እግዚአብሔርን ባህለ ሃይማኖትን ሁሉ የሚያጠቃልልና እንደ መንፈሳዊ ሕግ ሆኖ ሊያዝ የሚችል ነው፡፡” ይላሉ (ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታዬ፤ ፈለገ ጥበብ መጽሔት ፪ኛ ዓመት ቁጥር ፲፭/፲፱፻፺፪ ዓ.ም. ገጽ ፲፭)

🔴👉 ትውፊት ከትውልድ ወደ ትውልድ በሦስት መንገዶች የሚተላለፍ ሲሆን፤ እነርሱም፡- የሚዳሰስ፣ የማይዳሰስ እና በቃል ይተላለፋሉ፡፡

🔷👉 አንድን ትውፊት ክርስቲያናዊ ነው ይምንለው፦

👉 1) ቅዱሳን አበው በኑሮአቸው የገለጡት ማለትም የተናገሩት የሰሩትና ያስተማሩት ሲሆን
👉 2) በቤተ ክርስቲያን ተጠብቆ የሚሰራበት ሲሆን
👉 3) እኛን ከቀደሙ አበው ጋር አንድ የሚያደገን፤ አሰረ ፍኖታቸውን እንድንከተል የሚያበቃን ሲሆን ነው።

🔴👉 "እግዚአብሔር፦ ሕዝቡን ወደ እኔ ሰብስብ፥ በምድርም በሕይወት በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ እኔን መፍራት ይማሩ ዘንድ፥
ልጆቻቸውንም ያስተምሩ ዘንድ ቃሌን አሰማቸዋለሁ ብሎ
በተናገረኝ ጊዜ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት በኮሬብ
በቆምህበት ቀን ዓይኖችህ ያዩትን ነገር እንዳትረሳ፥ በሕይወትህም
ዘመን ሁሉ ከልብህ እንዳይወድቅ ተጠንቀቅ፥ ነፍስህንም በትጋት
ጠብቅ ለልጆችህም ለልጅ ልጆችህም አስታውቀው"። ዘዳ.4:9-
10

🔴👉 በአጭሩ ይሔን ይመስላል አነሳስቶ ያስጀመረን አስጀምሮም ያስፈፀመን የአባቶቻችን አምላክ ይክበር ይመስገንልን።

       ለሁሉም እንዲደርስ ላይክ ሼር አድርጉ

።።።።
#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
    ።።።።።
#ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
     ።።።።።
#ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።

 

ፔጁን
#Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
#ሥግደት_የማይሰግባቸው_ቀናቶች
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን በሃይማኖት ይዘትም ሆነ በሃይማኖት ሥርዐት ፍጽምት ነች፡፡ የሃይማኖት ይዘቷ (ዶግማዋ) ይህ ይቀረዋል ተብሎ የማይጨመርበት በእግዚአብሔር አንድ ጊዜ ፍጹም ሆኖ ለቅዱሳን የተሰጠ ነው፡፡

🔵👉 (ይሁዳ 3) እግዚአብሔርን የምታመልክበት ሥርዐትም እንዲሁ መንፈስ ቅዱስ በመራቸው ቅዱሳን ሰዎች የተቀነነ ቅዱስ ሥርዐት ነው፡፡ ጊዜንና ቦታን በመዋጀትም (ግንዛቤ ውስጥ በማስገባትም) እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ሥርዐትን እንድትሠራ ቀኖና አለ፡፡ ከዚህ አንጻር ስግደትንም በተመለከተ መች ሊሰገድ እንደሚገባና መች እንደማይሰገድ ሥርዐትን ሠርታልናለች እንጂ እንዲሁ በዘፈቀደ እንዲተገበር ቸል አላለችም፡፡

🔴👉 ከሁሉ አስቀድሞ ግን እንደ ቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ መሠረት ያሉትን የአሰጋገድ አይነቶች ማወቅ ያስፈልጋል በመሆኑም
#ሦስት አይነት #የስግደት_አሰጋገድ_አይነት_አሉ ። እነሱም ፦

(1ኛ)፦
#አድንኖ ስግደት ይባላል።ይህም ማለት እራስን ዝቅ አድርጎ ወገብን ጎበስ በማለት ጉልበትና ግንባር ምድር ሳይነካ የምንቃናው ማለት ነው።

(2ኛ)፦
#አስተብርኮ ይባላል ይህም አሰጋገድ በጉልበት ወድቆ ግንባር መሬት ሳይነካ የምንነሳው የስግደት አይነት ነው።

(3ኛ)፦
#ሠጊድ ይባልላ። ይህ አግጋገድ ሙሉ በሙሉ በጉልበት መሬት ላይ በመውደቅ ግባርን መሬት በማስነካት የምንሰግደው የስግደት አይነት ነው።

🔵👉 ታዲያ ከእነዚህ የአሰጋገድ አይነቶች በአምስቱ (5) የግዝት በዓላት የማይሰገደው የትኛው የአሰጋገድ አይነት ነው ስንል አባቶቻችን በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው እስከዛሬ ያስተማሩን ያስቀመጡልን ሠጊድ የምንለውን ስግደት ነው።

🔴👉 ስለዚህ የአሰጋገድ አይነቶቹን ከተመለከትን ዘንዳ ይህንን ሠጊድ የምንለውን የአሰጋገድ አይነት የማንሰግድባቸውን አምስቱን የግዝት ዓላት ደግሞ እንመልከት !

     🔴👉 ሥግደት የሚሰገድባቸው ጊዜያት እንዳሉት ሁሉ የማይሰገድባቸው ጊዜያት አሉት የግዝት በዓላት አምስት ሲሆኑ
እነርሱም :- 1 👉ወር በገባ በ29 
#የወልድ_በዓል
              🔴 የነጻነት ቀን ጌታ የተወለደበት ቀን ስለሆነ።

          2 👉ወር በገባ በ 21
#የእመቤታችን_በዓል
        🔴የነፍሳችን ዕረፍት፥ ነጻ የወጣንባት ስለሆነ።

           3 👉ወር በገባ በ 12
#የቅዱስ_ሚካኤል በዓል፣
          🔴ራዕ᎐፲፪ ሰይጣን የወደቀበት ቀን ስለሆነ።

          4 👉
#ቀዳሚት_ሰንበት (ቅዳሜ)
             🔴ጌታ ከስራው ያረፈበት ቀን ስለሆነ

          5 👉እሑድ_ሰንበት (ሰንበተ ክርስቲያን ናቸው።
           🔴ጌታ ከሙታን መካከል ተለይቶ የተነሳበት ቀን የዕረፍት ቀን ስለሆነ ።
በእነዚህ ቀናቶችም ሠጊድ የምንለው ስግደት አይሰገድም

🔴👉 ከነዚህ በተጨማሪም ሥግደት የማይሰገድባቸው ጊዜያት የሚከተሉት ናቸው !

1ኛ.
#በዕለተ_እሑድ

🔵👉ከአልቦ ነገር ወይም ከምንም የተፈጠረ ፍጥረት ሁሉ ክርስቶስ ዳግም ሲመጣ ጠፍቶ ወደ ምንምነት ሲቀየር ከማይጠፉ ከአምስቱ ፍጥረታት አንዷ ሰንበት ናት፡፡ ጌታ የተነሣባት ፣ ዳግምም የሚመጣባት ዕለት ናት፡፡ በዚህና በሌሎች ምክንያቶችም ሰንበተ ክርስቲያን እሑድ በዓል ነች፡፡

🔴👉 ስለዚህ በዕለተ እሑድ መስገድ የተከለከለ ነው፡፡ ይህንን ፍትሐ ነገሥቱ እንዲህ በማለት ይገልፀዋል፡- “ከአድንኖና ከአስተብርኮ በቀር እስከ ምድር መስገድን የሚተዉባቸው የታወቁ ጊዜያቶች እነዚህ ናቸው፡፡ ኒቅያ 20፣ በዕለተ እሑድና በበዓለ ሃምሳ ወራት፣ ” ፍት.መን. አን. 14 ቁ. 537 ይህንን ይበልጥ ሲያጸናው በሰንበታትና በበዓላት አንቀጹ እንዲህ ሲል ደግሞታል፡- “በእሑድና በተከበሩት በዓላት ቀን ስግደት አይገባም፤ እነዚህ የደስታ ቀኖች ናቸውና” ፍት. መን. አን. 19 ቁ. 715።

2ኛ.
#በበዓለ_ሃምሳ_ወራት

🔴👉 በዓለ ሃምሳ የፍስሐና የሰላም ጊዜ ነው፡፡ ስሙ እንደሚጠቁመው ሃምሳውም ቀን በሙሉ በዓል ነው፡፡ በዓል ስለሆነም እንደ ፋሲካና እንደ ልደት እንበላበታለን እንጂ ረቡዕና አርብ ቢሆን እንኳን አንጾምበትም፡፡ በበዓልነቱ ጾም እንደተሻረበት ስግደትም እንዲሁ ይሻርበታል፡፡ ከላይ እንዳየነው ፍትሐ ነገሥቱም በፍት.መን. አን. 14 ቁ. 537 በእሑድ መስገድን ሲከለክል በበዓለ ሃምሳም እንዲሁ ከልክሏል፡፡

3ኛ.
#በጌታችን_በዓላት

🔵👉 ፍትሐ ነገሥቱ “በእሑድና በተከበሩት በዓላት ቀን ስግደት አይገባም፤ እነዚህ የደስታ ቀኖች ናቸውና” (ፍት.መን.
አን. 19 ቁ. 715) ካለ በኋላ “የተከበሩት በዓላት” ያላቸው የትኞቹን እንደሆነ ሲዘረዝር ትስብእት/ጽንሰት ፣ ልደት ፣ ጥምቀት ፣ ሆሣዕና ፣ ትንሣኤ ፣ ዕርገት ፣ በዓለ ሃምሳ ፣ ደብረ ታቦር በማለት ከጌታ ዘጠኝ ዐበይት በዓላት 8ቱን ይገልፃል፡፡ ሳይገለፅ የቀረው ስቅለት ነው፤ ያልተገለፀበትም ምክንያት በስቅለት ስግደት ስለማይከለከል ነው፡፡

🔴👉 ስለዚህ ከስቅለት በቀር በጌታ ዐበይት በዓላት (በተቀሩት በ8ቱ) ስግደት የተከለከለ ነው፡፡ ፍትሐ ነገሥቱ ይህንን ሲያጸና በአንቀጽ 14 እንዲህ ብሏል፡- “መስገድን የሚተዉባቸው የታወቁ በዓላት እነዚህ ናቸው.... ኒቅያ 32፣ በጌታችን በዓላትና በእመቤታችን በዓላት” ፍት.መን. አን. 14 ቁ. 536-537፡፡

4ኛ.
#የእመቤታችን_በዓላት

🔴👉 ከላይ ያየነው የፍትሐ ነገሥት ንባብ በፍት. መን. አን. 14 ቁ. 536-537 ድረስ በጌታ በዓላት መስገድ እንደተከለከለው ሁሉ በእመቤታችን በዓላትም መከልከሉን ይጠቁመናል፡፡

5ኛ
#ሥጋውንና_ደሙን_ከተቀበሉ_በኋላ

🔴👉 የሥርዐት ምንጫችን የሆነው ፍትሐ ነገሥት አሁንም በዚህ ዙሪያ እንዲህ ብሏል፡- “መስገድን የሚተዉባቸው የታወቁ በዓላት እነዚህ ናቸው... ሥጋውንና ደሙን ከተቀበሉ በኋላ” ይላል፡፡ ፍት. መን. አን. 14 ቁ. 536-537፡፡ ሥጋውንና ደሙን ከተቀበልን በኋላ ከሚሰገድለት እንጂ ከማይሰግደው ጋር አንድ መሆናችንን ለማጠየቅና ለቅዱስ ሥጋውና ለክቡር ደሙ ክብር ስንል ዝቅ ብለን አንሰግድም።

    🔵👉ለሌችም እንዲደርስ በቅንነት
                 ሼር አድርጉ !
።።።
#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
       ።።።።።
#ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
       ።።።።።
#ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።
       ህዳር 28/2017 ዓ.ም
             

ፔጁን
#Like_Follow_Share በማድረግ ትክክለኛ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርት እንዲሁም መረጃ ያግኙ

🔴👉 በቴሌግራም | Telegram
       👇👇👇👇👇👇
https://www.tgoop.com/sratebetkrstyane
የተቀደደ ልብስ መልበስ
።።።.።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን " የለምጽ ደዌ
ያለበት ሰው ልብሱ የተቀደደ ይሁን፥.....ርኩስ
ርኩስ ነኝ ይበል።"(ኦሪ ዘሌ.13፥45) እንደሚል
የተቀደደ ልብስ ያለበሰ ሰው የተዋረደና
በኃጢአት እንደረከሰ እርኩስ ነኝ እያለን ነው
ማለት ነው ። ለዚህም ሌላ ማስረጃ የቅዱስ
ዳዊት ልጅ ትእማር በወንድማ በተደፈረች ጊዜ "
ትዕማርም በራስዋ ላይ አመድ ነስንሳ፥ ብዙ
ኅብርም ያለውን ልብስዋን ተርትራ፥ እጅዋንም
በራስዋ ላይ ጭና እየጮኸች ሄደች። ነው
እሚለን (1ኛሳ.13፥19)
ከእስራኤል ወገን በሆነው በአካን ምክንያት
እሥራኤል በደረሰባቸው መከራ ምክንያት "
ኢያሱም ልብሱን ቀደደ፥ ......"እንዲል መጽሐፍ
ቅዱስ። ( ኢያሱ 7፥6) እኛም የተቀዳደደ ልብስ
ስንለብስ እንደረከስንና በኃጢአታችን መከራ
እየደረሰብን እየገለጽን ነው። እንዲያም ቢሆን
ደግሞ ማቅ ለብሰን አመድ ነስንሰን በንስሃና
በጸሎት ልንበረታ እንጂ ደረታችንን ነፍተን
ባልዘነጥንበት ነበር።
ሌላው መጽሐፍ ቅዱስ በሐዘን ምክንያት
ልብሳቸውን የቀደዱና ያዘኑ እንዳሉ" ያዕቆብም
ልብሱን ቀደደ፥ በወገቡም ማቅ ታጥቆ ለልጁ
ብዙ ቀን አለቀሰ።" ሲል አባታችን ያዕቆብ
በዮሴፍ ምክንያት ያለቀሰውን ለቅሶ ጽፎልናል
(ኦሪ.ዘፍ 37÷34) እንዲህ አይነቱን ሐዘን
እዮብም አድርጎታል። " ኢዮብም ተነሣ
መጐናጸፊያውንም ቀደደ፥ ....."(ኢዮ.1÷20)
ሰለዚህ ክርስቲያን የተቀደደን ልብስ ሊለብስ
አይገባም በተለይ በቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ
ውስጥ ስንገባ እንዲህ አይነት አለባበሶችን
መልበስ ነውር ነው። ገላን እያሳዩ ወደ
ቤተክርስቲያን መግባት ለቤተክርስቲያን ያለንን
ንቀት ከማሳየት ያለፈ ሌላ ትርጉም የለውም።
ምክንያቱም ቤተክርስቲያን የራሷ የሆነ የአለባበስ
ሥርዓት አላትና።
ታህሣሥ 3 በዓታ ለማርያም
,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,,
🔴👉 ታህሣሥ 3 በዚህች ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሦስት ዓመት ሲሆናት ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት ነው ምክንያቱም እርሷ ለእግዚአብሔር የስዕለት ልጅ ነበረችና።

🔷👉 ታዲያ ቤተ መቅደስ የገባችበት ዕለት ነው ብለን ብቻ ማለፍ ሳይሆን እንዴት እንደገባች ማወቅ ያስፈልጋልና አጠር አድርገን እንመለከታለን።

🔴👉 የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ወላጅ እናት ቅድስት ሐና ትባላለች። እናታችን ቅድስት ሐናም አድጋ ለአካለ መጠን ስትደርስ ከቤተ መንግሥት ወገን ከነቅዱስ ዳዊት ወገን ከሆነው ከቅዱስ ኢያቄም ጋር አጋቧት።

🔴👉 እነዚህ ቅዱሳን ኢያቄም እና ሐና በአንድነት ተጋብተው ሲኖሩ ልጅ አጡ፤ ከእለታት አንድ ቀን ወደ ቤተ እግዚአብሔር ሂደው ሲጸልዩ ሲያዝኑ ዋሉ። ሀዘናቸው እንዴትስ ነው ቢሉ፡- ኢያቄም፡- "አቤቱ ጌታዬ ያባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ አትጣለኝ አትናቀኝ ጸሎቴን ስማኝ ፈቃዴን ፈጽምልኝ፤ ለዐይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የሚሆን የተባረከ/ች ወንድ ወይም ሴት ልጅ ስጠኝ" ብሎ ሲለምን ዋለ። ሐናም በበኩሏ "አቤቱ ጌታዬ የአባቶቼ የእስራኤል አምላክ እኔ ባርያህ እለምንሃለሁ፤ ስማኝ ለዐይኔ ማረፊያ ለልቤ ተስፋ የምትሆነኝ የተባረከች ሴት ልጅ የማኅጸኔን ፍሬ ስጠኝ" ብላ ስትለምን ዋለች።

🔷👉 እንዲህ ብለው ሲያዝኑ ሲጸልዩ ውለው ርግብ ከልጆቿ ጋር ስትጫወት ዐይታ አቤቱ ጌታዬ ለዚች ግእዛን ለሌላት እንስሳ ልጅ የሰጠህ አምላክ ምነው ለኔ ልጅ ነሳኸኝ ብላ ምርር ብላ አለቀሰች። ከሊቀ ካህናቱ ዘካርያስ ሄደው አቤቱ ጌታችን ሆይ ወንድ ልጅ ብንወልድ ተምሮ፣ ቤተ እግዚአብሄርን አገልግሎ እንዲኖር እንሰጣለን፤ ሴት ልጅም ብንወልድ ማይ (ውሃ) ቀድታ፣ መሶብ ወርቅ ሰፍታ፣ መጋረጃ ፈትላ፣ ካህናትን አገልግላ እንድትኖር እንሰጣለን ብለው ስዕለት ገቡ። ዘካርያስም እግዚአብሔር ጸሎታችሁን ይስማችሁ ስእለታችሁን ይቀበልላችሁ ጻህቀ ልቦናችሁን ይፈጽምላችሁ ብሎ አሳረገላቸው።

🔷👉 ከዚያም በኋላ ቅድስት ሐና እና ቅዱስ ኢያቄም ዕለቱኑ ራዕይ ዐይተው ነገር አግኝተው አደሩ። ራዕዩም ኢያቄም “ርኢኩ በህልምየ እንዘ ይትረኀው ሰባቱ ሰማያት - ፯ቱ ሰማያት እንደ መጋረጃ ተገልጠው ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ አየሁ” አላት ፤ ወፍ የተባለው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ነጭነቱ ንጽሐ ባሕሪው ነው፤ ከላይኛው ሰማይ ነጭ ወፍ ወርዶ በራሴ ላይ ሲቀመጥ ዐየሁ ማለቱ፤ አምላክ የኢያቄምን ( የሰውን) ባሕርይ ባሕርይ እንዳደረገው ሲያጠይቅ ነው፤ ፯ቱ ሰማያት የተባሉ የጌታችን ልዩ ልዩ ባሕርይው፣ ምልአቱ፣ ስፍሃቱ፣ ርቀቱ፣ ልእልናው፣ ዕበዩ መንግሥቱ ናቸው።

🔴👉 ሐናም እኔም አየሁ አለችው፤ ምን አየሽ ቢላት፤ “ዖፍ ጸዓዳ መጽአት ኀቤየ ወነበረት ዲበ ርዕስየ ወቦአት ውስተ ዕዝንየ ወኀደረት ውስተ ከርስየ - ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማኅጸኔ ስትተኛ አየሁ” አለችው። ርግብ የተባለች እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት። ነጭ መሆንዋ ንጽህናዋ፣ ቅድስናዋ፣ ድንግልናዋ ነው። ነጭ ርግብ መጥታ በራሴ ላይ ተቀምጣ ከራሴ ወርዳ በጆሮዬ ገብታ በማሕጸኔ ስትተኛ አየሁ ማለቷ ብሥራተ ገብርኤልን በጆሮዋ ሰምታ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን መጽነሷን ነው። ይህንኑም ራዕይ ያዩት ሐምሌ ፴ (ሠላሳ) ዕለት ነው።

🔷👉 እነሱም እንዲህ ያለ ራዕይ ካየን ነገር ካገኘን ብለው ዕለቱን በሩካቤ ሥጋ አልተገናኙም፤ ፈቃደ እግዚአብሔር ቢሆን ብለው አዳምንና ሔዋንን ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሏት ብሎ ያበሰረ አምላክ ለኛስ ይልክልን የለምን? ብለው ዕለቱን አልጋ ምንጣፍ ለይተው እስከ ፯ ቀን ድረስ ለየብቻቸው ሰነበቱ። በነሐሴ በሰባተኛው ቀን ከሰው የበለጠች ከመላእክት የከበረች ደግ ፍጥረት ትወልዳላችሁና ዛሬ በሩካቤ ሥጋ ተገናኙ ብሏችኋል ጌታ ብሎ መልአኩ ለሐና ነገራት። በፈቃደ እግዚአብሔር በብሥራተ መልአክ እመቤታችን እግዝእትነ ማርያም ነሐሴ ፯(7) ቀን ተፀነሰች።

🔴👉 እመቤታችን ከተፀነሰች በኋላ አይሁድ ቀንተው ተነሱባቸው። ከቅናትም የተነሳ ሊገድሏቸው ይፈልጉ ነበርና በመልአኩ ትዕዛዝ ሸሽተው በሊባኖስ ተራራ ላይ እመቤታችን እግዝትእነ ማርያም በተፀነሰች በ፱(9) ወር ከአምስት ቀን የግንቦት መባቻ ዕለት ግንቦት ፩(1) ተወለደች።

🔴👉 የእመቤታችን እድሜ ሦስት ዓመት ሲሞላው ጠቢቡ ሰሎሞን “ሰነፎች ደስ አያሰኙትምና ለእግዚአብሔር ስእለት በተሳልኽ ጊዜትፈጽመው ዘንድ አትዘግይ የተሳልኸውን ፈጽመው ተስለህ የማትፈጽም ብትኾን ባትሳል ይሻላል” መክ 5፡4-5 ብሎ የተናገረውን በማሰብ ባሏ ኢያቄምን ይኽቺ ብላቴና የብጽአት ገንዘብ እንደኾነች ታውቃለኽ ወስደን ለቤተ እግዚአብሔር እንስጣት አለችው፡፡

🔷👉 እርሱም ፍቅርሽ ይለቅልሽ ብዬ ነው እንጂ እኔማፈቃዴ ነው አለ፤ ኢያቄም ይኽነን ማለቱ ሐና እመቤታችንን በመካንነት ኑራ ያገኘቻት አንድያ ልጇ ናትና ከፍቅሯ ጽናት የተነሣ ተለይታት አታውቅም ነበርና ነው፡፡ ከዚህም በኋላ ቅድስት ሐና ከቅዱስ ኢያቄም ጋር በመሆን ካህኑ ዘካርያስ ወደሚገኝበት ቤተመቅደስ ልጃቸውን ወሰዷት፡፡ ኢያቄምና ሐና እግዚአብሔርን በማመስገን ካህኑ ዘካርያስን ‹‹ይህቺ ብላቴና ስዕለት ተስለን አምላካችን በቸርነቱ የሰጠን ናትና ተቀበለን›› አሉት፡፡ እርሱም ቢያያት እንደ ፀሓይ የምታበራ እንደመብረቅ ግርማዋ የሚያስፈራ የምታበራ ዕንቈ ባሕርይ መስላታየችው፡፡

🔴👉 ወደ ቤተመቅደስ በወሰዷት ወቅትም እርሱም በአድናቆት ይህቺን የመሰለች ፍጥረት ምን እናደርጋታለን፣ ምን እናበላታለን፣ ምንስ እናጠጣታለን፣ ምን እናነጥፍላታለን፣ ምን እንጋርድላታለን ብሎ ሕዝቡን ሰብስቦ ሲጨነቁ ሳለ ለእስራኤል ደመና ጋርዶ መናን አውርዶ የመገበ፤ ለኤልያስም በመልአኩ እጅ በመሶበ ወርቅ ኅብሥት የመገበ፤ ለዕዝራ ሱቱኤልም በመልአኩ በቅዱስ ዑራኤል እጅ መልኩ እሳት የሚመስል ጽዋዐ ልቡና ያጠጣው ልዑል እግዚአብሔር ለእናትነት ወደ መረጣት ወደ እናቱ መልአኩ ቅዱስ ፋኑኤልን ላከላት (ዘፀ 16፡ 31፤ 1ኛነገ 19፡6፤ ዕዝ. ሱቱ. 13፥38-41)::

🔷👉 በዚያን ጊዜ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤል ኅብስት ሰማያዊ በብርሃን ጽዋዕ ስቴ ሕይወት ይዞ ረቦ ወረደ፤ ዘካርያስ ለእርሱ የመጣ ሀብት መስሎት ሊቀበል ቢነሣ ወደ ላይ ሰቀቀበት፤ ያን ጊዜ ጥበበ እግዚአብሔር አይመረመርምና ለዚህች ብላቴና የመጣ ሀብት ይኾናል እስኪ እልፍ አድርጋችኊ አኑሯት አለ፤ እልፍ አድርገው ቢያኖሯት እመቤታችን እናቷን ስትከተል መልአኩ አንድ ክንፉን አንጽፎ አንዱን ክንፉን አጐናጽፎ ከመሬት የሰው ቁመት ያህል ከፍ ብሎ ኅብስቱን መግቧት ጽዋውን አጠጥቷት ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡

የእናታችን የቅድስት በዓታ ለማርያም ረድኤት በረከቷ ይደርብን

ለሁሉም እንዲደርስ ላይክ ሼር አድርጉ

    ።።።።
#ወስበሐት_ለእግዚአብሔር ።።።።
     ።።።።።
#ወለወላዲቱ_ድንግል ።።።።።
     ።።።።።
#ወለመስቀሉ_ክቡር ።።።።።
[ታኅሣሥ 22 የአምላክ እናት ተአምሯን ለጻፈላት ለቅዱስ ደቅስዮስ በረከቷን የሰጠችበት]
ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ
💥 ደቅስዮስ የተወለደው በ607 ዓ.ም. ሲኾን ከጊዜ በኋላ የቶሌዶ ጳጳስ የሆነው አጎቱ ዩጄኒየስ በወጣትነቱ ቃለ እግዚአብሔርን ያስተምረው ነበረ። ከዚያም በ632 ዓ.ም አካባቢ የቶሌዶ ኤጲስ ቆጶስ ኤላዲዎስ ዲያቆን አድርጎ ሾሞታል። ከፍ ካለ በኋላ በቶሌዶ አቅራቢያ ወደሚገኘው የአጋሊያ ገዳም በመግባት የገዳሙ አበምኔት ኾነ። ከዚያም በ657 የቶሌዶ ሊቀ ጳጳስ ኾኖ ተመረጠ።

💥 ደቅስዮስ እመቤታችንን በፍጹም ልቡ ከመውደዱ የተነሣ በተቻለዉም ኹሉ ያገለግላት ነበር “ወእምንደተ ፍቅሩ አስተጋብአ መጽሐፈ ተአምሪሃ” ይላል ከፍቅሩም ጽናት የተነሣ ክብሯን፣ ንጽሕናዋን፣ ቅድስናዋን፣ ዘላለማዊ ድንግልናዋን፣ ወላዲተ አምላክነቷን፣ ተአምሯን የሚናገር መጽሐፍን ሰበሰበ።

💥 ደቅስዮስ መሰብሰብ ብቻ ሳይኾን ድርሰትም ደራሲ ነበረ። ከጻፋቸው ከደብዳቤዎቹ ሁለቱ እና አራቱ ጽሑፎቹ አሁንም ድረስ አሉ። በተለይ የመዠመሪያው እና ዋናው ክፍል ስድስት ድርሰቶችን ያቀፈና ልክ እንደ ጀሮም ርሱም ሄልቪደስን ተቃውሞ ስለ እመቤታችን ዘላለማዊ ድንግልና የጻፈው "De virginitate perpetuâ sanctae Mariae adversus tres infideles" (On the Perpetual Virginity of Holy Mary) በመባል የሚታወቅ ሥራው ነው። ይኽ የደቅስዮስ መጽሐፍ ለ3 የተከፈለ ሲኾን "ቅድመ ወሊድ፣ ጊዜ ወሊድ፣ ድኅረ ወሊድ" ዘላለማዊት ድንግል መኾኗን ይተነትናል።

💥 ቅዱስ ደቅስዮስ የእመቤታችን ዘላለማዊ ድንግልናዋ የልጇ የክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት የሚገልጽ ምልክት እንደኾነ ሲገልጽ ልጇ እግዚአብሔር ነውና ብቻውን በድንግልና ተፀንሶ በድንግልና ሊወለድ ችሏል ብሏል።

💥 ደቅስዮስ እመቤታችንን በጽሑፉ ማርያም ብቻ ብሎ በስሟ አይጠራትም። ይልቁኑ ድንግሊቱ፣ የእኛ ድንግል ይላታል።

💥 ያን ጊዜ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተገልጻለት “ይኽን መጽሐፍ ስለ ጻፍኽልኝ ደስ ብሎኛል” ብላው ባርካው ተሰወረች፡፡

💥 በተጨማሪም በ304 ዓ.ም. በዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ሰማዕትነትን በተቀበለችው በቅድስት ሊዮካዲያ (Saint Leocadia) የከበረ ዐፅም ፊት ሲጸልይ በተአምራት ተነሥታ የአምላክን እናት ስላከበራት አመስግናዋለች።

💥 ቅዱስ ደቅስዮስም ይኽነን ኹሉ ካየ በኋላ እጅጉን በመደሰት ለእመቤታችን ክብር ምን መሥራት እንዳለበት በማሰብ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን ያበሠረበት መጋቢት 29 ቀን የዐቢይ ጾም በመኾኑ ምክንያት ሰዎች ማክበር ያልተቻላቸውን በዓለ ብሥራትን ከልደት በዓል ስምንት ቀናት ቀደም በማድረግ ታኅሣሥ 22 ዕለት እንዲከበር ሥርዐትን ሠራ። በቶሌዶ በተደረገ ጉባኤ ለአምላክ እናት ክብር የተለየ የበዓላቷን ቀን ተደነገገ።

💥 ምእመናንም እጅጉን በመደሰት በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ወልደ እግዚአብሔር በማሕፀነ ማርያም የተፀነሰበትን በዓል ለውጥ በማሰብ በዓሉን በድምቀት አከበሩ፡፡ ያን ጊዜ በወርኃ ታኅሣሥ በ665 ዓ.ም. በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች እመቤታችን ለደቅስዮስ ለብቻው ተገልጻለት “ወዳጄ ደቅስዮስ ባንተ ደስ አለኝ፤ ሥራኽንም ወደድኊ፤ በዓሌን አክብረኽ ስለ እኔ ሰውን ኹሉ ደስ አሰኝተኻልና እኔም ዋጋኽን ልሰጥኽ እወዳለኊ ትቀመጥበትም ዘንድ ይኽነን ወንበር አመጣኹልኽ” በማለት በወንበሩም ላይ ማንም ሊቀመጥባት የሚቻለው እንደሌለ ነግራው ከርሱ ተሰወረች፡፡

💥 በሌላ ጊዜ ኤጲስ ቆጶሱ ደቅስዮስ ከምእመናን ጋር የእመቤታችንን መዝሙር ሲዘምሩ ከፍተኛ ብርሃን ወርዶ ቤተ ክርስቲያኒቱን ሲከብባት አብዛኞቹ ምእመናን ፈርተው ሲሸሹ ደቅስዮስ ከጥቂት ዲያቆናት ጋር ብቻ ቀረ። ያንጊዜ ቅድስት ድንግል ማርያም ደናግልን አስከትላ ወርዳ በኤጲስ ቆጶስ ዙፋን ላይ ተቀምጣ አየ። እመቤታችንም ደቅስዮስን ለታማኝነቱ አመስግናው እጅግ የተለየ ልብሰ ተክህኖ በበዓላቷ ላይ ብቻ እንዲለብስ ሰጥታው በእመቤታችን በዓላት ይለብሰው ነበር።

💥 ቅዱስ ደቅስዮስም በ667 ዓ.ም. ከዚኽ ዓለም በሕይወተ ሥጋ በተለየ ጊዜ እመቤታችን የባረከችውን ልብስ በቤተ ክርስቲያን ዕቃ ቤት በክብር አኖሯት፤ ከርሱ በኋላ የተሾመው ኤጲስ ቆጶስ ግን ያችን ልብስ ሊለብሳትና በደቅስዮስም ወንበር ሊቀመጥ ወደደ።

💥 ቀሳውስትና መምህራን ግን የልብሷን ክብር በመንገር ይኽነን እንዳያደርግ ቢለምኑት ርሱ ግን ልክ እንደ ዖዝያን በድፍረት ልብሷን ለብሶ በወንበሩ በተቀመጠ ጊዜ ሐናንያና ሰጲራ በቅዱስ ጴጥሮስ ፊት ተቀሥፈው እንደሞቱ፤ ርሱም “ወድቀ በጊዜሁ እምላዕለ ውእቱ መንበር በቅድመ ኲሎሙ ሰብእ እለ ሀለዉ ውስተ ቤተ ክርስቲያን ወሞተ በእኩይ ሞት ወሕሡም ፈድፋደ” ይላል በዚኽ የድፍረት ኀጢአቱ ከዚያ ወንበር ላይ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ባሉ ሰዎች ኹሉ ፊት ወድቆ ክፉ አሟሟትን ሞቷል፤ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተደረገው ተአምር ሕዝቡ በመደነቅ ምስጉን እግዚአብሔርን በማመስገን አምላክን የወለደች ክብርት እመቤታችንን ስለ አደረገችው ተአምር እጅጉን አክብረዋታል፡፡ በግእዝ በብራና በተጻፉት ተአምረ ማርያም ላይ ይኽ የቅዱስ ደቅስዮስ ታሪክ ተሥሎ ማየት የተለመደ ነው።

💥 ከዚያ በኋላ የሰጠችው ልብስ ቢሰወርም ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ለደቅስዮስ ስትገለጥለት እግሯን ያሳረፈችበት ድንጋይ ግን በቶሌዶ ካቴድራል ጸሎት ቤት ውስጥ ይከበራል።

💥 ንጉሥ ዳዊትም እንደነ ደቅስዮስ ላሉ እመቤታችንን ለሚወዷት ኹሉ በምልጃዋ ከልጇ ስለምታሰጣቸው ታላቅ መንፈሳዊ በረከት መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ ገልጦለት “ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ” (በአባቶችሽ ፈንታ ልጆች ተወለዱልሽ) በማለት ከገለጠ በኋላ “ወትሠይሚዮሙ መላእክተ ለኲሉ ምድር” (በምድርም ኹሉ ላይ ገዢዎች አድርገሽ ትሾሚያቸዋለሽ) በማለት የሠያሜ ነገሥት፣ የሠያሜ ካህናት የክርስቶስ እናት መኾኗንና፤ ይኽነንም የአምላክ እናትነቷን ለመሰከሩ ለነ ደቅስዮስ ወንበር፤ ለነ ኒቆላዎስ ዐጽፍ፣ ለነ ቅዱስ ኤፍሬም “አኀዝ እግዚኦ መዋግደ ጸጋከ” (አቤቱ የጸጋኽን ማዕበል ግታው፤ ወስነው) እስኪሉ ድረስ በቃል ኪዳኗና በአማላጅነቷ ያሰጠቻቸው ታላቅ በረከት መንፈሳዊ ሹመትና ብቃት መኾኑን አሳይቷል፡፡

💥 “ወይዘክሩ ስመኪ በኲሉ ትውልደ ትውልድ” (ለልጅ ልጅ ኹሉ ስምሽን ያሳስባሉ) በማለት በክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት በርሷ ወላዲተ አምላክነት በማመን የጸና ያለፈውና የሚመጣው ትውልድ ኹሉ “ሰአሊ ለነ ቅድስት” (ቅድስት ሆይ ለምኝልን) እያለ የተቀደሰ ስሟን ሳይጠራ የሚውል ማንም እንደማይኖር ቅዱስ ዳዊት በመንፈሰ እግዚአብሔር ገላጭነት ተናግሯል (መዝ ፵፬፥፱-፲፯)፡፡

💥 ሊቁ አባ ጊዮርጊስም በሕማማት ሰላምታው ላይ፦
“ማርያም ሀብኒ ልብሰ ትፍሥሕት ወተድላ
ከመ ወሀብኪዮሙ ቅድመ ምስለ መሐላ
ለደቅስዮስ ወለኒቆላ ሰላም ለኪ"
(ለኒቆላና ለደቅስዮስ ከቃል ኪዳን ጋራ አስቀድመሽ እንደሰጠሻቸው ሰላምታ የተገባሽ ማርያም የፍጹም ደስታና ተድላ ልብስን ስጪኝ) በማለት ተማፅኗታል፡፡

💥 የነገረ ማርያም ሊቃውንት የነበሩት አባ ጽጌ ድንግልና አባ ገብረ ማርያም ዘደብረ ሐንታም በማሕሌተ ጽጌ መጽሐፋቸው ላይ እመቤታችን ተአምሯን ሰብስቦ ላዘጋጀላት ለደቅስዮስ ታላቅ ጸጋን በቃል ኪዳኗ እንዳሰጠች ሲገልጹ፦
“ሶበ ጸሐፈ ደቅስዮስ ተአምረኪ ቅዱሰ
መንበረ ወዐጽፈ ዕሤተ ጻማሁ ወረሰ
ማርያም ድንግል ዘታብእሊ ፅኑሰ
ዐስበ ማሕሌትየ ዐቅመ ልብየ ኀሠሠ
ጸግውኒ አትሮንሰ ወጽጉየ ልብሰ”

(ደቅስዮስ ልዩ የኾነ ተአምርሽን በጻፈ ጊዜ የድካሙን ዋጋ ልብስንና ወንበርን አገኘ፤ ድኻውን ባለጠጋ የምታደርጊ (ነዳየ አእምሮውን በቃል ኪዳንሽ ባለ አእምሮ የምታደርጊ) ድንግል ማርያም ልቡናዬ በፈለገ መጠን የምስጋናዬን ደሞዝ ወንበርንና የክብር ልብስን ስጪኝ) በማለት የሿሚ የክርስቶስ እናት የቅድስት ድንግልን በረከት ልክ እንደ አባ ጊዮርጊስ ሽተዋል፡፡
በቤተ ክርስቲያን 5 አይነት አክሊላት አሉ

1 አክሊለ ሰማዕት
ይህ አክሊል ሰማእታት በተጋድሎ የሚያገኙት አክሊል ነው  ቅዱስ
ጳውሎስም ስለዚህ አክሊል ሲናገር ሃይማኖቴን ጠብቄለው ሩጫዬን ጨርሻለው ወደፊት የጽድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል ብሎ ጠቅሶታል
2 ጢሞ 4+6-7
በተመሳሳይ ባለራዕዩ ቅዱስ ዮሐንስም እስከሞት ድረስ የታመንክ ሁን የሕይወት አክሊል እሰጥሃለው ብሎ የተናገረው ስለ ሰማእታት አክሊል ነው ራዕ 2+10 ክርስቶስም አክላሎሙ ለሰማእት ተብሏል እመቤታችንም አክሊለ ሰማእት ትባላለች

2 አክሊለ ሶክ (አስኬማ መላእክት)
ይሄ አክሊል የአባ እንጦንዮስ አክሊል ሲሆን መነኮሳት የሚያደርኩት አክሊል ነው ይሄ አክሊል በምንኩስና ዓለምን ከናቁ በኋላ የሚገኝ ነው ክርስቶስ በዕለተ አርብ የተቀበለው አክሊለ ሶክ የሚታሰብበት ሲሆኔ ይሄን አክሊል ያደረጉ መነኮሳት እንደ መላእክት በንጽሕና በቅድስና ስለሚኖሩ አስኬማ መላእክት ተብሏል

3 ተክሊል (የተክሊል አክሊል)
ይህ አክሊል በድንግልና ኑረው ለሚጋቡ ኦርቶዶክሳውያን የሚደረግ የድንግልና ምልክት የሆነ አክሊለ ከብካብ ነው ደናግል ላልሆኑ ፈጽሞ የማይደረግ ነው 

4 አክሊለ ነገሥት ይህ አክሊል ለነገሥታት ብቻ የሚደረግ ነው ሰሎሞን ሲነግሥ ሲቀባ የተደረገለት አክሊል ነው አባ ሕርያቆስ በቅዳሴው  ወአክሊሉ ለሰሎሞን የሰሎሞን አክሊል ነሽ ብሎ የተናገረው  የነገሥታት አክሊል እመቤታችን እንደሆነችና ነገሥታት ሲነግሢ ተቀብተው አክሊል እንደሚያደርጉ ለመግለጽ ነው

5 አክሊለ ካህናት
ይህ አክሊል በክህነት የሚያገለግሉ ካህናትና ዲያቆናት የሚያደርርጉት አክሊል ነው
ክህነት ለሌለው ፈጽሞ የማይደረግ ሲሆን የካህናት አክሊል አሰራሩ ከላይ 4 ማዕዘን ሲሆን የዲያቆናት አክሊለም በአሰራር ከካህናት የተለየ ክብ ነው ዲያቆን የቄሱን አክሊል ፈጽሞ ማድረግ አይችልም  አምስቱ አክሊላት እነዚህ ናቸው
አሁን አሁን ግን የካህኑን እና የዲያቆኑን አክሊል ሴቶች ሳይቀር አድርገውት እየታየ ስለሆነ እጅግ የሚያሳዝን ነው 
ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን እየተጣሰ  ቸል ተብሎ እየታየ ነው ስለዚህ  የሊቃውንት ጉባኤ ይሄን ጉዳይ እልባት ሊሰጥበት ይገባል ።
​​ጾመ ሰብአ ነነዌ

ጾመ ነነዌ ከሰባቱ የአዋጅ አጽዋማት አንዷ ስትኾን የምትጾመውም ለሦስት ቀናት ነው፡፡ ይህቺ ጾም የምትጀመርበት ዕለትም ልክ እንደ ዐቢይ ጾም ሰኞን አይለቅም፡፡ ጾሟ የምትጀመርበት ቀን ሲወርድ ወይም ወደ ኋላ ሲመጣ እስከ ጥር ፲፯ ቀን ድረስ ነው፡፡

ቀኑ ሲወጣ ወይም ወደ ፊት ሲገፋ ደግሞ እስከ የካቲት ፳፩ ቀን ይረዝማል፡፡ ጾመ ነነዌ በእነዚህ ፴፭ ቀናት ውስጥ ስትመላለስ (ከፍ እና ዝቅ ስትል) ትኖራለች፤ ከተጠቀሱት ዕለታት አትወርድም፤ አትወጣም፡፡ በዚህ ዓመትም የካቲት ፫ ቀን ትጀመራለች፡፡

‹‹ጾመ ሰብአ ነነዌ፤ የነነዌ ሰዎች ጾም›› የሚለው የጽሑፋችን ርእስ እንደሚያስረዳው ይህቺን የሦስት ቀን ጾም የጾሟት በነነዌ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ከተማዋም (ነነዌ) በጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ የምትገኝ ስትኾን መሥራቿም ናምሩድ ነው  ዘፍ.፲፥፲፩-፲፪/ ፡፡ ጥንታዊቷ የነነዌ ከተማ ለአሦር መነሻ የኾነች፤ እጅግ ሰፊና ያማረች፤ የቅጥሯ ርዝመትም ፲፪ ኪሎ ሜትር የሚሸፈን ነበር። በከተማዋ ንጉሡ ሰናክሬም ብዙ ሕንጻዎችን ገንብቶባት ነበር /ዮናስ ፬፥፲፩/፡፡

በዚያ ዘመን የነበሩ የነነዌ ሰዎች ኀጢአታቸው በዝቶ እግዚአብሔር ሊያጠፋቸው ሲል ቸርነትና ምሕረቱ የማያልቅበት እግዚአብሔር መክሮ፣ ዘክሮ እንዲመልሳቸውና ንስሐ እንዲገቡ ነቢዩ ዮናስን ወደ ነነዌ ሕዝብ ላከው /ሉቃ.፲፩፥፴/፡፡

ዮናስ የስሙ ትርጕም ‹ርግብ› ማለት ነው፡፡ በዳግማዊ ኢዮርብዓም ዘመነ መንግሥት የነበረ ነቢይ ነው፡፡ ይህ ነቢይ መኖሪያው በገሊላ በጋትሔፌር ድንበር ከተማ ነበረ፡፡ አባቱም አማቴ ይባላል፡፡ ኢዮርብዓም ሶርያውያንን አባሮ የእስራኤልን ድንበር እንዲመልስ ነቢዩ ዮናስ ትንቢትን ተናግሯል /፪ኛነገ.፲፬፥፳፭፤ ዮናስ ፩፥፩/፡፡

ነቢዩ ኤልያስ ያስነሣው የሰራጵታዋ መበለት ሕፃን ነቢዩ ዮናስ እንደ ኾነ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ያስረዳል /፩ኛ ነገ.፲፯፥፲፱/፡፡ መድኀኔታችን ክርስቶስም የዮናስን ከዓሣ ኾድ መውጣት የራሱ ትንሣኤ ምሳሌ አድርጎ ነግሮናል /ማቴ.፲፪፥፲፱-፵፪፤ ሉቃ.፲፩፥፴-፴፪/፡፡

እግዚአብሔር ‹‹ሔደህ በነነዌ ላይ ስበክ›› ባለው ጊዜ ነቢዩ ዮናስ ‹‹አንተ መሐሪ ነህ ፤ ልትጠፉ ነው ብዬ ተናግሬ ብትምራቸው ሐሰተኛ ነቢይ እባላለሁ›› ብሎ ላለመታዘዝ እስራኤልን ለቆ በመርከብ ወደ ተርሴስ ሸሸ፡፡

እግዚአብሔርም ታላቅ ነፋስን አስነሥቶ መርከቧ በማዕበል እንድትመታ አደረገ፡፡ ከዮናስ ጋር በመርከቧ ተሳፍረው የነበሩ ነጋድያንም ያላቸውን ሀብት ወደ ባሕሩ መጣል ሲጀምሩ ነቢዩ ዮናስ ጥፋቱን ተገንዝቦ ‹‹ማዕበሉ በእኔ ምክንያት የመጣ ስለ ኾነ ንብረታችሁን ሳይኾን እኔን  ወደ ባሕር ጣሉኝ›› ብሎ ተማጸናቸው፡፡

እነርሱም ‹‹ስለዚህ ሰው ነፍስ እንዳንጠፋ፣ ንጹሕም ደም በእኛ ላይ እንዳይደረግብን አይኾንም›› አሉ፡፡

ወደ ባሕሩ ለመጣል ዕጣ በተጣጣሉ ጊዜም ዕጣው በዮናስ ላይ ስለ ወጣ ነጋድያኑ ዮናስን ወደ ባሕሩ ጣሉት፡፡ ወዲያውኑ ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዘ ታላቅ ዓሣ አንበሪ ዮናስን በአፉ ተቀብሎ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት አሳድሮ ወደ ነነዌ አደረሰው፡፡

እግዚአብሔር የቅል ተክልን ምሳሌ በማድረግ ቅጠሉ በመድረቁ ዮናስ ባዘነ ጊዜ ‹‹አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ ቀን በቅሎ ላደገ ቅል ስታዝን እነሆ በታላቂቱ ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለ ኾኑ ያሳዝኑኛል›› በማለት ነቢዩ ዮናስም ውሸታም ላለመባል መኮብለሉ ስሕተት መኾኑን አስረድቶታል፡፡

ዮናስም ነነዌ መሬት ላይ መድረሱን ባወቀ ጊዜ ከእግዚአብሔር መሸሽ አለመቻሉን ተረዳ፤ የነነዌ ሰዎችንም ‹‹ንስሐ ግቡ›› እያለ መስበክ ጀመረ፡፡ የነነዌ ሰዎችም ንስሐ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር ይቅር ብሎ ከጥፋት አድኗቸዋል። ሐሰት እንዳይባልም እሳቱ እንደ ደመና ኾኖ ከላይ ታይቶአል፡፡

የታላላቁ ዛፍ ቅጠል እስኪጠወልግ ድረስ አድርቆ ለሕዝቡ አሳይቷቸዋል፡፡ ንስሐቸው በከንቱ እንዳልቀረ አስረድቷቸዋል /ትንቢተ ዮናስን በሙሉ ይመልከቱ/። ታኅሣሥ ፭ ቀን የሚነበበው የመጽሐፈ ስንክሳር ክፍል ‹‹ወበልዐ አሐደ ኀምለ›› በማለት ንስሐ ያልገቡ አንድ አገር ያህል ሰዎች በእሳቱ እንደ ጠፉ ይነግረናል፡፡

ጾመ ነነዌ የሦስት ቀን ሱባኤ ናት፤ በሦስት ቀናት ጾምና ጸሎት ንስሐ የገቡ የነነዌ ሰዎች ከጥፋት እንደ ዳኑ ዅሉ፣ በብሉይ ኪዳን አስቴር ሦስት ቀን ጾማ፣ ጸልያ በእስራኤል ላይ የመጣውን መቅሠፍት እንዲመለስ አድርጋለች /አስ.፬፥፲፭-፲፮/፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ከበዓል ስትመለስ ሕፃኑ ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ ላይ ጠፍቶአት ከሦስት ቀን ፍለጋ በኋላ በቤተ መቅደስ አግኝታዋለች /ሉቃ.፪፥፵፮/፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለሄሮድስ በሰጠው ምላሽ መልስ ሦስት ቀን የሱባኤ ፍጻሜ መኾኑን ገልጿል /ሉቃ.፲፫፥፴፪/፡፡

ጾመ ነነዌ የእግዚአብሔርን ቸርነትና መሐሪነት የምናስታውስበት ጾም ነው። ይኸውም እኛ ፍጡራኑ በበደልን ጊዜ ፈጽሞ ከማጥፋት ይልቅ ምክንያት ፈልጎ እንድንድን ያደርገናል፡፡ ዮናስ ለስብከት ፈቃደኛ ባይኾን እንኳን እግዚአብሔር በተለየ ጥበቡ እንዲሔድ አድርጎታል፡፡

በእርግጥ እግዚአብሔር ሌላ የሚልከው ነቢይ አጥቶም አይደለም፤ እርሱንም ጭምር ሊያስተምረው ስለ ፈለገ እንጂ። የነነዌ ሰዎች የተነሳ ሕያን ምሳሌ ናቸው፡፡ ይህም ማለት ሰው ጥፋቱን አምኖ ንስሐ ከገባ እግዚአብሔር ይቅር ማለቱን አይተውም፡፡ ለዚህም ነው ዮናስን ‹‹አንተ ላልደከምክበት እና በአንድ  ቀን በቅሎ  ላደገ ቅል  ስታዝን እነሆ በታላቂቱ  ነነዌ ከተማ ያሉ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ በላይ ሕዝብና እንስሳቱ የእጄ ፍጥረቶች ስለ ኾኑ ያሳዝኑኛል›› ያለው፡፡

ቀደምት የቤተ ክርስቲያን አባቶቻችን ይህን እና ሌሎች አጽዋማትን እንድንጾም የወሰኑልን ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ ሕጉ የተዘጋጀልን እንደ ነነዌ ሰዎች እኛም ጾመን፣ ጸልየን ከኀጢአታችን እንነጻ ዘንድ ነው፡፡ ዛሬ ዓለማችን በኀጢአት ማዕበል እየተናወጠች ባለችበት ወቅት እኛም እንደ ነነዌ ሰዎች ከበደላችን ብንመለስ እና ንስሐ ብንገባ ቸሩ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ይቅርታና ምሕረት የባሕርይ ገንዘቡ ስለ ኾነ ‹‹ወደ እኔ  ተመለሱ፤ እኔም ይቅር  እላችኋለሁ፤›› ይለናል፡፡

ስለኾነም በነቢዩ ዮናስ ላይ የተደረጉ ተአምራትንና ካለመታዘዝ የሚመጣ ቅጣት ቀላል አለመኾኑን በማስተዋል፣ ለነነዌ ሰዎች የወረደውን ምሕረት በመገንዘብ ለእግዚአብሔርም ኾነ ለሃይማኖት አባቶች እና ለወላጆቻችን መታዘዝ ይገባናል፡፡

ስንጾምም እግዚአብሔር አምላካችን መዓቱን በምሕረት፣ ቍጣውን በትዕግሥት መልሶ በኀጢአት ለጠፋው ዓለም ይቅርታውን ይልካል፡፡ በመጾማችን ራሳችን ከመዓትና ከመቅሠፍት ከመዳናችን ባሻገር በእኛ በደል ምክንያት አገራችን፣ ዕፀዋቱና እንስሳቱም ሳይቀር ከድርቅና ከቸነፈር ይተርፋሉና፡፡

✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞
ለተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE
  
https://www.tgoop.com/DIYAKONAE
#ዐብይ_ጾም

#ዐብይ_ጾም ፦ማለት ምን ማለት ነው በመጀመሪያ ‹‹ዐቢይ›› የሚለው ቃል ‹‹አበየ›› ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ ነው፡፡ ትርጓሜውም ‹‹ከፍ አለ›› ማለት ነው፡፡

የዐብይ ጾም የተለያየ ስያሜዎች ዐብይ ጾም ከቀኑ ርዝማኔ በተጨማሪ ጾሙ የተለያዩ ስያሜዎች አሉት፡፡

#ጾመ_ሁዳዴ፡- ሁዳድ ማለት ሠፊ (ትልቅ) የእርሻ ቦታ ማለት ነው፡፡ ይህም ጾም ደግሞ በቀኑ ብዛት ትልቅ (ሠፊ) በመሆኑ የሁዳዴ ጾም ይባላል፡፡

#የካሳ_ጾም፡- እንዲህ የተባለበት ምክንያቱ ደግሞ አዳምና ሔዋን በዲያቢሎስ ግዞት እያሉ ክርስቶስ ደሙን በመክፈል (በመካስ) ነጻ ስላውጣቸው የካሳ ጾም ተብሎሏል

#የድል_ጾም ፡-ይህም ደግሞ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ጾም ሰይጣንን ድል ያደረገበት በመሆኑ የድል ጾም ተብሏል፡፡

#የመሸጋገሪያ_ጾም ፦ጌታችን ከሕገ ኦሪት ወደ ሕገ ወንጌል ሊያሸጋግረን የጾመው ጾም በመሆኑ የመሸጋገሪያ ጾም ተብሏል።

#ጾም_አስተምህሮ፡- ይህ ጾም ‹‹ጾም አስተምህሮ›› የተባለበት ምክንያት ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማስተማር የጾመው በመሆኑ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ደግሞ የተለያዪ ስያሜዎች አሉት
‹‹የመሸጋገሪያ ጾም ››
‹‹የስራ መጀመሪያ ጾም ››

ይህ ፆም ታላቅ መባሉም ለ55 ቀናት ያህል መፆሙና ከሌሎቹ አፅዋማት ጋር ሲነፃፀር በቁጥር
መብለጡ ብቻ ሳይሆን ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በገዳመ
ቆሮንቶስ መፆም ሳይገባው ለእኛ አርአያና ትልቅ ምሳሌ ለመሆን የፆመው ፆምም
በመሆኑ ነው።

ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎች እንዲሁም ደግሞ ሶስቱ ርዕሰ ኃጢአት የሚባሉት
#ትዕቢት
#ስስት
#ፍቅረ_ነዋይ
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ድል የተመቱበት ስለሆነ ይህ ጾም አብይ (ታላቅ) ተብሏል፡፡

የአብይ ጾም ሳምንታት 8 ናቸው፤
1. 
#ዘወረደ
2. 
#ቅድስት
3. 
#ምኩራብ
4. 
#መጻጉዕ
5. 
#ደብረዘይት
6. 
#ገብርሔር
7. 
#ኒቆዲሞስ
8. 
#ሆሣዕና

አቢይ ጾም ሦስቱ ክፍሎች
1.     ዘወረደ (ጾመ ሕርቃል)፤ ይህም ጾሙ ከሚገባበት ሰኞ ጀምሮ እስከ እሑድ ያረስ ያለው 7 ቀን ነው።
2.    የጌታ ጾም፤ ይህም ከቅድስት ሰኞ እስከ ሆሣዕና ዋዜማ ዓርብ ድረስ ያለው 40 ቀን ነው።
3.    ሕማማት፤ ይህም ጌታችን በአልዓዛር ቤት ለማዕድ ከተቀመጠበት የሆሳዕና ቅዳሜ ጀምሮ እስከ ሥዑር ቅዳሜ ያለው መከራን የተቀበለበት 8 ቀን ሕማማት ነው።

ይህም 7+40+8 = 55 ቀን ማለት ነው።

የዲያብሎስን ሥራ ሊያፈርስየተገለጠው የእግዚአብሔር ልጅም በፆም ድል ማድረግን ለእኛ አስተምሮናል። እኛምበዚህ በአብይ ፆም የለመነውና የጠየቅነው ነገር ሁሉ ከኃጢአት በስተቀርእንዲከናወንልን ፆምን ገንዘባችን እናድርግ። በፆም የተጠቀሙ ቅዱሳን አባቶችና ቅዱሳንእናቶች እንዳሉን እናስተውል።

ጾም ጸሎታችን የቅዱሳን አምላክ እግዚአብሔር ይቀበልልን አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ደብረ ዘይት
የዐብይ ጾም አምስተኛ እሑድ(ሳምንት)
(የዐብይ ጾም እኩሌታ)
ደብረ ዘይት ማለት የወይራ ዛፍ ያለበት ተራራ ማለት ነው፡፡ቦታው ከኢየሩሳሌም በስተምሥራቅ የሚገኝ የወይራ ዛፍ የበዛበት ተራራ ሲሆን ስሙም ከወይራ ዛፉ:- ደብረ ዘይት (የወይራ ዛፍ ተራራ) በመሰኘት ተገኝቷል። በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ደብረ ዘይት በዓል ሆኖ የሚከበርበት ምክንያት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረዘይት ተራራ ላይ ሳለ ለቅዱሳን ደቀመዛሙርቱ ስለ ዓለም ፍጻሜ እና ስለ ዳግም ምጽአቱ ስላስተማራቸዉ በጌታችን ትምህርት መሠረት ነገረ ምጽአቱን እንድናስታውስ ወይም እያሰብን እንድንዘጋጅ ለማድረግ ነው።

ስለ ዓለም መጨረሻና ስለ ዳግም ምጽአቱ ምልክቶች ምን እንደሆኑ ሐዋርያው ቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል ላይ በሦስት መሠረታዊ ክፍሎች ከፍሎ ጽፎልናል፡፡

፩. ሃይማኖታዊ ምልክቶች

"እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉ፤ ብዙዎችንም ያስታሉ" /ማቴ 24፥5/፡፡

፪. ፖለቲካዊ ምልክቶች

“ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ” /ማቴ 24፥6/ “ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና” /ማቴ 24፥7/

፫. ተፈጥሯዊ ምልክቶች

“ረሐብም ቸነፈርም የምድር መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል” /ማቴ.24፥7/

ከላይ ያየናቸውን ምልክቶች በዓለማችን ላይ ዕለት ዕለት የምናየው የምንሰማው የአደባባይ ምስጢር ነው፡፡ ጌታችን ለደቀመዛሙርቱ የነገራቸውን ምልክቶች የቤተ ክርስቲያናችን አራት
ዐይና ሊቃውንት የወንጌሉን ገጸ ንባብ እንዲህ ብለው ያመሰጥሩታል፡፡

“እነዚህ ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያዎች ናቸው” /ማቴ.24፥8/

ምጥ ሲመጣ አስቀድሞ የምጡ መጀመሪያ ሕመም (ጣር) እንዳለ ሁሉ የዓለምም ፍጻሜ በጣር ነው የሚጀምረው። ይህንንም ጌታችን በግልጽ አስረድቶናል፦ ጦርና የጦር ወሬ መሰማት፣ ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ መነሳት፣ ርሃብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ መታየት ለዓለም ፍጻሜ የምጥ ጣር መጀመሪያዎች ናቸዉ። እነዚህ ነገሮች በሁሉም ቦታ በአንድ ጊዜ ላይከሰቱ ይችላሉ፤ ነገር ግን በልዩ ልዩ ቦታዎች ለብዙ ዘመናት ታይተዋል፤ እየታዩም ናቸው።

“ስለ ስሜ በአሕዛብ ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ” /ማቴ.24፥9/

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ "ስለ ስሜ ክርስቲያኖች በመሆናችሁ በዓለም ዘንድ ትጠላላችሁ" ብሎናል። ዓለም ክፉ ስለሚሠራ የጥሩ ነገር ተቃራኒ ሆኖ ለብዙ ዘመናት ቆይቷል። ጌታችን “ብርሃንም ወደ ዓለም ስለመጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለወደዱ ፍርዱ ይህ ነው። ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፣ሥራዉም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤ እውነትን የሚያደርግ ግን ሥራው በእግዚአብሔር ተደርጎ እንደሆነ ይገለጥ ዘንድ ወደ ብርሃን ይመጣል” /ዮሐ. 3፥19-21/ እንዳለን በክፉ ሥራ ውስጥ ያለው ይህ ዓለም በጎ ሥራ የሚሠሩትን የክርስቶስን ተከታዮች ይጠላል። ጨለማ ብርሃንን ብርሃንም ጨለማን እንደሚጠላ፤ ይህ ዓለም እኛን እንዲጠላን፣ እኛ ክርስቲያኖች ደግሞ ይህንን ዓለም ልንጠላው ይገባል።
አሁን ባለንበት ዘመን ክርስትና እየተጠላ፣ እየተናቀ ነው ያለው። “ባደጉት” ዓለማት ባዶ አብያተ መቅደሶች ቀርተው እነሆ እንመለከታቸዋለን፤ ትውልዱ በዓለም ስሜትና በሥጋ ፈቃድ ብቻ እየሔደ ነው። ክርስቲያን ነን በሚሉትም አውሮፓውያን ዘንድ የአንገት በላይ የማስመሰል ክርስትና እንጂ እንደ ቅዱስ ቃሉ የሚጓዝ አማኝ ማግኘት አይቻልም። እውነተኞች አይወደዱም፤ ይገፋሉ፤ ይናቃሉ። ሁኔታው የዘመኑ ፍጻሜ እጅግ እየቀረበ መምጣቱን በእርግጥ ያስረዳል።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከዚህም በላይ “ስለ ስሜ ለመከራ አሳልፈው ይሰጧችኋል፤ ይገድሏችሁማል” ብሏል። ክርስቲያን በመሆናቸው ብቻ ማንንም ሳይበድሉ ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ በልዩ ልዩ ሀገራት ክርስቲያኖች ሰማዕትነትን እስከ አሁን ድረስ እየተቀበሉ ነው፡፡ቅዱስ ጳዉሎስ  “ስለ አንተ ቀኑን ሁሉ እንገደላለን፤ እንደሚታረዱ በጎች ተቆጠርን” /ሮሜ 8፥36/ እንዳለው። ይህ በቅዱሱ በክርስቶስ ስም መጠላትና መከራ መቀበል ከዓለም የሚጠበቅ የፍጻሜዉ ዘመን ምልክት መሆኑን አውቀን መዘጋጀትና ከሐዋርያው ጋር “በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን” /ሮሜ 8፥37/ እያልን በእምነታችን ጸንተን መጋደል ይገባናል።

የክርስቲያኖች ቁጥር እያነሰ መምጣት፣ የአብያተ ክርስቲያናት መዘጋት፣ ሰው ሰው የሚያሰኘውን ክብርና ሞገስ ትቶ በግብሩ እንስሳትን ሲመስል የቅድስና ሕይወት ሲጠላና ሲናቅ፤ በአንጻሩ ደግሞ የሰው ልጅ ለረከሰው ለዚህ ዓለም ምኞትና ፈቃድ ሲገዛ ስናይ የዚህ ዓለም ፍጻሜ ጊዜው እየደረሰ መሆኑን አውቀን፤ ኖኅ በብዙ ኃጢአተኞች መካከል ቢኖርም ራሱን በቅድስና ጠብቆ እንደኖረ /ዘፍ.6-8/፤ ሎጥም እንዲሁ በብዙ ኃጢአተኞች መካከል ሲኖር በነርሱ ኃጢአት እንዳልተባበረ /ዘፍ. 19/ ከዚህ ዓለም ክፉ ሥራ ተለይተን ራሳችንን በቅድስና በመጠበቅ እንጋደል። ዓለሙ ስለ እምነታችን ቢጠላንም እኛም ስለ ክፉ ሥራው ንቀነው መኖር የግድ መሆኑን እንወቅ እንጂ ስለ እምነት፣ ስለ ቅድስናም ከዓለም በጎ ነገር አንጠብቅ። በተለያዩ ሁኔታዎች የሚደርሱብንን ፈተናዎች ሁሉ በትዕግስት እንቀበላቸው እንጂ በማማረር አንዘን፤ ምክንያቱም ስለ ስሜ በዓለም ዘንድ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ ተብለናልና።

“የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ አንባቢው ያስተውል!” ማቴ.24፥15/

ዓለም ራሱን በማርከስ ብቻ ሳይወሰን በፍጻሜ ዘመን በተቀደሰው ስፍራ እንኳን ሳይቀር የጥፋትን ርኩሰት ያቆማል። የተቀደሰው ስፍራ የተባለው በተቀደሰ ሃይማኖት የሚኖሩትን ሀገራት፣ ሕዝቦች የሚመለከት ነው። እንደ ኢትዮጵያ የመሳሰሉትን ሀገራት ዲያብሎስ በመልእክተኞቹ ላይ አድሮ በብዙ ርኩሰት ተፈታትኗቸዋል፤ እየተፈታተናቸውም ነው። የየሀገራቱን እምነትና ታሪክ ለማጥፋት ጥሯል፤ ብዙውንም የቅድስና ሥርዓት በርዟል፤ የቻለውንም ከነጭራሹ አጥፍቶታል። አሁን እንኳ አምልኮተ እግዚአብሔር በሚፈጸምባቸዉ ቅዱሳት መካናትና ገዳማት ሳይቀር በልዩ ልዩ ምክንያት የጥፋት ርኩሰት አዉጇል። ይህም የፍጻሜ ዘመኑ አንዱ ምልክት ስለሆነ አንባቢዉ  እንደተባለ የዘመኑን መፍጠን የጊዜውን መድረስ በመረዳት መዘጋጀት ይገባናል።

“ብዙ ሐሰተኛዎች ነቢያትም ይነሣሉ ብዙዎችንም ያስታሉ” /ማቴ.24፥11/፡፡

ብዙ ሐሰተኞች ነቢያት በየዘመኑ ተነስተው እውነተኛይቱን  ታግለዋታል፤ ሊያጠፏት ባይችሉም እንኳን ብዙ ልጆቿን ነጥቀው ወስደውባታል። የነዚህን  ሠራተኞች አመጣጥ ከባድ የሚያደርገው በተአምራትና በድንቅ ምልክቶች መምጣታቸው ነው። ጌታችን እንደተናገረ “ቢቻላቸውስ የተመረጡትን እንኳን እስኪያስቱ ድረስ ታላላቅ ምልክትና ድንቅ ያሳያሉ” /ማቴ.24፥24/ ስለዚህ በምትሐታዊ ምልክቶቻቸው የብዙ የዋሃንን ልብ በማታለል ከተቀደሰ እምነታቸው እያስኮበለሉ አጥፍተዋቸዋል፤ በማጥፋትም ላይ ይገኛሉ። ስለዚህም ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ  “ወዳጆች ሆይ መንፈስን ሁሉ አትመኑ ነገር ግን መናፍስት ከእግዚአብሔር ሆነዉ እንደሆነ መርምሩ”/1ዮሐ 4፥1-3/ አለን።
ቅዱስ ጳዉሎስም “የክርስቶስን ሐዋርያት እንዲመስሉ ራሳቸዉን እየለወጡ ውሸተኞች ሐዋርያትና ተንኮለኞ ሠራተኞች ናቸው። ይህም ድንቅ አይደለም ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለዉጣልና” ብሏል /2ቆሮ.11፥13-15/። ሐዋርያት ሁሉ በየመልእክቶቻቸው ከሐሰተኞች አስተማሪዎች እንድንጠበቅ ደጋግመው አሳስበዋል። ብዙ ሰው ግን በየዋሕነት ስለሚጓዝ የነዚህ ተኩላዎች ሰለባ ሆኗል።
ጊዜው ክፉ ነውና የሐሰተኞች ነቢያት መረብ ጠልፎ ወደ ሐሰተኞች ክርስቶሶች እንዳይወስደን
#በጥንቃቄ መጓዝ ይጠበቅብናል። ሐዋርያዉ ቅዱስ ይሁዳም በመልእክቱ ቁ.3  “ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኳችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ” ሲል እንደመከረን በተቀደሰ እምነታችን እስከመጨረሻ ጸንተን እንጋደል።

#በቅዳሴ #ጊዜ# የሚነበቡ #ጥቅሶች
-፩ኛ ተሰ ፬፥፲፫ እስከ ፍጻሜ
-፪ኛ ጴጥ ፫፥፯-፲፭
-የሐዋ ሥራ ፳፬፥፩-፳፪

#ምስባኩም፦ መዝ ፵፱፥፫
"እግዚአብሔርሰ ገሀደ ይመጽእ ወአምላክነሂ ኢያረምም #
እሳት ይነድድ ቅድሜሁ"
"እግዚአብሔር ግልጥ ሆኖ ይመጣል አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም እሳት በፊቱ ይቃጠላል"

#ወንጌል፦ ማቴ ፳፬፥፩-፴፮
Forwarded from ELOHE PICTURES ♱ (几ㄖᐯ卂ᵘᶜʰⁱʰᵃ)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from ELOHE PICTURES ♱ (几ㄖᐯ卂ᵘᶜʰⁱʰᵃ)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from ELOHE PICTURES ♱ (Elohe pictures) via @dooxbot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በእናንተው ደጋፍ የተጀመረው እዚህ ደርሷል አሁንም ድጋፋችሁ አይለየን 🙏🙏🙏
የቤተክርስቲያኑ የባንክ አካውንት
💰 👉 1000265718063 👈
ገላን ቅዱስ ሚካኤል

ሁላችንም 100 ብር ብናስገባ ብዙ ነገር መሸፈን እንችላለን የቅዱስ ሚካኤል ምልጃው እና ጥበቃው አይለየን 🙏🙏🙏

ለበለጠ መረጃ የደብሩ ስልክ

+251950008283

የቅዱስ ሚካኤል ወዳጅ የሆናችሁ
የአቅማችሁን ሼር በማድረግ ማገዝ ለሚችሉ እናድርስ

T.me/Elohe_picture
2025/03/30 01:03:39

❌Photos not found?❌Click here to update cache.


Back to Top
HTML Embed Code: